TIKVAH-ETHIOPIA
የለሊሳ ዳንኤል እና ቢቂላ ዳንኤል አውሮፕላን ! በኦሮሚያ ምስራቅ ወለጋ ከነቀምቴ ቅርብ ርቀት በምትገኘው የሲቡ ሲሬ ከተማ ነዋሪ የሆኑት ወንድማማቾች ለሊሳ ዳንኤል እና ቢቂላ ዳንኤል ከሰሞኑ የሰሯትን 'አውሮፕላን' ለማብረር ጥረት ማድረጋቸው የበርካቶች መነጋገሪያ ሆነዋል። ወጣቶቹ "ኦሮሚያ" ሲሉ የሰየሟትን 'አውሮፕላናቸውን' ለማብረር ሙከራ ማድረጋቸው የአከባቢ ሰዎች በታሪክ መዝገብ ለመጀመሪያ ጊዜ…
ወንድማማቾቹ የማበረታቻ ሽልማት ተበረከተላቸው።
የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ማኔጅመንት በፈጠራ ሥራ ላይ ለተሳተፉት ወጣቶች የማበረታቻ ሽልማት አበረከተ።
በሁለት ወጣት ወንድማቾች (ቢቅላ ዳንኤልና ለሊሳ ዳንኤል) አውሮፕላን ሠርተው ለማብረር ላደረጉት ፈጠራና ሙከራ አድናቆት ነው የማበረታቻ ሽልማት የተሰጣቸው።
የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ፕረዝዳንት ዶክተር ሀሰን ዩሱፍ ፥ ዩኒቨርሲቲው በሚቀጥሉት 10 ዓመታት ሊመራበት ባዘጋጀው ስትራቴጅክ ዕቅድ አንዱ የትኩረት አቅጣጫ የቴክኖሎጂ ሽግግርና ፈጠራን ማስፋፋት እንደሆነ አስታውሰዋል።
አክለው፥ የወንድማቾቹ ቢቅላ ዳንኤልና ለሊሳ ዳንኤል ከዩኒቨርሲቲው ዓላማ የትኩረት አቀጣጫ ጋር ስለምሄድ ወንድማቾቹን ብሎም ሌሎች ወጣቶችን ለማበረታታት ሽልማት እንደተበረከተላቸው ገልፀዋል።
ወንድማቾቹ ራዕይያቸው የኦሮሚያ አየር መንገድ መመሥረትና ኦሮሚያ የቴክኖሎጂ መፍለቂያ በማድረግ ክልሉን ብሎ ኢትዮጵያን ሥመ-ጥር ለማድረግ እንደሆነ ተናግረዋል።
ዩኒቨርሲቲው ተመሳሳይ ድጋፎች ማድረግን አጠናክሮ እንደሚቀጥል በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ ላይ ገልጿል።
ምንጭ፦ ወለጋ ዩኒቨርሲቲ
@tikvahethiopia

የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ሪፖርት ፦
- በትግራይ አክሱም ከተማ ህዳር 19 እና 20፣ 2013 ዓ.ም በነበረው ውጊያ የኤርትራ ወታደሮች 110 ንጹሃን ሰዎች ገድለዋል።
• 70 ሰዎች በአክሱም ከተማ ውስጥ በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ መንገድ ላይ እያሉ ተደገድለዋል ከሟቾቹ ውስጥ ወታደራዊ የደንብ ልብስ ባይለብሱም በጦርነቱ የተሳተፉ ሰዎች ነበሩ።
• 40 ንጹሃን ሰዎች የኤርትራ ወታደሮች ቤት ለቤት ባደረጉት አሰሰሳ ከቤታቸው እንዲወጡ ተደርገው እና በቤታቸው ውስጥ ተገድለዋል።
- በከተማዋ በርከት ያሉ የንብረት ዘረፋ እና ውድመት ደርሷል፥ ከእነዚህም ውስጥ የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ካምፓሶች፣ ቅድስት ማርያም ሆስፒታል ብራና ሆቴል ይገኙበታል።
- ጠቅላይ አቃቤ ህግ በትግራይ በንጹሃን ግድያና በጾታ ጥቃት ላይ ትኩረት በማድረግ ባካሄደው ምርመራ፣ የወታደራዊ ግዴታ በሌለበት ወቅት በግድያ የተጠረጠሩ 28 የኢትዮጵያ ወታሮች ላይ ክስ መስርቷል።
- የጾታ ጥቃት እና አስገድዶ መድፈር የፈጸሙ 25 ወታደሮች ክስ ተመስርቶባቸዋል።
* ሙሉ የአቃቤ ህግ ሪፖርት ከላይ ተያይዟል።
#አል_ዓይን #የፌዴራል_ጠቅላይ_አቃቤ_ህግ
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT

አሜሪካ ?
በአሜሪካ እስር ቤት አንድ ታራሚን ፖሊሶች መሬት ላይ አስተኝተውት "መተንፈስ መቻል የለብህም" እያለች አንዲት ፖሊስ ስትሳለቅበት እንደነበር የሚያሳይ ቪዲዮ ወጥቷል።
ቪዲዮው እንደሚያሳየው የ48 አመቱ ዊልያም ጄኔት የተባለ ታራሚ በቴኔሲ ግዛት ማርሻል ካውንቲ እስር ቤት ውስጥ ከኋላ ታስሮና ደረቱ ከመሬት ላይ ተጣብቆ ነው።
"እባካችሁ እርዱኝ" በማለት የእስር ቤቱን ሰራተኞች ሲማፀን ይሰማል አክሎም በተቆራረጠ ድምፅ "ሊገሉኝ ነው" ይላል።
ፖሊሶቹ ከጀርባው ተጭነውት የነበረ ሲሆን መተንፈስ አልቻልኩም እያለ ሶስት ጊዜ ሲማፀንም ሊነሱለት አልቻሉም።
እንዲያውም አንደኛዋ ፖሊስ "መተንፈስ መቻል የለብህም" በማለትም አፀያፊ ስድብ ስትሰድበው ይሰማል።
ለ5 ደቂቃ ያህል በደረቱ መሬት ላይ አጣብቀውት ነበር ተብሏል።
አንደኛው ፖሊስ በበኩሉ ታፍኖ ሊሞት ይችላል እንዲተነፍስ እናድርገው ሲል ይሰማል።
ክሱ እንደሚያስረዳው ታራሚውን በጀርባው በሚገለብጡበት ወቅት ፊቱ ወይንጠጅ ቀለም የታየበት ሲሆን ሰውነቱም በድን ሆኖ ነበር።
የታራሚው አስከሬን የምርመራ ውጤት እንደሚያሳየው ግለሰቡ መጠጥና አደንዛኝ ዕፅ በመጠቀም መሞቱንና ከዚህ በተጨማሪ ፖሊስ በቁጥጥር ስር ለማዋል የተጠቀመበት መንገድ እንዲያፍነው ማድረጉ ለሞቱ መንስኤዎች ተብለው ተጠቅሰዋል።
በተለይ ታራሚው ከሞተ በኋላ ጥቁር አሜሪካዊውን ጆርጅ ፍⶀይድ መሬት ላይ ደፍቀውና አንገቱ ላይ ተንበርክከው መግደላቸውን ተከትሎ ውዝግብ አስነስቷል።
ይህ ታራሚ ነጭ ሲሆን ልጁም በአባቷ ሞት ፖሊስ ተጠያቂ ነው ስትል ክስ መስርታለች።
በዚህ ክስ ላይ ሰባት ፖሊሶች ኃይልን ያለ አግባብ መጠቀም በሚል ክስ ቀርቦባቸዋል። #ቢቢሲ

#ፋሲል_ከነማ
ዛሬ በሀዋሳ ከተማ የፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ የ2013 የቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን ይረከባል።
ቡድኑ ዋንጫውን የሚረከበው በአሁን ሰዓት ከሃዋሳ ጋር እያካሄደ ያለውን ጨዋታ እንዳጠናቀቀ ነው።
ጨዋታው ሊጠናቀቅ ጥቂት ደቂቃዎች የቀሩት ሲሆን ፋሲል ሀዋሳን 1 ለ 0 እየመራ ነው።
2 ሺህ የፋሲል ደጋፊዎች በስታዲየሙ ተገኝነዋል::
@tikvahethsport

#ፋሲል_ከነማ ዛሬ በሀዋሳ ከተማ የፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ የ2013 የቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን ይረከባል። ቡድኑ ዋንጫውን የሚረከበው በአሁን ሰዓት ከሃዋሳ ጋር እያካሄደ ያለውን ጨዋታ እንዳጠናቀቀ ነው። ጨዋታው ሊጠናቀቅ ጥቂት ደቂቃዎች የቀሩት ሲሆን ፋሲል ሀዋሳን 1 ለ 0 እየመራ ነው። 2 ሺህ የፋሲል ደጋፊዎች በስታዲየሙ ተገኝነዋል:: @tikvahethsport
#ፋሲል_ከነማ
ዛሬ በሀዋሳ ከተማ የፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ የ2013 ዓ/ም የቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን ተረክቧል።
ፋሲል ከሀዋሳ ጋር ያደረገው ጨዋታ 1 ለ 1 ነው የተጠናቀቀው።
@tikvahethsport
ዛሬ በሀዋሳ ከተማ የፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ የ2013 ዓ/ም የቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን ተረክቧል።
ፋሲል ከሀዋሳ ጋር ያደረገው ጨዋታ 1 ለ 1 ነው የተጠናቀቀው።
@tikvahethsport
#Election2013
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ለ6ተኛው አጠቃላይ ምርጫ የመራጮች ምዝገባን በአጠቃላይ ያጠናቀቀ ቢሆንም ዘግይተው የጀመሩ ምርጫ ክልሎች ምዝገባ ሲከናወን እንደነበር አስታውቋል።
በጊዜ ሰሌዳው መሰረት ዘግይተው የጀመሩ ምርጫ ክልሎች ላይ ያለው የመራጮች ምዝገባ ትላንትና በይፋ መጠናቀቁን አሳውቋል።
የመራጮች ምዝገባ በትላንትና ግንቦት 13 ቀን 2013 የተጠናቀቀባቸው ቦታዎች፦
• በምእራብ ወለጋ ዞን ( ለቤጊ እና ሰኞ ገበያ ምርጫ ክልል ውጨ)
• በምስራቅ ወለጋ ዞን ( ከአያና እና ገሊላ ምርጫ ክልል ውጪ)
• በቄለም ወለጋ ዞን ( ጊዳም ምርጫ ክልል ውጪ)
• በሆሮ ጉድሩ ዞን ( ከአሊቦ እና ኮምቦልቻ ምርጫ ክልል ውጪ) የሚገኙት 24 የምርጫ ክልሎች ናቸው።
ከዚህ በተጨማሪ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሽ ዞን ሲከናወን የነበው ምዝገባ እና የአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔር ልዪ ዞን የሚገኙት ዳዋ ጨፌ፣ ጨፋ ሮቢት እና ባቲ ምርጫ ክልሎች በተመሳሳይ ሁኔታ ተጠናቋል።
በዚህም መሰረት በነዚህ ምርጫ ክልሎች የመራጮች መዝገብ ለሚቀጥሉት 10 ቀናት ማለትም እስከ ግንቦት 23 ቀን 2013 ድረስ ለህዝብ ይፋ የሚሆን ሲሆን የመራጮች መዝገባ ቀን ከተጠናቀቀበት ቀን በኋላ ምንም አይነት ምዝገባ ማካሄድ አይቻልም።

#NewsAlert
በዛሬው ዕለት ሚኒስትሮች ም/ቤት ለግሎባል ፓርትነርሺፕ ፎር ኢትዮጵያ የኢትዮጵያ የኮሙኒኬሽን ባለሥልጣን አዲስ ሀገር አቀፍ የቴሌኮም ፈቃድ እንዲሰጥ በአንድ ድምፅ አፀደቀ።
ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት "ታሪካዊ ውሳኔን ወስኗል" ብለዋል።
በአጠቃላዩ ከ8 ቢሊዮን ዶላር በሚበልጥ የሙዓለ ነዋይ ፍሰትና እስከ ዛሬ በኢትዮጵያ ከተደረጉት የውጪ ቀጥተኛ የሙዓለ ነዋይ ፍሰቶች ብልጫ እንዲኖረው ያደርገዋልም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ ገልፀዋል።

ተጨማሪ ፦
በኢትዮጵያ የቴሌኮም አገልግሎት ልምድ እና አቅም ያላቸው የውጭ ኩባንያዎች እንዲሳተፉ ለማድረግ ለረጅም ጊዜ ሲሰራ ነበር።
በዚህ መሰረት ሜይ 21/2020 በኢትዮጵያ ኮሚኒኬሽን ባለስልጣን ለቀረበው ጥሪ 12 ኩባንያዎች በጨረታው ለመሳተፍ ፍላጎት አሳይተው ነበር።
ከነዚህ መካከል 9 ድርጅቶች የጨረታ ሰነዱን ገዝተዋል።
በገንዘብ ሚኒስቴር በኩል የተቋቋመው የቴክኒክ ኮሚቴ ባደረገው ማጣራት ቴክኒካል እና ፋይናሻል ፕሮፖዛል ያቀረቡ ሁለት ኩባንያዎች ፦
• Global partnership for Ethiopia (Vodafone, Vodacom, Safaricom, Sumitomo Corporation, and the CDC Group የተባሉ ዓለም አቅፍ የቴሌኮም ኩባንያዎች በጥምረት ያቋቋሙት ኩባንያ) እና
• MTN International (Mauritius) Limited የተሰኙ ኩባንያዎች ጨረታውን መስፈርቶች አሟልተው ተገኝተዋል።
ለተጠቀሱት ድርጅቶች ለሁለቱም /ለአንዱ የቴሌኮም አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ ፍቃድ እንዲሰጥ አልያም የጨረታቅ ውጤት እንዲሰረዝ እንዲወሰን ለሚኒስትሮች ም/ቤት ቀርቦ ነበር።
ምክር ቤቱ ቁጥር 1 ላይ የተጠቀሰው ድርጅት ፦
- የኦፕሬሽን ፈቃድ ለማግኘት ያቀረበው ዋጋ 850 ሚሊዮን ዶላር (ከ2ኛ ድርጅት ዋጋ በ250 ሚሊዮን ዶላይ ብልጫ አለው) ፥
- ለ1.5 ሚሊዮን ዜጎች የስራ እድል ስለሚፈጥር፣
- ከ8 ቢሊዮን ዶላር በላይ ኢንቨስትመንት በአገር ውስጥ የሚያከናውን ስለሆነ እና ካለው የስራ ልምድ አንፃር ለኢትዮጵያ ጥራት ያለድ የቴሌኮም አገልግሎት ለማቅረብ አቅም ያለው መሆኑን ከግምት በማስገባት (Global partnership for Ethiopia) የኦፕሬሽን ፍቃድ እንዲሰጠው ተወስኗል።
ያንብቡ: telegra.ph/ETHIOPIA-05-22

#EthiopianElection2013 #NEBE
6ተኛው አጠቃላይ ምርጫ የሚካሄደው በሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሆነ ይታወቃል።
ድምጽ መስጠት ሂደቱ በተለያዩ ምክንያቶች ሊከናወንባቸው የማይችልባቸው የምርጫ ክልሎች እና የምርጫ ጣቢዎች የትኞቹ ናቸው ?
ሌሎችም ከምርጫ 2013 ዝግጅት ጋር የተያያዘ እና ማወቅ ያሉብን ጉዳዮች ምን ምንድናቸው ?
በዚህ ያንብቡ : https://telegra.ph/Election-2013-05-22