TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጊዜው የለውጥ ነው! እንደ ኢትዮጵያ የምናስብበት ወቅት ነው። እኔ በበኩሌ ወደ ክልል የማወርደው ጉዳይ የለኝም። ስንት አመት ወደኋላ እንጓዛለን?? መሬት የፈጣሪ ነው። እኔ ባለ ክልል አይደለሁም የኢትዮጵያ ምድር ሁሉ የኔ ነው።

ኦሮሚያ የኔ ናት! ሲዳማ የኔ ናት! ሀረሪ የኔ ናት! ትግራይ የኔ ናት! አማራ የኔ ናት! ወላይታ የኔ ናት!

የኢትዮጵያ ምድር ሁሉ የኔ ነው!
.
.
.
ምክንያቱም እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ!

አንተስ? አንቺስ? እናተስ?

#ኢትዮጵያዊነት_ይፋፋም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ተፈቅዷል! የቅዳሜው የአዲስ አበባ የድጋፍ ሰልፍ ፍቃድ አግኝቷል።

ድብዳቤውን ከላይ አንብቡት⬆️

ምንጭ፦ መምህር ስዩም ተሾመ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አፋልጉን⬆️⬆️ወጣት ሮዛ አደም ሙሀመድ በ02-08-2010 ከኳስሜዳ (አዲሱ ሚካኤል) አካባቢ ዘመድ ለመጠየቅ ብላ እደወጣች አልተመለሰችም ያያት ወይም የሚያቃት ካለ
0910510752
0911807611
0923669966
በዚህ ቁጥር ቢያሳዉቁን ወረታ ከፋዬች ነን ቤተሰቦቿ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ገብተዋል! የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዘዳንት ሳልቫ ኬር አዲስ አበባ ገብተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ቦሌ በመገኘት ለፕሬዘዳንቱ አቀባበል አድርገዋል።

ዶክተር አብይ የደቡብ ሱዳን ችግር እንዲፈታ እየሰሩ እንደሆነ ይታወቃል ለዚህም ሁለቱን ተቀናቃኞች ለማደራደር አ.አ ጋብዘዋቸዋል ።

@tsegabwolde
ለፈገግታ! ሰው ግን ለሐገር የተነገረ ነገርን ለግል ጥቅሙ ማዋል ጀምሯል ልበል? አሁን እኮ ነው አንዱ ታክሲ ውስጥ አጠገቡ ወደተቀመጠች ቆንጆ ሴት ዞሮ ምን ቢላት ጥሩ ነው?
.
.
.
«የኔ ቆንጆ ... እንደመር?»

ምንጭ፦ አረ እኔ አላውቅም
~ከፌስቡክ መንደር የተወሰደ~
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አግ7! በዶክተር ብርሀኑ ነጋ የሚመራው የአርበኞች ግንቦት 7 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ያ ቀረቡትን የሰላም ጥሪ መቀበሉን ገልጿል። በዚህ ጉዳይን መግለጫ አውጥቷል ከደቂቃዎች በኋላ አቀርበዋለሁ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
መግለጫ⬆️አርበኞች ግንቦት 7 የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጥሪ መቀበሉን ተከትሎ ባለሁለት ገጽ መግለጫ አውጥቷል።

ግንባሩ በመግጫው አሁን እየታየ ያለውን የዶክተር ዐቢይና ቡድናቸው ለውጥን ከማድነቅ ባለፈ ድጋፍ ጭምር ማድረግ እንደሚፈልግ አመልክቷል:: ራስን ለመከላከል መሳሪያ ማንሳቱ ከዚህ ቀደም የነበረው የገዢው ፓርቲ ባህሪ አስገድዶት መሆኑን አስረድቷል::

ምንጭ፦ አቶ ካሳሁን ይልማ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የማብራት ነገር! ሀዋሳ፣ዲላን ጨምሮ እንዲሁም ይርጋለም ከሰሞኑ የማብራት መቆራረጥ ምክንያቱ ሳይታወቅ ሳምንት ሊሞላ ነው። ማንም በጉዳዩ ላይ መግለጫ ሲሰጥ አልተሰማም።

በተያያዘ...
የኔትዎርክ መቆራረጥ በከፍተኛ ደረጃ እየታየ ነው። በዚህም ጉዳይ ምንም አልተሰማም።

የሚመለከታቸው አካላት ችግሩ በፍጥናት ይቀርፋሉ ተብሎ ይታመናል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቂም በቀል ክፉ ነው
ካምላክ ያለያያል
ተዋዶ መትጋት ግን ቅጣት ያስተሰርያል
ኦ..... ያስተሰርያል
.
.
ቅርብ ነው አይርቅም የኢትዮጵያ ትንሳኤ
ባንድነት ከገባን የፍቅር ሱባኤ!

#TEDDY_AFRO
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከዐብይ ጎን እቆማለሁ!

ጀርመናዊው ጳውሎስ ፖልማን በብሩህ ተሰፋ ስለተሞሉ መሪዎች ሲናገር ''የፖለቲካ መሪዎቻችን ከፍ ያሉ ኃላፊነቶች አሉባቸው፡፡ ነገር ግን እንደማንኛውም የሕይወት ውጣ ውረድ ፍላጎቶቻችንን ለሟሟላት ሊሳካላቸውም ላይሳካላቸውም ይችላል፡፡ እንደ ዜጋ የአኛ ድርሻ መሪዎቻችንን እንዲሳካላቸው በቂ ድጋፍ መስጠት ነው'' ይላል፡፡

ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይን የምደግፈው ለዚሁ ነው፡፡ አሳሪውን ስወቅስ ከነበረ ፈቺውን፣ እንዴት አላመሠግንም? በአሳዳጁ ሳዝን በመላሹ ለምን አልደሰትም? በታኙን ከተቃወምኩ አሰባሳቢውን እንዴት አልደግፍም? ከከፋፋዩን ስጸየፍ ከአስታራቂውስ ጎን እንዴት አልቆምም?

ወገን! በጎ ጅምርን ማሳደግ የሚቻለው በተዓምር አይደለም፡፡ በሚቻለው ሁሉ በመደገፍ እንጂ! እንድትኖረን የምንመኛት ኢትዮጵያን የምንሠራት አብረን በጋራ ነው፡፡ ስለዚህም ለራሴ፣ ለወገኔ እና ለኢትዮጵያዬ ስል በምችለው ሁሉ ከዓብይ ጎን እቆማለሁ!

ሀሳቤን የምትጋሩ ከሆነ መልእክቱንም አጋሩ!

©Yoni
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቤተ መንግስት! በአሁን ሰዓት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የደቡብ ሱዳን ተቀናቃኞችን እያደራደሩ ይገኛሉ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከጅማ የአይን እማኝ...

"ፀግሽ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ሰራተኛ ነኝ እና ዛሬ በፀጥታ ሀይሎች ተመትተው የመጡ ሰዎችን ብዛት ልነግርህ አልችልም። አብዛኛው በጥይት ነው የተመቱት። እኔ OPD ነበርኩ እና አልቻልነውም ብዛቱን እኛ እራሱ ብዙ ሆነን። መንገድ ሁላ አምቡላንስ እንዲመላለስ ተብሎ ለሌላው ዝግ ነበር። ቢያንስ ከ20 በላይ ሰዎች ተጎድተዋል። ደግሞ የግቢ ሰራተኛ ሰርቪስ መኪና የሚነዱ ሹፌር ሁላ ተመተዋል ።

ምክንያቱን ብዙ ነገር ሰምቻለሁ...

1.መኪና ሰው ገጭቶ ከዛ በዛ ምክንያት ግርግር ተፈጥሮ መኪና አናሳልፍም ብሎ የሰፈሩ ሰው ከልክሎ ነበር የሚል
2.ከሰሞኑን ከእስር የተፈቱ ሰዎችን ለመቀበል ብሎ ከአጋሮ የመጡ ሰዎች ነበሩ ሰልፍ ነገር ይመሥል ነበር የነበሩት የመከላከያ ካምፕ ነበር በዚህ መሀል ግጭት ተፈጥሮ ነው የሚልም ሰምቻለሁ።

ሳይለዩ ሁሉንም ነው የመቱት አመታታቸው ግን ያስጠላል። በጥይትም በዱላም በእጅም እራሱ የተመቱ አሉ። ከጭንቅላት እስከ እግር ጥፍር ድረስ ያልተመታ የለም። የዱላው ይበዛል። ስሜ እንዳይጠቀስ ከጅማ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዲስ አበባ⬆️ለቅዳሜው ታላቁ የአዲስ አበባ የድጋፍ ሰልፍ የዶክተር አብይ ምስል ያለበት ቲሸርት በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ እየተሸጠ ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቦንጋ! ለጠቅላይ ሚኒትር ዶክተር አብይ አህመድ የድጋፍ ሰልፍ ለማድረግ ፍቃድ እንዲሰጣቸው አስተባባሪ ኮሚቴው የቦንጋ ከተማ አስተዳደርን ጠይቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከነጌሌ ቦረና ለኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ሀይል የተላለፈ...

"እረረረረ ባከህ ፀግሽ መብራት አይኑን ካየን ይኸው ስድስተኛ (6) ቀናችን ነው በበዓል (ኢድ) ቀን ማጥፋታቸው ሳያንስ ይኸው እስካሁን በጨለማ ውስጥ ነው ያለነው እባክህ ለሚመለከተው አካል አቤት በልልን እባክህ እባክህ! አድራሻ በጉጂ ዞን ነጌሌ ቦረና"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለኩ! ከዛሬ ሁለት ቀን በፊት የለኩ ወዳጆቼን(ጉዳዩን በቅርበት ሲከታተሉ የነበሩ) የተዘረፉ ንብረቶች በአንዳንድ አመራሮች ቤት ተገኝተዋል የሚል ነገር ሰማሁ ምን ያህል እውነት ነው ብዬ ጠይቄያቸውን ይህ ነበር የመለሱልኝ...

"እንዴት ዋልክ ፀጊሽ እውነት ነው ዛሬ ጠዋት ጀምሮ ትናንትናም ልዩ አይል በደረገው ብርበራ ንብረቶች እየተገኙ ነው። ፀጊሽ እውነት ነው ከንቲባው መታሰሩንም ነግሬክ ነበር። ዛሬ ከነጋም ብኋላ ንብረት ሲያሸሹ እየተያዙ ነው ፖሊሶች ቤት እናም አንዳንድ አመራሮች ቤት ንብረት ተገኝቶአል። እውነት ነው ፀጊሽ ወደ ገጠር ድረስ ገብተው አጋዜ ልዩ አይል ንብረት እያስመለሰ ነው ፀጊሽ ዛሬ ከነጋ አንድ መኪና ተጨማሪ ሀይል ገብቶ አሰሳው ተጠናክሮ ቀጥሉአል። ትናንትና አንድ ፖሊስ የዘረፈው ፍራሽ ላይ ቁጭ ብሎ የዘረፈውን መጠጥ ቁጭ ብሎ ሲጠጣ ተደርሶበት በልዩ አይሎች ተደርሶበታል እይልኝ እንግዲ ፀጊሽ የዚህ አይነቱ ነው ህዝቡንና አገሪቱን እንዲ እንድትሆን ትልቁን ሚና የተጫወቱት እንደዚህ አይነት ሆዳሞች ናቸው እግዚሃብሔር ኢትዮጵያንና ህዝቧን ይጠብቅ።"

.
.

"አዎ የተያዘው ንብረትማ ከከተማው ጥግ ጥግ ካሉት ቤቶች በበርካታ መኪኖች እየተመለሱ ነው ወደ 3 የሚጠጉ የፖሊስ አባላት ቤት ውስጥም ተገኝቷል እነሱም በመከላከያ ሰራውት እየተለቀሙ ነው!"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Forwarded from MarkdownBot
የአለም ዋንጫ ምድብ ሁለት ሁለተኛ ዙር ስፔን ኢራን።
ስፔንና ኢራን ዛሬ ከምሽቱ 3:00 የተገናኙ ሲሆን በመጀመርያ አጋማሽ ምንም አይነት ጎል ያልተቆጠረ ሲሆን። ሁለተኛ አጋማሽ በ54 ደቂቃ የስፔን ብቸኛ ጎል በኮስታ አማካኝነት ያገኙ ሲሆኑ ከጎሏ መግባት ብሀላ ኢራኖች ተጭናው መጫወት ቢችሉም ጎል ሳያስቆጥሩ መውጣት ችለዋል።

አለም ዋንጫን ከYenesport ጋር ያሳልፉ Join