TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
60.7K photos
1.54K videos
215 files
4.22K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
 የአፍሪካ ህብረት ምርጫ ታዛቢ ቡድኖች አ/አ ገብተዋል።

የአፍሪካ ህብረት ከኢትዮጵያ መንግሥት በደረሰው ጥያቄ መሠረት የአጭር እና የረዥም ጊዜ የምርጫ ታዛቢዎች ቡድኖችን መላኩን የህብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማህማት ማስታወቃቸውን ቪኦኤ ዘግቧል።

ሰኔ 14 የሚካሄደውን አጠቃላይ ብሄራዊ ምርጫ የሚታዘቡት ከተለያዩ የህብረቱ አባል ሃገሮች የተውጣጡ 8 አባላት የሚገኙበት የረዥም ጊዜ ክትትል ቡድን ሐሙስ እና ረቡዕ አዲስ አበባ መግባቱን የአፍሪካ ህብረት ባወጣው የፕሬስ መግለጫ አመልክቷል።

ቡድኑ በኢትዮጵያ ቆይታው ቁልፍ የሚባሉ የምርጫ ሂደቱ ክፍሎች ላይ ቅኝት እንደሚያደርግና ትንተና እንደሚሰጥ ተጠቁሟል።

በተለይ የፖለቲካውን አየር፣ የምርጫውን የህግ ማዕቀፍ፣ የምርጫ ዝግጅቱን ውጤታማነትና ግልፅነት እንዲሁም የአስተዳደርና የመገናኛ ብዙኃን ነፃነትንና በመላ ሂደቱ ውስጥ ለተሣትፎ መብቶች መከበር የሚሰጠውን ትኩረት ጨምሮ የዘመቻውን አካሄድ ሁኔታ እንደሚያካትት አስታውቋል።

የረዥም ጊዜ ታዛቢ ቡድኖች በሃገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች እንደሚሰማሩ የአፍሪካ ኅብረት ጠቁሞ ምርጫው ሊካሄድ ወደ አንድ ሳምንት ሲቀር ብርካታ የአጭር ጊዜ ታዛቢ ቡድኖች አዲስ አበባ እንደሚገቡ ገልጿል።

ኢትዮጵያ ውስጥ የሚሠማራው የአፍሪካ ህብረት ታዛቢ ተልዕኮ በህብረቱ ድንጋጌዎች መሠረት በምርጫው ሂደት ላይ መረጃ የመሰብሰብና የመተንተን መብትና ችሎታ እንዳለው የፕሬስ መግለጫ በተለያዩ ጊዜዎች የወጡና የተፈረሙ ውሎችና መግለጫዎችን አጣቅሶ አስታውቋል።

ምንጭ፦ ቪኦኤ
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ትራምፕ ከፌስቡክ እና ኢንስታግራም ለ2 ዓመት ታገዱ። የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከፌስቡክና ከኢንስታግራም ለሁለት ዓመታት መታገዳቸውን ፌስቡክ ኩባንያ ዛሬ አስታወቀ። ፌስቡክ እገዳው መጀመሪያ ከተጣለበት እ.አ.አ ጥር 7 ጀምሮ ለሁለት ዓመት ተግባራዊ የሚሆን ነው ብሏል። ኩባንያው ፕሮቶኮሎቹን በሚጥሱ ህዝብ በሚከተላቸው አካላት ላይ “ከፍተኛ ቅጣቶችን” ተግባራዊ እያደረገ መሆኑን አክሏል።…
"... በሚቀጥለው ጊዜ ኋይት ሀውስ 'ስገባ' በእሱ ጥያቄ ከማርክ ዙከንበርግ እና ባለቤቱ ጋር የእራት ግብዣ ብሎ ነገር አይኖርም" - ዶናልድ ትራምፕ

የቀደሞው የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከፌስቡክ እና ኢንስታግራም ለሁለት ዓመት መታገዳቸውን ተከትሎ መግለጫ አውጥተዋል።

ዶናልድ ትራምፕ ባወጡት መግለጫ "የፌስቡክ ውሳኔ 75 ሚሊዮን ሰዎችን ጨምሮ ለመረጡን ብዙ ሰዎች ስድብ ነው ..." "በዚህ ሳንሱር እና ማፈን እንዲቀጥሉ ሊፈቀድላቸው አይገባም። በመጨረሻም እኛ እናሸንፋለን። ሀገራችን ከእንግዲህ ይህን በደል መሸከም አትችልም!" ብለዋል።

ትራምፕ በሰጡት መግለጫ በፌስቡክ መስራች ላይ ትችት ሰንዝረዋል።

በቀጣዩ የአሜሪካ ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ ብርቱ ተፎካካሪ ለመሆን ዝግጅት እያደረጉ መሆኑን የገለፁት ትራምፕ ዳግም ወደ ኋይት ሀውስ ሲመጡ ከማርክ ዙከርበርግ እና ባለቤታቸው ጋር እራት እንደማይኖራቸው ተናግረዋል።

ትራምፕ ፥ "በሚቀጥለው ጊዜ በኋይት [ስገባ] በእሱ ጥያቄ ከማርክ ዙከንበርግ እና ባለቤቱ ጋር የእራት ግብዣ ብሎ ነገር አይኖርም። ሁሉም ነገር ሥራ ይሆናል!" ብለዋል።

የፌስቡክ ውሳኔ ትራምፕ ከ2024 ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በፊት ወደ መድረኩ እንዲመለሱ ያስችላቸዋል።

ከ ፌስቡክ በተጨማሪ ትራምፕ በጥር ወር ካፒቶል ሂል ረብሻ ምክንያት ከትዊተር፣ ዩቲዩብ፣ ስናፕቻት፣ ትዊች እና ከሌሎች ማህበራዊ ሚዲያ መድረኮች ታግደዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tikvahethiopia
#Happening_now

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በኤፍራታና ግድም ወረዳና አጣዬ ከተማ አስተዳደር እና በኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ነዋሪዎች መካከል ተፈጥሮ የነበረውን ግጭት #በእርቅ_ለመፍታት ያለመ የሰላም ውይይት መካሄድ ጀምሯል።

የሰላም ውይይቱ እየተካሄደ የሚገኘው በአጣዬ ከተማ ነው።

የእርቀ ሰላም ውይይቱን ሌተናል ጀኔራል ደስታ አብቼ እየመሩት ይገኛሉ።

በተጨማሪ የኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ አህመድ ያሲን ፣ የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ጀማል ሀሰን እና የአጣዬ ከንቲባ አቶ አገኘሁ መክቴ ከአወያዩቹ መካከል ይገኛል።

የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ነዋሪዎችና አመራሮች ፣ የአጣዬ ከተማ ነዋሪዎችና አመራሮች እየተሳተፉበት እንደሚገኙ ከሰሜን ሸዋ ዞን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአዲስ ተማሪዎች ምዝገባ ሰኔ 1 እና ሰኔ 2/2013 (በኦንላይን) መሆኑን ገለፀ።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2013 ትምህርት ዘመን በመደበኛ የዲግሪ ትምህርት መርሃ-ግብር በትምህርት ሚ/ር መስፈርት መሠረት አዲስ የተመደቡ ተማሪዎች ሰኔ 01 ቀን 2013 ዓ.ም እና ሰኔ 02 ቀን 2013 ዓ.ም በ https://portal.aau.edu.et በመጠቀም #የኦንላየን ምዝገባ እንዲያከናውኑ አሳሰበ።

ተማሪዎቹ በተመደቡበት የዩኒቨርስቲ ካምፓስ ሪፖርት የሚያደርጉት ሰኔ 19 እና ሰኔ 20 2013 ዓ.ም እንደሚሆን እና የገጽ ለገጽ ትምህርት ሰኞ ሰኔ 21 ቀን 2013 እንደሚጀምር ተገልጿል።

መረጃው የአዲሰ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ጽ/ቤት ነው።

ተጨማሪ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጉዳዮችን እንዲሁም ጥሪዎችን ቲክቫህ እና ካርድ በጋር በሚሰሩበት t.iss.one/joinchat/RYD_4tbNBwRoKR2h (በቲክቫህ ኢትዮጵያ የዩኒቨርሲቲ ገፅ ማግኘት ይቻላል።

@tikvahethiopia @tikvahuniversity
ለ2014 በጀት ዓመት 561.7 ቢሊዮን ብር ረቂቅ በጀት ፀደቀ።

ዛሬ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለ 2014 በጀት ዓመት የ 561. 7 ቢሊዮን ብር ረቂቅ በጀት አፅድቋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትዊተር ገፃቸው ላይ በጀቱ ምርታማነትን ለማሳደግ ትልቅ ትኩረት የሰጠ መሆኑንና ፤ ከ10 ዓመቱ መሪ የልማት ዕቅድ ጋር የተጣጣመ እንደሚያደርገው ገልፀዋል።

@tikvahethiopia
በጉራፈርዳ ወረዳ 6 የጸጥታ ኃይሎች በታጣቂዎች ተገደሉ።

6 የደቡብ ክልል ልዩ ኃይል አባላት በቤንች ሸኮ ዞን በሚገኘው ጉራፈርዳ ወረዳ ውስጥ ትላንት በታጣቂዎች ተገድለዋል።

የልዩ ኃይል አባላቱ የተገደሉት በወረዳው ስር ባለው ወጀምታ ቀበሌ ነው።

"ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ድረገፅ" ቃላቸውን የሰጡት የጉራፈርዳ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሲሳይ ሻሎም ፥ ጥቃት የተፈጸመባቸው የደቡብ ክልል ልዩ ኃይል አባላት፤ በወጀምታ ቀበሌ ልዩ ስሙ ሰንበሊጥ በተባለ ቦታ ባለ ካምፕ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።

8 የልዩ ኃይል አባላት፤ ትላንት ከጠዋት 2 ሰዓት ገደማ፤ አንድ የካምፑን ሰራተኛ አጅበው ውሃ ለመቅዳት ወደ ወንዝ ሲሄዱ ተኩስ እንደተከፈተባቸው አስረድተዋል።

በጥቃቱ ስድስት የልዩ ኃይል አባላት ሲገደሉ አብሯቸው የነበረው የካምፑ ሰራተኛ ጉዳት ደርሶበት ህክምና ላይ ይገኛል ብለዋል።

ለአጀባ ከተሰማሩት የጸጥታ ኃይሎች ውስጥ 2ቱ ምንም ጉዳት እንዳልደረሰባቸውም ሲሉ ገልፀዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ : ethiopiainsider.com/2021/3451/

(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

@tikvahethiopia
የደቡብ ክልል የ8ኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ 28 እስከ ሰኔ 30 ይሰጣል።

በደቡብ ክልል የ8ኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ 28 እስከ 30 2013 ዓ.ም እንደሚሰጥ የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡

ቢሮው አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማድረግ የተማሪዎች መመዝገቢያ ቅጽ እንግሊዝ ሀገር ከሚገኝ DRS ድርጅት ግዢ እንደተፈጸመና ቢሮ መግባቱን አሳውቋል።

የቅጽ አሟላሉን በተመለከተ በክልሉ ለሚገኙ ሁሉም የፈተና ክፍል ኃላፊዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠቱን ቢሮው ገልጿል።

በክልሉ የሚገኙ 16 ዞኖችና 7 ልዩ ወረዳዎች ፎርሙን ወስደው በመንግስትና በግል ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎችን እያስሞሉ ነው ተብሏል።

የፈተና ዝግጅት ተጠናቆ የህትመት ስራ እየተሰራ ይገኛል።

ፈተናው በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች ከሰኔ 28 እስከ ሰኔ 30/2013 ይሰጣል ተብሏል። #SRTA

@tikvahethiopia
#Ethiopia #COVID19

ኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ካደረገችው 4,505 የኮቪድ19 የላብራቶሪ ምርመራ 173 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል፤ ይህም አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር 272,805 አድርሶታል።

በ24 ሰዓት 8 ሰዎች ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን በአጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 4,201 ደርሷል።

የኮቪድ-19 ክትባት የተከተቡ ዜጎች 1,878,367 ደርሰዋል።

@tikvahethiopia
ቴምቲዮፔ ባሎጉን ጆሹዋ ህይወታቸው አለፈ።

ታዋቂው ናይጄሪያው የሃይማኖት ሰባኪ ቴምቲዮፔ ባሎጉን ጆሹዋ ትናንትና ህይወታቸው አለፈ።

ቴምቲዮፔ ባሎጉን ጆሹዋ ወይም በተለምዶ ቲቢ ጆሹዋ ማረፋቸውንም ይፈዊ በሆነው ፌስቡክ ገፃቸውም ላይ "አምላክ አገልጋዩን ቲቢ ጆሹዋን ወደቤቱ ወስዷል" በሚልም ሰፍሯል።

ስመ ጥር የሆኑት የኢቫንጀሊካን ሃይማኖት ሰባኪ በትናንትናው ዕለት የቤተክርስቲያን ፕሮግራማቸውን ከጨረሱ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ምሽት ላይ ማረፋቸው ተገልጿል።

በተከታዮቻቸው ዘንድ የነብይነትን ማዕረግ ያገኙት ቲቢ ጆሹዋ በአህጉሪቷ ውስጥ ተፅእኖ መፍጠር ከቻሉ የኢቫንጀሊካል ሰባኪዎች አንዱ ናቸው ።

በአፍሪካ ውስጥም ያሉ ታዋቂ ፖለቲከኞችንም በተከታይነት ማፍራት ችለዋል።

"ቸርች ኦፍ ኦል ኔሽንስ" የሚባል የእምነት ተቋምን የመሰረቱ ሲሆን እንዲሁም በቴሌቪዥንም በሚያደርጓቸው ስብከቶችም በርካታ የእምነቱ ተከታይ ምዕመናንን ማፍራት ችለዋል።

በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በሌጎስ የሚያደርጓቸውን ሳምንታዊ የአገልግሎት ስርዓት ይከተላሉ ነበር።

ቴምቲዮፔ ባሎጉን ጆሹዋ በ57 ዓመታቸው ነው ህይወታቸው አለፈ።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

@tikvahethiopia
የጣና በለስ የተቀናጀ የስኳር ፋብሪካ ዛሬ እየተመረቀ ነው።

በ231 ሚሊየን ዶላር የተገነባው የጣና በለስ የተቀናጀ የስኳር ፋብሪካ እየተመረቀ ነው።

በምረቃ ስነ-ስርአቱ ላይ የፌደራል፣ የክልልና የዞን ባለስልጣናትና የስራ ሀላፊዎች እንዲሁም የአካባቢው ማህበረሰብ አባላት ተገኝተዋል ።

የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አብርሃም ደምስ እንዳሉት ለፋብሪካው ግንባታ 231 ሚሊየን ዶላር ወጭ ተደርጓል።

የጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ በ2003 አ.ም ግንባታው ተጀምሮ በተለያዩ ምክንያቶች ሳይጠናቀቅ መቆየቱ የሚታወስ ነው።

በ2010 አ.ም የፋብሪካው ግንባታውን ለቻይናው ሲ ኤም ሲ ኢ ኩባንያ በመሰጠቱ ቀሪው ስራ በ14 ወራት ተጠናቆ ዛሬ ለምረቃ በቅቷል። #ENA

@tikvahethiopia
#Update

የ "አበበች ጎበና ህፃናት ክብካቤ እና ልማት ማህበር" ከሰዓታት በፊት ባሰራጨው መልዕክት ክብርት ዶ/ር አበበች ጎበና (እዳዬ) አሁንም በጳውሎስ ሆስፒታል በጽኑ ሕሙማን ክፍል ሕክምና እያገኙ መሆኑን አሳውቋል።

ዶክተሮቻችው ለቤተሰብ እንደገለፁት ጤናቸው በጣም መሻሻል አሳይተዋል፡፡

የልብ፣ የኩላሊት፣ የጉበት፣ የደም ግፊትና የመሳሰሉት ምርመራ ተደርጎላቸው ጥሩ የሚባል ሁኔታ ላይ መሆናቸው ዶክተሮች ገልፀዋል ብሏል ማህበሩ ባሰራጨው መልዕክት።

ማህበሩ ፥ "የጳውሎስ ሆስፒታል የጤና ባለሙያዎች ደከመኝ ሰለጨኝ ሳይሉ 24 ሰዓታት የእዳዬን ጤና ለመመለስ የህምና እርዳታ ላደረጉላቸው ከልብ የመነጨ ምስጋና እናቀርለን" ሲል አመስግኗል።

ወዳጆቻቸው፣ ልጆቻችው እና ሎሎችም ከኢትዮጵያ ና ከተለያዩ ሀገራት በእንዳዬ መታመም ተጨንቀው ስልክ በመደወልና መልዕክት በመላክ የጠየቁትን በአጠቃለይ በፀሎትም አብረው ለሆኑ ሁሉም ማህበሩ አመስግኗል።

በመጨረሻም፥ የሺዎች እናት የሆኑት ክብርት ዶ/ር አበበች ጎበና ፈጣሪ ጨርሶ ይምራቸው ዘንድ ሁላችንም እንፀልይላቸው ሲል የአበበች ጎበና ህፃናት ክብካቤ እና ልማት ማህበር መልዕክት አስተላልፏል።

ክብርት ዶ/ር አበበች ጎበና በኮቪድ-19 ተይዘው ለህክምና ሆስፒታል መግባታቸው ይታወሳል።

@tikvahethiopia
#TiffanyHaddish

የ41 ዓመቷ አሜሪካዊት ተዋናይትና ኮሜዲያን ቲፋኒ ሀዲሽ በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ስላለው ግጭት በሰጠቻቸው አስተያየቶች/በምታጋራው መልዕክቶ ምክንያት ከፍተኛ ተቃውሞ እየቀረበባት ነው።

የምታጋራው መልዕክቶች በርካታ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎችን አስቆጥቷል።

ቲፍኒ ሀዲሽ ፥ "በትግራይ ላይ የሚፈፀውን የንፁሃን ግድያ ፣ የሴቶች መደፈር፣ የህፃናት ሞት ክዳለች ፣ በትግራይ ጉዳይ ጦሯን ላሰማራቸው #ኤርትራ በተለይም አምባገነን ለሆነው የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ድጋፍ ትሰጣለች" በሚል ነው ከፍተኛ ተቃውሞ እያስተናገደች የምትገኘው።

ቲፍኒ ሀዲሽ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በትግራይ ስላለው ሁኔታ በትዊተር ገጿ የተለያዩ መልዕክቶችን እያስተላለፈች ሲሆን ከነዚህ ውስጥ አንዱ ከትግራይ ጦርነት ጋር በተያያዘ የሚሰራጩ #ሀሰተኛ መረጃዎች የሚመለከት ነው።

በተጨማሪ፥ በአንድ ሪትዊት ላይ የቀድሞ የትግራይ ክልል ፕሬዜዳንት ዶ/ር ደብረፅዮን "ጦርነቱ የህዝብ መሆኑን ህፃናትም የዚህ አካል ስለመሆናቸው" ተናግረውበታል የተባለውን የእሳቸውን ንግግር አጋርታለች።

ከተቃዋሚዎቹ በተቃራኒው ደግሞ የምታጋራቸውን መልዕክቶች ትክክል እንደሆኑ የሚገልፁ በርካታ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ታይተዋል።

ቲፍኒ ሀዲሽ በ1979 እ.አ.አ. በሎስ አንጀለስ የተወለደች ሲሆን አባቷ ፀሃዬ ረዳ ሀድሽ በወቅቱ የኢትዮጵያ አካል የነበረችውን ኤርትራን ጥለው የተሰደዱ ስደተኛ ነበሩ።

ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ ቲፋኒ ሀዲሽ ከኤርትራና ከመሪዋ ኢሳያስ አፍወርቂ ጋር ጥሩ የሚባል ወዳጅነትንና ቅርርብ ስለመፍጠራቸው ይነገራል።

ለመጀመሪያ ጊዜ ኤርትራን የጎበኘችው እ.ኤ.አ. በ2018 ሲሆን በወቅቱ የአባቷን ህልፈት ተከትሎ በእሳቸውን የቀብር ስነስርዓት ላይ ለመገኘት ነበር።

@tikvahethiopia