TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
61.5K photos
1.55K videos
215 files
4.26K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AddisAbaba

" በጉዳዩ ላይ ምርመራ እየተደረገ ነው " - የአዲስ አበባ የወንጀል ምርመራ ባልደረባ

የአዲስ አበባ ፖሊስ የወጣቷ አሟሟት በመጣራት ላይ መሆኑን አሳወቀ።

ቀነኒ አዱኛ ገና ለጋ ወጣት ስትሆን የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ምሩቅ ፤ ሞዴልና የማስታወቂያ ባለሙያም ነበረች።

በአፋን ኦሮሞ ዘፈኖቹ በእጅጉ የሚታወቀው የወጣት አንዷለም ጎሳ የፍቅር አጋር እንደነበረችም የተነገረ ሲሆን ሰኞ ሌሊት በአዲስ አበባ ከተማ ፣ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ሰንሻይን አካባቢ በሚገኝ መኖሪያ ቤታቸው በድንገት ሕይወቷ አልፏል።

ከ1 ዓመት በላይ ከፍቅር አጋሯ ጋር አንድ ላይ በአንድ ቤት እንደኖሩ የተገለጸ ሲሆን ከህልፈቷ በኃላ አንዷለምን ፖሊስ ለጥያቄ ፈልጎ እንደወሰደው ተመላክቷል።

የወጣቱ ድምጻዊ አንዷለም ማናጀር እንደሆኑ የገለጸው ሌሊሳ ኢንድሪስ ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ በሰጠው ቃል ፤ ቀነኒ ከሚኖሩበት ሕንጻ መውደቋን እና ንጋት 11 ሰዓት አካባቢ መሞቷን ፤ አንዷለም እና ቤተሰቦቹ ወድቃ እንዳገኟት ገልጿል።

" እኔ ንጋት 11 ሰዓት ስልክ ተደውሎ ቀነኒ ጉዳት ደርሶባት ሆስፒታል እንደገባች ተነገረኝ ፤ እስካሁን ባለው መረጃ መሠረት ከአምስተኛ ፎቅ ወድቃ ነው የሞተችው ሁኔታውን ለማጣራት ምርመራ ተጀምሯል " ብሏል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኢንስፔክተር ማርቆስ ታደሰ ለቪኦኤ ሬድዮ በጉዳዩ ላይ መረጃ ለመስጠት ጊዜው ገና መሆኑን ተናግረዋል።

አንድ የአዲስ አበባ ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ባልደረባ ለሬድዮ ጣቢያው ፣ ፖሊስ በጉዳዩ ላይ ምርመራ እያደረገ መሆኑን ከመግለጽ ውጭ ምንም መረጃ እንደማይሰጡ ተናግረዋል።

የወጣት ቀነኒ አዱኛ አስከሬን በዳግማዊ ሚኒልክ ሆስፒታል የአስክሬን ምርመራ ከተደረገለት በኋላ ሱሉልታ ወደሚገኝ እህቷ ቤት የተወሰደ ሲሆን በአዲስ አበባ ስርዓተ ቀብሯ ይፈጻማል።

ለጋዋ ወጣት በሚቀጥለው ቅዳሜ ልደቷን ለማክበር በሚል ፎቶዎች እየተነሳች ነበር።

በቅርቡ ከፍቅር አጋሯም ጋር ትዳር የመመሥረት ዕቅድ ይዛ እንደነበር ተገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ታላቁ የጎዳና ላይ ኢፍጧር ነገ ይካሄዳል። በተጨማሪ ሀገር አቀፍ የቁርኣን ሂፍዝ ውድድር ፍፃሜ ይካሄዳል። መርሀ ግብሮቹ የሚካሄዱት በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ነው። የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የፕሬዝዳንት ፅህፈት ቤት ሀላፊ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ፤ " ' ቁርዓን፣ የእውቀትና የሰላም ምንጭ ' በሚል መሪ ሃሳብ ምክር ቤቱ ያዘጋጀው ሀገር አቀፍ የቁርአን ውድድር ነገ ይካሄዳል…
#AddisAbaba

ነገ
የሚዘጉ መንገዶች ይፋ ሆነዋል።

በመስቀል አደባባይ ለሚከናወነው የኢፍጣር ፕሮግራም የሚዘጉ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ይፋ አድርጓል።

ነገ መጋቢት 7 ቀን 2017 ዓ/ም ከቀኑ 5:00 ሠዓት ጀምሮ በመስቀል አደባባይ የሚከናወነውን የኢፍጣር ፕሮግራም ምክንያት በማድረግ ፦

➡️ ከኦሎምፒያ ወደ መስቀል አደባባይ (ኦሎምፒያ አደባባይ ላይ )

➡️ ከጥላሁን አደባባይ ወደ ሳንጆሴፍ መብራት (ጥላሁን አደባባይ ሲሆን ከባድ ተሽከርካሪ አጎና ላይ )

➡️ ከለገሃር መብራት ወደ መሰቀል አደባባይ (ለገሃር መብራት)

➡️ ከቴሌ ማቋረጫ ወደ ስታድየም (ቴሌ ማቋረጫ ላይ)

➡️ ከሀራምቤ መብራት ወደ መስቀል አደባባይ (ሀራምቤ መብራት ላይ )

➡️ ከብሔራዊ ቤተ መንግሥት ወደ መስቀል አደባባይ (ብሔራዊ ቤተመንግሥት ላይ )

➡️  ከቅዱስ ዑራኤል አደባባይ ወደ መስቀል (ባምቢስ መቅረዝ ሆስፒታል መታጠፊያ ድረስ ይዘጋል።

አሽከርካሪዎች አማራጭ እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba #ገቢዎችቢሮ

🔴 " እጅ ከፍንጅ እናሲዛለን ግን በ3 ወር ውስጥ ይለቀቃሉ " - የስብሰባ ተሳታፊዎች

➡️ " የእኛ ሰራተኞች ፍጹም ናቸው አንልም አሁንም ብዙ ችግሮች አሉ ይህንን ችግር ለማስተካከል ክፍት ሆነን እየሰራን ነው " - የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ
ከአዲስ አበባ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት እና ከነጋዴ ተወካዮች ጋር ውይይት አካሂዷል።

በብሄራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ ሰኞ ምሽት የተላለፈው ውይይቱ ላይ የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ሃላፊ አቶ ቢኒያም ምክሩ ከታሳታፊዎች ለተነሳላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል።

ከነጋዴው ማህበረሰብ ምን ምን ጥያቄዎች ተነሱ ?

" ሙስና ውስጥ የተዘፈቁ የመስሪያ ቤቱን ስም የሚያጠለሹ የእናንተ መስሪያ ቤት ሰራተኞች አሉ።

ሁሉንም እያልን አይደለም ስነ ምግባር ያላቸው አመራሮች እንዳሉ ሁሉ ብልሹ አሰራር ውስጥ የተዘፈቁ ሰራተኞቻችሁ አሉ።

ብልሹ አሰራር ውስጥ የተዘፈቁትን እጅ ከፍንጅ እናሲዛለን ግን በ3 ወር ውስጥ
#ይለቀቃሉ

አሁንም ድርድር እና ሩጫ መርካቶ ላይ አለ መጠኑ አንሷል እንጂ በጭቆ የመሄድ ነገር አሁንም ይታያል። ... ይሄንን እንዴት አስታርቃቹ ትሄዳላቹ ?

የውጭ ሃገራት የሃገር ውስጥ ምርት የሆኑ ምግቦች ላይ ቫት አይጠየቅም እኛ ጋር ሚዛኑን ያልጠበቀ ዝቅተኛ እና ከፍተኛ ግምት እየተሰጠው ጎን ለጎን እንኳን ሰርቶ እንዳይበላ የሚያደርጉ ነገሮች ይፈጠራሉ። ሸቀጥ ላይ ቢቻል ቫት የሚነሳበት መንገድ ቢመቻች። "

... የሚሉ እና ሌሎችንም ጥያቄዎች አንስተዋል።

የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ሃላፊ አቶ ቢኒያም ምክሩ ምን ምላሽ ሰጡ ?

" የእኛ ሰራተኞች ፍጹም ናቸው አንልም አሁንም ብዙ ችግሮች አሉ ይህንን ችግር ለማስተካከል ክፍት ሆነን እየሰራን ነው፤ የሚመጣልንን ጥቆማ መሰረት አድርገን ችግሮችን ለመቅረፍ ዝግጁ ነን።

አላግባብ የሆነ ተቀባይነት የሌላቸው ወጪዎችን አንረው የሚያመጡ ሰዎች አሉ ኤክስፔንሱን ከፍ በማድረግ ፕሮፊቱን ለማሳነስ ተቀባይነት የሌላቸው ወጪዎችን አንሮ በማምጣት ለድርድር በር የሚከፍቱ አሉ።

ባንክ ላይ ያለ ትራንዛክሽን አብዛኛው ነጋዴ የቼክ አካውንት ኖሮት ሲያበቃ የቼክ አካውንት ላይ ያለውን ገንዘብ በአግባቡ ማኔጅ አያደርግም ።

የቼክ አካውንት ውስጥ ያለ ገንዘብ ዝም ብሎ አይወጣም ዝም ብሎም አይገባም የሚገባው በተሸጠው እቃ ልክ መሆን አለበት ሲወጣ ገንዘቡም ለምን አላማ እንደተከፈለ መረጃ መቅረብ አለበት አሁን ትልቁን ችግር እየፈጠረ ያለው ይሄ ነው።

ኦዲተሮች ባንክ ላይ የወጣ የገባውን እና ሂሳብ ላይ ያለውን ገንዘብ ሲያስተያዩ አይገናኝም።

በብዙ ሚሊየን የሚቆጠር ገንዘብ ባንክ አካውንቱ ላይ ይታያል እዚጋ ግን ምንም አላተረፍኩም ብሎ ያመጣልናል።

ወይም የገባውን ገንዘብ ህጋዊነት በሌላቸው ጉዳዮች ወጪ ያደርጋል ማስረጃ አቅርብ ሲባል አይችልም ለድርድር እራሱን አጋልጦ ይሰጣል።

የሚመጣው የሂሳብ መዝገብ ፕሮፌሽናል ባልሆኑ ሰዎች እየተዘጋጀ ነጋዴው ችግር ውስጥ እየገባ ነው።

75 በመቶ የሚሆነው ነጋዴ ይዞ የሚመጣው የሂሳብ መዝገብ ደረጃውን ያልጠበቀና ሙያው በሌላቸው ግለሰቦች የሚዘጋጅ በመሆኑ ተቀባይነት አያገኝም።

ጥቅምት ላይ ባደረግነው የቅድመ ኦዲት ስራ የሂሳብ መዝገባቸውን ይዘው መጥተው የሂሳብ መዝገባቸው ተቀባይነት ያገኙ ነጋዴዎች 25 በመቶ አይሆኑም።

ከቫት ጋር የተገናኙ እና ውሳኔ የሚፈልጉ እንደዚህ እንደዚህ አይነት ዘርፎች ቫት ውስጥ ባይገቡ ይሄ ይሄ ደግሞ ቢወጣ የሚለውን የተወሰኑትን አስተያየቶች አደራጅተን ልከናል።

ቫት ውስጥ የሚገቡትን እና የማይገቡትን ምርቶች የመወሰን ሥልጣን ያለው የገንዘብ ሚኒስቴር ብቻ ነው ጥያቄዎቹ ተይዘዋል የመጨረሻ ውሳኔ የመስጠት ሥልጣን ያለው የገንዘብ ሚኒስቴር መሆኑ መታወቅ አለበት " ብለዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

🔴 “ የንግድ ቦታችንን እቃ ሳናወጣ በላያችን ላይ አፈረሱት። ወዴት እንሂድ?” - አካል ጉዳተኞች

➡️ “ አባላቱ የኛ የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማኀበር አባላት ናቸው” - የአካል ጉዳተኞች ብሔራዊ ማኀበር

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10፣ “ኮልፌ አጣና ተራ ቴሌ ጀርባ” የነበረ ለዓመታት በሊዝ የከፈልንበት የንግድ ቦታ “ለባለሃብት ተሽጦ ትላንት ፈረሰብን” ሲሉ አካል ጉዳተኞች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናገሩ። 

"ቢያግድግልኝ የአካል ጉዳተኞች ማኀበር” የተሰኘው የአባላቱ አቃፊ፣ የ11 አካል ጉዳተኞች መስሪያ የነበሩ 11 ሱቆች መፍረሳቸውን፣ የሚመለከታቸውን በደብዳቤ ቢጠይቅም መፍትሄ እንዳልተገኘ አስረድቷል።

ቅሬታ አቅራቢዎቹ በዝርዝር ምን አሉ?

“አካል ጉዳተኞች ነን 11ዳችንም። ህጋዊ የሊዝ ቦታ ነው። በቃ መገድ ላይ ጥሎናል መግስት። ቦታው በ1996 ነው በሊዝ የተሰጠን ለማልማት። የሊዝ እየከፈልን ህጋዊ ንግድ ፈቃድ አውጥተን እየሰራንበት ነበር።

ድንገት ያለምንም ደብዳቤ መጡና ከሦስት ቀናት በፊት ‘እቃችሁን ይዛችሁ ውጡ እናፈርሳለን አሉን’፤ ትላንት ሙሉ በመሉ አፈረሱት። የንግድ ቦታችንን እቃ ሳናወጣ በላያችን ላይ አፈረሱት። ወዴት እንሂድ?

ለልማት ቢሆን እንኳ ተለዋጭ ቦታ ይሰጠን ነበር፤ ግን ለባለሀብት ነው የተሸጠው። ሦስት ሰዎች ናቸው የገዙት፤ ዝርዝራቸው አለን። በደብዳቤ ወረዳው ከሰማ ቆይቷል። ከከንቲባ ቢሮ ነው የመጣው ደብደቤው። 

አብዛኛዎቹ ሰዎች እቃ ወድቆ ማንሳት የማይችሉ አካል ጉዳተኞች ናቸው። እንዴት ቀድማችሁ አላሳወቃችሁንም? ስንል ‘እኛ ምንም ማድረግ አንችልም ከላይ ከቢሮ የመጣ ትዕዛዝ ነው’ አሉን። 

እግድ ለማውጣት ሞከርን፤ ከፌደራል ፍርድ ቤት እግድ ለማውጣት ‘አይፈረድላችሁም አለን’ ፍ/ቤት ራሱ አግዶን ማለት ነው። የፍ/ቤት መጥሪያ ደብዳቤ ‘እግድ አንቀበልም ሂዱና ለከቲንባ ቢሮ ስጡ’ አሉን። የወረዳ አስተዳደሩ ‘እዛው ሄዳችሁ ጠይቁ’ አለን።

ፍርድ ቤት ትንላት ቀጠሮ ነበረን ‘ልማትን አናደናቅፍም መዝገቡ ተዘግቷል ውጡ’ አሉን። እጃቸው ረጅም ነው ባለሀብቶቹ። ሁሉም ቦታ ይሄነው ያለው ነገር ” ብለዋል።

የአካል ጉዳተኞቹ ቅሬታ እንደደረሰውና አካል ጉዳተኞቹን በመወገን እንዲተባበራቸው፣ የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ብሔራዊ ማህበር በ9/07 2017 ዓ/ም የፃፈውና ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተው ደብዳቤ ያስረዳል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ደብዳቤውን ጽፋችኋል? ሲል የጠየቀው የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ብሔራዊ ማኀበር፣ “ደብዳቤ ተጽፎላቸዋል። አባላቱ የኛ የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማኀበር አባላት ናቸው” ሲል አረጋግጧል።

የአካል ጉዳተኞቹን ቅሬታ ይዘን ምላሽ የጠየቅነው የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ኮሚዩኒኬሽን ግን ምላሽ ያልሰጠ ሲሆን፣ ከሰጠ በቀጣይ የምናቀርብ ይሆናል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tivahethiopia
#AddisAbaba : የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በተቋሙ ቢሮ አካባቢ በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ነበሩ ያላቸው 25 ሴቶች የሚገኙባቸው 65 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ገለጸ።

መ/ቤቱ ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን እና ከልደታ ክፍለ ከተማ  ወረዳ 7 አስተዳደር ጋር በመቀናጀት እንደሆነ አመልክቷል።

ተጠርጣሪዎች ፦
➡️ በተለያየ የህገ-ወጥ የድለላ ስራዎች ላይ የተሰማሩ፣
➡️ የስራ ከባቢውን በማወክ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ችግር እየፈጠሩ ያሉ፣
➡️ በተለያየ የማጭበርበር እና የማታለል ተግባር ላይ ተሰማርተው የነበሩ
➡️ በህገ-ወጥ መንገድ የኦን ላይን የአስቸኳይ ፓስፖርት የሚሞሉ ናቸው ሲል ገልጿል።

በአጠቃላይ 7 በህገወጥ የንግድ እንቅስቃሴ ላይ የተሰማሩ ቤቶች እንደታሸጉ አመልክቷል።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

ነገ የሚዘጉ መንገዶች ይፋ ሆኑ።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ነገ እሁድ ከሚከበረው ከ1446ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል ጋር ተያይዞ የዒድ ሶላት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን ይፋ አድርጓል።

ዝግ የሚሆኑት መንጋዶች የትኞቹ ናቸው ?

➡️ ከመገናኛ በ22 አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ቅዱስ ዑራኤል  አደባባይ በተመሳሳይ ከቦሌ አካባቢ በአትላስ መብራት ወደ ቅዱስ ዑራኤል አደባባይ ለሚሄዱ አትላስ መብራት እና ፒኮኪ መብራት ላይ፣

➡️ ከቦሌ ወሎ ሠፈር መታጠፊያ ወደ ኦሎምፒያ አደባባይ ለሚሔዱ አሽከርካሪዎች ኦሎምፒያ አደባባይ ላይ፣

➡️ ከወሎ ሠፈር ጀምሮ እስከ ጋዜቦ አደባባይ ውስጥ ውስጡን ወደ ዋናው መንገድ የሚያስወጡት መንገዶች ዝግ የሚደረጉ ይሆናል፣

➡️ ከአጎና መስቀለኛ ወደ ጥላሁን አደባባይ -ሳንጆሴፍ መብራት አጎና ሲኒማ መስቀለኛ ላይ፣

➡️ ከቡልጋሪያ መብራት ወደ ገነት ሆቴል ሜክሲኮ አደባባይ  ለሚሄዱ አሽከርካሪዎች ቡልጋሪያ መብራት ላይ፣

➡️ ከቅድስት ልደታ ፀበል በAU ቅዱስ ሚካኤል መታጠፊያ ወደ ወደ ሜክሲኮ አደባባይ AU ሚካኤል መታጠፊያ፣

➡️ ከጦር ኃይሎች በከፍተኛ ፍ/ቤት  ወደ ሜክሲኮ አደባባይ ለሚሔዱ ከፍተኛ ፍ/ቤት አደባባይ ላይ፣

➡️ ከአብነት አካባቢ በፈረሰኛ ፖሊስ  መብራት ወደ ጨፌ ሜዳ መብራት  ፈረሰኛ መብራት ላይ፣

➡️ ከሞላ ማሩ መስቀለኛ ወደ ጌጃ ሰፈር መውረጃ ሞላ ማሩ መታጠፊያ ላይ፣

➡️ ከመርካቶ አካባቢ በአቡነ ተክለ ኃይማኖት አደባባይ ወደ ጥቁር አንበሳ ለሚሄዱ አቡነ ተክለ ኃይማኖት አደባባይ ላይ

➡️ ከፒያሳ በባንኮዲሮማ መብራት ወደ ቴዎድሮስ አደባባይ ባንኮዲሮማ መብራት ላይ፣

➡️ ከሲግናል አካባቢ በሴቶች አደባባይ ወደ ካዛንቺስ ለሚሄዱ ተሽከርካሪዎች ሴቶች አደባባይ ላይ ከንጋቱ 11:00 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ መንገዶቹ ዝግ ይሆናሉ።

አሽከርካሪዎች ሌሎች አማራጮችን እንዲጠቀሙ ፖሊስ አሳስቧል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ዛሬ ከበዓሉ ዋዜማ ምሽት ጀምሮ በተጠቀሱት ቦታዎች ላይ ተሽከርካሪዎችን ለአጭርም ይሁን ለረጅም ሠዓት ማቆም የተከለከለ ነው ተብሏል።

#AddisAbabPolice

@tikvahethiopia
#AddisAbaba : የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዛሬ ለህዝብ ትራንስፖርት የሚሰጡ 100 ዘመናዊ የኤሌክትሪክ አውቶቢሶች ወደ ስራ መግባታቸውን አሳውቋል።

አውቶብሶቹ በሁሉም የከተማችን አቅጣጫዎች ለነዋሪዎች ነጻ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደሚገኙ አመልክቷል።

ከተማ አስተዳደሩ በመንግስትና የግል አጋርነት መርሃግብር የመጀመሪያው የትራንስፖርት ኦፕሬተር በመሆን ዛሬ አገልግሎት መስጠት የጀመረውን የበላይነህ ክንዴ ግሩፕ መሆኑ ተመላክቷል።

#MayorOfficeofAA

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

" የመንጃ ፈቃድ ዕድሳት አገልግሎት በየአቅራቢያው ማግኘት ይቻለል " - የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን

ከመጋቢት 24 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ የመንጃ ፈቃድ ዕድሳት አገልግሎት በየአቅራቢያው በመታወቂያ አድራሻ ሳይገደብ እንዲሰጥ መፈቀዱን የአዲስ አበባ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን አሳውቋል።

ከዚህ ቀደም የአዲስ አበባ መንጃ ፈቃድ ለማሳደስ በመንጃ ፈቃዱ ላይ ወደ ተገለጸው እና ፋይሉ ወዳለበት ክፍለ ከተማ (የመታወቂያ አድራሻ) የሚገኝ የአሽከርካሪና ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለሥልጣን ቢሮ መሄድ ግድ ይል ነበር።

ከነገ በኃላ ግን በየትኛውም አቅራቢያ በሚገኝ ቦታ በመታወቂያ አድራሻ ሳይገደብ መንጃ ፈቃድ ማሳደስ ይቻላል ተብሏል።

ተገልጋዮች በሚቀርባቸው ቅርንጫፍ ፋይላቸው ያለበት ቅርንጫፍ ሳይጠየቅ የጤና ምርመራ ሰርተፍኬትን በመያዝ የመንጃ ፈቃድ ዕድሳት አገልግሎት እንዲያገኙ መወሰኑን ባለስልጣን መ/ቤቱ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር " መደበኛ ያልሆነን የጎዳና ላይ ንግድ ስርዓት ለማስያዝ ይረዳል " ያለውን ደንብ አውጥቷል።

የደንቡን መውጣት ተከትሎ ንግዱ የሚካሄድበት ሰዓት በ5 ፈረቃ ተከፋፍሎ ይፋ ሆኗል።

በዚሁ መሰረት ፦

➡️ ከንጋቱ 11:00 ሰዓት እስከ ንጋቱ 1:00 ሰዓት የአትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም የአልባሳት እና መጫሚያዎች ንግድ እንዲካሄድ፤

➡️ ከንጋቱ 1:00 ሰአት እስከ ረፋዱ 3:00 ሰዓት እንደ ብስኩት ፣ ሻይ ፣ ቡና ፣ የታሸገ ውሃ እና ለስላሳ መጠጦች ያሉ እና ለቁርስ የሚሆኑ ቀላል ያሉ ምግቦች ንግድ እንዲካሄድ ፤ የጫማ ፅዳት ወይም ሊስትሮ አገልግሎት በዚሁ ሰዓት እንዲካሄድ፤

➡️ ከረፋዱ 3:00 ሰዓት እስከ ቀኑ 6:00 የመፅሃፍት ፣ መፅሄቶች እና ጋዜጦች ንግድ እንዲካሄድ፤

➡️ ከቀኑ 6:00 ሰዓት እስከ 8:00 ሰዓት ቀላል ምግቦች በመባል የሚታወቁት እንደ ኬክ ፤ ብስኩት ፤ ሻይ ፤ ቡና ፤ የታሸገ ውሃና ለስላሳ መጠጦች ንግድ እንዲካሄድ፤

➡️ ከአመሻሽ 11:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 3 ሰዓት ተኩል የተጠበሱ ምግቦች ፣ ጁስ ፣ ብስኩት ፣ ኬክ ፣ ሻይ ፣ ቡና ፣ የታሸገ ውሃ እና ለስላሳ መጠጦች እንዲሁም አልባሳት እና መጫሚያዎች ፣ ቀላል የኤሌክትሮኒክስ መገልገያዎች ፣ የውበት መጠበቂያ ኮስሞቲኮስች ንግድ እንዲካሄድ የከተማ አስተዳደሩ መርሃ ግብር አውጥቷል።

ንግዱ የሚካሄድባቸው ቦታዎች
#ወደፊት እንደሚለዩና ይፋ እንደሚደረጉ የከተማ አስተዳደሩ አሳውቋል።

መደበኛ ያልሆነ የጎዳና ላይ ንግድ " ኮንትሮባድን ያበረታታል፤ ለትራፊክ መጨናነቅ እና አደጋም መንስኤ ይሆናል እንዲሁም በህጋዊ ንግዱ ላይ ተፅዕኖ ያሳድራል " በሚል በከተማው አስታዳደር ቁጥጥር እንዲደረግበት ሲሞከር እንደነበር ይታወሳል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ነው።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

" ከአራት ኪሎ እስከ ሽሮ ሜዳ ያለዉ አካባቢ የዩኒቨርሲቲ መንደር ለማድረግ የቀረበው ጥናት ፀድቋል " - የአዲስ አበባ ካቢኔ

በዛሬዉ እለት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አስተላልፏል።

ከነዚህም አንዱ ፥ በፕላንና ልማት ቢሮ እና በት/ት ሚኒስቴር በጋራ ተጠንቶ የቀረበውን ከአራት ኪሎ እስከ ሽሮ ሜዳ ያለዉ አካባቢ የዩኒቨርሲቲ መንደር የማድረግ ነው።

ካቢኔው " በአካባቢው ያሉትን አገልግሎቶች አካቶ የትምህርት ፣ የምርምር ፣ የእውቀት እና የባህል ልህቀትን በከተማዋ ለማሳደግ በሚያስችል አግባብ የቀረበ በመሆኑ የመንደር ምስረታውን ዉሳኔ ፀድቋል " ሲል አሳውቋል።

ከዚህ ባለፈ ካቢኔው ፦

- የአደጋ ስጋት አመራር ምክር ቤትና ፤የአደጋ ዝግጁነት ፈንድ ማቋቋሚያ ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ ዉሳኔ አሳልፏል።

- በመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የቀረበዉን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያላቸዉ ፕሮጀክቶች፤ የመሬት ምደባ ጥያቄዎች አስመልክቶም ዉሳኔ አስተላልፏል።

- የምግብ ስርዓትና ኒዉትሪሽን ምክር ቤት ማቋቋሚያ ረቂቅ ደንብ ላይም ተወያይቶ ዉሳኔ አስተላልፏል።

@tikvahethiopia