TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ.pdf
"...በአክሱም ከተማ የተካሄደውን ጭፍጨፋ ለመሸፋፈን ያለመ መግለጫ ነው" - አምነስቲ ኢንተርናሽናል

(አል አይን)

ጠቅላይ አቃቤ ህግ ከቀናት በፊት በአክሱም በነበረ ውጊያ 93 ሰዎች መሞታቸውንና ሟቾቹ ወታደራዊ የደንብ ልብስ ባይለብሱ አብዛኞቹ በጦርነቱ የተሳተፉ መሆናቸውን በምርመራ መረጋገጡን መግለፁ ይታወሳል።

በምርመራው “በጦርነቱ ተሳትፎ ያልነበራቸው በመንገድ ላይ የነበሩ ንጹሀን” ጭምር መግደላቸውንም ነበር ዐቃቤ ህግ ያስታወቀው፡፡

በተጨማሪ የህወሓት ታጣቂዎች ኤርትራ ሰራዊት ላይ ጥቃት መፈፀማቸው እንዲሁም በእስር ለነበሩ ወንጀለኞች የኤርትራ ወታደራዊ የደምብ ልብስ በመስጠት ከእስር ቤት መልቀቃቸው በአክሱም ለተፈፀመ ድርጊት ምክንያት እንደሆነ ገልፆ ነበር።

አምስነስቲ ኢንተርናሽናል ግን የጠቅላይ ዐቃቤ ህግን መግለጫ ተቃውሟል።

አምነስቲ ምን አለ ?

- ጥቃቱ ያነጣጠረው በታጣቂዎች ላይ ሳይሆን ንፁሀን ላይ ነው።

- ከሞት ለማምለጥ ሲሞክሩ የነበሩ ንፁሀን መጠቃታቸውን በምርመራ አረጋግጫለሁኝ።

- በኤርትራ ሰራዊት ሲደረግ በነበረ ቤት ለቤት አሰሳ ወጣቶችና አዛውንቶችን ጨምሮ በርካታ ንጹሀን ተገድለዋል፤ እስከ አመሻሽ በቆየው የቤት ለቤት አሰሳ በርካቶች ቤተሰቦቻቸው ፊት ተረሽነዋል።

- ወንጀሉን በመፈጸም ረገድ የኤርትራ ጦር ሚናን በተመለከተ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ በልኩ አላስቀመጠም።

- ከምስክሮች በቃለ መጠይቅ እንዳረጋገጥኩት የቤት ለቤት አሰሳ ሲያካሂዱ የነበሩት የኤርትራ ወታደሮች ከለበሱት የደምብ ልብስ በተጨማሪ በባህል እና የቋንቋ ዘያቸው ይለያሉ።

- በዓለም አቀፍ ሕግ መሰረት የኢትዮጵያ መንግሥት ይህንን ጭፍጨፋ የመመርመር ኃላፊነት አለበት።

ያንብቡ : telegra.ph/AL-AIN-05-14

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#DrAbiyAhmed

በዛሬው ዕለት ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድና ልዑካን ቡድናቸው ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ጅቡቲ ገብተዋል።

የጅቡቲ ሪፐብሊክ ፕሬዚደንት በዓለ ሲመትን እንደሚታደሙም የጠ/ሚ ፅ/ቤት አስታውቋል።

@tikvahethiopia
"...መላው ዓለም ችላ ቢልም ፤ ቱርክ ግን ዝም አትልም" - ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን

የቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ በምትፈፅመው የአየር ድብደባ “በጣም ተቆጥቻለሁ” ሲሉ ተናገሩ።

ፕሬዜዳንቱ የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ም/ቤት ሰላማዊ መፍትሄ እንዲፈልግም አሳሰበዋል።

ኤርዶጋን በኦንላይ ባደረጉት ንግግር ፥ አሸባሪ ሲሉ በጠሯት እስራኤል ፍልሥጤማውያን ላይ በፈፀመችው የጭካኔ ተግባር "አዝነናል ተቆጥተናልም" ብለዋል።

"የእስራኤልን የደም ማፋሰስ ተግባር ዝም ብለው የሚያዩ ወይም በግልፅ የሚደግፉ አንድ ቀን የእነሱ ተራ እንደሚሆን ማወቅ አለባቸው" ሲሉም ተደምጠዋል።

ኤርዶጋ የተመድ ፀጥታው ምክር ቤት የእየሩሳሌምን ሰላም ለማረጋገጥ እርምጃዎችን መውሰዱ “አስፈላጊ እና አስቸኳይ” መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻ ፕሬዜዳንት ኤርጎጋን መላው ዓለም እስራኤል በፍልስጤም ላይ የምታደርደውን ግፍና ጭካኔ ቻላ ቢልም ቱርክ ግን ዝም አትልም ብለዋል።

በእስራኤል እና በፍልሥጤም መካከል በተነሳው ግጭት ሀገራት እና መሪዎች የተለያየ ሃሳቦችን እየሰጡ ነው።

ትላንት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን በእስራኤል ላይ የፍልስጤም ታጣቂዎች የሚፈፅሙት የሮኬት ጥቃት መቆም እንዳለበት በመግለፅ ፤ አሜሪካ እስራኤል እራሷን የመከላከል መብት እንዳላት ግልፅ ማድረጓን መግለፃቸው ይታወቃል።

48ኛው የአሜሪካ ምክትል ፕሬዜዳንት የነበሩት ማይክ ፔንስም በይፋዊ ትዊተር ገፃቸው ላይ "አሜሪካ ከእስራኤል ጋር ትቆማለች" ብለዋል፤ ይህ ትዊታቸውም PIN ተደርጓል።

@tikvahethiopia
ቃሊቲ እስር ላይ የሚገኙት አቶ እስክንድር ነጋ የፃፉት 'ድል ለዴሞክራሲ' የተሰኘ መፅሃፍ ገበያ ላይ እንደሚውል ተሰምቷል።

አቶ እስክንድር ነጋ በቃሊቲ እስር ቤት ሆነው የፃፏቸው ፅሁፎች ስብስብ በመፅሐፍ መዘጋጀታቸውን ባለቤታቸው ወ/ሮ ሰርካለም ፋሲል በይፋዊ ፌስቡክ ገፃቸው አሳውቀዋል።

ባለቤታቸው ፥ መፅሀፉ በነገው ዕለት ግንቦት 7 ቀን 2013 በገበያ ላይ እንደሚውል ገልፀዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ በትግራይ ክልል ጉዳይ የተናገሩበት ቪድዮ ፦ ይህ ከ14 ደቂቃ በላይ ርዝማኔ ያለው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ በትግራይ ጉዳይ የሚናገሩበት ቪድዮ የተቀረፀው በሞባይል ነው። ቪድዮው Dennis Wadley በተባሉና የሳቸው የቅርብ ወዳጅ በሆኑ ሰው በሞባይል የተቀረፀ መሆኑ ነው የተገለፀው። Dennis Wadley በአሜሪካ መቀመጫነቱን…
"...የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ንግግር ትግራይ ክልል እየተፈጸመ ያለውን ግፍ በትንሹ የሚያሳይ እንጂ የደረሰውን ሙሉ ግፍ የሚያስረዳ አይደለም" - መቐለ ሐገረ ስብከት

በመቐለ ሐገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ኢሳይያስ የተመራ ጉባኤ በብጹእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ንግግር የተካተተውን ሐሳብ እንደሚቀበል አስታወቀ፡፡

- የወረዳ ቤተክህነት ሠራተኞች፣
- የአብነት መምህራን፣
- ማኅበረ ካህናት፣
- ማኅበረ ምእመናን፣
- ሰንበት ትምህርት ቤቶች
- የትግራይ ነገረ-መለኮት ምሩቃን ማኅበር በጋራ መክረው ትላንት በትግርኛ ቋንቋ ባወጡት መግለጫ በትግራይ ሴቶች ላይ የደረሰውና እየደረሰ ያለው አረመኔያዊ ድርጊት ዘመን የማይረሳው ክፉ ታሪክ እንደሆነ ቅዱስነታቸው በከባድ ሐዘን መግለጻቸው ተቀባይነት ያለው ጉዳይ ነው ብሏል፡፡

የኢትዮጵያ እንዲሁም የቤተክርስትያኒቷ አንድነት እንዲበታተን በሚሰሩ ኢትዮጵያውያን ተጋሩን ለማጥፋት የሚካሄደው ጦርነት በፋይናንስ እና በሃሳብ የደገፉ ቢሆኑም ለሃገሪቱ እና ለቤተክርስቲያኗ ግን ሰላም አላመጣም ይላል መግለጫው።

የቅዱስነታቸው ንግግር ትግራይ ክልል እየተፈጸመ ያለውን ግፍ በትንሹ የሚያሳይ እንጂ የደረሰውን ሙሉ ግፍ የሚያስረዳ አይደለምም ብሏል መግለጫው።

የቅዱስነታቸው ንግግር ከተሰራጨ በኋላ በትግራይ ክልል የሚደርሰው ግፍ እንዲታፈን የሚጥሩ አካላትን እንቃወማለን ከቅዱስነታቸው ጎን እንደምንቆም እናረጋግጣለን ማለቱን አዲስ ዘይቤ ድረገፅ አስነብቧል።

@tikvahethiopia
* የአሜሪካ መግለጫ !

የጄፍሪ ፌልትማንን የምስራቅ አፍሪካ ጉብኝት አስመልክታ አሜሪካ በውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቷ ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት በኩል መግለጫ አውጥታለች።

በመግለጫዋ ምን አለች ?

- የአፍሪካ ቀንድ በወሳኝ የለውጥ ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝ ጠቁማለች፤ በቀጣይ ሳምንታትና ወራት የሚተላለፉ ውሳኔዎች ለቀጠናው ህዝቦች ለራሷ ፍላጎቶች ጭምር ትልቅ እንደምታ እንደሚኖራቸው አስታውቃለች፡፡

- በኢትዮጵያ የሚስተዋለው የፖለቲካና የጎሳ ጽንፈኝነት እጅጉን እንደሚያሳስባት ገልፃለች።

- በትግራይ እየተፈፀሙ ያሉ ግፍ እና ጭካኔዎች እንዲሁም ኢ-ሰብአዊ ሁኔታዎች ተቀባይነት የላቸውም ብላለች።

- በትግራይ የሚካሄደውን ጦርነት ለማቆም፣ የህይወት አድን እርዳታዎችን ለማድረግ እና ጥፋተኞችን ተጠያቂ ለማድረግ ከዓለም አቀፍ አጋሮቿ ጋር እንደምትሰራ አስታውቃለች።

- በትግራይ ያጋጠመው ችግር ተስፋ ተጥሎበት የነበረው ሃገራዊ ለውጥ ለገጠሙት ዘርፈ ብዙ ችግሮች ማሳያ ሆኖ በምልክትነት ሊጠቀስ እንደሚችል ገልፃለች።

- ጄፍሪ ፌልትማን ከፕሬዜዳንት ኢሳያስ ጋር በአስመራ በነበራቸው ቆይታ የኤርትራ ወታደሮች በቶሎ መውጣት የግድ ስለመሆኑ አፅንዖት ሰጥተው እንደነገሯቸው አሜሪካ አሳውቃለች።

- የግድቡ ጉዳይ የኢትዮጵያን የመልማት ፍላጎት በማከለ መልኩ በአፍሪካ ህብረት መሪነት መፍትሄ ሊያገኝ እንደሚችል አሜሪካ አሳውቃለች።

- በአፍሪካ ህብረት መሪነት የሚካሄደው ድርድር በአስቸኳይ ሊጀመር እንደሚገባ አሜሪካ አሳስባለች።

በዝርዝር ያንብቡ : telegra.ph/AL-AIN-05-14-2

ምንጭ፦ አል አይን

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
የኮቪድ-19 ሪፖርት ፦

ባለፉት 24 ሰዓት 13 ሰዎች በኮቪድ-19 ህይወታቸው አልፏል።

በተመሳሳይ ከተደረገው 4,270 የላብራቶሪ ምርመራ 453 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

ትላንት 1,636 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

በአጠቃላይ 265,413 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 3,964 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 217,370 ሰዎች አገግመዋል።

አሁን ላይ 620 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

በሀገራችን እየተሰጠ ያለውን የኮቪድ-19 ክትባት የተከተቡ ዜጎች ቁጥር 1,436,665 ደርሷል።

#Purpose
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
* የአሜሪካ መግለጫ ! የጄፍሪ ፌልትማንን የምስራቅ አፍሪካ ጉብኝት አስመልክታ አሜሪካ በውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቷ ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት በኩል መግለጫ አውጥታለች። በመግለጫዋ ምን አለች ? - የአፍሪካ ቀንድ በወሳኝ የለውጥ ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝ ጠቁማለች፤ በቀጣይ ሳምንታትና ወራት የሚተላለፉ ውሳኔዎች ለቀጠናው ህዝቦች ለራሷ ፍላጎቶች ጭምር ትልቅ እንደምታ እንደሚኖራቸው አስታውቃለች፡፡ - በኢትዮጵያ…
አሜሪካ ስለታላቁ የህዳሴ ግድብ ፦

"...ጄፍሪ ፌልትማን በውሃ እና በግድቡ ደህንነት እና አስተዳደር ጉዳዮች ላይ ስጋት አለን ከሚሉት ከግብጽ እና ሱዳን መሪዎች ጋር መክረዋል።

ጉዳዩ የኢትዮጵያን የመልማት ፍላጎት በማከለ መልኩ በአፍሪካ ህብረት መሪነት መፍትሄ ሊያገኝ ይችላል።

ለዚህም በአፍሪካ ህብረት መሪነት የሚካሄደው ድርድር በአስቸኳይ ሊጀመር እንደሚገባ እናሳስባለን።

በ2015ቱ የመርሆዎች ስምምነት መግለጫ (DoP) እና የአፍሪካ ህብረት ቢሮ ባሳለፍነው ክረምት የሰጠው መግለጫ ለድርድሩ መሰረት ሆኖ ያገለግላል በሚል እናምናለን።

አሜሪካ ለድርድሩ ስኬት ቴክኒካዊ እና ፖለቲካዊ ድጋፎችን ለማድረግ ቁርጠኛ ናት።"

#AlAIN
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከግቢ ይወጣሉ መባሉን ከተከትሎ ቅሬታ አለን ያሉ ተማሪዎች አሉ ፤ ምንድነው ቅሬታቸው ?

የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች 6ኛው ሀገራዊ ምርጫን ተከትሎ ተማሪዎች ወደቤታቸው እንደሚሄዱ ከወዲሁ እያሳወቁ ይገኛሉ።

ይህን ተከትሎትም ቅሬታ አለን የሚሉ ተማሪዎች ለቲክቫህ አሳውቀዋል።

መልዕክት የላኩ ተማሪዎች ፥ በፀጥታ፣ በሽታና በትምህርታዊ በሌሎችም ምክንያቶች መመለስ እንደማይፈልጉ ገልፀውልናል።

ተማሪዎቹ በ2012 ዓ/ም በኮሮና ምክንያት ተቋርጦ የቆየው ትምህርት አሁን ደግሞ በምርጫ በሚል ድጋሚ ትምህርት ከተቋረጠ በተማሪዎች ላይ የሚያሳድረው ስነልቦናዊ ጫና ፣ ተስፋ የመቁረጥ ስሜት ከፍተኛ ነው ሲሉ አስረድተዋል።

ተማሪዎች እንዲበተኑ የሚደረግበት ምክንያት በዝርዝር እንዲገለፅ ፤ በሌላ በኩል አንፃራዊና አስተማማኝ ሰላም ባለባቸው ቦታዎች ተማሪዎች ባሉበት ሆነው ትምህርት እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

ነገር ግን የግዴታ ከግቢ የሚወጣ ከሆነ የሰላም እና ፀጥታ ችግር ካለባቸው የሀገሪቱ ክፍሎች ማለትም ከትግራይ ፣ ከመተከል፣ ወለጋ...የመጡ እና አንፃራዊ ሰላም ባለባቸው ከተሞች የሚማሩ ተማሪዎች በግቢ እንዲቆዩ ጠይቀዋል።

በሌላ በኩል አካል ጉዳተኛ የሆኑ እና የተማሪ ህብረቶች በግቢ እንቆይ ብለዋል።

የግዴታ ከግቢ የሚወጠ ከሆነ ተማሪዎች በቂ የትራንስፖርት አገግልግሎት እንዲመቻችላቸው ከወዲሁ ጠይቀዋል።

ቅሬታና ጥያቄያቸውን ለ @tikvahuniversity ያሳወቁ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጥያቄያቸውን ለተማሪ ህብረት ፅ/ቤት ፥ህብረቱም ለበላይ አመራሮች በማቅረብ ምላሽ በመጠባበቅ ላይ መሆናቸውን አስረድተዋል።

ከዚህ ቀደም MoSHE ለቲክቫህ በዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የምርጫ ተሳትፎ ዙሪያ ውሳኔን ይፋዊ መግለጫ በመስጠት እንደሚያሳውቅ መግለፁ የሚዘነጋ አይደለም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ከደቡብ ሌባኖስ እስራኤል ላይ ሮኬት ተተኮሰ። በእስራኤልና በፍልስጤም መካከል ያለው ግጭት አካሄዱ ብዙዎችን እያሰጋ ነው። ከደቂቃዎች በፊት አልጀዚራ በሰበር ዜና ከደቡብ ሊባኖስ በትንሹ 3 ሮኬቶች ወደ እስራኤል መተኮሳቸውን የሊባኖስ ፀጥታ ኃይሎች መግለፃቸውን ዘግቧል። የእስራኤል ጦር ሮኬቶቹ በሜዴትራንያን ባህር ላይ እንዳረፉ እና ምንም ጉዳት እንዳላደረሱ ገልጿል። እስካሁን ለተተኮሱት ሮኬቶች ኃላፊነት…
ከሶሪያ በኩል እስራኤል ላይ ሮኬቶች ተወነጨፉ።

በእስራኤል እና ፍልስጤማውያን መካከል የጀመረው ግጭት እየተባባሰ መጥቷል።

ግጭቱ ወደለየለት ጦርነት እንዳይገባ በእጅጉ ተሰግቷል።

ዛሬ ምሽት የእስራኤል ጦር ከሶሪያ በኩል ሶስት ሮኬቶች እስራኤል ላይ እንደተወነጨፉ አሳውቋል።

አንደኛው እዛው ሶሪያ ውስጥ ነው ያረፈው።

ዛሬ የሶሪያ ጎረቤት በሆነችው ሊባኖስ ከእስራኤል ጋር በምትዋሰንበት ቦታ ፍልስጥማውያንን ለመደገፍ እና እስራኤል በፍልስጤማውያን ላይ የምታደርሰውን ጥቃት ለመቃወም ሰልፍ ተደርጎ ነበር።

የተቃውሞ ሰልፈኞቹ ከእስራኤል ጋር የሚያዋሰነውን ድንበር ለመሻገር ከሞከሩ በኋላ አንድ ሊባኖሳዊ በእስራኤል ወታደሮች በጥይት ተመቶ ሲገደል ሌላ አንድ ሰው ቆስሏል።

ከሶሪያ በኩል የተፈፀመው የሮኬት ጥቃት ይህ ክስተት ከተከሰተ በኃላ ሲሆን በሁለቱ ክስተቶች መካከል ቀጥተኛ ግንኙነት ይኑር ፤ አይኑር የሚታወቅ ነገር የለም።

ትላንት ከሊባኖስ በኩል በእስራኤል ላይ ሮኬት መወንጨፉ ይታወሳል።

በሌላ በኩል እስራኤል ጋዛ ሰርጥ ላይ በፈፀመችው ጥቃት ተጨማሪ 4 ፍልስጤማውያንን ገድላለች።

አጠቀላይ በፍልስጤም በኩል የሟቾች ቁጥር 126 ደርሷል፤ 31 ህፃናት እና 20 ሴቶች ይገኙበታል፤ ቁስለኞች ደግሞ ከ920 መብለጣቸውን በጋዛ ጤና ሚኒስቴር ሪፖርት ተደርጓል።

በሌላ መረጃ የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ከእስራኤል ጠ/ሚ ቤኒያሚን ኔታንያሁ ጋር በስልክ የተነጋገሩ ሲሆን ማክሮን በቀጠናው ሰላም ይወርድ ዘንድ ጥሪ አቅርበዋል።

"ሀማስ" የሚፈፅመውን የሮኬት ጥቃት አውግዘው ፤ እስራኤል እራሷን የመከላከል መብት አላት ብለዋል።

@tikvahethiopia
የሙያ ብቃት ምዘና የተፈተኑ የጤና ሳይንስ ምሩቃኖች ጉዳይ ፦

በ2013 ዓ.ም. ከተለያዩ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በጤና ሳይንስ ተመርቀው የሙያ ብቃት ምዘና የወሰዱ ምሩቃኖች የትምህርት ማስረጃቸው ትክክለኛነት እንዲረጋገጥ ዝርዝራቸው ከጤና ሚኒስቴር ወደ ከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ ተልኳል፡፡

ይህ የተደረገበት ምክንያት የትምህርት ማስረጃቸው ህጋዊነትና ትክክለኛነት በኤጀንሲው ሳይረጋገጡ የሙያ ብቃት ምዘና የወሰዱ ምሩቃኖች በመኖራቸው የማጣራትና የማረጋገጥ ስራን ለማከናወን መሆኑ ተገልጿል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ የብቃት ምዘና የወሰዱ በርካታ የጤና ባለሙያዎች በኦንላይን(በኢንተርኔት) ውጤታቸውን ለማየት ጥረት እያደረጉ ሲሆን የሙያ ብቃት ምዘና ውጤታቸውን ሊያዩ የሚችሉት የትምህርት ማስረጃቸው ትክክለኛነት ከተረጋገጠ በኋላ መሆኑን ተገልጿል።

* ተጨማሪ ከላይ የተያያዘው ደብዳቤ ያንብቡ !

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
TIKVAH-ETHIOPIA
የሙያ ብቃት ምዘና የተፈተኑ የጤና ሳይንስ ምሩቃኖች ጉዳይ ፦ በ2013 ዓ.ም. ከተለያዩ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በጤና ሳይንስ ተመርቀው የሙያ ብቃት ምዘና የወሰዱ ምሩቃኖች የትምህርት ማስረጃቸው ትክክለኛነት እንዲረጋገጥ ዝርዝራቸው ከጤና ሚኒስቴር ወደ ከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ ተልኳል፡፡ ይህ የተደረገበት ምክንያት የትምህርት ማስረጃቸው ህጋዊነትና ትክክለኛነት በኤጀንሲው…
* HERQA

የሙያ ብቃት ምዘና ወስደው ውጤታቸውን እየጠበቁ ያሉ ምሩቃኖች የትምህርት ማስረጃቸው እንዲረጋገጥላቸው የሚከተሉትን ቅድመ-ሁኔታዎች አሟልተው በአካል መገኘት ይኖርባቸዋል፦

1. ከመሰናዶ ትምህርት ተሸጋግረው የዲግሪ ትምህርታቸውን የተማሩ ከሆነ የመሰናዶ ትምህርት ያጠናቀቁበትን የት/ት ማስረጃ ከጀርባው ፊርማና ማህተም ያረፈበት ማረጋገጫ ማቅረብ፤ (የማረጋግጠው ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ነው፤ አዲስ አበባ 4 ኪሎ)

2. ከቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተሸጋግረው የዲግሪ ትምህርታቸውን የተከታተሉ ከሆነ ከት/ት ማስረጃው በስተጀርባ ላይ ፊርማና ማህተም ያረፈበት ማረጋገጫ ማቅረብ፤ በክልል የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ ከጀርባው ማህተም በማስደረግ ማረጋገጫ ማቅረብ፤

3. የዲግሪ ጤና ስልጠናውን ለመከታተል ሲመዘገቡ ሌላ ዲግሪ በማቅረብ ከሆነ ዲግሪውን ተምረው ያገኙበት ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ከጀርባው ማረጋገጫ ማህተም እና ፊርማ ያረፈበት ማስረጃ ማቅረብ፤

4. አሁን ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ያገኙትን የዲግሪ ትምህርት ማስረጃ ከበስተጀርባው ማህተም እና ፊርማ ያረፈበት ማረጋገጫ ማቅረብ፤ (አሁን የተመረቁበት ተቋም)፡፡

በቀጣይ 2 ሳምንታት ውስጥ ባሉት የስራ ቀናት ከላይ የተገለጹትን ቅድመ-ሁኔታዎች በማሟላት አዲስ አበባ ሽሮ ሜዳ አሜሪካን ኢምባሲ ፊት ለፊት በሚገኘው የከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 115 ቁጥር በአካል ማስረጃቸውን ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል ተብሏል።

ኤጀንሲው አረጋግጦ ከሚያስተላልፈው የስም ዝርዝር ውጪ ለሙያ ብቃት ምዘና መመልመል እና የሙያ ፈቃድ መስጠት አይቻልም።

@tikvahethiopia
' የካራማራው ጀግና '

የብርጋዴር ጄኔራል ኃይሌ መለሰ አስከሬን ከባሕር ዳር ጋምቢ ሆስፒታል ወደ ፈለገ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል አሸኛኘት እየተደረገለት ነው።

የካራማራው ጀግና ብርጋዴር ጄኔራል ኃይሌ መለሰ ቀብር ሥነ ሥርዓት ነገ ግንቦት 08/2013ዓ.ም በደብረታቦር መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ይፈፀማል።

አስከሬናቸው በባሕርዳር ፈለገ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ፍትሃት ተደርጎለት ዛሬ ወደ ደብረታቦር ይሸኛል።

ነገ በደብረታቦር አጅባር ሜዳ የጀግና አሸኛኘት ከተደረገላቸው በኋላ ነው ሥርዓተ ቀብራቸው የሚፈፀመው። (አሚኮ)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
TIKVAH-ETHIOPIA
' የካራማራው ጀግና ' የብርጋዴር ጄኔራል ኃይሌ መለሰ አስከሬን ከባሕር ዳር ጋምቢ ሆስፒታል ወደ ፈለገ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል አሸኛኘት እየተደረገለት ነው። የካራማራው ጀግና ብርጋዴር ጄኔራል ኃይሌ መለሰ ቀብር ሥነ ሥርዓት ነገ ግንቦት 08/2013ዓ.ም በደብረታቦር መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ይፈፀማል። አስከሬናቸው በባሕርዳር ፈለገ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ፍትሃት…
ብ/ጄኔራል ኃይሌ መለሰ ተሰማ ፦

- በድሮው አስተዳደራዊ አወቃቀር በደብረ ታቦር አውራጃ በፋርጣ ወረዳ ጥር 28 /1933 ዓ/ም ነበር የተወለዱት።

- እስከ ጄነራልነይ ማዕረግ ያደረሳቸውን ህይወታቸውን በውትድርና የጀመሩት በ1960 ዓ/ም ነበር።

- በሶማሊያ ወረራ ወቅት የ69ኛውን ሚሊሻ ብርጌድ በማሰልጠን በግንባርም አዋጊ ሆነው በመምራት ታላላቅ ጀብዶችን ለሀገራቸው የፈፀሙ ነበሩ።

- መስከረም 1970 ዓ/ም ላይ በድሬዳዋ ግንባር ወደውጊያ የገቡ ሲሆን ካራማራ፣ ጅግጅጋ፣ ደጋሀቡር እና ቀብሪደሃር (መጋቢት 1/1970) ከሶማሊያ ጦር ወረራ ነፃ አውጥተው በመቆጣጠር የምስራቁን ግንባር ጦርነት በድል እንዲጠናቀቅ ያደረገውን ብርጌድ መርተዋል።

- ከወታደራዊ ስራቸው ተጨማሪ የተለያዩ የኢትዮጵያ ክ/ሀገሮችን አስተዳድረዋል።

- የፌዴራል መንግስት ተቋማትን መርተዋል።

- ለሀገራዊ አገልግሎታቸው የህበረተሰባዊ ኢትዮጵያ ታላቅ የክብር ኮከብ ኒሻን እና የየካቲት 66 አብዮት ኒሻን እና ሌሎች ሽልማቶችን አግኝተዋል።

- ባለትዳር እና የ7 ልጆች አባት ነበሩ።

#አሚኮ

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT