TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"...በአንደኛው ሟች ኪስ ውስጥ ተጨማሪ ያልፈነዳ ቦንብ ተገኝቷል" - ፖሊስ

[አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን]

በልደታ ክ/ከተማ ለጊዜው ምክንያቱ ባልታወቀ የቦንብ ፍንዳታ የሁለት ግለሰቦች ህይወት ማለፉን የአዲስ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

ዛሬ ከቀኑ 8 ሰዓት አካባቢ ነው በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ቦታው "ከሚትሮሎጂ ፊት ለፊት"ለልማት በተዘጋጀ ቦታ ላይ በተከሰተ የቦንብ ፍንዳታ የሁለት ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ያለፈው።

በፍንዳታው አንድ ግለሰብ በፅኑ ተጎድቶ ወደ ሆስፒታል መሄዱን ፖሊስ አሳውቋል።

በልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወንጀል መርማሪ ኢንስፔክተር ዳንኤል ታፈሰ የምርመራ መዝገብ ዋቢ አድርገው ተከታዩን ማብራሪያ ሰጥተዋል ፦

"ዛሬ ከቀኑ 8 ሰዓት አካባቢ አንድ በግምት ዕድሜው ከ50 እስከ 55 የሚገመት ግለሰብ ከሁለት በተመሳይ የዕድሜ ደረጃ ላይ ከሚገኙ 2 ሴቶች ጋር እየተገፈታተረ ወደቦታው ከገባ በኋላ ፍንዳታ ተሰምቷል ጉዳት ደርሷል። የግለሰቦቹ ማንነት እና የፍንዳታው ምክንያት ለማወቅ በምርመራ ሂደት ላይ ነው።"

በሠዓቱ የአዲስ አበባ ፖሊስ እና የፌደራል ፖሊስ የቴክኒክ እና የፈንጂ አምካኝ ባለሙያዎች ቦታው ላይ ፈጥነው በመድረስ ተጨማሪ ፍንዳታ እንዳይከሰት አካባቢውን ነፃ የማድረግ ስራ መስራታቸው ተገልጿል።

ፖሊስ በአንደኛው ሟች ኪስ ውስጥ ተጨማሪ ያልፈነዳ ቦንብ መገኘቱን አሳውቋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#FDREDefenseForce

"በሰሜን ሸዋና ደቡብ ወሎ የኦሮሞ ልዩ ዞን ወረዳዎች ኮማንድ ፖስት ተቋቁሟል" - መከላከያ ሚኒስቴር

መከላከያ ሚኒስቴር ዛሬ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ በሰሜን ሸዋና ደቡብ ወሎ የኦሮሞ ልዮ ዞን ወረዳዎች ከተከሰተው የፀጥታ ችግር ጋር ተያይዞ ከክልል እና ከፌዴራል ፀጥታ ተቋማት ጨምሮ ሶስቱንም ዞኖች ያካተተ ኮማንድ ፖስት መቋቋሙን አስታውቋል።

* መከላከያ በወቅታዊ የሀገሪቱ የፀጥታ ሁኔታ ላይ ያወጣው መግለጫ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
በኮማንድ ፖስት የተጣሉ ክልከላዎች ፦

1ኛ. ከደብረ ሲና እስከ ኮምቦልቻ አዋሳኝ ወረዳዎች መንገድ ላይ ከመንገዱ ግራ እና ቀኝ እስከ 20 ኪ/ሜ ውስጥ የጦር መሳርያ ይዞ መንቀሳቀስ በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

2ኛ. መንገድ መዝጋትን ጨምሮ የእምነት ተቋማትን ፣ የመንግስት ተቋማትን የግለሰብ መኖርያ ቤትንና ንብረት ማውደም ወይም ለዚህ ተግባር በተናጥልም ይሁን በቡድን መንቀሳቀስ በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡

ከላይ የተዘረዘሩትን እንዲሁም በቀጣይ በኮማንድ ፖስቱ በኩል ለህብረተሰቡ የሚገለጹ ክልከላዎችን ተላልፎ የተገኘ የፖለቲካ ድርጅት የመንግስት መዋቅር እና በድኖች ላይ ህጋዊ እርምጃ ይወሰድበታል።

ሀገር መከላከያ ሰራዊት
ሚያዚያ 10 ቀን 2013

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
በአንድ ቀን 42 ሰዎች በኮቪድ-19 ሞቱ።

ባለፉት 24 ሰዓት 42 ሰዎች በኮቪድ-19 መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል።

በተመሳሳይ ከተደረገው 7,312 የላብራቶሪ ምርመራ 1,792 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

ትላንት 610 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

በአጠቃላይ 242,028 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 3,370 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 179,315 ሰዎች አገግመዋል።

አሁን ላይ 1,028 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

@tikvahethiopia
የሚያዚያ ወር ሲታወስ ፦

የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት በሀገራችን በተለይ በማህበራዊ ሚዲያ የተንሰራፋውን የእርስ በእርስ ጥላቻ በማውገዝ ፥ ከዛሬ 2 ዓመት በፊት በዚህ ወር ነው የፀረ ጥላቻ ንግግር ንቅናቄ/ የሰላም ጉዞውን አንድ ብለው የጀመሩት።

ሁሉም አባላት የሀገራቸው ሁኔታ ያሳሰባቸውና በዚሁ በቲክቫህ ውስጥ የተሰባሰቡ ነበሩ።

ያለምንም ድጋፍ ንቅናቄው ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ በየሳምንቱ አርብ ፣ ቅዳሜ እና እሁድ እጅግ አድካሚ የነበሩ ጎዞዎችን ወደ ትግራይ ፣ ኦሮሚያ ፣ አማራ ፣ ደቡብ ...ክልሎች በማድረግ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን በጥቂቱ ለመስራት ተችሏል።

በተጨማሪ በወቅቱ ሰፊ የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ተደርጓል።

ዛሬ የምናወጣት ክፉ ቃል ነገ የሰዎችን ህይወት ልታሳጣ ትችላለች እና ዘውትር ንግግራችን ሰዎችን ከመዝለፍ ፣ ከመስደብ ፣ ከማንቋሸሽ ፣ በማንነታቸውና በአመለከታቸው ከመሳደብ መቆጠብ እንደሚገባ ያስገነዘብንበት ነበር።

የፖለቲካ ሰዎች እና ድርጅቶች እንዲሁም አክቲቪስቶች የሚሰሯቸው ስራዎች የሚነዙት ጥላቻ ፣ የማህበራዊ ሚዲያዎች ተጠቃሚዎች በማወቅ ይሁን ባለማወቅ የሚያሰራጩት የጥላቻ መልዕክት ምንም ፖለቲካ የማያውቁ /ንቁ ተሳትፎ የሌላቸው ፣ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ምን እየሆነ እንዳለ እንኳን በቅጡ የማያውቁ ንፁህ ዜጎችንህ ህይወት የሚቀጥፍ እንደሆነ ለማስገንዘብ ተሞክሯል።

በእጅጉ በተበላሸው ፖለቲካ ምክንያት የሰዎች ህይወት እያለፈ እንደሆነ ለሀገሪቱ የፖለቲካ ችግር መፍትሄ ይፈለግ ዘንድ ፣ ሁሉም ወገን ቁጭ ብሎ በመነጋገር በሀገሪቱ ያንዣበበውን አደገኛ ሁኔታ እንዲቀለብሱ /ይህን ማድረግ ካልቻሉ እጃቸውን ከኢትዮጵያ ላይ እንዲያነሱ የሚያስገነዝብ ዘመቻ ነበር።

በ2012 በኮቪድ ምክንያት እንቅስቃሴ ማድረግ አልተቻለም።

@tikvahethiopia
#Update

የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ታደሰ ገብረፃድቅ ዛሬ ጥዋት ከሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተከታዮቹ መረጃዎች ሰጥተወል ፦

- አጣየ እና አካባቢው ስጋት ቢኖርም ትላንት እና ዛሬ አንፃራዊ ሰላም/መረጋጋት አለ/የተኩስ ድምፅ የለም።

- ከሸዋሮቢት ወጥተው የነበሩ ዜጎችም እየተመለሱ ነው።

- በአጣየ ከተማ የደረሰው ውድመት ከፍተኛ በመሆኑ ነዋሪው ከመመለሱ በፊት ዳግም ጥቃት እንደማይከሰት ዋስትና ስለመኖሩ ከሚመለከታቸው አካላት ውይይት ይደረጋል ተብሏል።

- በአብዛኛው ከተቃጠለችው እና ከወደመችው አጣየ ከተማ ፣ ከሸዋሮቢት የሸሹ ዜጎች በደብረብርሃን፣ መሀል ሜዳ፣ የተለያዩ የገጠር ቀበሌዎች ተጠልለዋል።

- ከአጣየ ከተማ ጥቃት የሸሹ በርግቢ፣ ይምሎ፣ መሀልሜዳ በሚባሉ አካባቢዎች ብቻ ከ10 ሺህ - 15 ሺህ ዜጎች ይገኛሉ።

- በአጣየ በርካታ የግለሰብ ቤቶች ተቃጥለዋል፣ የመንግስት ተቋማት ፈርሰዋል፣ ውሃ መብራት የለም። እስረኞች ተለቀዋል።

- የከተማው አመራሮችም ከነዋሪዎች ጋር ከተማውን ጥለው ሸሽተዋል። አመራሮች እንዲመለሱ ፣ የውሃ እና መብራት ችግር እንዲፈታ እየተሰራ ነው ተብሏል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ታደሰ ገብረፃድቅ ዛሬ ጥዋት ከሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተከታዮቹ መረጃዎች ሰጥተወል ፦ - አጣየ እና አካባቢው ስጋት ቢኖርም ትላንት እና ዛሬ አንፃራዊ ሰላም/መረጋጋት አለ/የተኩስ ድምፅ የለም። - ከሸዋሮቢት ወጥተው የነበሩ ዜጎችም እየተመለሱ ነው። - በአጣየ ከተማ የደረሰው ውድመት ከፍተኛ በመሆኑ ነዋሪው ከመመለሱ በፊት…
የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደሪ አቶ ታደሰ ገብረፃዲቅ ፦

"...የአካባቢው ማህበረሰብ እንዲህ ያለ ግጭት ውስጥ ገብቷል ብለን አናምንም። እንዲህ ያለው ግጭት መከሰት የጀመረው ከቅርብ ዓመታት ጊዜ ጀምሮ ነው።

በተለይ ከ2011 ዓ/ም ጀምሮ በየዓመቱ እንደ ዓመታዊ ክብረ በዓል ችግሩ እየተከሰተ ነው ያለው በ2011 ፣ በ2012 አሁን በዚህ ዓመት።

ይሄን ግጭት በአካባቢው ያለው ማህበረሰብ የፈጠረው ነው ብለን አናምንም።

ስለዚህ ምንድነው የሚለውን ፥ ለምን ይሄ ግጭት ሊሆን ቻለ የሚለውን እኛ የምናነሳቸው ሃሳቦች እንደተጠበቀ ሆኖ ተጎጂው ማህበረሰብ በሁለቱም በኩል ያለው ህዝብ በኦሮሞ ብሄረሰብ፣ በሰሜን ሸዋ ዞን ውስጥ ያሉ ህዝቦች ችግሩን እና ያጣላቸውን ሰው በደንብ ስለሚለዩ ፣ ያጣላቸውን አካል ስለሚለዩ እዛ ላይ በደንብ ተወያይቶ ዘላቂ መፍትሄ መስጠት ተገቢ ነው ብለን እናምናለን።

የህግ የበላይነት በቀጠናው ላይ መከበር አለበት ብለን እናምናለን፥ እንጂ እዛ አካባቢ ያለው ህዝብ በብዛት ሄዶ ቤት የሚያቃጥልበት፣ አረጋውያን የሚገልበት፣ ህፃናት የሚገድልበት ስነልቦና ፀባይም፣ ቁመናም የለውም።

ዘላቂ መፍትሄውን በተመለከተ በገለልተኛ ወገን ታይቶ ለግጭቱ አነሳሽ፣ አደራጅ፣ ቀስቃሽ እና ግብዓት አቅራቢዎች አካላት ያለ ምህረት መጠየቅ አለባቸው።"

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
በቻድ ያለው አረመረጋጋት :

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በቻድ የሚገኙ ዲፕሎማቶች አገሪቱን ለቀው እንዲወጡ አዘዘ።

ዲፕሎማቶቹ አገሪቱን ለቀው እንዲወጡ የታዘዙት አለመረጋጋት በመፈጠሩና የቦኮ ሃራም ቡድን ታጣቂዎች እንዳሉ በመገለጹ ነው።

የሰርጎ ገቦች ጥቃት ሊኖር እንደሚችል ያመለከተው የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በቻድ የሚገኙ አሜሪካውያን ከነቤተሰባቸው እንዲወጡ መክሯል።

“...መንግስታዊ ያልሆኑ የታጠቁ ቡድኖች ከሰሜናዊ ቻድ ወደ ዋና ከተማዋ ጃሜና እያቀኑ ነው። ወደ ከተማዋ በመቃረባቸው ጥቃት ሊፈጸም እንደሚችል ስጋት በመኖሩ ወሳኝ ያልሆነ ተግባር ላይ የተሰማሩ አሜሪካውያን ሰራተኞች ለቀው መውጣት አለባቸው” ብሏል።

ወደ ቻድ ለመጓዝ ዕቅድ ያላቸው አሜሪካውያንም የጉዞ እቅዳቸውን እንዲሰርዙ አሳስቧል።

በተመሳሳይም UK ዜጎቿ ቻድን ለቀው እንዲወጡ አስጠንቅቃለች። - ENA

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
መፍትሄው ምንድነው ? ሀሳብዎን ያካፍሉ :

በሀገራችን የተለያዩ አካባቢዎች ላይ እጅግ በተደጋጋሚ ጊዜ የንፁሃን ግድያ ፣ ጥቃት፣ ንብረት ውድመት እየደረሰ እንደሆን ይታወቃል።

በየጊዜው እንዲህ ያሉ ነገሮች ይፈጠራሉ ፥ አንዳንዱ ለራሱ አጀንዳ ያውለዋል ከሳምንታት በኃላ የተፈፀመው ሁሉ ይረሳና ሌላ አጀንዳ ይፈጠራል ፤ ይህ አዙሪቱ ላለፉት አመታት የነበረ ዛሬም የቀጠለ ነው።

በዚህ መሃል ልጆቻውን የሚያጡ እናቶች ፣ አባቶች ፤ ወላጆቻቸውን የሚያጡ ልጆች በመሪር ሃዘን ለዓመታት ይኖራሉ ነገር ግን በየጊዜው ሌላ አጀንዳ ስለሚኖር ማንም አያስታውሳቸውም።

ይህ አዙሪት ወይም በየጊዜው የሚፈፀመው ግድያ የሚሰማው ሞት በዜጎች መኃል የሚፈጥረው ክፍተት እጅግ አደገኛ/ሊቆም ካልቻለም ለነገ አብሮነት ጥሩ ያልሆነ አሻራ የሚያሳርፍ ነው።

የንፁሃን ሞት ፣ መፈናቀል፣ ጥቃት ማስቆም የመንግስት የመጀመሪያው ስራ መሆን እንዳለበት ብዙዎች ያምናሉ፥ የራሱን ዜጎች ደህንነት መጠበቅ ያልቻለ መንግስት መንግስትነቱ ምኑ ጋር ነው ብለው የሚጠይቁም አሉ ፤ በአንፃሩ ለሚፈጠሩት ችግሮች የአክቲቪስቶች፣ የፖለቲካ ድርጅቶችን፣ አመራሮች እንዳሉበት የሚያምኑ አሉ።

ነገር ግን በየጊዜው አጀንዳ ሆኖ ሁሉም በሚያምንበት ሃሳብ በኩል ሆኖ በማህበራዊ ሚዲያ የቃላት ምልልስ ከማድረግ ውጭ የዜጎችን ሞት መታደግ አልተቻለም።

በአንድ በኩል ስሜታዊነት ተንፀባርቆ ፣ እውነተኛ ተቆርቋሪ ሆኖ ፣ ለህዝቡ አስቦ፣ ነገ የሱም እጣፋንታ እንደሆነ አምኖ ፍትህ የሚጠይቀው እንዳለ፤ በሌላ በኩል ፍፁም ግጭቶች እንዳይቆሙ ፣ እንዲባባሱ፣ በዚህም የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት የሚሰራው ኃይል ብዙ ነው።

መፍትሄው ምንድነው ? ምን ቢደረግ የንፁሃ ሞት እና ስቃይ፣ ሰቆቃ ይቆማል ? ሀሳባችሁን በጨዋ ቃላት አካፍሉ።

@TikvahDiscussionandPoll
#Ethiopia😷

ባለፉት 24 ሰዓት 22 ሰዎች በኮቪድ-19 መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል።

በተመሳሳይ ከተደረገው 5,833 የላብራቶሪ ምርመራ 1,603 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

ትላንት 1,330 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

በአጠቃላይ 243,631 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 3,392 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 180,645 ሰዎች አገግመዋል።

አሁን ላይ 972 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

@tikvahethiopia
2021.04.19_MUSE_REPORT.pdf
1.3 MB
#ሪፖርት

በሩዋንዳ በ100 ቀን ውስጥ ብቻ 800 ሺህ ገደማ ቱትሲዎች በተጨፈጨፉበት የ1994ቱ የሩዋንዳ ጭፍጨፋ ፈረንሳይ የተባባሪነት ሚና እንደነበራት የሚያመለክት የምርመራ ሪፖርት ይፋ ሆነ፡፡

የምርመራ ሪፖርቱ ይፋ የሆነው በሩዋንዳ መንግስት ቀጣሪነት ምርመራውን ባካሄደው ‘ሌቪ ፋይር ስቶን ሚዩዝ’ በተባለ አሜሪካዊ የምርመራ ተቋም ነው፡፡

ተቋሙ እ.ኤ.አ ከ2017 ጀምሮ ላለፉት 5 ዓመታት ሲያካሂድ የነበረውን ምርመራ የመጨረሻ ውጤት ሪፖርት ይፋ አድርጓል፡፡

ሪፖርቱ ይፋ የሆነው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ በመሩት እና ዛሬ በተካሄደ ልዩ የሃገሪቱ ካቢኔ ስብሰባ ነው፡፡

ቦቢ ሚዩዝ የተባሉት የመርማሪው ተቋም ባልደረባም ፥ “A Foreseeable Genocide: The Role of the French Government in Connection with the Genocide against the Tutsi” በሚል ርዕስ የተካሄደውን ምርመራ የመጨረሻ ሪፖርት አቅርበዋል፡፡

ከ600 ገጾች በላይ ጥንቅር በሆነ ሪፖርቱ ፈረንሳይ ቱትሲዎች ሰለባ በሆኑበት ጭፍጨፋ የ ‘ተባባሪነት ሚና’ እንደነበራት አስቀምጧል፡፡

“ተገማች የነበረው ጭፍጨፋ እውን እንዲሆን ፈረንሳይ ‘የጎላ ሚና’ ነበራት ነው ሪፖርቱ ያለው፡፡ ይህን ሪፖርት ለማጠናቀር በሚሊዬን የሚቆጠሩ የሰነድ ማስረጃዎች ተመርምረዋል፡፡ የ250 ምስክሮች ቃል ተደምጧል፡፡

#Republic_of_Rwanda #AlAIN

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT