TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ስለፊቼ ጨምባላላ ምን ያህል አውቃለሁ ?

- የሲዳማ ሕዝብ የጨረቃና ከዋክብትን አቀማመጥ በማጥናት አዲስ ዓመት ያከብራል። በዓሉም ፊቼ ጨምበላላ ይባላል።

- ፊቼ ጫምባላላ መከበር ከጀመረ ከ1800 ዓመታት በላይ ማስቆጠሩን የአገር ሽማግሌዎች ይናገራል።

- በዓሉ የሲዳማ ሕዝብ ማንነቱን ከተረዳበት ጊዜ አንስቶ ሲከበር ቆይቷል።

- ፊቼ ጨምበላላ በዓል የሚከበርበት ቋሚ ቀን የለውም። በአያንቱዎች ጥቆማ መሰረት በዓሉ የሚከበርበት ቀን ይቆረጣል።

- 'የፊቼ ጨምበላላ ዋነኛ ትርጉም ሰላም ነው'፤ አንድነትና ፍቅር የበዓሉ መለያ ነው።

- የተጣሉ ሰዎች በፊቼ ጨምበላላ በዓል ላይ ይታረቃሉ። ሃዘን ላይ የነበሩ ሰዎችም የሃዘን ልብሳቸውን ይቀይራሉ።

- ከቀዬው ርቆ የነበረ ሰው ለፊቼ ጨምበላላ ወደቀዬው ይመለሳል።

- ለዚህ በዓል ተብሎ እርድ አይፈጸምም፤ ስጋም አይበላም። ክብቶችን መምታትም ክልክል ነው። ላሞች ሳር የበዛበት መስክ ላይ ይሰማራሉ።

- በሲዳማ ሕዝብ ዘንድ በፊቼ ጨምበላላ በዓል ወቅት ማረስ ነውር ነው። ለዚህም ምክንያቱ ደግሞ የፊቼ ጨምበላላ በዓል የሲዳማ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን የተፈጥሮም ነው ተብሎ ስለሚታመን ነው።

- ፊቼ የአዲስ ዓመት በዓል ዋዜማ ሲሆን፤ ጨምበላላ ደግሞ የአዲስ ዓመት መጀመሪያው ቀን ነው።

- ሲዳማ ከአንድ ዓመት ወደሌላው የሚሸጋገርበት ሂደት ሁሉቃ ይባላል። ሁሉቃ ማለት ከሸምበቆና ከአርጥብ ቅጠል ተሠርቶ የሚቆም ነገር ነው። ሁሉቃ በቤተሰብና በማኅበረሰብ ደረጃ የሚሠራ ሲሆን፤ አዲስ ዓመት ሲገባ ሰዎችና ከብቶች ይተላለፉበታል።

- የሲዳማ ሕዝብ አዲስ ዓመትን ሲቀበሉ፤ ዓመቱ የብልጽግና እንዲሆንላቸው 'ፊቼ ጄጂ' ይላሉ።

ይህ መረጃ የቀረበው ከ2019 የቢቢሲ ድረገፅ ላያ ከወጣው ፅሁፍ ነው።

@tikvahethiopiaaBot @tikvahethiopia
ችሎት !

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት፤ በእነ ስብሃት ነጋ መዝገብ የቅድመ ምርመራ የምስክሮች አሰማም ሂደት፤ በዝግ ችሎት እና የምስክሮች ስምና አድራሻቸው ሳይጠቀስ እንዲካሄድ ዛሬ አርብ ውሳኔ አስተላለፈ።

ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን ያስተላለፈው ዐቃቤ ህግ “ለምስክሮች ጥበቃ አድርጊያለሁ” ማለቱን ተከትሎ በተከሳሽ ጠበቆች የቀረበውን መቃወሚያ ከመረመረ በኋላ ነው።

በዐቃቤ ህግ በኩል የተነሳው የምስክሮች ጥበቃ ህገ-መንግስታዊ መሆኑን የገለጸው ፍርድ ቤቱ፤ ከቀረቡለት ሶስት የምስክር አሰማም ሂደቶች ሁለቱን መቀበሉን በውሳኔው አመልክቷል።

ተቀባይነት ካገኙት የምስክር አሰማም ሂደቶች የመጀመሪያው ማንኛውም ሚዲያ እና ታዳሚ ሳይገባ በዝግ ችሎት የቅድመ ምርመራ ምስክሮች የሚሰሙበት ነው።

የምስክሮች ስም እና አድራሻ ለተጠርጣሪዎች ሳይጠቀስ የምስክሮች ቃል የሚሰማበት ሁለተኛው አካሄድም እንዲሁ በፍርድ ቤቱ ተቀባይነት አግኝቷል።

ፍርድ ቤቱ ውድቅ ያደረገው የምስክር አሰማም ሂደት፤ ምስክሮች በአካል ሳይታዩ ከመጋረጃ ጀርባ ሆነው እንዲመሰክሩ በሚል በዐቃቤ ህግ የቀረበውን ነው።

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት፤ በእነ ስብሃት ነጋ መዝገብ የቅድመ ምርመራ የምስክሮች አሰማም ሂደት፤ በዝግ ችሎት እና የምስክሮች ስምና አድራሻቸው ሳይጠቀስ እንዲካሄድ ዛሬ አርብ ውሳኔ አስተላለፈ።

ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን ያስተላለፈው ዐቃቤ ህግ “ለምስክሮች ጥበቃ አድርጊያለሁ” ማለቱን ተከትሎ በተከሳሽ ጠበቆች የቀረበውን መቃወሚያ ከመረመረ በኋላ ነው።

ምንጭ፦ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር ነበር የተባለ 110 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ተያዘ !

በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እና በብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ጋር አረኩት ባለው ክትትል በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 110 ሺህ የአሜሪካ ዶላር መያዙን አስታውቋል።

ፖሊስ ገንዘቡን ከነተጠርጣሪዎቹ ነው በቁጥጥር ስር መዋሉን ያሳወቀው።

መቼ እና የት ?

በህገ ወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረው ዶላር የተያዘው ሚያዚያ 28 ለ29 አጥቢያ 2013 ዓ/ም የካ ክፍለ ከተማ በተለምዶ "ላምበረት" ተብሎ በሚጠራው መናኸሪያ ግቢ ውስጥ በግምት ከለሊቱ 10 ሰዓት ከ40 ደቂቃ ገደማ ነው፡፡

ገንዘቡ እንዴት ሊገኝ ቻለ ?

የአ/አ ፖሊስ እንዳለው ገንዘቡ የተገኘው ከህዝብ በተገኘ ጥቆማ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት በቅንጅት በተደረገው ክትትል ነው።

110 ሺህ ዶላሩ ከአዲስ አበባ ወደ ሃረር ሊጓዙ የተዘጋጁ 2 ተጠርጣሪዎች በያዙት ሻንጣ ላይ በተደረገ ፍተሻ በጥቁር ላስቲክ ተጠቅልሎ ነው የተገኘው።

ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

@tikvahethiopia
የመራጮች ምዝገባ ዛሬ ይጠናቀቅባቸዋል በተባሉ ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች እስከ ግንቦት 06 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ተራዘመ !

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ6ተኛው አጠቃላይ ምርጫ ዋና ተግባር የሆነው የመራጮች ምዝገባን እያከናወነ እንደሆነ አስታውሷል።

በአሁኑ ወቅት በጊዜያዊነት በተሰበሰበው መረጃ (ያለፉት 3 ቀናትን ሳይጨምር) 28,731,935 ያህል መራጮች የተመዘገቡ መሆኑን ገልጿል።

የመራጮች ምዝገባ በ41,798 ያህል ምርጫ ጣቢያዎች እየተከናወነ ይገኛልም ብሏል።

የመራጮች ምዝገባ ከተያዘለት የጊዜ ገደብ በተጨማሪ ለ15 ቀን ተጨምሮ ከአፋርና ከሶማሌ ክልሎች ውጪ የማጠናቀቂያ ጊዜው በዛሬ ሚያዝያ 29 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚሆን ማሳወቁ አስታውሷል።

በዚህ ወቅት ፦

1. የመራጮች ምዝገባ በተራዘመበት ወቅት ተደራራቢ የበአላት ቀናት መኖራቸው እና በዚያም የተነሳ በህጉ መሰረት ብሔራዊ በአላት ዝግ በመሆናቸው የመራጮች ምዝገባ ሊከናወን አለመቻሉን

2. የመራጮች ምዝገባ በተራዘመበት ወቅት 1500 መራጮች የመዘገቡ ጣቢያዎቸን ለይቶ ንኡስ ጣቢያዎችን የማደራጀት ሂደት ጊዜ መውሰዱን በዚህም ምክንያት ከፍተኛ የመራጮች መጨናነቅ ምርጫ ጣቢያ ላይ መፈጠሩን

ይህንን ከግምት ውስጥ በማስገባት የመራጮች ካርድ በመውሰድ መምረጥ የሚችሉ ቀላል የማይባሉ ዜጎች በዚህ የተነሳ የመራጮች ካርድ አለመውሰዳቸውን ቦርዱ ተገንዝቢያለሁ ብሏል።

ቦርዱ ባደረገው ስብሰባ የመራጮች ምዝገባ ዛሬ ይጠናቀቅባቸው በነበሩ፦
- አዲስ አበባ ከተማ
- ድሬዳዋ ከተማ
- አማራ
- ቤኒሻንጉል ጉሙዝ
- ደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል
- ጋምቤላ
- ሃረሪ
- ኦሮሚያና ሲዳማ ክልሎች የመራጮች ምዝገባ እስከ አርብ ግንቦት 6/2013 ድረስ ለተጨማሪ 7 ቀናት እንዲከናወን ወስኗል።

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የሞጀ-ሀዋሳ ክፍያ መንገድ !

92 ኪሜ ርዝመት ያለው የሞጆ-ሀዋሳ የክፊያ ፍጥነት መንገድ የመጀመሪያው ክፍል የሆነው የሞጆ-ባቱ ክፍያ የፍጥነት መንገድ መጠናቀቁ ተገልጿል።

ይህ መንገድ በቅርቡ ለአገልግሎት ክፍት ይሆናል ተብሏል።

መንገዱ መሄጃ እና መምጫውን ጨምሮ 4 ተሽከርካሪዎችን በአንድ ጊዜ የሚያስተናግድ ዘመናዊ መንገድ እንደሆነ ተገልጿል።

እንደ አዲስ አበባ- አዳማ እንዲሁም ድሬደዋ-ደዋሌ የፍጥነት መንገዶች ሁሉ አገልግሎቱ በክፍያ የሚሰጥ ነው።

Via Kassahun Gofe Balami
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
"በምርጫ ወቅት ተማሪዎች ወደ መጡበት ይመለሳሉ" - ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ

[ በ www.addiszeybe.com የቀረበ ]

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ነባር (የቅድመ ምረቃና የድህረ ምረቃ) ተማሪዎች ወደ ቤተሰቦቻቸው ተመልሰው በምርጫው እንዲሳተፉ በማለት ምርጫው ከሚካሄድበት ከግንቦት 28/2013 ዓ.ም. አንድ ሳምንት በፊትና በኋላ በአጠቃላይ ለ2 ሳምንታት የዕረፍት ጊዜ ይወጣሉ ተብሏል።

ከግንቦት 20/2013 ዓ.ም. ጀምሮ ሁሉም የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች ግቢዎቻቸውን ለቀው እንደሚወጡ ተገልጿል።

በሌላ በኩል የድህረ ምረቃ ተማሪዎች ግንቦት 20 እና 21/2013 ዓ.ም. የሚካሄደውን ዓለም አቀፍ የድህረ ምረቃ የምርምር ጉባኤ ከተሳተፉ በኋላ ግንቦት 22/2013 ዓ.ም. ወደ መጡበት አካባቢ ይመለሳሉ ብሏል ዩኒቨርሲቲው።

ዩኒቨርሲቲው ይህ የወሰነው ዛሬ ባከናወነው የበይነ-መረብ ስብሰባ ላይ ነው ተብሏል።

በመማር ማስተማር ሂደቱ ክፍተት እንዳይፈጠር ከመውጣታቸው በፊት ለተማሪዎች የማካካሻ ትምህርት ይሠጣቸዋል ተብሏል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ችሎት !

በአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ የተጠረጠረችው አራተኛ ተከሳሽ ላምሮት ከማል ዛሬ በጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ቀረበች።

ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት በቀጥታ በፕላዝማ ችሎቱን የተከታተለችው ተከሳሿ ከዚህ ቀደም የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የፀረ-ሽብርና ህገ-መንግስት ጉዳዮች ወንጀል ምርመራ ችሎት በቂ ማስረጃ አላገኘሁባትም ሲል በነገጻ ካሰናበታት ወዲህ ፍርድ ቤት ስትቀርብ ይህ የመጀመሪያው ነው።

ከሳሽ አቃቤ ህግ የተከሳሽ በነጻ መለቀቅን በመቃወም ለፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ብሎ ነበር።

በዛሬው እለትም የከሳሽ አቃቤ ህግ እና የተከሳሽ ክርክር ለመስማት ያስቻለው ፍርድ ቤቱ ተከሳሽዋ የአቃቤ ህግ የይግባኝ ወረቀት እንዳልደረሳት በመግለጧ ወደ ክርክሩ አልተገባም። 

በፕላዝማ ቀርባ ለፍርድ ቤቱ ሃሳቧን የገለጸችው ተጠርጣሪዋ ላምሮት ከማል ለችሎቱ የቀረበችው በማረሚያ ቤት ትዕዛዝ መሆኑን በመግለጽ፤ የይግባኝ ክሱን ጭብጥ ጉዳይ ለማግኘት ግን ማረሚያ ቤቱን ጠይቃ መከልከሏን ገልጻለች። 

አቃቤ ህግ በበኩሉ የይግባኝ ክስ ወረቀቱ ከመስሪያ ቤቱ ወጪ ሆኖ ወደ ማረሚያ ቤቱ መላኩን ለፍርድ ቤቱ አሳውቋል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/DW-05-07-2 (ዶቼ ቨለ)

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
"በምርጫ ወቅት ተማሪዎች ወደ መጡበት ይመለሳሉ" - ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ [ በ www.addiszeybe.com የቀረበ ] የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ነባር (የቅድመ ምረቃና የድህረ ምረቃ) ተማሪዎች ወደ ቤተሰቦቻቸው ተመልሰው በምርጫው እንዲሳተፉ በማለት ምርጫው ከሚካሄድበት ከግንቦት 28/2013 ዓ.ም. አንድ ሳምንት በፊትና በኋላ በአጠቃላይ ለ2 ሳምንታት የዕረፍት ጊዜ ይወጣሉ ተብሏል። ከግንቦት 20/2013…
"...የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እንዴት በምርጫው ይሳተፉ በሚለው መንገድ ላይ የተወሰነ ነገር የለም" - የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ለ @tikvahuniversity

ከቅድመ ምረቃ ጀምሮ በዩኒቨርሲቲ የሚገኙ ተማሪዎች እንዴት በምርጫው የሚሳተፉበት መንገድ ላይ በሚለው ጉዳይ ላይ የተወሰነ ነገር አለመኖሩን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ለ @tikvahuniversity ገልጿል።

በጉዳዩ ላይ ውሳኔውን በቅርቡ ይፋ እንደሚያደርግ/መግለጫም እንደሚሰጥ ነው የገለፀልን።

በሌላ በኩል የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አዲስ የተመደቡ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ቅሬታ ማቅረቢያ ግዜ ዛሬ ማብቃቱን አሳውቋል።

ቅሬታዎችን ዛሬም ሲቀበል መዋሉን የገለፀው ሚኒስቴሩ ፤ ከዛሬ በኋላ ምንም አይነት ቅሬታ እንደማይቀበል ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ገልጿል።

አዲስ የተመደቡ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ያላቸውን ቅሬታ በድረ ገጽ፣ በኢ-ሜይል እና በስልክ ላለፋት አምስት ቀናት ለሚኒስቴሩ ሲያቀርቡ ቆይተዋል።

@tikvahuniversity @tikvahethiopia
#ጥንቃቄ_ይደረግ !

እየጣለ ያለው የበልግ ዝናብ በኢትዮጵያ በአንዳንድ አካባቢዎች የጎርፍ አደጋ ሊያስከትል ስለሚችል ከውዲሁ ጥንቃቄ እንዲደረግ የብሔራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አሳሰበ።

በብሔራዊ ሜትሮሎጂ ኤጀንሲ በሚያዚያ ወር ትንበያ መሰረት ፦

- በኦሮሚያ፣
- በጋምቤላ፣
- በቤኒሻንጉል ጉሙዝ
- በአማራ
- በመከለኛውና እ ምዕራብ ትግራይ ክልል ፣
- በደቡብ ክልል መደበኛ እና ከመደበኛ በላይ ዝናብ ይኖራቸዋል።

በኦሮሚያ፣ ሶማሌ፣ ሲዳማ እና ደቡብ ክልሎች አንዳንድ አካባቢዎች ከዝናቡ መጠን መጨመር ጋር ተያይዞ የጎርፍ አደጋ ሊያስከትል ይችላል።

በብሄራዊ ሜትሮሎጂ ኤጀንሲ የአየር ትንበያ መሰረት በቀሪው የበልግ ወቅት ለጎርፍ ተጋላጭ የሆኑ አካባቢዎች መለየታቸውን የብሔራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ማስታወቁን ኢዜአ ዘግቧል።

@tikvahethmagazine
TIKVAH-ETHIOPIA
#ጥንቃቄ_ይደረግ ! እየጣለ ያለው የበልግ ዝናብ በኢትዮጵያ በአንዳንድ አካባቢዎች የጎርፍ አደጋ ሊያስከትል ስለሚችል ከውዲሁ ጥንቃቄ እንዲደረግ የብሔራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አሳሰበ። በብሔራዊ ሜትሮሎጂ ኤጀንሲ በሚያዚያ ወር ትንበያ መሰረት ፦ - በኦሮሚያ፣ - በጋምቤላ፣ - በቤኒሻንጉል ጉሙዝ - በአማራ - በመከለኛውና እ ምዕራብ ትግራይ ክልል ፣ - በደቡብ ክልል መደበኛ እና…
#ጥንቃቄ_ይደረግ !

የብሄራዊ ሚቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ የአየር ትንበያ መሰረት በቀሪው የበልግ ወቅት ለጎርፍ ተጋላጭ ናቸው ያላቸው አካባቢዎች ፦

- በኦሮሚያ ክልል ፦ ምዕራብ ሐረርጌ፣ ባሌ፣ አርሲ፣ ቦረና፣ ጉጂ እና ምዕራብ ጉጂ የጎርፍ ስጋት መኖሩን ተጠቁሟል፤

- በሶማሌ ክልል ፦ ሸበሌ ፣ አፍዴር፣ ሊበን፣ ዶሎ ፣ ፋፋን፣ ሲቲ፣ ዳዋ አንዳንድ አካባቢዎች ጎርፍ ሊኖር እንደሚችልም ተገምቷል፤

- በደቡብ ክልል ፦ በሀዲያ ፣ በወላይታ፣ በጋሞ፣ በዳውሮ ፣ በሰገን፣ በስልጤ፣ ጉራጌ አንዳንድ አካባቢዎችም የጎርፍ አደጋ ሊያጋጥም እንደሚችል ተገልጿል፤

- በሲዳማ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች የጎርፍ ስጋት አለ።

- በድሬዳዋ ከተማና የገጠር ቀበሌዎች የጎርፍ ስጋት አለ።

ከላይ በተጠቀሱት አካባቢዎች የዝናብ መጠን መጨመርን ተከትሎ የጎርፍ ስጋት አለ።

ለጎርፍ ስጋት ተጋላጭ ለሆነ ማህበረሰብ የቅድመ ጥንቃቄ እና ወቅታዊ መረጃ ተደራሽ ማድረግ እንደሚገባ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

ፎቶ : ፋይል
@tikvahethmagazine @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ዕለታዊ ሪፖርት ፦

ባለፉት 24 ሰዓት 18 ሰዎች በኮቪድ-19 ህይወታቸው አልፏል።

በተመሳሳይ ከተደረገው 5,521 የላብራቶሪ ምርመራ 778 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

ትላንት 1,412 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

በአጠቃላይ 261,580 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 3,840 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 206,870 ሰዎች አገግመዋል።

አሁን ላይ 765 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

በሀገራችን እየተሰጠ ያለውን የኮቪድ-19 ክትባት የተከተቡ ዜጎች ቁጥር 1,287,801 ደርሷል።

#Purpose
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#DrTedrosAdhanom

በዓለም ዙሪያ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር በተከታታይ ለዘጠነኛ ሳምንት ፣ በበሽታው ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉት ሰዎች ቁጥር ደግሞ ለስድተኛ ሳምንት ማሻቀቡን መቀጠሉን የዓለም የጤና ድርጅት አስታውቋል።

የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ቴድሮስ አደሃኖም ይህን ያሳወቁት ትናንት በአባል ሃገራቱ የመረጃ ልውውጥ ጉባኤ ላይ ነው።

ዶ/ር ቴድሮስ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ የተመዘገበው የኮሮና ቫይረስ ተያዦች ቁጥር በወረርሽኙ የመጀመሪያ 6 ወር ውስጥ ከተመዘገቡት ይበልጣል ብለዋል።

በመሆኑም ወቅቱ የቫይረሱ ስርጭት እየቀነሰላቸው ባሉትም ሃገሮች ጭምር ከመጠንቀቅ ወደኋላ የሚባልበት አይደለም ሲሉ ማሳሰባቸውን ቪኦኤ በድረ ገፁ አስነብቧል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ስለምርጫ 2013 ወቅታዊ ጉዳይ ምን ማወቅ አለብኝ ?

- 6ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ሊደረገው የቀረው ጊዜ 3 ሳምንታት : 06 ቀናት : 21 ሰዓታት ብቻ ነው።

- በጊዜያዊነት በተሰበሰበው መረጃ (ያለፉት ሶስት ቀናትን ሳይጨምር) 28,731,935 ያህል መራጮች ተመዝግበዋል።

- የአውሮፓ ህብረት ምርጫውን ለመታዘብ አይመጣም።

- መንግስት የኢትዮጵያን ሉኣላዊነት የሚፃረሩ ፣ ነፃነቷን የሚዳፈሩ፣ ደህንነቷን አደጋ ላይ የሚጥሉ ከዚህ በፊት ተጠይቆ የማያውቅ ጥያቄ ጠይቀው አይሆንም ስለተባሉ ነው የቀሩት ብሏል።

- የአውሮፓ ሕብረት የኢትዮጵያን ምርጫ ላለመታዘብ የያዘውን አቋም በማጤን ምርጫውን እንዲታዘብ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት ጠይቋል፤ መንግስት ሆነ አውሮፓ ህብረት የልተስማሙበትን ጉዳይ በግልፅ ለህዝብ ይግለፁም ብሏል።

- በአዲስ አበባ ፣ ድሬዳዋ ፣ አማራ ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ፣በደቡብ ፣ ጋምቤላ ፣ ሃረሪ፣ ኦሮሚያና ሲዳማ የመራጮች ምዝገባ እስከ ግንቦት 6 ተራዝሟል።

- አሁንም የአገልግለት ክፍያ አልተፈፀምልንም የሚሉ ምርጫ አስፈፃሚዎች ያሉ ሲሆን ምርጫ ቦርድ ከጥቂት ቀናት በፊህ ምርጫ ቦርድ 67,405 ክፍያ መክፈሉን ለቀሪዎቹም ለመክፈል እየሰራ መሆን አሳውቆ ነበር።

- የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የምርጫ ምዝገባ በ www.nebe.org.et/ovrs እየተካሄደ ይገኛል።

- የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን ለምርጫው በሚል ከምርጫው በፊት 1 ሳምንት እና ከምርጫ በኋላ 1 ሳምንት አጠቃላይ 2 ሳምንት ያህል ተማሪዎቻቸውን እንደሚበትኑ እያሳወቁ ነው።

- MoSHE ለ @tikvahuniversity ተማሪዎች በምርጫው ላይ እንዴት እንደሚሳተፉ ገና እንዳልተወሰነ ፤ በቅርቡ ግን መግለጫ እንደሚሰጥበት አሳውቋል።

@tikvahethiopia
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ በትግራይ ክልል ጉዳይ የተናገሩበት ቪድዮ ፦

ይህ ከ14 ደቂቃ በላይ ርዝማኔ ያለው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ በትግራይ ጉዳይ የሚናገሩበት ቪድዮ የተቀረፀው በሞባይል ነው።

ቪድዮው Dennis Wadley በተባሉና የሳቸው የቅርብ ወዳጅ በሆኑ ሰው በሞባይል የተቀረፀ መሆኑ ነው የተገለፀው።

Dennis Wadley በአሜሪካ መቀመጫነቱን ያደረገው የBridges of Hope ድርጅት መሪ ሲሆኑ ለረጅም ዓመታት የብፁእነታቸውን ወዳጅ እንደሆኑ ተነግሯል።

ባለፈው ወር Dennis Wadley ወደ አዲስ አበባ መጥተው በነበረበት ወቅት ነው ይህ ቪድዮ በአይፎን እጅ ስልካቸው ቀርፀው የሄዱት።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ በቪድዮው ላይ ምን ሲናገሩ ይደመጣል ?

- ትግራይ ውስጥ ይሰራል ያሉት አረመኒያዊ ስራ እንዲቆም ያቀረቡት ጥይቄ አልተሳካም ፤ ፍቃድ አልተሰጠም ብለዋል።

- የሚናገሩት ሁሉ በተደጋጋሚ ሁሌ እንደሚመለስ እና ፍቃድ እንዳላገኙ ተናግረዋል።

- የእኔን ችግር እኔ ብቻ ነኝ የማውቀው ያሉ ሲሆን በትግራይ እየተፈፀመነው ያሉትን አረመኒያዊ ስራ ለመቃወም ብዙ ጊዜ እነድሞከሩ ነገር ግን ስላልተፈቀደ እየታፈነ እየቀረ ነው ያለው ብለዋል።

- በኦሮሚያ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ፣ በሸዋሮቢት በሌሎችም ቦታዎች ችግር አለ ያሉ ሲሆን የትግራይ ግን እጅግ የከፋ ፣ ጭካኔ የተሞላበት ነው ብለዋል።

- ዓለም አውቆታል ብዬ ሚያዚያ 7/2013 ያደረኩት ቃለምልልስ ታግዶ ቀርቷል ብለዋል።

- አሁን 6 ወር ሆኗል እስካሁን ግድያ እና ግፍ አሁንም አለ ብለዋል። ይህን ሁኔታ እግዚአብሔር እንዴት እንደሚመልሰው የራሱ ዳኝነት አለው ብለዋል።

ያንብቡ : telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-05-08

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የሞጀ-ሀዋሳ ክፍያ መንገድ ! 92 ኪሜ ርዝመት ያለው የሞጆ-ሀዋሳ የክፊያ ፍጥነት መንገድ የመጀመሪያው ክፍል የሆነው የሞጆ-ባቱ ክፍያ የፍጥነት መንገድ መጠናቀቁ ተገልጿል። ይህ መንገድ በቅርቡ ለአገልግሎት ክፍት ይሆናል ተብሏል። መንገዱ መሄጃ እና መምጫውን ጨምሮ 4 ተሽከርካሪዎችን በአንድ ጊዜ የሚያስተናግድ ዘመናዊ መንገድ እንደሆነ ተገልጿል። እንደ አዲስ አበባ- አዳማ እንዲሁም ድሬደዋ-ደዋሌ የፍጥነት…
* Update

ከአዲስ አበባ ሞያሌ - ከናይሮቢ ሞንባሳ የመንገድ ኮሊደር የሆነው የሞጆ - ሀዋሳ መንገድ በኮንትራት 1 እና 2 ያሉት ወደ 90 ኪሎሜትር ግንባታ ተጠናቋል፤ መንገዱ ዛሬ እንደሚመረቅም ከetv የተገኘው መረጃ ያሳያል።

አጭር መረጃ፦

- ከሞጆ - ሀዋሳ ድረስ እየተገነባ ያለው የፍጥነት መንገድ አጠቃላይ 13.7 ቢሊዮን ብር የተበጀተለት ሲሆን ውጪው ከዓለም ባንክ፣ ከአፍሪካ ልማት ባንክ፣ ከቻይና እና ኮሪያ ኤግዚም ባንክ በተገኘ ብድር ቀሪው በኢትዮጵያ መንግስት የሚሸፈን ነው።

- ከሞጆ እንደ ሀዋሳ ባለው ግንባታ 4 ኮንትራክተሮች እየተሳተፉ ነው።

- ዛሬ የሚመረቀው በኮንትራንት አንድ ከሞጆ - መቂ ፤ ከመቂ - ባቱ ያለው መንገድ ነው።

- ከሞጆ - መቂ 56 ኪሎሜትር መንገድ ግንባታ ያከናወነው የቻይናው ሬልዌይስ ሰቨን ግሩፕ ነው።

- ከመቂ - ባቱ 37 ኪሎሜትር መንገድ ግንባታ ያከናወነው የኮሪያው ዲዮ ኢንጃነሪግን ግሩፕ ነው።

- መንገዱ 37 ሜትር ስፋ አለው፤ በሁለት አካፋይ የ9 ሜትር ልዩነት ላይ ሁለት ተሽከርካሪዎች በአንዴ ማንቀሳቀስ ይችላል።

- መንገዱ ላይ የሚገኙ ከተሞችን እድገት ያፋጥናል ተብሎ ታምኗል።

- የሀገሪቱን ኢኮኖሚያ ይበልጥ ከፍ ያደርገዋል ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#FDREDefenseForce

የ15ኛ ሞተራይዝድ ሻለቃ በሁርሶ ኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ት/ቤት የ3 ወራት ስልጠና ዝግጅቱን አጠናቆ ቀጠናውን ለመረከብ በድሬድዋ ኤርፖርት አሸኛኘት ተደረጎለታል።

በተመሳሳይ በዩኒሚስ ሚሽን የተሰማራዉ የ12ኛ ሞተራይዝድ ሻለቃ ከ18 ወራት ቆይታ በኋላ በደቡብ ሱዳን የሰላም ማስከበር ግዳጁን አጠናቆ ወደ ሀገሩ ተመልሷል፡፡

በተጨማሪ በዩናሚድ ዳርፉር ሚሽን የተሰማራው የ25ኛ ሞተራይዝድ ሻለቃም ከ 6 ወራት ቆይታ በኋላ በሱዳን ዳርፉር ግዳጁን አጠናቆ ወደ ሀገሩ ተመልሷል፡፡

ሁለቱ የሞተራይዝድ ሻለቆች አመራርና አባላቱ በድሬዳዋ ኤርፖርት አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

በአቀባበል ስነስርዓቱ ወቅት በሀገር መከላከያ ሰላም ማስከበር ማዕከል የኮንቴንጀንት ዝግጅትና ስምሪት ቡድን መሪ ኮ/ል ጌታቸው አስማረ ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል።

መረጃው ከሀገር መከላከያ ሰራዊት የተገኘ ነው።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia