ዛሬ ከባህር ዳር ወደ እንጅባራ ህገወጥ በሆነ መንገድ ሲዘዋወር ነበር የተባለ ፦
- 900 የብሬል፣
- 120 የክላሽ ጥይቶች፣
- አንድ የቱርክ ሽጉጥ እና 43 የተለያዩ ስለታማ ነገሮች በቁጥጥር ስር ማዋሉን የፋግታ ለኮማ ወረዳ ፖሊስ አስታውቋል።
ከፋግታ ኮሚኒኬሽን እንዳገኘነው መረጀ ከሆነ ከህገወጥ መሳሪያው ጋር የተያዙ ተጠሪጣሪዎችን ላይ ፖሊስ የማጣራት ስራ እየሰራ ነው።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT

"... በሲቪል ሰዎች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች ተደጋጋሚነት እና መስፋፋት የፀጥታ መዋቅሩ የመከላከልና ዝግጁነት አቅም ከፍተኛ መሻሻል ሊደረግበት እንደሚገባ ሚጠቁም ነው" - ኢሰመኮ
ኢሰመኮ በጅማ ሊሙ ኮሳ ወረዳ ፣ ቀጮ ክርክራ እና ጋሌ ቀበሌ ሚያዚያ 15 ቀን 2013 ዓ/ም በታጠቁ ኃይሎች ጥቃት መድረሱን ገልጾ ክትትል በማድረግ ላይ መሆኑን አሳውቋል።
በተመሳሳይ በደቡብ ክልል አማሮ ልዩ ወረዳ ፣ ዳኖ ቀበሌ በሚያዚያ 14 ታጣቂዎች 6 ሰዎች እንደገደሉ የአካባቢው አስተዳደር ማሳወቁን ገልጿል።
በኮሳ ወረዳ የደረሰውን አደጋ ተከትሎም በእለቱ የክልል እና የፌዴራል ፀጥታ ኃይሎች ወደ አካባቢው መሰማራታቸውን ኢሰመኮ መረዳቱን አሳውቋል።
ኢሰመኮ ከሚመለከታቸው የፌዴራል እና ክልል አካላት ተገቢውን አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጡ በቅርበት እናት ነጋጋረ መሆኑ ገልጾ ፤ የክትትል ተግባሩን እንደሚቀጥል ገልጿል።
ኮሚሽኑ ፥ ነዋሪዎች ላይ ተጨማሪ ጉዳትና የሰዎች ሞት ለመከላከል አፋጣኝ እርምጃ እንዲወሰድ ያሳሰበ ሲሆን በሲቪል ሰዎች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች ተደጋጋሚነት እና መስፋፋት የፀጥታ መዋቅሩ የመከላከል እና ዝግጁነት አቅም ከፍተኛ መሻሻል ሊደረግበት እንደሚገባ የሚጠቁም ነው ብሏል።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

#update
መንግሥት የቴሌኮሙዩኒኬሽን ዘርፉን ለውድድር ክፍት ለማድረግ ያሳለፈውን ውሳኔ ተከትሎ የኢትዮጵያ ኮሙዩኒኬሽን ባለሥልጣን ባወጣው ዓለም አቀፍ ጨረታ ከተሳተፉ የውጭ ኩባንያዎች መካከል አሸናፊ የሆኑ ሁለት ኩባንያዎች፣ ነገ ሚያዚያ 18 ቀን 2013 ዓ.ም. ይፋ እንደሚደረጉ ተገልጿል።
መንግሥት ለውድድር ክፍት ያደረገውን የቴሌኮሙዩኒኬሽን ገበያ እንዲመራና እንዲቆጣጠር ያቋቋመው፣ የኢትዮጵያ ቴሌኮሙዩኒኬሽን ባለሥልጣን ለሁለት የግል የቴሌኮም ኩባንያዎች ለአገሪቱ የመጀመሪያ የሆነውን የግል የቴሌኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ፈቃድ ለመስጠት፣ በኅዳር ወር 2013 ዓ.ም. ዓለም አቀፍ ጨረታ ማውጣቱ የሚታወቅ ነው።
ዓለም አቀፍ ጨረታው ከመውጣቱ አስቀድሞ የኢትዮጵያ ቴሌኮሙዩኒኬሽን ባለሥልጣን ወደ ኢትዮጵያ የቴሌኮሙኒኬሽን ገበያ መግባት የሚፈልጉ ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች የፍላጎት መግለጫ እንዲያስገቡ በይፋ ባቀረበው ጥሪ መሠረት፣ 12 ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች ፍላጎታቸውን መግለጻቸው ይታወሳል።
ከ12 ኩባንያዎች መካከል በቴሌኮሙዩኒኬሽን አግልግሎት ለመሳተፍ ፍላጎት ያሳዩት ዘጠኝ ኩባንያዎች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ መካከል ዓለም አቀፍ ጥምረት ለኢትዮጵያ ቴሌኮም አገልግሎት በሚል አንድ ጥላ ሥር ሆነው ፍላጎታቸውን የገለጹት ቮዳፎን፣ ቮዳኮምና ሳፋሪኮም የተባሉት እህትማማች ድርጅቶች አንድ ተብለው የሚጠቀሱ ናቸው፡፡በርካታ የዘርፉ ተንታኞች የማሸነፍም ቀዳሚ ግምት ለሦስቱ ኩባንያዎች ጥምረት ሰጥተዋል።
ከእነዚህ በተጨማሪ ኢቴሳልት፣ ኤዢያን፣ ኤምቲኤን፣ ኦሬንጅ፣ ሳዑዲ ቴሌኮም፣ ቴልኮም፣ ስኔል ሞባይልና ካንዱ ግሎባል ፍላጎታቸውን የገለጹ ታዋቂ ኩባንያዎች ናቸው።
ያንብቡ : telegra.ph/Reporter-Newspaper-04-25 [ሪፖርተር]
@tikvahethiopiaBOT

ሞቃዲሾ ውስጥ ውጥረት ነግሷል።
የፕሬዜዳንቱ የስልጣን ጊዜ መራዘሙን የሚቃወሙ ተቃዋሚ ኃይሎችን በሚደግፉት /የፕሬዜዳንቱን የስልጣን ዘመን መራዘም በሚቃወሙት እና ለፕሬዜዳንቱ ታማኝ በሆኑ የመንግስት ወታደሮች መካከል ግጭት መፈጠሩ ተሰምቷል።
በሳንአ እና ፋግአህ አካባቢ የተኩስ ልውውጦች ሲደረጉ ተሰምቷል።
በምስራቅ ሞቃዲሾ ክፍል በሚገኘው ፋግአህ የመንግስት ተቃዋሚዎች ጎማዎችን ሲያቃጥሉ ታይተዋል።
አለመረጋጋት በተከሰተባቸው የከተማው ክፍሎች የሚኖሩ ዜጎች ሰላም ፍለጋ እየሸሹ ናቸው።
Photo , Video - Abdalle Ahmed Mumin

#Update
በሞቃዲሾ የተቃዋሚ ደጋፊ በሆኑት እና የመንግስት ወታደሮች መካከል በነበረው ከባድ ግጭት የሰው ህይወት ማለፉ ተነግሯል።
እንደአካባቢው ሚዲያዎች መረጃ በፋጋህ እና ሳንአ አካባቢዎች በነበረው ከባድ ግጭት ቢያንስ ሁለት ሰዎች ሲገደሉ፥ በርካቶች ቆስለዋል።
አለመረጋጋት በተፈጠረባቸው አካባቢዎች ላይ የንግድ ተቋማት ተዘግተዋል፣እንቅስቃሴ ቋሟል፤ ሰዎች ሰላምን ፍለጋ ሸሽተዋል።
የአፍሪካ ህብረት የሰላምና ፀጥታ ምክርቤት በሶማሊያ ባለው ወቅታዊ የፖለቲካ እና ፀጥታ ሁኔታ ላይ ከቀናት በፊት ስብሰባ አድርጎ ነበር ፥ የሶማሊያ የፖለቲካ መሪዎች በሀገሪቱ ውጥረትን ከሚያባብሱ ተግባራት በመቆጠብ በአስቸኳይ ወደ ውይይት እንዲመለሱ ጥሪ አቅርቦ ነበር።
የሶማሊያ ፓርላማ ከ10 ቀን በፊት ሌሎች የፖለቲካ ሀይሎችን ባገለለ መልኩ የሀገሪቱን ፕሬዝደንትና የፓርላማውን የስልጣን ቆይታ ጊዜ ለማራዘም ያሳለፈው ውሳኔ እንዳሳሰበውም ምክር ቤቱ አስታውቋል።
የሶማሊያ ፓርላማ ያሳለፈው ውሳኔ በአውሮፓውያኑ መስከረም 2020 የሀገሪቱ የፖለቲካ ኃይሎች ምርጫ እንዲደረግ የደረሱትን ስምምነት የሚጥስ ነው ብሎታል።
የፓርላማው ውሳኔ በከፍተኛ መስዋእትነት በመክፈል የተገኘውን አንጻራዊ ሰላም እና ፀጥታን አደጋ ላይ የሚጥል መሆኑን እና የሀገሪቱን አንድነትና መረጋጋት እንዲሁም አዲስ የተጀመረውን ዴሞክራሲያዊ እና ህገ-መንግስታዊ ሂደቶች የሚጎዳ ነው ሲል ም/ቤት ስጋቱን አስቅምጦ ነበር።
በተጨማሪም አሁን ያለው የፖለቲካ ሁኔታ የሶማሊያ ፌዴሬሽንና የሀገሪቱን የፀጥታ አካላት አንድነትን ሊጎዳ ይችላል ያለው ምክር ቤቱ ፣ አልሸባብን ለማዳከም የሚሰራውን ስራም ሊያስተጓጉል እንደሚችል አሳስቦ ነበር።
መረጃው በሶማሊያ ካሉ ሚዲያዎችና ከአል ዓይን የተውጣጣ ነው።
@tikvahethiopia

ወ/ሮ ኑሪያ የሱፍ በኮቪድ-19 ህይወታቸው አለፈ።
ወ/ሮ ኑሪያ የሱፍ በኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሴቶች ህፃናት እና ወጣቶች ዳይሬክቶሬት በዳይሬክተርነት እና በብሔራዊ የሕብረተሰብ ጤና አደጋ ማስተባበሪያ ማዕከል የኮቪድ - 19 ምላሽ ማስተባበሪያ ስር ልዩ ድጋፍ ለሚሹ የማሕበረሰብ ክፍሎች በኮቪድ -19 ዙሪያ የተለያዩ ግንዛቤ ማስጨበጫና የድጋፍ ስራዎችን ለሀገራቸውና ለማሕበረሰባቸው በመስራት ላይ እያሉ በኮቪድ - 19 ቫይረስ ተይዘው የሕክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ሕይወታቸው አልፏል።
ወ/ሮ ኑሪያ የሱፍ በጤና ዘርፍ የላቀ አስተዋፅኦ ስላበረከቱም ከጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ እውቅና አግኝተው ነበር ።
የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በወ/ሮ ኑሪያ የሱፍ ህልፈት ሀዘንኑን ገልጿል።

#Ethiopia😷
ባለፉት 24 ሰዓት 20 ሰዎች በኮቪድ-19 መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል።
በተመሳሳይ ከተደረገው 6,299 የላብራቶሪ ምርመራ 1,324 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
ትላንት 2,734 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
በአጠቃላይ 252,279 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 3,551 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 192,747 ሰዎች አገግመዋል።
አሁን ላይ 1,010 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።
#Purpose

አርቲስት መስፍን ጌታቸው በኮቪድ-19 ህይወቱ አለፈ።
አርቲስት መስፍን ጌታቸው በኤካ ኮተቤ ሆስፒታል በህክምና ሲረዳ ቆይቶ በኮቪድ-19 ምክንያት በተወለደ በ50 አመቱ ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል።
አርቲስት መስፍን በርካታ የጥበብ ስራዎችን በድርሰት፣ በአዘጋጅነት እና በትወና ለአገሩ ያበረከተ ሁለገብ ባለሞያ ነበር።
በኢትዮጵያ ሬድዮ ዝነኛ የነበረው የቀን ቅኝት ድራማ ደራሲ እንዲሁም በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያገኘው የሰው ለሰው ተከታታይ ድራማ ደራሲ እና ተዋናይ ነበር።
አርቲስት መስፍን ጌታቸው የዙምራ ፊልም ፣ በመንታ መንገድ የሬድዮ ተከታታይ ድራማ ፣ ሌሎችም ስራዎችን በተለያዩ የቴሌቪዥን እና የሬድዮ ጣቢያዎች ለህዝብ ማድረስ ችሏል።
አርቲስት መስፍን ጌታቸው ባለትዳር እና የሶስት ልጆች (የሁለት ሴት እና የወንድ ልጅ) አባት ነበር።
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን

በቤንች ሸኮ ዞን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝበ ውሳኔ የምርጫ ምልክት የማስተዋወቂያ መድረክ በሚዛን አማን እየተካሄደ ነው።
Via Bench Sheko Zone
@tikvahethiopia
Via Bench Sheko Zone
@tikvahethiopia
ጋጮ ባባ ወረዳ በደረሰ ናዳ 3 ሰዎች ሞቱ።
በጋሞ ዞን ጋጮ ባባ ወረዳ በደረሰ የናዳ አደጋ የ3 ሰዎች ህይወት አለፈ።
የጋጮ ባባ ወረዳ የአደጋ ስጋት አመራር ዘርፍ ኃላፊ አቶ ኢዮብ ዳርጻ እንደገለፁት በወረዳው ላካ ቀበሌ ሚያዝያ 16/2013 ዓ.ም ከሌሊቱ 8 ሠዓት አካባቢ በጣለው ከባድ ዝናብ በደረሰ የናዳ አደጋ የ1 ወንድ እና የ2 ሴቶች ህይወት አልፏል።
በአደጋው 3 መኖሪያ ቤቶች ከሙሉ ንብረታቸው ገር የወደሙ መሆናቸውን ገልጸው 8 የቤት እንስሳት በአደጋው ሞተዋል።
በተጨማሪ በ2. 5 ሄክታር መሬት ላይ ያለ ቋሚ እና ጊዜያዊ ሰብል ላይ ጉዳት ደርሷል።
የጋሞ ዞን እርሻ እና ተፈጥሮ ሀብት ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ አንደኛ ሽናሌ በአደጋው ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የመጠለያ ሸራ፣ የአልባሳት እና የቤት ቁሳቁድ ድጋፍ ተደርጓል ብለዋል።
አደጋው በደረሰበት አከባቢ ተጨማሪ 10 ቤተሰብ ለአደጋ ስጋት ተጋላጭ በመሆናቸው መለየቱን ገልጸው ለተጎጂዎች ተጨማሪ የመጠለያ እና የምግብ ቁሳቁስ ድጋፍ እንደሚደረግ መናገራቸውን ከጋሞ ዞን ኮሚኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
በ2012 ዓ.ም ወቅቱን ባልጠበቀ ዝናብ የአስር ሰዎች ህይወት ማለፉ ይታወሳል።