TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#TiffanyHaddish

የ41 ዓመቷ አሜሪካዊት ተዋናይትና ኮሜዲያን ቲፋኒ ሀዲሽ በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ስላለው ግጭት በሰጠቻቸው አስተያየቶች/በምታጋራው መልዕክቶ ምክንያት ከፍተኛ ተቃውሞ እየቀረበባት ነው።

የምታጋራው መልዕክቶች በርካታ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎችን አስቆጥቷል።

ቲፍኒ ሀዲሽ ፥ "በትግራይ ላይ የሚፈፀውን የንፁሃን ግድያ ፣ የሴቶች መደፈር፣ የህፃናት ሞት ክዳለች ፣ በትግራይ ጉዳይ ጦሯን ላሰማራቸው #ኤርትራ በተለይም አምባገነን ለሆነው የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ድጋፍ ትሰጣለች" በሚል ነው ከፍተኛ ተቃውሞ እያስተናገደች የምትገኘው።

ቲፍኒ ሀዲሽ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በትግራይ ስላለው ሁኔታ በትዊተር ገጿ የተለያዩ መልዕክቶችን እያስተላለፈች ሲሆን ከነዚህ ውስጥ አንዱ ከትግራይ ጦርነት ጋር በተያያዘ የሚሰራጩ #ሀሰተኛ መረጃዎች የሚመለከት ነው።

በተጨማሪ፥ በአንድ ሪትዊት ላይ የቀድሞ የትግራይ ክልል ፕሬዜዳንት ዶ/ር ደብረፅዮን "ጦርነቱ የህዝብ መሆኑን ህፃናትም የዚህ አካል ስለመሆናቸው" ተናግረውበታል የተባለውን የእሳቸውን ንግግር አጋርታለች።

ከተቃዋሚዎቹ በተቃራኒው ደግሞ የምታጋራቸውን መልዕክቶች ትክክል እንደሆኑ የሚገልፁ በርካታ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ታይተዋል።

ቲፍኒ ሀዲሽ በ1979 እ.አ.አ. በሎስ አንጀለስ የተወለደች ሲሆን አባቷ ፀሃዬ ረዳ ሀድሽ በወቅቱ የኢትዮጵያ አካል የነበረችውን ኤርትራን ጥለው የተሰደዱ ስደተኛ ነበሩ።

ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ ቲፋኒ ሀዲሽ ከኤርትራና ከመሪዋ ኢሳያስ አፍወርቂ ጋር ጥሩ የሚባል ወዳጅነትንና ቅርርብ ስለመፍጠራቸው ይነገራል።

ለመጀመሪያ ጊዜ ኤርትራን የጎበኘችው እ.ኤ.አ. በ2018 ሲሆን በወቅቱ የአባቷን ህልፈት ተከትሎ በእሳቸውን የቀብር ስነስርዓት ላይ ለመገኘት ነበር።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የጣና በለስ የተቀናጀ የስኳር ፋብሪካ ዛሬ እየተመረቀ ነው። በ231 ሚሊየን ዶላር የተገነባው የጣና በለስ የተቀናጀ የስኳር ፋብሪካ እየተመረቀ ነው። በምረቃ ስነ-ስርአቱ ላይ የፌደራል፣ የክልልና የዞን ባለስልጣናትና የስራ ሀላፊዎች እንዲሁም የአካባቢው ማህበረሰብ አባላት ተገኝተዋል ። የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አብርሃም ደምስ እንዳሉት ለፋብሪካው ግንባታ 231 ሚሊየን…
#Update

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ በ231 ሚሊዮን ዶላር የተገነባው የጣና በለስ የተቀናጀ የስኳር ፋብሪካ መርቀው በይፋ ስራውን አስጀምረዋል።

በምረቃ ስነ-ስርአቱ የፌዴራል፣ የክልልና የዞን ባለስልጣናት እና የስራ ሀላፊዎች እንዲሁም የአካባቢው ማህበረሰብ አባላት መገኘታቸውን ከ #etv የተገኘው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
የአትሌት አልማዝ አያና ሪከርድ ተሰበረ !

ከአምስት ዓመታት በፊት በ #ሪዮ_ኦሎምፒክ 10,000 ሜትር ውድድር በኢትዮጵያዊቷ አትሌት አልማዝ አያና ተይዞ የነበረው የዓለም ሪከርድ ዛሬ ተሰብሯል።

በሄንግሎ በተካሄደ የ10,000 ሜትር ውድድር በትውልደ ኢትዮጵያዊቷ #ኔዘርላንድን ወክላ በምትሮጠው ሲፋን ሀሰን 29:06.82 በሆነ ደቂቃ በመግባት ሪከርዱን ሰብራለች።

ቲክቫህ ስፖርት : t.iss.one/joinchat/VvwzStMNcNHmhK0x

@tikvahethsport
#GERD🇪🇹

'የኢትዮጵያ ጦር ግድቡን እንደአይኑ ብሌን እየጠበቀ ነው'

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሜጀር ጀነራል ይልማ መርዳሳ ፥ የኢትዮጵያ ሉአላዊነት መገለጫ የሆነውን የታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሰራዊቱ እንደ አይኑ ብሌን በመጠበቅ ላይ ሲሉ ተናገሩ።

ሜጄር ጄነራል ይልማ ይህን ያሉት ትላንት በኢ.ፌ.ዲ.ሪ አየር ኃይል የምስራቅ አየር ኃይል ምድብ ለሠራዊቱ የዕውቅናና የምስጋና መርሃ ግብር በተካሄደበት ወቅት መሆኑን ከኢዜአ ድረገፅ ተመልክተናል።

ሰራዊቱ የ2ተኛው ዙር የግድቡ የውሃ ሙሌት በተቀመጠው ጊዜ እንዲፈፀም የሚጠበቅበትን ስራ እየሰራ መሆኑንም ሜጄር ጀነራል ይልማ በዚሁ ጊዜ አስረድተዋል።

በሌላ በኩል ፥ በውስጥ ሆነ በውጭ ቀጣዩን ምርጫ ተገን በማድረግ አገሪቱን ለማተራመስ እና ሁከትና ብጥብጥ ለመፍጠር የሚከናወኑ ተግባራት መቼም ቢሆን አይሳኩም ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethiopia
#Ethiopia #COVID19

ኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ካደረገችው 3,835 የኮቪድ19 የላብራቶሪ ምርመራ 109 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል፤ ይህም አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር 272,914 አድርሶታል።

በ24 ሰዓት 8 ሰዎች ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን በአጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 4,209 ደርሷል።

የኮቪድ-19 ክትባት የተከተቡ ዜጎች 1,882,719 ደርሰዋል።

@tikvahethiopia
ከነገ ጀምሮ ሁሉም የመንግስት ሰራተኛ በስራ ገበታው ላይ እንዲገኝ የአጣዬ ከተማ አስተዳደር አሳሰበ።

ይህ ማሳሰቢያ የተላለፈው ዛሬ ለአጣዬ ከተማ አስተዳደር ለመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የሚውል 10 ሚሊዮን ብር የሚገመት የቁሳቁስ ድጋፍ ድጋፍ በኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር አሕመዲን መሐመድ አስተባባሪነት በተደረገበት ወቅት ነው።

በዚሁ ወቅት የአጣዬ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አገኘሁ መክቴ ፥ ከነገ ሰኞ ግንቦት 30/2013 ዓ.ም ጀምሮ የከተማ አስተዳደሩ የመንግሥት ሠራተኞች በሥራ ገበታቸው ላይ እንዲገኙ አሳስበዋል፡፡

ከንቲባው ፥ የከተማው ነዋሪዎች በአሉባልታ ሳይሸበሩ ወደነበሩበት አካባቢ በመመለስ ከተማዋን ለመገንባት የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ጠይቀዋል።

የአጣዬ ከተማ ነዋሪዎች አሁንም ቢሆን በአካባቢው ላይ የጸጥታ ችግር ሊከሰት እንደሚችል ስጋት ስላላቸው ከማንኛውም ሥራ በፊት ሰላም እንዲረጋገጥ ስለመጠየቃቸው አሚኮ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
"...ታጣቂዎች መሣሪያ በማቀባበል ጭምር ቅስቀሳ ማድረግ አይቻልም በማለት መንገድ በመዝጋታቸው የምርጫ ቅስቀሳው ሳይካሄድ ቀርቷል" - ኢዜማ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ በኦሮሚያ ክልል ስሬ ምርጫ ወረዳ ሊያደርግ የነበረው የምርጫ ቅስቀሳ ዝግጅት በአካባቢው አስተዳደር ክልከላ እንደተስተጓጎለበት አመለከተ።

ፓርቲው በይፋዊ ፌስቡክ ገፁ ባወጣው መረጃ ፥ የፓርቲው ዋና ጸሐፊ አበበ አካሉ የጎዳና ላይ የምርጫ ለማድረግ ወደስሬ ሄደው የነበረ ሲሆን በስሬ ምርጫ ወረዳ ሻሜዳ ቀበሌ ሊቀመንበር እና የቀበሌው ሥራ አስኪያጅ የተመሩ ታጣቂዎች መሣሪያ በማቀባበል ጭምር ቅስቀሳ ማድረግ አይቻልም በማለት መንገድ በመዝጋታቸው የምርጫ ቅስቀሳው ሳይካሄድ ቀርቷል ብሏል።

ፓርቲው በስሬ ወረዳ ምርጫ ቅስቀሳ ለማድረግ ያጋጠመውን ችግር ለምርጫ ቦርድ አመለክታለሁ ብሏል።

ኢዜማ ፥ መጋቢት 3 ቀን 2013 ከምርጫው ሂደት ጋር በተያያዘ ከሌሎች ቦታዎች በተለየም ዕጩ ለማስመዝገብም ሆነ በነፃነት እንቅስቃሴ ለማድረግ በከፍተኛ ሁኔታ ከተቸገረባቸው ቦታዎች የኦሮሚያ ክልል አንዱ መሆኑን በመጥቀስ አስቸኳይ የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ ጠይቆ እንደነበር አስታውሷል።

በተጨማሪም በየአካባቢው በሚገኙ የገዢው ፓርቲ (ብልፅግና) አባላት ምርጫው ነፃ፣ ፍትሃዊ እና ዴሞክራሲያዊ እንዳይሆነ የሚፈፀሙትን እኩይ ተግባር በአስቸኳይ እንዲያቆሙ ግንቦት 19 ባወጣው መግለጫ መጠየቁን አስታውሷል።

@tikvahethiopia
የባለሀብቱ ወርቁ አይተነው "WA የዘይት ፋብሪካ" ዛሬ ግንቦት 30 ይመረቃል።

በደብረ ማርቆስ ከተማ ከ5 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጭ በአቶ ወርቁ አይተነው የተገነበው ግዙፉ WA የዘይት ፍብሪካ ዛሬ ሰኞ ግንቦት 30/2013ዓ.ም የፌደራልና የክልል ባለስልጣናት እንዲሁም ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት እንደሚመረቅ ይጠበቃል።

የWA የምግብ ዘይት ፋብሪካ በደብረማርቆስ ከተማ በ101,103 ካ.ሜ በሊዝ በተገኘ ቦታ የተገነባ ነው፡፡

የፋብሪካው ግንባታ ከአራት ዓመታት በፊት ተጀምሮ በአሁኑ ሰዓት ወደ ምርት ማምረት እየገባ ይገኛል፡፡

ፋብሪካው ጥሬ የቅባት እህል በማቀነባበር የተጣራ ዘይት ማምረት እና በተጨማሪ ድፍድፍ የፓልም ዘይትን ከዉጭ በማስገባት በግብዓትነት ተጠቅሞ በማጣራት ያለቀለት የፓልም ዘይት ያመርታል፡፡

ፋብሪካው የሰሊጥ፣ የአኩሪ አተር፣ ኑግ፣ ሱፍ እና ለውዝ የምግብ ዘይት በዋነኛነት የሚያመርት ሲሆ ድፍድፍ የፓልም ዘይትንም ያጣራል፡፡

ለግንባታ ተከላውም 5 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጓል።

በአሁኑ ጊዜ ከ 1500 በላይ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍል ቀጥተኛ የሆነ የሥራ እድል ፈጥሯል።

ፋብሪካው በሙሉ አቅሙ ማምረት ሲጀምር ከ3000 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ እድል ይፈጥራል ተብሎ ታምኗል፡፡

የፋብሪካው የምርት ዓይነቶች
ባለ 1 ሊትር፣
ባለ 3 ሊትር፣
ባለ 5 ሊትር፣
ባለ 10ሊትር እና
ባለ 20 ሊትር ዘይት አምርቶና አሽጎ ለገበያ ያቀርባል ተብሏል።

ከፋበሪካዉ የሚገኘዉ ተረፈ ምርትም ለእንስሳት መኖ የሚያገለግል ሲሆን ለዉጭ ገበያ ለማቅረብ በዝግጅት ላይ እንደሆነ ከደብረማርቆስ ኮሚኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
ትላንት ምሽት 1:45 አካባቢ በባህርዳር ከተማ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህገወጥ ሲሚንቶ በቁጥጥር ስር መዋሉን በባህር ዳር ከተማ አስተዳደር የግሽ ዓባይ ክ/ከተማ አስታወቀ።

ህገወጥ ሲሚንቶው በቁጥጥር ስር የዋለው በግሽ ዓባይ ክ/ከተማ ነው።

ይኸው በርካታ ቁጥር አለው የተባለው ሲምንቶ በህገወጥ መንገድ በመጫን ወደ ሌላ ቦታ ይዘው ሊሄዱ የነበሩ ግለሠቦች በህብረተሰቡ ጥቆማ በፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

በአሁኑ ሰዓት ወደ ፖሊስ ጣቢያ በመውሰድ ምርመራ እየተደረገ ነው ተብሏል።

የግሽዓባይ ክፍለ ከተማ ንግድ እና ገበያ ልማት ጽ/ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ ሃብተማሪያም፥ በከተማው የሲሚንቶ እጥረት መኖሩ እየታወቀ ስግብግብ ህገወጥ ነጋዴዎች የራሳቸውን ሃብት ያለአግባብ ለማካበት ጨለማን ተገን አድርገው መንቀሳቀስን መርጠዋል ብለዋል።

ህብረተሰቡ የተለመደውን ጥቆማ በመስጠት ከፀጥታ ሀይሉና ከተቋሙ ጋር በመሆን ህገወጥ ነጋዴዎችን የማጋለጥ ስራ ሊሰራ ይገባል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

@tikvahethiopia
የአዊ ዞን ከተሞችና የገጠር ቀበሌዎች በሙሉ መብራት ተቋርጧል !

ከባህር ዳር - ዳንግላ ማከፋፈያ በ66 KV የብረት ታወር ላይ በተፈፀመ ስርቆት የአዊ ዞን ከተሞች መብራት ተቋርጧል።

ከባህር ዳር - ዳንግላ ማከፋፈያ ጣቢያ በተዘረጋ 66 KV የኤሌክትሪክ አስተላላፊ መስመር ላይ ይነሳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በተፈፀመ የታወር ብረት ስርቆት አንድ ታወር በመውደቁ ከዳንግላ እና ግልገል በለስ ማከፋፈያ ጣብያዎች /ሰብስቴሽን/ ኤሌክትሪክ የሚያገኙ የአዊ ዞን ከተሞች እና የምዕራብ ጎጃም ዞን የተወሰኑ ከተሞች ከትናንት ግንቦት 29 ቀን 2013 ዓ.ም ማታ ጀምሮ ኤሌክትሪክ ተቋርጧል፡፡

ስለሆነም ዳንግላ ፣ እንጅባራ፣አዲስ ቅዳም፣ ቲሊሊ፣ ግምጃ ቤት፣ ሰከላ፣ ቻግኒ፤ ጃዌ እና በአካቢቢያቸው ባሉ የገጠር መንደሮች የሚኖሩ ዜጎች አገልግሎቱ የተቋረጠው ከተቋሙ ቁጥጥር ውጪ በሆነ ጉዳይ መሆኑን እንዲገነዘቡ ተብሏል።

የተቋረጠውን አገልግሎት ወደነበረበት ለመመለስ ርብርብ እየተደረገ መሆኑ የተግለፀ ሲሆን ነዋሪዎች በትዕግስት እንዲጠብቁ የአማራ መብራት ሀይል ዲስትሪክት መልዕክት አስተላልፏል።

@tikvahethiopia