TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ለ2014 በጀት ዓመት 561.7 ቢሊዮን ብር ረቂቅ በጀት ፀደቀ።

ዛሬ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለ 2014 በጀት ዓመት የ 561. 7 ቢሊዮን ብር ረቂቅ በጀት አፅድቋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትዊተር ገፃቸው ላይ በጀቱ ምርታማነትን ለማሳደግ ትልቅ ትኩረት የሰጠ መሆኑንና ፤ ከ10 ዓመቱ መሪ የልማት ዕቅድ ጋር የተጣጣመ እንደሚያደርገው ገልፀዋል።

@tikvahethiopia
በጉራፈርዳ ወረዳ 6 የጸጥታ ኃይሎች በታጣቂዎች ተገደሉ።

6 የደቡብ ክልል ልዩ ኃይል አባላት በቤንች ሸኮ ዞን በሚገኘው ጉራፈርዳ ወረዳ ውስጥ ትላንት በታጣቂዎች ተገድለዋል።

የልዩ ኃይል አባላቱ የተገደሉት በወረዳው ስር ባለው ወጀምታ ቀበሌ ነው።

"ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ድረገፅ" ቃላቸውን የሰጡት የጉራፈርዳ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሲሳይ ሻሎም ፥ ጥቃት የተፈጸመባቸው የደቡብ ክልል ልዩ ኃይል አባላት፤ በወጀምታ ቀበሌ ልዩ ስሙ ሰንበሊጥ በተባለ ቦታ ባለ ካምፕ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።

8 የልዩ ኃይል አባላት፤ ትላንት ከጠዋት 2 ሰዓት ገደማ፤ አንድ የካምፑን ሰራተኛ አጅበው ውሃ ለመቅዳት ወደ ወንዝ ሲሄዱ ተኩስ እንደተከፈተባቸው አስረድተዋል።

በጥቃቱ ስድስት የልዩ ኃይል አባላት ሲገደሉ አብሯቸው የነበረው የካምፑ ሰራተኛ ጉዳት ደርሶበት ህክምና ላይ ይገኛል ብለዋል።

ለአጀባ ከተሰማሩት የጸጥታ ኃይሎች ውስጥ 2ቱ ምንም ጉዳት እንዳልደረሰባቸውም ሲሉ ገልፀዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ : ethiopiainsider.com/2021/3451/

(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

@tikvahethiopia
የደቡብ ክልል የ8ኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ 28 እስከ ሰኔ 30 ይሰጣል።

በደቡብ ክልል የ8ኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ 28 እስከ 30 2013 ዓ.ም እንደሚሰጥ የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡

ቢሮው አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማድረግ የተማሪዎች መመዝገቢያ ቅጽ እንግሊዝ ሀገር ከሚገኝ DRS ድርጅት ግዢ እንደተፈጸመና ቢሮ መግባቱን አሳውቋል።

የቅጽ አሟላሉን በተመለከተ በክልሉ ለሚገኙ ሁሉም የፈተና ክፍል ኃላፊዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠቱን ቢሮው ገልጿል።

በክልሉ የሚገኙ 16 ዞኖችና 7 ልዩ ወረዳዎች ፎርሙን ወስደው በመንግስትና በግል ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎችን እያስሞሉ ነው ተብሏል።

የፈተና ዝግጅት ተጠናቆ የህትመት ስራ እየተሰራ ይገኛል።

ፈተናው በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች ከሰኔ 28 እስከ ሰኔ 30/2013 ይሰጣል ተብሏል። #SRTA

@tikvahethiopia
#Ethiopia #COVID19

ኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ካደረገችው 4,505 የኮቪድ19 የላብራቶሪ ምርመራ 173 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል፤ ይህም አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር 272,805 አድርሶታል።

በ24 ሰዓት 8 ሰዎች ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን በአጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 4,201 ደርሷል።

የኮቪድ-19 ክትባት የተከተቡ ዜጎች 1,878,367 ደርሰዋል።

@tikvahethiopia
ቴምቲዮፔ ባሎጉን ጆሹዋ ህይወታቸው አለፈ።

ታዋቂው ናይጄሪያው የሃይማኖት ሰባኪ ቴምቲዮፔ ባሎጉን ጆሹዋ ትናንትና ህይወታቸው አለፈ።

ቴምቲዮፔ ባሎጉን ጆሹዋ ወይም በተለምዶ ቲቢ ጆሹዋ ማረፋቸውንም ይፈዊ በሆነው ፌስቡክ ገፃቸውም ላይ "አምላክ አገልጋዩን ቲቢ ጆሹዋን ወደቤቱ ወስዷል" በሚልም ሰፍሯል።

ስመ ጥር የሆኑት የኢቫንጀሊካን ሃይማኖት ሰባኪ በትናንትናው ዕለት የቤተክርስቲያን ፕሮግራማቸውን ከጨረሱ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ምሽት ላይ ማረፋቸው ተገልጿል።

በተከታዮቻቸው ዘንድ የነብይነትን ማዕረግ ያገኙት ቲቢ ጆሹዋ በአህጉሪቷ ውስጥ ተፅእኖ መፍጠር ከቻሉ የኢቫንጀሊካል ሰባኪዎች አንዱ ናቸው ።

በአፍሪካ ውስጥም ያሉ ታዋቂ ፖለቲከኞችንም በተከታይነት ማፍራት ችለዋል።

"ቸርች ኦፍ ኦል ኔሽንስ" የሚባል የእምነት ተቋምን የመሰረቱ ሲሆን እንዲሁም በቴሌቪዥንም በሚያደርጓቸው ስብከቶችም በርካታ የእምነቱ ተከታይ ምዕመናንን ማፍራት ችለዋል።

በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በሌጎስ የሚያደርጓቸውን ሳምንታዊ የአገልግሎት ስርዓት ይከተላሉ ነበር።

ቴምቲዮፔ ባሎጉን ጆሹዋ በ57 ዓመታቸው ነው ህይወታቸው አለፈ።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

@tikvahethiopia
የጣና በለስ የተቀናጀ የስኳር ፋብሪካ ዛሬ እየተመረቀ ነው።

በ231 ሚሊየን ዶላር የተገነባው የጣና በለስ የተቀናጀ የስኳር ፋብሪካ እየተመረቀ ነው።

በምረቃ ስነ-ስርአቱ ላይ የፌደራል፣ የክልልና የዞን ባለስልጣናትና የስራ ሀላፊዎች እንዲሁም የአካባቢው ማህበረሰብ አባላት ተገኝተዋል ።

የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አብርሃም ደምስ እንዳሉት ለፋብሪካው ግንባታ 231 ሚሊየን ዶላር ወጭ ተደርጓል።

የጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ በ2003 አ.ም ግንባታው ተጀምሮ በተለያዩ ምክንያቶች ሳይጠናቀቅ መቆየቱ የሚታወስ ነው።

በ2010 አ.ም የፋብሪካው ግንባታውን ለቻይናው ሲ ኤም ሲ ኢ ኩባንያ በመሰጠቱ ቀሪው ስራ በ14 ወራት ተጠናቆ ዛሬ ለምረቃ በቅቷል። #ENA

@tikvahethiopia
#Update

የ "አበበች ጎበና ህፃናት ክብካቤ እና ልማት ማህበር" ከሰዓታት በፊት ባሰራጨው መልዕክት ክብርት ዶ/ር አበበች ጎበና (እዳዬ) አሁንም በጳውሎስ ሆስፒታል በጽኑ ሕሙማን ክፍል ሕክምና እያገኙ መሆኑን አሳውቋል።

ዶክተሮቻችው ለቤተሰብ እንደገለፁት ጤናቸው በጣም መሻሻል አሳይተዋል፡፡

የልብ፣ የኩላሊት፣ የጉበት፣ የደም ግፊትና የመሳሰሉት ምርመራ ተደርጎላቸው ጥሩ የሚባል ሁኔታ ላይ መሆናቸው ዶክተሮች ገልፀዋል ብሏል ማህበሩ ባሰራጨው መልዕክት።

ማህበሩ ፥ "የጳውሎስ ሆስፒታል የጤና ባለሙያዎች ደከመኝ ሰለጨኝ ሳይሉ 24 ሰዓታት የእዳዬን ጤና ለመመለስ የህምና እርዳታ ላደረጉላቸው ከልብ የመነጨ ምስጋና እናቀርለን" ሲል አመስግኗል።

ወዳጆቻቸው፣ ልጆቻችው እና ሎሎችም ከኢትዮጵያ ና ከተለያዩ ሀገራት በእንዳዬ መታመም ተጨንቀው ስልክ በመደወልና መልዕክት በመላክ የጠየቁትን በአጠቃለይ በፀሎትም አብረው ለሆኑ ሁሉም ማህበሩ አመስግኗል።

በመጨረሻም፥ የሺዎች እናት የሆኑት ክብርት ዶ/ር አበበች ጎበና ፈጣሪ ጨርሶ ይምራቸው ዘንድ ሁላችንም እንፀልይላቸው ሲል የአበበች ጎበና ህፃናት ክብካቤ እና ልማት ማህበር መልዕክት አስተላልፏል።

ክብርት ዶ/ር አበበች ጎበና በኮቪድ-19 ተይዘው ለህክምና ሆስፒታል መግባታቸው ይታወሳል።

@tikvahethiopia
#TiffanyHaddish

የ41 ዓመቷ አሜሪካዊት ተዋናይትና ኮሜዲያን ቲፋኒ ሀዲሽ በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ስላለው ግጭት በሰጠቻቸው አስተያየቶች/በምታጋራው መልዕክቶ ምክንያት ከፍተኛ ተቃውሞ እየቀረበባት ነው።

የምታጋራው መልዕክቶች በርካታ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎችን አስቆጥቷል።

ቲፍኒ ሀዲሽ ፥ "በትግራይ ላይ የሚፈፀውን የንፁሃን ግድያ ፣ የሴቶች መደፈር፣ የህፃናት ሞት ክዳለች ፣ በትግራይ ጉዳይ ጦሯን ላሰማራቸው #ኤርትራ በተለይም አምባገነን ለሆነው የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ድጋፍ ትሰጣለች" በሚል ነው ከፍተኛ ተቃውሞ እያስተናገደች የምትገኘው።

ቲፍኒ ሀዲሽ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በትግራይ ስላለው ሁኔታ በትዊተር ገጿ የተለያዩ መልዕክቶችን እያስተላለፈች ሲሆን ከነዚህ ውስጥ አንዱ ከትግራይ ጦርነት ጋር በተያያዘ የሚሰራጩ #ሀሰተኛ መረጃዎች የሚመለከት ነው።

በተጨማሪ፥ በአንድ ሪትዊት ላይ የቀድሞ የትግራይ ክልል ፕሬዜዳንት ዶ/ር ደብረፅዮን "ጦርነቱ የህዝብ መሆኑን ህፃናትም የዚህ አካል ስለመሆናቸው" ተናግረውበታል የተባለውን የእሳቸውን ንግግር አጋርታለች።

ከተቃዋሚዎቹ በተቃራኒው ደግሞ የምታጋራቸውን መልዕክቶች ትክክል እንደሆኑ የሚገልፁ በርካታ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ታይተዋል።

ቲፍኒ ሀዲሽ በ1979 እ.አ.አ. በሎስ አንጀለስ የተወለደች ሲሆን አባቷ ፀሃዬ ረዳ ሀድሽ በወቅቱ የኢትዮጵያ አካል የነበረችውን ኤርትራን ጥለው የተሰደዱ ስደተኛ ነበሩ።

ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ ቲፋኒ ሀዲሽ ከኤርትራና ከመሪዋ ኢሳያስ አፍወርቂ ጋር ጥሩ የሚባል ወዳጅነትንና ቅርርብ ስለመፍጠራቸው ይነገራል።

ለመጀመሪያ ጊዜ ኤርትራን የጎበኘችው እ.ኤ.አ. በ2018 ሲሆን በወቅቱ የአባቷን ህልፈት ተከትሎ በእሳቸውን የቀብር ስነስርዓት ላይ ለመገኘት ነበር።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የጣና በለስ የተቀናጀ የስኳር ፋብሪካ ዛሬ እየተመረቀ ነው። በ231 ሚሊየን ዶላር የተገነባው የጣና በለስ የተቀናጀ የስኳር ፋብሪካ እየተመረቀ ነው። በምረቃ ስነ-ስርአቱ ላይ የፌደራል፣ የክልልና የዞን ባለስልጣናትና የስራ ሀላፊዎች እንዲሁም የአካባቢው ማህበረሰብ አባላት ተገኝተዋል ። የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አብርሃም ደምስ እንዳሉት ለፋብሪካው ግንባታ 231 ሚሊየን…
#Update

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ በ231 ሚሊዮን ዶላር የተገነባው የጣና በለስ የተቀናጀ የስኳር ፋብሪካ መርቀው በይፋ ስራውን አስጀምረዋል።

በምረቃ ስነ-ስርአቱ የፌዴራል፣ የክልልና የዞን ባለስልጣናት እና የስራ ሀላፊዎች እንዲሁም የአካባቢው ማህበረሰብ አባላት መገኘታቸውን ከ #etv የተገኘው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
የአትሌት አልማዝ አያና ሪከርድ ተሰበረ !

ከአምስት ዓመታት በፊት በ #ሪዮ_ኦሎምፒክ 10,000 ሜትር ውድድር በኢትዮጵያዊቷ አትሌት አልማዝ አያና ተይዞ የነበረው የዓለም ሪከርድ ዛሬ ተሰብሯል።

በሄንግሎ በተካሄደ የ10,000 ሜትር ውድድር በትውልደ ኢትዮጵያዊቷ #ኔዘርላንድን ወክላ በምትሮጠው ሲፋን ሀሰን 29:06.82 በሆነ ደቂቃ በመግባት ሪከርዱን ሰብራለች።

ቲክቫህ ስፖርት : t.iss.one/joinchat/VvwzStMNcNHmhK0x

@tikvahethsport
#GERD🇪🇹

'የኢትዮጵያ ጦር ግድቡን እንደአይኑ ብሌን እየጠበቀ ነው'

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሜጀር ጀነራል ይልማ መርዳሳ ፥ የኢትዮጵያ ሉአላዊነት መገለጫ የሆነውን የታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሰራዊቱ እንደ አይኑ ብሌን በመጠበቅ ላይ ሲሉ ተናገሩ።

ሜጄር ጄነራል ይልማ ይህን ያሉት ትላንት በኢ.ፌ.ዲ.ሪ አየር ኃይል የምስራቅ አየር ኃይል ምድብ ለሠራዊቱ የዕውቅናና የምስጋና መርሃ ግብር በተካሄደበት ወቅት መሆኑን ከኢዜአ ድረገፅ ተመልክተናል።

ሰራዊቱ የ2ተኛው ዙር የግድቡ የውሃ ሙሌት በተቀመጠው ጊዜ እንዲፈፀም የሚጠበቅበትን ስራ እየሰራ መሆኑንም ሜጄር ጀነራል ይልማ በዚሁ ጊዜ አስረድተዋል።

በሌላ በኩል ፥ በውስጥ ሆነ በውጭ ቀጣዩን ምርጫ ተገን በማድረግ አገሪቱን ለማተራመስ እና ሁከትና ብጥብጥ ለመፍጠር የሚከናወኑ ተግባራት መቼም ቢሆን አይሳኩም ሲሉ ተደምጠዋል።

@tikvahethiopia
#Ethiopia #COVID19

ኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ካደረገችው 3,835 የኮቪድ19 የላብራቶሪ ምርመራ 109 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል፤ ይህም አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር 272,914 አድርሶታል።

በ24 ሰዓት 8 ሰዎች ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን በአጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 4,209 ደርሷል።

የኮቪድ-19 ክትባት የተከተቡ ዜጎች 1,882,719 ደርሰዋል።

@tikvahethiopia