#BREAKING
ዛሬ ሚያዚያ 23 ቀን 2013 ዓ/ም የሚንስትሮች ምክር ቤት ባካሄደው ስብሰባ የ "ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት)" እና "ሸኔ" ድርጅቶች #በሽብርተኛ ድርጅትነት እንዲሰየሙ የውሳኔ ሐሳብ ማቅረቡ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት አስታውቋል።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT

የሚኒስትሮች ም/ቤት 👆
የሚንስትሮች ምክር ቤት ዛሬ 'ሕወሓት' እና 'ሸኔ' ድርጅቶች በሽብርተኛ ድርጅትነት እንዲሰየሙ የውሳኔ ሐሳብ አቅርቧል።
የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት በጉዳዩ ላይ ከላይ ያለውን ዝርዝር መግለጫ ሰጥቷል።
በተጨማሪም መንግለጫውን በዚህ ማስፈንጠሪያ ማንበብ ትችላላችሁ https://telegra.ph/PM-Office-05-01
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

"...በዓላትን ስናሳልፍ የተቸገሩትን ወገኖች በመደገፍ እና በመከባከብ ይሁን" - ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ
"ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ" ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ለብርሃነ ትንሳኤው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላልፈ ሲሄን በዓሉ የሰላም፣ የፍቅርና የደስታ እንዲሆን ምኞቱን ገልጿል።
ሜሪ ጆይ በላከልን የበዓል መልዕክት ፥ ሁላችንም በዓላትን ስናሳልፍ የተቸገሩትን ወገኖች በመደገፍና በመከባከብ እንዲሆን አደራ ብሏል።
ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያን ለማግኘት የተቸገሩ ወገኖችን ለማገዝ እና ለመደገፍ በነዚህ ስልክ ቁጥሮች ልትደውሉ ትችላላችሁ : 0987626262/ 0983636363/ 0911208518
“ሁሌም ስሰጥ የምቀበለው አለ”

የበዓል ገበያ በኩዊንስ ሱፐር ማርኬት :
የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ አካል የሆነው ኩዊንስ ሱፐርማርኬት ለበዓል የሚሆኑ ግብዓቶችን ተመጣጣኝ በተባለ ዋጋ ለህዝቡ እያቀረበ ነው።
ለትንሳኤ በዓል ቅድመ ዝግጅት ሲያደርግ የከረመው ኩዊንስ ሱፐር ማርኬት ለበዓል አስፈላጊ ናቸው የተባሉ ግብዓቶችን በበቂ ሁኔታ እና በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ ለህዝቡ ተደራሽ እያደረገ ይገኛል።
እንደማያሳያነት :
- 58 ሺህ በህይወት የሚሸጡ ዶሮዎችን ያቀረበ ሲሆን ወንድ ዶሮ 350 ብር ፤ ሴት ዶሮ ደግሞ 300 ነው እየተሸጠ ያለው።
- ስጋ ፦ የበሬ ፣ የበግ እና የፍየል ስጋ ያቀረበ ሲሆን የበግ 250 ብር ፣ የበሬ 340 ብር (ንቅል) ፤ የወጥ 303 ብር ፣ ጎድን 110 ብር ነው እየተሸጠ ያለው።
- እንቁላል 4.50 ነው የሚሸጠው።
- ሽንኩርት 10 ብር ነው እየተሸጠ የሚገኘው።
- ቅቤ ፣ አይብ ፣ ዱቄት ተመጣጣኝ በሚባል ዋጋ ነው ድርጅቱ ያዘጋጀው።
ድርጅቱ የተለያዩ ለበዓል አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረቡን ሸማቾች የተናገሩ ሲሆን ውጭ ካለው ገበያ በተሻለ እና ርካሽ በሆነ ዋጋ ማግኘት እንደቻሉ ገልፀዋል።
ድርጅቱም ለበዓል ምንም አይነት ዋጋ ጭማሪ እንደማያደርግ ይልቁንም ለበዓል ቅናሽ አድርጎ እንደሚሸጥ ከኤፍ ቢ ሲ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

TIKVAH-ETHIOPIA
ሞቃዲሾ ውስጥ ውጥረት ነግሷል። የፕሬዜዳንቱ የስልጣን ጊዜ መራዘሙን የሚቃወሙ ተቃዋሚ ኃይሎችን በሚደግፉት /የፕሬዜዳንቱን የስልጣን ዘመን መራዘም በሚቃወሙት እና ለፕሬዜዳንቱ ታማኝ በሆኑ የመንግስት ወታደሮች መካከል ግጭት መፈጠሩ ተሰምቷል። በሳንአ እና ፋግአህ አካባቢ የተኩስ ልውውጦች ሲደረጉ ተሰምቷል። በምስራቅ ሞቃዲሾ ክፍል በሚገኘው ፋግአህ የመንግስት ተቃዋሚዎች ጎማዎችን ሲያቃጥሉ ታይተዋል። …
#Update
የተራዘመው የፕሬዜዳንቱ የስልጣን ጊዜ ተሰረዘ።
በዛሬው ዕለት የሶማሊያ የታችኛው ምክር ቤት ከወር በፊት አራዝሞት የነበረውን የፕሬዜዳንት ሞሀመድ ፋርማጆን የ2 ዓመት የስልጣን ጊዜ ሰርዞታል።
የሶማሊያ ፓርላማ አባላት የተራመዘመው የፕሬዜዳንቱ የስልጣን ጊዜ እንዲሰረዝ በሙሉ ድምፅ መወሰናቸው ተሰምቷል።
የፓርላማውን ውሳኔ በርካቶች እያወደሱት ይገኛሉ፤ ለሱማሊያ ሰላም ሆኖ መቀጠል የምርጫው መደረግ አስፈላጊነት እጅግ ወሳኝ መሆኑን እያነሱ ነው።
ውሳኔው ከጥቂት ቀናት በፊት በሞቃዲሾ ከተማ የተቀሰቀሰውን ግጭት እንዲሁም አሁን ላይ ያለውን ውጥረት እንዲያበቃ ያደርጋል ተብሎ ታምኗል።

ዶ/ር አሸብር ወ/ጊወርጊስ የአኖካ የዞን 5 ፕሬዝደንት ሆነው ተመረጡ።
11 አባል ሀገራት ያሉት የአፍሪካ የዞን 5 ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማህበር ዛሬ ባካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ ለፕሬዝደንትነት ኢትዮጵያ እና ግብፅ ለመጨረሻው ምእራፍ ደርሰው #ኢትዮጵያ 7 ድምፅ በማግኘት የፕሬዝደንትነት ቦታውን ተረክባለች።
የኢትዮጵያ ተቀናቃኝ የነበረችው #ግብፅ 3 ድምፅ ማግኘቷ ታውቋል።
በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝደንት ዶክተር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ የዞን 5 የአፍሪካ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማህበር ፕሬዝደንት ሆነው ተመርጠዋል።
ይህንም ተከትሎ ኢትዮጵያ በአኖካ (የአፍሪካ ኦሊምፒክ ኮሚቴዎች ማህበር) ላይ የስራ አስፈፃሚ አባልነት ቦታን ታገኛለች ተብሏል።
መረጃው የፌዴራል ስፖርት ኮሚሽን ነው።

"...ችግሩ የተፈጠረው ሰልጥነው ስራ ያልጀመሩ እና የጀመሩ አስፈፃሚዎችን ለመለየት ጊዜ በመውሰዱ ነው" - ወ/ሪት ሶሊያና ሽመልስ በምርጫ አስፈፃሚነት እየሰሩ ያሉ የምርጫ አስፈፃሚዎች ከክፍያ ጋር በተያያዘ ባለፉት ቀናት በርካታ ጥያቄዎችን እያነሱ ይገኛሉ። ጥያቄያቸውም "ክፍያ አልተከፈለንም" የሚል ነው። በጉዳዩ ዙሪያ የፅሁፍ መልዕክት ያስቀመጥንላቸው የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር…
"...ለ67,405 የምርጫ አስፈጻሚዎች ክፍያ ተፈፅሟል" - ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ከምርጫ አስፈፃሚዎች ጋር በተያያዘ ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል።
ቦርዱ ለ6ተኛው አጠቃላይ ምርጫ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ምርጫ አስፈጻሚዎችን በመቅጠር የምርጫ ስራን እያስፈጸመ እንደሆነ አስታውሷል።
በሂደቱ ካጋጠሙት ችግሮች መካከል አንዱ የሆነው የምርጫ አስፈጻሚዎች ክፍያ መዘግየት መሆኑን አንስቷል።
ቦርዲ ፥ በተለያየ ወቅት የተለያዩ ክፍያዎች ሲደረጉ ቢቆዩም ከአስፈጻሚዎች በኩል ቅሬታ ሲያስነሳ የነበረ ጉዳይ መሆኑ አልቀረም ብሏል።
የክፍያዎቹ መዘግየት ችግር ስልጠና ከወሰዱ አስፈጻሚዎች መካከል ስራ ያልጀመሩ በመኖራቸው እንዲሁም ስልጠና ሳይወስዱ በስራ ላይ የተሰማሩ በመገኘታቸው ትክክለኛው ሂደት ተከትለው ወደስራ የተሰማሩ አስፈጻሚዎችን መለየት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ መሆን ነው ሲል አስረድቷል።
እነዚህን ልዩነቶች የታዮባቸው ቦታዎችን ለመለየት እና የኮንትራት ማጣራት ማድረግ ጊዜ መፍጀቱን ገልጿል።
በዚህ ሳምንት ይህንን ችግሩን ለመፍታት በተደረገ ጥረት ለ67,405 የምርጫ አስፈጻሚዎች ክፍያ ለመፈጸም መቻሉን አሳውቋል።
በክልል/ከተማ መስተዳድር ደረጃ ሲታይ ፦
1. ኦሮሚያ - 15,758
2. አማራ -28,950
3. ሲዳማ - 6,257
4. አዲስ አበባ - 4,890
5. ድሬዳዋ - 792
6. ደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች - 15,326
7. ጋምቤላ- 1,114 አስፈጻሚዎች ክፍያ ተፈፅሞላቸዋል።
በቀሩት ክልሎች እና በከፊል ክፍያ የተፈጸመባቸው ቦታዎች የሚገኙ አስፈጻሚዎችን ክፍያ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት እንደሚጠናቀቅም ገልጿል።
ቦርዱ በሂደቱ ለተፈጠረው መጉላላት አስፈጻሚዎችን ይቅርታ ጠይቋል።
@tikvahethiopia

ዛሬ ሰመራ ላይ የተደረገው የፓናል ውይይት :
በአፋርና በሶማሌ መካከል ያለውን ግጭት ብዥታዎችን በታሪክ መነፀር ለማጥራት በሚል የተዘጋጀ የፓናል ውይይት መድረክ ዛሬ በአፋር መዲና ሰመራ ተካሂዷል።
በመድረኩ ላይ የአገር ሽማግሌዎች ፣ ምሁራን ፣ ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ፣ ወጣቶች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ተሳትፈውበታል።
በፓናል ዉይይቱ ላይ፦
- አቶ ጀማል አበበ
- አቶ ሀቢብ መሓመድ
- አቶ መሓመድ አህመድ ያሲን ጥናታዊ ፅሁፍ አቅርበዋል።
የመድረኩ አዘጋጅ የነበረው Association of Afar Intellectual ነበር።
መረጃውን በፎቶ አደራጅቶ የላከልን የቤተሰባችን አባል Acmad Dalol Abu Jaefar ከአፋር ሰመራ ነው።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopiaBOT

'የትንሳኤ ሎተሪ ወጣ'
ትንሳኤ ሎተሪ ቅዳሜ ሚያዝያ 23/ 2013 ዓ.ም በብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ዕድል አዳራሽ ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ላይ በህዝብ ፊት ወጥቷል፡፡
በዚህም መሰረት የወጡት የአሸናፊ ዕጣ ቁጥሮች እንደሚከተሉት ሆነዋል ፦
1ኛ. 5,000,000 ብር የሚያስገኘው የ1ኛ ዕጣ ቁጥር 0148806
2ኛ. 2,500,000 ብር የሚያስገኘው የ2ኛ ዕጣ ቁጥር 0418875
3ኛ. 1,250,000 ብር የሚያስገኘው የ3ኛ ዕጣ ቁጥር 0779594
4ኛ. 600,000 ብር የሚያስገኘው የ4ኛ ዕጣ ቁጥር 1653940
5ኛ. 300,000 ብር የሚያስገኘው የ5ኛ ዕጣ ቁጥር 0100008
6ኛ. 150,000 ብር የሚያስገኘው የ6ኛ ዕጣ ቁጥር 0380649
7ኛ. 100,000 ብር የሚያስገኘው የ7ኛ ዕጣ ቁጥር 0232719
8ኛ. 17 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 3,000 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 58185
9ኛ. 17 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 1,500 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 49566
10ኛ. 170 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 600 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 7679
11ኛ. 170 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 300 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 5709
12ኛ. 170 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 150 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 3085
13ኛ. 1,700 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 120 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 819
14ኛ. 1,700 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 90 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 106
15ኛ. 17,000 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 45 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር 46
16ኛ. 170,000 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው ብር 30 የሚያስገኘው ዕጣ ቁጥር (የማስተዛዘኛ ዕጣ) ደግሞ 7 ቁጥር በመሆን ወጥቷል፡፡
(ብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር)

"... የክልሉን ሰላም የበለጠ ሙያ እና ልምድ ባላቸው ሰዎች መምራት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ነው አዳዲስ የፀጥታ ኃላፊዎች የተሾሙት" - ወይዘሮ ህሊና መብራቱ
[ በዶቼ ቨለ ]
የአማራ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት የክልሉን የፀጥታ ኃላፊዎች በአዲስ ተክቷል።
• አቶ ሰማ ጥሩነህ - በም/ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የሰላምና የህዝብ ደህንነት ቢሮ ሃላፊና የመልካም አስተዳደር ክላስተር አስተባባሪ፣
• ኮሚሽነር ተኮላ አይፎክሩ - የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር
• ኮሎነል ባምላኩ አባይ በቢሮ ሃላፊ ደረጃ የአማራ ክልል ሚሊሻ ፅ/ ቤት ሃላፊ ሆነው ተሹመዋል።
ከነበሩበት ስልጣን የተነሱት ፦
- የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ አበረ አዳሙ ፣
- የአማራ ክልል የሰላምና ህዝብ ደህንነት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሲሳይ ዳምጤ
- የአማራ ክልል ሚሊሺያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መኳንንት መልካሙ ናቸው፡፡
አዳዲስ አመራሮችን ለምን መተካት እንዳስፈለገ ቃላቸውን ለዶቼ ቨለ የሰጡት የክልሉ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ምክትል ዳይሬክተር ወይዘሮ ህሊና መብራቱ ፥ "የክልሉን ሰላም የበለጠ ሙያ እና ልምድ ባላቸው ሰዎች መምራት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ነው አዳዲስ የፀጥታ ኃላፊዎች የተሾሙት" ብለዋል።
የቀድሞዎች የተቋማቱ አመራሮች የት እንደተመደቡ ግን ወ/ሮ ህሊና አልገለፁም፡፡
መስተዳድር ምክር ቤቱ ከዚህ ለአማራ ክልል ሥነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን እንዲሁም ለአማራ ክልል ፍትህ ማሰልጠኛና ህግ ምርምር ኢንስቲትዩት ኃላፊዎችን ሾሟል።

"...ይህ አድማ ምን ያክል እንደመረረን የሚያሳይ ነው" - ሳንጃይ ባንዳሪ
የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ፣ እንግሊሽ ፉትቦል ሊግ እንዲሁም የሴቶች ሱፐር ሊግ ክለቦች ለአራት ቀናት ከማሕበራዊ ሚዲያዎች ራሳቸውን አግልለዋል።
አድማውን የጀመሩት ትላንት ሚያዚያ 22 ጀምሮ ሲሆን ለአምስት ቀናት ይቆያል።
ክለቦች ከዚህ ውሳኔ የደረሱት ማሕበራዊ ሚዲያዎች ላይ የሚታዩ ብዘበዛዎችና ማግለሎችን በመቃወም ነው።
የእግር ኳስ ማሕበር፣ እንዲሁም ሌሎች ይመለከተናል የሚሉ መሥሪያ ቤቶችን ጨምሮ ኪክ ኢት ኦፍ የተባለው ፀረ-ማግለል ድርጅት በዚህ አድማ ላይ እየተሳተፉ ነው።
አድማው ከመጀመሩ ከቀናት በፊግ የኪክ ኢት ኦፍ ሊቀመንበር ሳንጃይ ባንዳሪ በሰጡት አስተያየት፥ "ይህ አድማ ምን ያክል እንደመረረን የሚያሳይ ነው፤ ማሕበራዊ ሚዲያ አሁን አሁን በጣም መርዛማ ለሆኑ ብዝበዛዎች የተጋለጠ ሆኗል" ብለዋል።
አክለውም ፥ "እኛ አንድ ላይ ሆነን ይህን አድማ የምንመታው ሥልጣኑ ላላቸው መልዕክት ለማስተላለፍ ነው፤ እርምጃ እንድትወስዱ እንፈልጋለን። ለውጥ እንድታመጡ እንሻለን" ሲሉ ተናግረዋል።
ከትላንት ጀምሮ ክለቦች፣ አስተዳዳሪ አካላት እና የእግር ኳስ ዳኞች ማሕበር ከትዊተር፣ ፌስቡክና ኢንስታግራም ራሳቸውን አግልለዋል።
አድማ መቺዎች ዋነኛ ዓላማቸው የማሕበራዊ ሚዲያዎች ጥላቻን እንዲያስወግዱና ትምህርትም እንዲሰጡ መሆኑን ከቢቢሲ ያገኘነው መረጃ ይገልጻል።