TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
214 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ የትንሳኤ በዓል ሪፖርት :

- በትራፊክ አደጋ ዙሪያ በበዓሉ ዋዜማ እና በበዓሉ እለት በደረሱ አደጋዎች የ2 ሰዎች ህይወት አልፏል።

- በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ልዩ ቦታው "ካዲስኮ" አካባቢ አንድ የ30 ዓመት ግለሰብ ከጓደኛው ጋር በመሆን ቤት ውስጥ ጥሬ ስጋ ሲበላ አንቆት ሕይወቱ አልፏል።

- ከወንጀል ድርጊት ጋር ተያይዞ ግን ከወትሮ የተለየ ወንጀል ድርጊት አልተፈፀመም።

በአጠቃላይ በዓሉ በሰላም ተከብሮ ማለፉን የአ/አ ከተማ ፖሊስ ያሳወቀ ሲሆን በዓሉ በሰላም እንዲከበር ህብረተሰቡ ላደረገው ቀና ትብብርና ኃላፊነታቸውን ለተወጡት የፀጥታ ኃይሎች ምስጋና አቅርቧል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
*Update

"የቻድ ጁንታ (ወታደራዊ መንግስት) የሽግግር መንግስት ሰይሟል"

በማሃማት ኢድሪስ ዴቢ የሚመራው የቻድ ጊዜያዊ ወታደራዊ ም/ቤት የሽግግር መንግስት መሰየሙን አስታውቋል። የሽግግር መንግስቱ የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካዮችን ጨምሮ 40 ሚኒስትሮችንና ዴዔታዎችን ያካተተ ነው።

አዲስ የእርቅ ሚኒስቴርም ተቋቁሟል።

የሽግግር መንግስቱ ከወታደር ቤቱ እንዲሁም ከአማፅያን የተውጣጡ አካላት በውስጡ አካቷል።

በ14 ጄኔራሎች በተከበቡት መሐማት ኢድሪስ ዴቢ የሚመራው ወታደራዊ ም/ቤት በ “ወታደራዊ መፈንቅለ መንግስት” የተመሰረተ ነው በሚል ይተቻል፡፡

ይሁን እንጂ የማርሻል ዴቢ ዋና ተፎካካሪ የሆኑት ሳሌህ ኬብዛቦ ለአዲሶቹ ባለሥልጣናት ዕውቅና ሰጥተዋል፡፡

ሁለት የኬብዛቦ ፓርቲ (ብሔራዊ የዴሞክራሲና ሪፎርም ፓርቲ) አባላትም ለእንስሳት እርባታ ሚኒስትርነት እና ምክትል ዋና ፀሐፊነት ተሹመዋል፡፡

ሌላኛው የኢድሪስ ዴቢ ኢትኖ ተቃዋሚ የሆኑት የ ’ለነፃነት እና ልማት ፓርቲ’ ው መሃማት አህማት አልሃቦ የፍትህ ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል።

አብዛኛዎቹ የክልል ሚኒስትርነት የኃላፊነት ቦታዎች በሟቹ ፕሬዝዳንት የሀገር ማዳን ንቅናነቄ (MPS) ፓርቲ እጅ ውስጥ ቀርተዋል።

አብዛኞቹ የቀድሞ ሚኒስትሮች በነበሩበት እንዲቀጥሉ ካልሆነ በሌላ የኃላፊነት ቦታ እንዲሾሙ ተደርጓል።

በአዲሱ አዋጅ የ37 ዓመቱ ፕሬዝዳንት ማሃማት ኢድሪስ ዴቢ የ “እርቅ እና ውይይት ሚኒስቴር” የፈጠሩ ሲሆን በቅርቡ “ሁሉን አቀፍ ውይይት” ለማዘጋጀት ቃል ገብተዋል ፡፡

በ18 ወራት ውስጥ "ነፃ እና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ" ለማካሄድ ነው ወታደራዊ ም/ቤቱ ቃል የገባው፡፡

ያንብቡ : telegra.ph/AL-AIN-News-Agency-05-03

ምንጭ፦ አል ዓይን
@tikvhaethiopia @tikvahethiopiaBOT
TIKVAH-ETHIOPIA
አዲስ የተመደቡ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከዛሬ ጀምሮ ቅሬታቸውን ማቅረብ ይችላሉ ! የ2013 ዓ.ም የተማሪዎች ምደባ ቅሬታ ማቅረቢያ ቀናት ከዛሬ ሚያዚያ 25 እስከ ሚያዚያ 28/2013 ዓ.ም ነው። ቅሬታ ያላቸው ቅሬታቸውን በአካል መምጣት ሳያስፈልግ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ባዘጋጀው ከታች ባለው ድረገፅ ላይ ወይም የኢሜል እና በስልክ አድርሻዎች ማቅረብ ይችላሉ። ማሳሰቢያ : MoSHE…
"...ለተማሪዎቻችን ደህንነት እንጨነቃለን፤ የሚቀርቡ የጤና እክል ማስረጃዎችን ሚኒስቴሩ ይመለከታል" - የMoSHE የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አመለወርቅ ህዝቄል

አዲስ የተመደቡ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ያላቸውን ቅሬታ በአካል መሄድ ሳያስፈልጋቸው በድረ ገጽ፣ በኢ-ሜይል እና በስልክ ማቅረብ እንደሚችሉ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

ይሁን እንጂ ከጤና እክል ጋር በተያያዘ የሚቀርቡ ቅሬታዎች ያሏቸው ተማሪዎች በአካል ሊስተናገዱ የሚችሉበት እድል መኖሩን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

ተማሪዎች ከመንግስት የሕክምና ተቋም የሀኪሞች ቦርድ የተፈረመ ትክክለኛ ማስረጃ ይዘው መቅረብ እንደሚችሉ የሚኒስቴሩ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አመለወርቅ ህዝቄል ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ገፅ ተናግረዋል።

ለተማሪዎቻችን ደህንነት እንጨነቃለን ያሉት ኃላፊዋ፤ የሚቀርቡ የጤና እክል ማስረጃዎችን ሚኒስቴሩ እንደሚመለከት ገልፀዋል።

የ2013 አዲስ ዩኒቨርስቲ ገቢ ተማሪዎች የዩኒቨርስቲ ምደባ ፤ በዩኒቨርስቲዎች ልየታ መሰረት ተማሪዎቹ ምርጫቸውን ካስተካከሉ በኋላ የተፈፀመ መሆኑን ኃላፊዋ አስታውሰዋል።

በቀጣይ ዩኒቨርስቲዎች በራሳቸው ፕሮግራም መሠረት ተማሪዎችን መጥራት እንደሚጀምሩ ኃላፊዋ ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ገልፀዋል።

ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ : https://t.iss.one/joinchat/RYD_4tbNBwRoKR2h

@tikvahuniversity @tikvahethiopia
ኮቪድ-19 በህንድ :

- ዛሬ 368,147 አዲስ የኮሮና ቫይረስ ተያዦች ተመዝግበዋል።

- በየቀኑ ከ300,000 በላይ አዲስ የቫይረሱ ተያዥች ሲገኙ ዛሬ 12ኛ ቀን ነው።

- ከዓለም የሚበዛው የኮቪድ-19 ክትባት የሚያመርተው “ዘ ሴረም ኢኒስትቲዩት” የተባለው የመድሃኒት አምራች ተቋም የሚገኘው ህንድ ውስጥ ሆኖ ሳለ ከ1 ነጥብ ሦስት ቢሊዮኑ ህዝቧ የተከተበው ሁለት ከመቶው ብቻ መሆኑ ታውቋል።

- የአሜሪካ የፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ጽህፈት ቤት ሹም ሮን ክሌይን ለሲቢኤስ ቴሌቭዥን በሰጡት ቃል ፥ "ለህንድ በጥድፊያ እርዳታ በመላክ ላይ ነን" ብለዋል። አሜሪካ ያን እያደረገች ቫይረሱ እንዳይስፋፋ ለመከላከል ርምጃዎች በመውሰድ ላይ ናት ብለዋል።

- አሜሪካ ከነገ ማክሰኞ ጀምሮ ከህንድ በረራዎች አታስገባም።

- አውስትራሊያ ከህንድ በረራ እንዳይገባ ከልክላለች። ወደህንድ ተጉዞ ሲመለሱ የሚገኙ አውስትሬሊያውያን በገንዘብ እና በእስራት ሊቀጡ ይችላሉ።

በሌላ የኮቪድ-19 መረጃ ፦

ኢንዶኔዥያ ሁለት የተቀየሩ የኮሮናቫይረስ ዝርያዎች ሃገርዋ መግባታቸውን አስታውቃለች። አንደኛው ከደቡብ አፍሪካ ሌላው ከህንድ መሆኑን ነው የገለጸችው።

ይህንኑ ተከትሎ የአሜሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከል (ሲዲ) ተጓዥች ወደኢንዶኔዥያ ከመሄድ እንዲቆጠቡ መክሯል።

የኮቪድ መከላከያ ክትባት የወሰዱ ሰዎችም ቢሆኑ በልውጦቹ ቫይረሶች ሊያዙ እና ሊያዛምቱ እንደሚችሉ ነው ሲዲሲ ያሳሰበው።

ምንጭ፦ ቪኦኤ
@tikvahethiopiaBOT @tikvhaethiopia
ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም WHOን ለመምራት ሁለተኛ ዙር ለመወዳደር ፍላጎት እንዳላቸው ተዘገበ !

የዓለም ጤና ድርጅት [WHO] ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም የድርጅቱን ኃላፊ ሆነው ለቀጣይ አምስት አመታት ለምምራት በሚያስችላቸው የሁለተኛ ዙር ውድድር ለመሳተፍ ፍላጎት እንዳላቸው ሮይተርስ ስቴት ኒውስን ዋቢ በማድረግ ዘግቧል።

ዶ/ር ቴድሮስ ለ2ኛ ዙር በሚወዳደሩበት ወቅት “በሌሎች ተቀናቃኞች ይፈተኑ ይሆን?” ለሚለው ግን የታወቀ ነገር የለም፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ ለሁለተኛ ዙር በሚያደርጉት ውድድር ከአፍሪካ ሀገራት ወሳኝ ድጋፍ እንደሚያገኙ ከወዲሁ ቢገመትም ከሀገራቸው ኢትዮጵያ ድጋፍ ልያገኙ ስለመቻላቸው ግን እርግጠኛ መሆን እንደማይቻል ሮይተርስ ዲፕሎማቶች ነግረውኛል ሲል ዘግቧል፡፡

ምክንያቱም የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ግጭት ጉዳይ ዋና ዳይሬክተሩ ለቀድሞ ድርጅታቸው ህወሀት ወግነዋል እንዲሁም ለትግራይ ክልል መንግስት የዲፕሎማሲ ድጋፍ አድረገዋል በማለት ከሷቸዋል፡፡

ምንጭ፦ telegra.ph/AL-AIN-News-Agency-05-03-2

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
"...ለተማሪዎቻችን ደህንነት እንጨነቃለን፤ የሚቀርቡ የጤና እክል ማስረጃዎችን ሚኒስቴሩ ይመለከታል" - የMoSHE የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አመለወርቅ ህዝቄል አዲስ የተመደቡ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ያላቸውን ቅሬታ በአካል መሄድ ሳያስፈልጋቸው በድረ ገጽ፣ በኢ-ሜይል እና በስልክ ማቅረብ እንደሚችሉ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል። ይሁን እንጂ ከጤና እክል ጋር በተያያዘ የሚቀርቡ ቅሬታዎች…
"...ተማሪዎች የእርስ በእርስ የዩኒቨርሲቲ ቅያሬ ሙከራ አይቻልም" - ወ/ሮ አመለወርቅ ሕዝቅኤል

[የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን]

አዲስ የተመደቡ ተማሪዎች በግል የሚያደርጉት የእርስ በእርስ የዩኒቨርሲቲ ቅያሬ ሙከራ ህገ-ወጥ እንደሆነ እና እንደማይቻል የኢፌዴሪ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ከዩኒቨርሲቲ ዩኒቨርሲቲ በግል ለመቀያየር እየተቀመጡ ያሉ መልዕክቶች ተገቢ ያልሆኑ እና ህጋዊ አለመሆናቸውን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስታውቋል።

ዘንድሮ የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ከ147 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ለመቀበል የተዘጋጁ ሲሆን የተማሪዎች ምደባም ይህን የመቀበል አቅም መሰረት በማድረግ እንደተካሄደ ወ/ሮ አመለወርቅ ሕዝቅኤል ለኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

ወ/ሮ አመለወርቅ አክለው ፥ "ወደ ተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ለመሄድ የማያስችል ምክንያት ያላቸው ተማሪዎች ማስረጃቸውን በማቅረብ ውሳኔ እያገኙ ነው ፤ ይህ አሰራር ከዚህ በፊትም እየተሰራበት ነበር" ብለዋል።

በተለይ ከህመም ጋር በተያያዘ ችግር ያለባቸው ተማሪዎች በሀኪሞች ቦርድ የተረጋገጠ ማስረጃ ካቀረቡ ቅድሚያ ይሰጣቸዋል ሲሉ ገልፀዋል።

ከዚህ ውጭ ሚኒስቴሩ አዲስ የተመደቡ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በአመዳደብ ላይ ያላቸውን ቅሬታ በአጭር ጊዜ ውስጥ ምላሽ ይሰጣል ብለዋል።

@tikvhaethiopiaBOT @tikvahethiopia
#Ethiopia😷

ባለፉት 24 ሰዓት 31 ሰዎች በኮቪድ-19 ህይወታቸው አለፈ።

በተመሳሳይ ከተደረገው 4,008 የላብራቶሪ ምርመራ 429 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

ትላንት 648 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

በአጠቃላይ 258,813 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 3,757 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 201,156 ሰዎች አገግመዋል።

አሁን ላይ 858 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

በሌላ በኩል በሀገራችን እየተሰጠ ያለውን የኮቪድ-19 ክትባት የተከተቡ ዜጎች ቁጥር 1,168,268 ደርሷል።

#Purpose
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
TIKVAH-ETHIOPIA
የሚኒስትሮች ም/ቤት 👆 የሚንስትሮች ምክር ቤት ዛሬ 'ሕወሓት' እና 'ሸኔ' ድርጅቶች በሽብርተኛ ድርጅትነት እንዲሰየሙ የውሳኔ ሐሳብ አቅርቧል። የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት በጉዳዩ ላይ ከላይ ያለውን ዝርዝር መግለጫ ሰጥቷል። በተጨማሪም መንግለጫውን በዚህ ማስፈንጠሪያ ማንበብ ትችላላችሁ https://telegra.ph/PM-Office-05-01 @tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
'ሸኔ' እና 'ህወሓት'

የህግ ምሁራንና ባለሞያዎች አስተያየት እና የህ.ተ.ም/ቤት ጥሪ ፦

ዛሬ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባስተላለፈው ማስታወቂያ "ህወሓት" እና "ሸኔ" የሚባሉት ድርጅቶች በአሸባሪነት እንዲፈረጁ ሚንስትሮች ምክር ቤት ባቀረበው ውሳኔ ሃሳብ ላይ የተቃውሞ ማስረጃ ካላቸው በአካል እንዲያቀርቡ ጥሪ አቅርቧል።

የምዑራን አስተያየት በሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ ላይ ፦

• የህግ ጠበቃ እና አማካሪው አቶ አመሃ መኮንን ፡

"እነዚህ ድርጅቶች በረጅም ጊዜ ሂደት ውስጥ ስጋት፣ ለህዝቡ ፀጥታ ስጋት ፣ለሀገር ሰላም ስጋት የሚሆኑበት መንገድ በእጅጉ ይቀንሳል ብዬ ገምታለሁ።
በሽብረትኝነት የመሰየሙ ውጤት ፦
- እነዚህን ድርጅቶች መምራት የሚያስጠይቅ ይሆናል።
- የድርጅቶቹ አባል መሆን ያስጠይቃል።
- ድርጅቶቹን ባማቸውም ሁኔታ መደገፍ እና መተባበር የሚያስጠይቅ ነው የሚሆነው።
ስለዚህ በእጅጉ አቅም የሚያሳጣቸው ነው የሚሆነው።"

• በአምቦ ዩኒቨርሲቲ የህግ መምህሩ አቶ ሚኪያስ በቀለ :

"...አሁን አጠያያቂ የሆነው አንዱ ጉዳይ ፥ ሸኔ የሚባል ድርጅት አለ ወይ ? የሚለው ነገር ነው። እራሱን "ሸኔ" ብሎ የሚጠራ ቡድን አይታወቅም። ስለዚህ መንግስት ማለት የፈለገው የኦነግ የወታደራዊ ክንፉን ለማለት ይመስለኛል። 

ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በደንብ አድርጎ መርምሮ እነዚህን ድርጅቶች እራሳቸውን እንዲከላከሉ እድል ሰጥቶ ሽብርተኛ ድርጅት ነው የሚለውን ስያሜ ሊሰጥ ይችላል።

ውሳኔው በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚፀድቅ ከሆነ በተለይ ህወሓት በትግራይ ፣ ሸኔ በኦሮሚያ መሰረታቸውን ያደረጉበት ህዝብ ላይ እንግልት እንዳይኖር ፍርድ ቤቶች ከፍተኛ ኃላፊነት ይጠብቃቸዋል።"

• ስማቸውን ያልተገለፀ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁር :

“በሽብርተኝነት ሊፈረጅ የሚችል አካል ለቁጥጥር ያስቸገረ ጠንካራ መዋቅር ያለው ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ መከላከያው ጭምር ህወሓት ስጋት ሊሆን በማይችልበት ደረጃ መመታቱን እና መዳከሙን ደጋግመው በአደባባይ በተናገሩ ማግስት እንዲህ መባሉ ምን ለማለት ተፈልጎ ነው የሚል ጥያቄ ያስነሳል።

‘አጥፍተነዋል’ በሚል ሲነገር የነበረው ፕሮፓጋንዳ እንደነበር እና ህወሓት አሁንም ስጋት እንደሆነ የሚያሳይ ነው። የመንግስትን ተዓማኒነት 'ይበልጥኑ የሚጎዳ' ነው።

• የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግ እና ፌደራሊዝም መምህሩ ዶክተር ሲሳይ መንግስቴ :

“ውሳኔ እንዲያውም ቢዘገይ እንጂ የሚጎዳ አይደለም።

ህወሓትን ሽብርተኛ ብሎ ለመፈረጅ በሰሜን እዝ ላይ ያደረሰው ጉዳት ብቻ በቂ ነው።

ህወሓት ባለፉት 3 ዓመታት በግልጽና በስውር በርካታ ጥፋቶችን አድርሷል። የዘገየ ግን ትክክለኛ የውሳኔ ሀሳብ ቀርቧል።

መንግስት በውሳኔ ሃሳቡ ኦነግ ሸኔ ከማለት ይልቅ ‘ሸኔ’ ማለቱ ምናልባት ለሌላ ትርጉም እንዳይጋለጥ በማሰብ ሊሆን ይችላል እንጂ ‘ሸኔ’ በሚል በኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናትን እና ሌሎች በክልሉ የሚኖሩ ማንኛውንም ማህበረሰብ እንደፈለገ እየገደለ ነው ይሄንን የሚያደርገው ደግሞ "ኦነግ ሸኔ" ነው።

ያንብቡ 👇
https://telegra.ph/SHANE--TPLF-05-03

#AL_AIN #Deutsche_Welle #SolomonMuchie #HoPR
"...የአውሮፓ ህብረት ለቀጣዩ ምርጫ ታዛቢዎችን ለመላክ ያደረገው ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል" - ጆሴፍ ቦሬል

የአውሮፓ ሕብረት ከመንግሥት ጋር ስምምነት ባለመደረሱ የምርጫ ታዛቢ የመላክ እቅዱን መሰረዙን ገልጿል።

የአውሮፓ ሕብረት ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ከስምምነት መድረስ ባለመቻለሁ ወደ ኢትዮጵያ ለመላክ አስቦ የነበረውን የምርጫ ታዛቢ እንዲቀር መወሰኑን ትላንት ይፋ አደርጓል።

የሕብረቱ የውጪ ጉዳዮች እና የደህንነት ፖሊሲ ከፍተኛ ተወካይ የሆኑት ጆሴፍ ቦሬል፤ የአውሮፓ ሕብረት ለቀጣዩ ምርጫ ታዛቢዎችን ለመላክ ያደረገው ጥረት ሳይሳካ መቅረቱን ነው ያሳወቁት።

ህብረቱ የምርጫ ታዛቢ ልዑክ ለመላክ ከፍተኛ ጥረት ቢያደረግም ከኢትዮጵያ መንግሥት ባለስልጣናት ጋር የአውሮፓ ሕብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን የሚሰማራበት ቁልፍ መለኪያዎች /ፓራሜትርስ/ ላይ ከስምምነት መድረስ አልተቻለም ብለዋል።

በዚህም ሕብረቱ ግንቦት 28 በሚደረገው ምርጫ ላይ ታዛቢ ልዑክ ላለመላክ መወሰኑን ይፋ አድርጓል።

የአውሮፓ ሕብረት የዲሞክራሲ ግንባታ ድጋፍ ዋናው ምሰሶ የምርጫ ታዛቢ ልዑክ ትክክለኛነት ነው ብሏል። ሕብረቱ የምርጫ ታዛቢ ልዑኩን ለመላክ ያቀረባቸው መስፈርቶች እንዳይሟሉ መከልከሉ አሳዝኖኛል ሲል አክሏል።

ሕብረቱ ያልተሟሉ መስፈርቶች ያላቸው የምርጫ ታዛቢው ልዑክ ገለልተኝነት ማረጋገጥ አለመቻሉ እና ልዑኩ የራሱን መገናኛ ስርዓቶች ወደ አገር ማስገባት አለመቻሉ ናቸው።

ሕብረቱ የጸጥታ ስጋት ባለበት አከባቢ ልዑኩ የግንኙነት ስርዓቶቹን መጠቀሙ የታዛቢዎቹን ደህንነት ለማረጋገጥ ቁልፍ ሚና አለው ብሏል።

ምንጭ፦ telegra.ph/BBC-News-Agency-05-04

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
* Update

የሀገር መከላከያ ሰራዊት ክስ መሰርትባቸዋለሁ ያላቸው ነቢይ ኢዩ ጩፋ በዛሬው ዕለት ባሰራጩት የ18 ደቂቃ ቪድዮ በእሳቸው ጉዳይ ትላንት ይፋ በሆነው መረጃ ላይ ምላሽ ሰጥተዋል።

ከሰጡት የቪድዮ ምላሽ ላይ የተወሰኑት :

- ፕሮግራሙ ከአንድ ወር በፊት የተለቀቀ ነው።

- የመከላከያ ልብስ የለበሱ ፣ አባልም የሆኑ ዩኒፎርማቸውን ለብሰው በአዲስ አበባ ክራይስት አርሚ ኢንተርናሽናል ቸርች ማንኛውም ሰው እንደሚገኝ ነው የተገኙት።

- ሲመጡ የመከላከያ ልብስ ፣ወይም ዩኒፎርም ለብሳችሁ ኑ ተብሎ የተጠሩ ሰዎች አይደሉም።

- አባላቱ ተደውሎላቸው የመጡ ሰዎች አይደሉም።

- ዩኒፎርም ለብሰው እንዲመጡ የተሰጠ ትዕዛዝ የላቸውም።

- በዕለቱ እንደሚመጡ አናውቅም፤ ስራችን ህዝቡን የምናገለግልበትን ቸርች ከፍተን መጠበቅ ነው። ስራችን የመጣውን ህዝብ ማገልገል ነው።

- ወታደሮቹ እኛ ጋር መጥተው የሰሩት ወንጀል የለም፤ አለ ከተባለ ተቋሙ ባስቀመጠው አቅጣጫ ሊጠየቁ ይችላሉ።

- ነቢይ እዩ ይከሰሳል የሚለው ጉዳይም ፥ ለአንዳድን ሰው የተለየ ህግ ካለ ሊሆን ይችላል፤ የተለየ ህግ ካለ የሚያስከስስ አይደለም። በምን አይነት አግባብ ሊያስጠይቅ የሚያስችል እውነት የለም።

- ከእነሱም በፊት የመከላከያ ልብስ የለበሱ ሰዎች ይገባሉ፣ ይገለገላሉ።

Video : 27 MB
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
* Update

የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች ልዩ መልዕክተኛ ጄፍሪ ፊልትማንወደ ግብፅ፣ ኤርትራ፣ ኢትዮጵያ እና ሱዳን የሚያደርጉትን ጉዞ ዛሬ ይጀምራሉ።

ጉዟቸው ከዛሬ ሰኞ ሚያዚያ 26 ቀን 2013 ዓ/ም የሚጀምር ሲሆን ለ9ኝ ቀናት ይቆያል ተብሎ ይጠበቃል።

በአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የተሰየሙት ልዩ መልዕክተኛው ፊልትማን የትግራይን ጦርነት ጨምሮ በሕዳሴው ግድብ በሱዳንና በኢትዮጵያ የድንበር ውዝግብ ዙሪያ መፍትሄ የማፈላለግ ተልዕኮ ተሰጥቷቸዋል።

በዚህ ጉዟቸውም በትግራይ ቀውስ እና በሌሎች ክፍለ አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ።

በሱዳን፣ ግብፅ፣ ኤርትራ እና ኢትዮጵያን ጉብኝንታቸው ከየሀገራቱ ባለስልጣናት ጋር የመነጋገር መርሀ ግብር አላቸው።

ልዑኩ በትግራዩ ቀውስ ዙሪያ ግጭት ቆሞ ሰላማዊ መፍትሄ እንዲፈለግ እስከ ድርድር የሚደርስ ሀሳብ እንዳላቸው በስፋት እየተነገረ ነው የሚገኘው።

በአዲስ አበባ ከአፍሪቃ ህብረትና ከመንግስታቱ ድርጅት ሀላፊዎች ጋር ውይይት እንደሚያደርጉም መገለፁን ዋዜማ ሬድዮ ድረገፅ የአሜሪካ የወጪ ጉዳይ መስሪያ ቤትን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

ጄፍሪ ፊልትማን አንጋፋ ዲፕሎማት ሲሆኑ የመንግስታቱ ድርጅት የፖለቲካና የፀጥታ አማካሪ በመሆን ስርተዋል። በመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት በተለይም በሶሪያና ሊባኖስ ጦርነት ቆሞ ሰለም እንዲመጣ በተደረጉ የዲፕሎማሲ ጥረቶች ዋና ልዑክ በመሆን አገልግለዋል።

@tikvhaethiopia @tikvahethiopiaBOT
#Bishoftu

ዛሬ ቢሾፍቱ በሚገኘነው የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኮሌጅ የባህር ኃይል አርማ፣ የትከሻ ምልክትና የደንብ ልብስ ይፋ ተደርጓል።

በሥነሥርዓቱ ላይ የመከላከያ ጠ/ኤታማዥር ሹም ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ፣ የባህር ኃይል ዋና አዛዥ አድሚራል ክንዱ ገዙና ጥሪ የተደረገላቸው የውጭ አገራት አታሼዎችና ከፍተኛ የጦር መኮንኖች መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

አርማው ቀይ፣ ነጭና ቢጫ ቀለማትን ሲይዝ፣ ቀዩ መስዋእትነት እና ዝግጁነትን ፣ ነጩ ሰላም ፣ እውቀት፣ ላብና የመለያ ክብርን እንዲሁም ቢጫው ለሀገርና ለህዝቦች መጪው ጊዜ የብሩህ ተስፋ ዘመን መሆኑን የሚያመላክት መሆኑ ተገልጿል።

በአርማው ላይ የባህር ኃይል ዓለምአቀፍ ምልክት የሆነው መልህቅ እና በቀላሉ የማይበገር የባህር ኃይል በተሰማራበት ቀጠና ላይ የሚሰጠውን ግዳጅ በብቃትና በጥንካሬ እንደሚወጣ የሚያሳየው የወይራ ዘለላ ተቀምጦበታል።

በአርማው ላይ ያለው ሰማያዊ መደብ ባህር ኃይሉ ተልዕኮውን የሚወጣው በባህርና በውቅያኖስ ላይ መሆኑን ሲያሳይ ሰንደቅ አላማው ደግሞ ለሀገርና ለሰንደቅ አላማ ዘብ መቆምን ያሳያል ተብሏል።

ዛሬ ይፋ የተደረገው የባህር ኃይል አርማ በጠቅላይ መምሪያው ፣ በመርከቦች እና በተለያዩ የህትመት ውጤቶች ላይ ጥቅም ላይ እንደሚውል መገለፁን የኢዜአ ዘገባ ያስረዳል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
* አነጋጋሪው የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ ! [ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ] በታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ድርድሮችና ሁለቱ አገሮች በይገባኛል በሚወዛገቡባቸው የድንበር ጉዳዮች የኢትዮጵያ ባለስልጣናት የሚያቀርቧቸው መከራከሪያዎች መልሰው ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ላይ የሉዓላዊነት ጥያቄ እንደሚያስነሱ ሱዳን አስጠንቅቃለች። የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትላንት ዕኩለ ለሊት ገደማ ባወጣው መግለጫ፤…
#Update

"ሱዳን ሰምኑን ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የእኔ ነው ማለቷ አሳፋሪ ነው" - አምባሳደር ዲና ሙፍቲ

ሱዳን ከቀናት በፊት ላወጣችው መግለጫ ኢትዮጵያ ምላሽ ሰጥታለች።

ሱዳን ሰምኑን ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የእኔ ነው ማለቷ አሳፋሪ ነው ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ አስታውቀዋል።

አምባሳደር ዲና ዛሬ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በወቅቱ የሱዳን ባለስልጣናት የህዳሴ ግድብ የሚገኝበትን የቤኒሻንጉል አካባቢ በተመለከተ የእኛ ነው የሚል መረጃ መልቀቃቸው አስነዋሪ ነው ሲሉ ተችተውታል።

የሱዳን ወታደሮች ድንበር አልፈው የኢትዮጽያን አርሶአደሮች ማፈናቀላቸው ሳያንስ እንዲህ አይነት መረን የወጣ መረጃ መልቀቃቸው የሚኮነን ነው።

የኢትዮጵያ መንግስትም ተገቢውን ምላሽ ይሰጣል ሲሉ አስታውቀዋል።

በዚሁ መግለጫ ላይም አምባሳደር ዲና እንደገለፁት ፤ ሱዳኖች የሚያወጡት መግለጫ ያለአግባብ የተለጠጠ እና አለም አቀፍ ህግጋትንም ያላከበረ ነው ብለውታል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#AddisAbabaCOVID19

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ በአዲስ አበባ ከተማ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቀነስ የህዝብ ትራስፖርት የሚሰጡ ተሸከርካሪዎች የመጫን አቅማቸውን እንዲቀንሱ የሚያስገድድ መመሪያ መዘጋጀቱን ይፋ አድርጓል።

አዲሱ መመሪያ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን ቢሮው አስታውቋል፡፡

የቢሮው ኃላፊ ኢ/ር ስጦታው አከለ ዛሬ በሰጡት መግለጫ አዲሱን መመሪያ በተመለከተ ተከታዮቹን መረጃ ሰጥተዋል ፦

- በአዲሱ መመሪያ መሰረት ተሽከርካሪዎች የሚቀንሱበት መጠን ይለያያ አንጂ ሁሉም አይነት የህዝብ አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎች የተሳፋሪ ቁጥር ይቀንሳሉ።

- በኢዲሱ መመሪያ መሰረት ታክሲዎች በወንበር ሙሉና እና ከኋላ 3 ሰውና ሃይገሮች (ቅጥቅጦች) በወንበር ልክና ተራርቀው የሚቆሙ 5 ሰዎች እንዲጭኑ ታዟል።

- ባሶች ከዚህ በፊት ከሚጭኑት በ50 በመቶ ቀንሰው እንዲጭኑ።

- የተሽካርካሪዎች የመጫን አቅም ዝቅ ቢልም በታሪፍ ላይ የተለየ ጭማሪ አይኖርም።

- የመመሪያውን ተፈጻሚነት የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ባለስልጣንና የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ቢሮ ይቆጣጠራሉ።

- ይህን መመሪያ ተላልፈው በሚገኙ አሽከርካሪዎች ላይ ከ500 እስከ 5ሺ የሚደርስ ቅጣት ይጠብቃቸዋል።

ምንጭ፦ አል ዓይን ኒውስ
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT