TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
' 1 ሺህ 442ኛው የዒድ-አልፈጥር በዓል '

1 ሺህ 442ኛው የዒድ ዓል ፈጥር በዓል በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በመከበር ላይ ይገኛል።

በአዲስ አበባ ስታዲየም በርካታ የእምነቱ ተከታዮች በተገኙበት ተከብሯል።

በዓሉ ላይ የኢትዮጵያ እሥልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ፕሬዝዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር ዒድሪስን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የእምነቱ ምሁራን ተገኝተው እንደነበር etv ዘግቧል።

ከላይ የተያያዙት ፎቶዎች በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች (ሀዋሳ፣ አሶሳ፣ ባህር ዳር፣ አ/አ፣ ጅግጅጋ፣ ድሬዳዋ ...) የበዓሉን አከባበር የሚያሳዩ ናቸው።

ተጨማሪ የፎቶ ክምችት በ @tikvahethmagazine ታገኛላችሁ።

በድጋሚ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለኢድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ፥ መልካም በዓል ለማለት እንወዳለን።

ፎቶ ፦ ሶሻል ሚዲያ
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ! በአ/አበባ ስታድዮም የሚደረገው የ1442ኛው የኢድ-አልፈጥር በዓል የኢድ ሶላት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ለጊዜው ለተሸከርካሪ ዝግ የሆኑ መንገዶች ፦ - ከ22 ወደ መስቀል አደባባይ - ከወሎ ሰፈር ወደ መስቀል አደባባይ - ከአጎና ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ - ከመስቀል ፍላወር አካባቢ ወደ መስቀል አደባባይ - ከኮካ ኮላ በከፍተኛው ፍ/ቤት ወደ መስቀል አደባባይ - ከበርበሬ…
"የኢድ አልፈጥር የሶላት ስነስርዓት በሰላም ተጠናቋል" - የአዲስ አበባ ፖሊስ

በርካታ የእስልምና እምነት ተከታዮች በተገኙበት በአ/አ ስታዲዮም እና በዙሪያው በሚገኙ ጎዳናዎች እንዲሁም በከተማው ልዩ ልዩ ስፍራዎች የተካሄደው 1 ሺህ 442ኛው የኢድ አልፈጥር የኢድ ሶላት በሰላም መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

የኢድ አልፈጥር ሶላት በሰላም እንዲጠናቀቅ ኮሚሽኑ በርካታ የሰው ኃይሉን በወንጀል መከላከል ስራ ላይ አሰማርቶ ከሚመለከታቸው የፀጥታ አካላት እና ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት እና ከአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ጋር በጋራ መስራቱን ገልጿል፡፡

ለበዓሉ በሰላም መከበር የከተማው ነዋሪ በተለይም ሙስሊሙ ማህበረሰብ ከፀጥታ አካላት ጎን በመቆም ተገቢውን ትብብር ማድረጉን የገለፀው ፖሊስ ህብረተሰቡ ለፀጥታው ስራ ስኬታማነት የድርሻውን እየተወጣ ነው ብሏል።

የአ/አ ፖሊስ ህብረተሰቡ እያበረከተ ላለው ቀና ትብብር እንዲሁም ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ለተወጡ የፀጥታ አካላት ምስጋናውን አቅርቧል፡፡

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
አል-አቅሳ መስጊድ !

ሰሞኑ ግጭት በነበረበት በጥታዊቷ እየሩሳሌም በሚገኘው የአል- አቅሳ መስጊድ (በሙስሊሞች 3ኛው የተቀደሰ ስፍራ) በመቶዎች የሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን የዛሬውን የኢድ ሶላት ተካፍለዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
"...የግድቡን 2ኛውን ዙር የውሃ ሙሌት ለማደናቀፍ የሚጥሩ ኃይሎች እንደማይሳካላቸው አውቀው ተስፋቸውን ሊቆርጡ ይገባል" - የሰራዊቱ አባላት

የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት ለሀገሪቱ ሰላም እና ለህዳሴው ግድብ ዕውን መሆን የማንከፍለው መስዋዕትነት የለም ብለዋል።

ይህንን ያሉት በቀጣናው ላይ ተልዕኳቸውን በመወጣት ላይ የሚገኙ የሠራዊት አባላት ናቸው።

የሰራዊት አባላቱ የሀገሪቱ ሰላም ሆነ ልማት በውጪ ኃይሎች ፍላጎት እና በውስጥ ባንዳዎች ተላላኪነት አይደናቀፍም ብለዋል።

የህዳሴውን ግድብ ሁለተኛውን ዙር የውሃ ሙሌት ለማደናቀፍ የሚጥሩ ኃይሎች እንደማይሳካላቸው አውቀው ተስፋቸውን ሊቆርጡ ይገባልም ሲሉም ተናግረዋል።

መላው ኢትዮጵያውያን ተስፋ የጣሉበትን የህዳሴ ግድብ ከማናቸውም ጥቃት ለመከላከል ተልዕኮ ተቀብለው በቀጣናው መሰማራታቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀው ለስኬታማነቱም ዝግጁነታችን ከመቼውም ጊዜ በላይ የላቀ መሆኑን ገልፀዋል።

#FDREDefenseForce

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
"... ከፍርድ ውጭ የሚካሄዱ ግድያዎች ህዝቦች በሕግ የበላይነት ላይ ዕምነት እንዲያጡ እና በዚህ ረገድ የተገኙ ስኬቶች እንዲቀለበሱ ያደርጋሉ" - ኢሰመኮ በኦሮሚያ ክልል ፥ ቄለም ወለጋ ዞን ፥ደምቢ ዶሎ በወንጀል ተጠርጥሯል የተባለው አማኑኤል ወንድሙ ከፍርድ ውጭ የተፈፀመበት ግድያ እና (extrajudicial killing) በአደባባይ ለህዝብ እንዲታይ የተደረገበት መንገድ እንዳሳሰበው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ…
"...በእውነት ልጄ ለምን እንደተገደለ አላውቅም" - የወጣት አማኑኤል ወላጅ አባት ወንድሙ ከበደ

በደምቢ ዶሎ ከተማ የተገደለው ወጣት አማኑኤል ወንድሙ ወላጅ አባት አቶ ወንድሙ ከበደ ስለልጃቸው ግድያ ለቪኦኤ ቃላቸውን የሰጡ ሲሆን ፥ የአካባቢው የመንግስት ኃላፊዎች ስላልጃቸው ግድያ የሚሰጡትን ሃሳብ እንደማይቀበሉት ገልፀዋል።

አቶ ወንድሙ ከበደ ፥ የመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ልጃቸውን ከገደሉ በኃላ ቤታቸውን ፈትሸው ፤ የልጃቸውን አስክሬን ከአደባባይ ወስደው እንዲቀብሩ እንዳደረጓቸው ተናግረዋል።

አክለውም፥ አስክሬኑን ከባለቤታቸው ጋር ሊያነሱ ሲሉ ፖሊስ ልጃቸው "አባቶርቤ" ነው በሚል ድብደባ እንደፈፀመባቸው ገልፀዋል።

አቶ ወንድሙ ከበደ ፦

"...የምርጫ ካርድ ወስደለሁ ብሎ ነው ጥዋት ከቤት የወጣው። ተኩስ ሲሰማ ነበር፤ ትንሽ ቆይቶ የፀጥታ አካላት መጡና ቤታችንን ፈትሸው እኔ እና ባለቤቴን ይዘው ወደ አደባባዩ ሄዱ ፤ ልጄ ከሞተ በኃላ ነው የደረስኩት። እኔም እናቱም በአደባባይ ላይ ተደብድበናል። ልጄ የ10ኛ ክፍል ተማሪ ሲሆን ቀና ብሎ ሰውንም አያይም ፤ ከሰፈርም አይወጣም። በእውነት ልጄ ለምን እንደተገደለ አላውቅም" ብለዋል።

በተጨማሪ ልጃቸው በወንጀል እንኳን ተጠርጥሮ ከሆነ ከሚገደል በህግ ሊዳኝ ይገባ እንደነበር ተናግረዋል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/Dembi-Dolo-05-13

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
"... ከቦርዱ ውጪ የሚገለጹ ማንኛውም አይነት የመራጮች ምዝገባ ቁጥሮች ተቀባይነት የሌላቸውም" - ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

ምርጫ ቦርድ ዛሬ ባወጣው መግለጫ የ6ተኛው የመራጮች ምዝገባ በ11 ክልሎችና የከተማ መስተዳድሮች እየተከናወነ እንደሆነ አስታውሷል።

በተለያዩ ጊዜያት የተመዘገቡ ጊዜያዊ መራጮችን ቁጥር እያሳወቀ እንደሚገኝም ገልጿል።

ምርጫ ቦርድ የምዝገባውን መረጃ በሚያጠናቅርበት ወቅት የምርጫ ክልል ማስተባበሪያ መዋቅሮቹን በመጠቀም እንደሆነ ከምርጫ ጣቢያ የሚገኙ መረጃዎችን በማጠናቀር ወደማእከል የኦፕሬሽን ዴስክ የሚላከውም በምርጫ ክልል ማስተባበሪያ ቢሮዎች አማካኝነት መሆኑን አስረድቷል።

ከቦርዱ ውጪ የሚገለጹ ማንኛውም የመራጮች ምዝገባ ቁጥሮች ተቀባይነት የላቸውም ብሏል። የመራጮች መረጃን የሚያስተላልፉ አካላት ከቦርዱ የሚያገኙትን ቁጥር ብቻ እንዲጠቀሙ መልዕክት አስተላልፏል።

@tikvahethiopia
አጭር መረጃ ስለመርካቶ የከተማ አውቶብስ ተርሚናል ፦

- ግንባታው የተካሄደው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ነው።

- ለተርሚናሉ ግንባታ 200 ሚሊዮን ብር ወጪ ተደርጎበታል፡፡

- በ4 ሺህ 125 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈ ነው።

- ለ20 አውቶቡሶች በባለሁለት ወለሎች አገልግሎት የሚሰጥ ይሆናል። ሁለቱ ወለሎች የራሳቸው መግቢያ እና መውጫ አላቸው።

- በአንድ ሰዓት ውስጥ 6 ሺህ ለሚጠጉ የብዙሃን ትራንስፖርት ተጠቃሚዎች አገልግሎት መስጠት ያስችላል፡፡

- ተርሚናሉ የአውቶቡስ መጠበቂያ ቦታ ፣ የትኬት ሽያጭ ፤ የተሳፋሪ መጫኛ እና የማራገፊያ ቦታ ፤ ዘመናዊ ስምሪት አገልግሎት፣ የአውቶቡስ መርሃ-ግብር እና የአስተዳደር ቢሮዎችን አካቷል፡፡

- ቅዳሜ ግንቦት 7/2013 ዓ.ም ይመረቃል።

መረጃው የትራንስፖርት ቢሮ ነው።

@tikvahethiopiaBOT
ኢምፔርያል ሆቴል አካባቢ እየተገነባ ያለው የመሻገሪያ ድልድይ ፕሮጀክት ፦

- ፕሮጀክቱ የጀመረው የካቲት ወር 2013 ዓ/ም የተጀመረ ነው።

- ግንባታው በቻይና ዓለም አቀፍ ኩባንያ (CFTC) ነው የሚካሄደው።

- በ791 ሚሊዮን ብር በጀት ነው እየተገነባ ያለው።

- 1.8 ኪሎ ሜትር ርዝመት አለው።

- ይህ ፕሮጀክት በከተማው ውስጥ ከሚገነቡት 7 የማሳለጫ ፣ ዋሻ እና የመሬት ስር መተላለፊያዎች መካከል አንዱ ነው።

- ፕሮጀክቱን ለማጠናቀቅ የተያዘው ጊዜ 1 ዓመት ከ8 ወር ሲሆን ቀደም ብሎ ለማጠናቀቅ እና መንገዱን ለተሽከርካሪ ክፍት ለማድረግ በቀን እና በማታ (ከመደበኛ ስራ ሰዓት ውጪ) ፣ በዝናብ ወቅትም እየተሰራ ነው።

- ተሻጋሪ ድልድዩ 14 ሜትር ስፋት አለው ፤ በአንድ ጊዜ በአንድ በኩል ሁለት መኪኖችን በአጠቃላይ 4 መኪኖችን ማስተላለፍ ይችላል።

- የመገናኛውን አቅም ለማሳደግ የግራ ታጣፊዎችን በመከልከል በመገናኛ እና በቦሌ አቅጣጫ በኩል ሉፖች ይኖሩታል። በአንድ ጊዜ ሁለት መኪና ብቻ በሁለት አቅጣጫ መልቀቅ እንዲቻል በማድረግ በሚገነባው ሉፕ በኩል የግራ ታጣፊዎች መስተናገድ እንዲችሉ አካባቢው ላይ ያለውን የትራፊክ መጨናነቅ የሚቀንስ ነው ተብሏል።

- በኢምፔሪያል አካባቢ በቀን ውስጥ እስከ 70 ሺህ ተሽከርካሪዎች ይስተናገዳሉ።

[ Addis Television , ኢ/ር ሞገስ ጥበቡ (የአ/አ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር) ]

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia