ዝግ የሚሆኑ መንገዶች !
በአ/አበባ ስታድዮም የሚደረገው የ1442ኛው የኢድ-አልፈጥር በዓል የኢድ ሶላት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ለጊዜው ለተሸከርካሪ ዝግ የሆኑ መንገዶች ፦
- ከ22 ወደ መስቀል አደባባይ
- ከወሎ ሰፈር ወደ መስቀል አደባባይ
- ከአጎና ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ
- ከመስቀል ፍላወር አካባቢ ወደ መስቀል አደባባይ
- ከኮካ ኮላ በከፍተኛው ፍ/ቤት ወደ መስቀል አደባባይ
- ከበርበሬ በረንዳ በቀድሞ 5ኛ ፖሊስ ጣቢያ ወደ መስቀል አደባባይ
- ከቀድሞ ፈረሰኛ ፖሊስ በጌጃ ሰፈር ወደ 5ኛ ፖሊስ ጣቢያ
- ከተ/ኃይማኖት በጥቁር አንበሳ ወደ ጎማ ቁጠባ
- ከአትላስ ወደ ኡራኤል ቤተክርስቲያን የሚወስዱ መንገዶች ከማለዳው 11፡30 ሰዓት ጀምሮ ለትራፊክ ዝግ ናቸው።
አሽከርካሪዎች ይህን አውቀው አማራጭ መንገዶችን በመጠቀም ተባባሪ እንዲሆኑና በተገለፁት መንገዶች ለአጭርም ሆነ ለረጅም ሰዓት ተሸከርካሪ አቁሞ መሄድ የተከለከለ መሆኑን የአ/አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
መልዕክት ፦
- ህዝበ ሙስሊሙ ወደ ኢድ ሶላት ሲጓዝ ከዕምነቱ አስተምሮት ውጭ የሆኑ መልዕክቶች ፣ ከበዓሉ ዓላማ ጋር ተቃራኒ የሆኑ ነገሮችን ይዞ መምጣት የተከለከለ ነው።
- ምዕመኑ ለፀጥታ አካላቱ የፍተሻ ተግባር ተባባሪ እንዲሆን ጥሪ ቀርቧል።
አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥም እና ለማንኛውም ፖሊሳዊ አገልግሎት በአ/አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የመረጃ ስልክ ቁጥሮች 011-1-11-01-11 እና በ991 ነፃ የስልክ መስመር መጠቀም ይቻላል።
@tikvahethiopia

በእስራኤል እየሆነ ስላለው ጉዳይ ምን ማወቅ አለብኝ ?
- ከሰሞኑን በእየሩሳሌም የተቀሰቀሰው ግጭት ምክንያት በSheikh Jarrah ፍልስጤማውያን ቤተሰቦችን ለአይሁድ ሰፋሪዎች ሊያስለቅቁ ነው የሚል ስጋት መደቀኑ ነው።
- አል-አቅሳ መስጊድ ውስጥ የእስራኤል የፀጥታ ኃይሎች በፀሎት ላይ ከሚገኙ ፍልስጤማውያን ጋር ተጋጭተው በርካቶች ተጎድተዋል።
- ከአርብ ጀምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ ፍልስጥኤማውያን ቆስለዋል ፤ የእስራኤል የፀጥታ ኃይሎችም ቆስለዋል።
- ከሰኞ ጀምሮ 53 ፍልስጥኤማውያንና 6 እስራኤላውያን ተገድለዋል። 13 ፍልስጥኤማውያን ህፃናት ይገኙበታል።
- ሀማስ ከ1500 በላይ ሮኬቶች ወደእስራኤል ከተሞች አስወንጭፏል፤ እስራኤል አብዛኛውን ብትከላከልም፤ አንዳንዱ ውድመት አድርሷል፤ የሰው ህይወት አጥፍቷል።
- ሀማስ የፈፀመው ጥቃት ከእስራኤላውያን በተጨማሪ አንድ የህንድ ዜጋ ገድሏል።
- የእስራኤል በመቶዎች ይቆጠራሉ የተባሉ የአየር ጥቃቶች በመፈፀም ጋዛ የሚገኙ የመኖሪያ ህንፃዎችን አውድማለች፤ የሰው ህይወት አጥፍታለች።
- የተለያዩ አለም ሀገራት እስራኤልን በፍልስጤማውን ተቃዋሚዎች ላይ እንዲሁም በአልአቅሳ መስጊድ የወሰደችውን እርምጃ ኮንነዋል።
- የተለያዩ ሀገራት መሪዎች ውጥረቱ እንዲረግብ እየተማፀኑ ነው።
- ተመድ በእስራኤል እና በፍልስጤም ታጣቂዎች መካከል በጋዛ ሰርጥ የተነሳው ግጭት ወደ ለየለት ጦርነት እንዳያመራ ሰግቷል።
በዝርዝር ያንብቡ : telegra.ph/East-Jerusalem-05-12
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Tigray
አስቸኳይ የእርዳታ ምግብ የጫኑ 500 ተሽከርካሪዎች ትግራይ መድረሳቸውን የዓለም ምግብ ፕሮግራም አስታወቀ፡፡ የእርዳታ ምግቡን የጫኑ ተሽከርካሪዎቹ ከሱዳን ነው ወደ ትግራይ የገቡት፡፡
በክልሉ በተደረገው ውጊያ ለተጎዱ 2.1 ሚሊዬን ዜጎች የምግብ እርዳታዎችን ለማድረግ በማሰብ እየሰራ መሆኑን ያስታወቀው የዓለም ምግብ ፕሮግራም ፣ ሌሎች ተጨማሪ 500 የእርዳታ ምግቦችን የጫኑ ተሽከርካሪዎች ወደ ክልሉ ለመግባት በጉዞ ላይ ይገኛሉ ብሏል፡፡
ድንበር ዘለሉን ሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረግ ላሳየው ትብብር የሱዳን መንግስትን ያመሰገነው የፕሮግራሙ የሱዳን ማስተባበሪያ እስካሁን ከ20 ሺ ሜትሪክ ቶን በላይ ምግብ ለማቅረብ መቻሉንና ተጨማሪ 25 ሺ ሜትሪክ ቶን የእርዳታ ምግብ በመጓጓዝ ላይ መሆኑን አስታውቋል፡፡
የምግብ እርዳታው አስቸኳይ ድጋፍን ለሚፈልጉ ዜጎች የሚውል ነው፡፡
ምንጭ፦ አል ዓይን / WFP

TIKVAH-ETHIOPIA
"...ወጣቱ በአደባባይ ሲገደል በአይናችን አይተናል" - የደምቢ ዶሎ ነዋሪ በምዕራብ ኦሮሚያ ቄለም ወለጋ ዞን በደምቢ ዶሎ ከተማ አማኑኤል ወንድሙ የተባለ ወጣት በአደባባይ በመንግሥት ኃይል መገደሉን ነዋሪዎች ተናግረዋል። የአካባቢ የመንግሥት ባለስልጣናት የወጣቱን መገደል አረጋግጠዋል። ወጣቱ ለሕዝብ እንዲታይ ተደረገ እንጂ በአደባባይ አልተገደለም ሲሉ አስተባብለዋል። የአካባቢው የመንግሥት ባለሥልጣናት…
"... ከፍርድ ውጭ የሚካሄዱ ግድያዎች ህዝቦች በሕግ የበላይነት ላይ ዕምነት እንዲያጡ እና በዚህ ረገድ የተገኙ ስኬቶች እንዲቀለበሱ ያደርጋሉ" - ኢሰመኮ
በኦሮሚያ ክልል ፥ ቄለም ወለጋ ዞን ፥ደምቢ ዶሎ በወንጀል ተጠርጥሯል የተባለው አማኑኤል ወንድሙ ከፍርድ ውጭ የተፈፀመበት ግድያ እና (extrajudicial killing) በአደባባይ ለህዝብ እንዲታይ የተደረገበት መንገድ እንዳሳሰበው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ገልጿል፡፡
ኮሚሽኑ ማንኛውንም ከፍርድ ውጭ የሚካሄዱ ግድያዎችን የሚያወግዝ መሆኑን አስታውቆ ሁሉም የሕግ አስፈፃሚ አካላት ሕጋዊ መንገዶች ብቻ አንዲተገብሩ መልዕክቱን አስተላለፏል፡፡
ኢሰመኮ "ከፍርድ ውጭ የሚካሄዱ ግድያዎች ህዝቦች በሕግ የበላይነት ላይ ዕምነት እንዲያጡ እና በዚህ ረገድ የተገኙ ስኬቶች እንዲቀለበሱ ያደርጋሉ" ብሏል።
ባለሥልጣናት ጉዳዩን በአፋጣኝ እንዲመረምሩ እና ተገቢ እርምጃዎችን እንዲወስዱ ጠይቋል።
ኢሰመኮ ፥ ሁኔታውን በቅርብ እየተከታተለ መሆኑ ገልፆ ስለውጤቱ ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡
ምንጭ፦ ኢሰመኮ/ቢቢሲ

በእስራኤል እየሆነ ስላለው ጉዳይ ምን ማወቅ አለብኝ ? - ከሰሞኑን በእየሩሳሌም የተቀሰቀሰው ግጭት ምክንያት በSheikh Jarrah ፍልስጤማውያን ቤተሰቦችን ለአይሁድ ሰፋሪዎች ሊያስለቅቁ ነው የሚል ስጋት መደቀኑ ነው። - አል-አቅሳ መስጊድ ውስጥ የእስራኤል የፀጥታ ኃይሎች በፀሎት ላይ ከሚገኙ ፍልስጤማውያን ጋር ተጋጭተው በርካቶች ተጎድተዋል። - ከአርብ ጀምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ ፍልስጥኤማውያን ቆስለዋል…
#Update
ዛሬ የፀጥታው ም/ቤት አስቸኳይ ስብሰባ ያደርጋል።
የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታ ምክር ቤት በእየሩሳሌም እና በጋዛ ሰርጥ ባለው ግጭት ዙሪያ ለመነጋገር በዝግ አስቸኳይ ስብሰባ እንደሚያደርግ ተሰምቷል።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT

የኮቪድ-19 ሪፖርት ፦
ባለፉት 24 ሰዓት 27 ሰዎች በኮቪድ-19 ህይወታቸው አልፏል።
በተመሳሳይ ከተደረገው 5,722 የላብራቶሪ ምርመራ 695 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
ትላንት 2,241 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
በአጠቃላይ 264,367 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 3,938 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 214,808 ሰዎች አገግመዋል።
አሁን ላይ 659 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።
በሀገራችን እየተሰጠ ያለውን የኮቪድ-19 ክትባት የተከተቡ ዜጎች ቁጥር 1,397,647 ደርሷል።
#Purpose

Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#CNN : በትግራይ በመንቀሳቀስ የሰራው ዘገባ ፦
- ኢትዮጵያ እና ኤርትራ መንግስታት የኤርትራ ወታደሮች የኢትዮጵያን ምድር ለቀው ይወጣሉ ካሉ ሳምንታት ቢያልፉም የኤርትራ ወታደሮች ግን በትግራይ አሉ።
- የኤርትራ ወታደሮች ሰብዓዊ ዕርዳታ እንዳይደርስ ያደናቅፋሉ።
- የCNN ጋዜጠኞች የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ ኬላዎችን ሲቆጣጠሩ፣ ወሳኝ የሆኑ የእርዳታ መስመሮችን በመያዝ እርዳታ ሲያደናቅፉ ፣ በክልሉ ካሉት ጥቂት ሆስፒታሎች በአንዱ ውስጥ ተዘዋውረው የህክምና ሰራተኞችን እንደሚያስፈራሩ ሪፖርት አድርገዋል።
- የኤርትራ ወታደሮች በማዕከላዊ ዞን ለ2 ሳምንት፣ በሰሜን ምዕራብ ለ1 ወር የዕርዳታ ማመላለሻ መንገዶችን ዘግተው ነበር።
- CNN ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደሩ ጋር የሚሰሩ የደህንነት ኃላፊዎች ነገሩኝ እንዳለው የኢትዮጵያ መንግስት በኤርትራ ወታደሮች ላይ ቁጥጥር የለውም።
- በትግራይ ክልል ማዕከላዊ ዞን የተንቀሳቀሱ የCNN ጋዜጠኞች የኤርትራ ወታደሮች መመልከታቸውን ተናግረዋል፤ የተወሰኑት የድሮውን የኢትዮጵያ ዩኒፎርም የለበሱ ናቸው።
https://amp.cnn.com/cnn/2021/05/12/africa/tigray-axum-aid-blockade-cmd-intl/index.html?__twitter_impression=true

እንኳን አደረሰን፤ አደረሳችሁ !
ለመላው እስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1442ኛው ለኢድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሰን ፤ አደረሳችሁ። ዒድ ሙባረክ !
በዓሉ የሰላም ፣ የአንድነት ፣ የፍቅር እንዲሁም የመተሳሰብ ይሆንልን ዘንድ እንመኛለን።
በዓሉን ስታከብሩ የተቸገሩት ፣ ያጡትን ፣ በሰላም እጦት የሚሰቃዩትን ፣ በሰላም እጦት ወገን ዘመዶቻቸውን ከጎናቸው የተነጠቁትን ፣ ከሞቀው ቄያቸው ተፈናቅለው ሜዳ ላይ የቀሩትን ወገኖቻችን በማሰብ ይሆን ዘንድ አደራ እንላለን።
ውድ ቤተሰቦቻችን በበዓሉ ወቅት አስፈላጊው የኮቪድ-19 ጥንቃቄ ማድረግ እንዳትዘነጉ።
ሀገራችንን ፈጣሪ ይጠብቅልን!!
የሰውን ልጆች ሁሉ በሰላም ያኑርልን!!
መልካም በዓል !
#TikvahFamily ❤️

' 1 ሺህ 442ኛው የዒድ-አልፈጥር በዓል '
1 ሺህ 442ኛው የዒድ ዓል ፈጥር በዓል በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በመከበር ላይ ይገኛል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም በርካታ የእምነቱ ተከታዮች በተገኙበት ተከብሯል።
በዓሉ ላይ የኢትዮጵያ እሥልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ፕሬዝዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር ዒድሪስን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የእምነቱ ምሁራን ተገኝተው እንደነበር etv ዘግቧል።
ከላይ የተያያዙት ፎቶዎች በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች (ሀዋሳ፣ አሶሳ፣ ባህር ዳር፣ አ/አ፣ ጅግጅጋ፣ ድሬዳዋ ...) የበዓሉን አከባበር የሚያሳዩ ናቸው።
ተጨማሪ የፎቶ ክምችት በ @tikvahethmagazine ታገኛላችሁ።
በድጋሚ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለኢድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ፥ መልካም በዓል ለማለት እንወዳለን።
ፎቶ ፦ ሶሻል ሚዲያ