TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59K photos
1.5K videos
211 files
4.08K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የ4G LTE አገልግሎት በደቡብ ደቡብ ምዕራብ ሪጅን ተጀመረ።

ኢትዮ ቴሌኮም በደቡብ ክልል የ4G LTE አድቫንስንድ አገልግሎት አገልግሎት በደቡብ ደቡብ ምዕራብ ሪጅን ባሉ ስድስት ከተሞች በዛሬው ዕለት በይፋ አስጀምሯል።

የ4G LTE አድቫንስንድ አገልግሎት የጀመረባቸው ከተሞች ፦

- ወላይታ ሶዶ፣
- አርባ ምንጭ፣
- ቡታጅራ፣
- ወልቂጤ፣
- ጂንካ እና ሆሳዕና ናቸው።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE ፕሮፌሰር ፈትየን ኣባይ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ግዚያዊ ፕሬዘዳንት ሆነው ተመርጠዋል። ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረህይወት የኃላፊነታቸው ጊዜ ስላበቃ በትላንትናው ዕለት ኃላፊነቱ እንደተነሳላቸው ይታወቃል። @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
መቐለ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዜዳንት ተሹሞለታል።

ዶ/ር ፋና ሀጎስ ብርሃኔ ናቸው የመቐለ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ሆነዉ የተሾሙት።

ዶ/ር ፋና ሀጎስ ማንናቸው ? ከMoSHE ያገኘነው መረጃ ፦

- የመጀመሪያ ድግሪያቸዉን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በህግ ትምህርት ተቀብለዋል። ሁለተኛ ድግሪያቸዉን በደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርስቲ ኦፍ ፍሪስቴትና ሶስተኛ ድግሪያቸዉን በዋርዊክ ዩኒቨርስቲ(Warwick University, UK) ተምረዋል፡፡

- ኬኒያ ናይሮቢ በሚገኘዉ የአፍሪካ ሳይንስ አካዳሚ የፖስት ዶክተሬት ተመራማሪ ሆነዉ ሰርተዋል፡፡

- በትግራይ ክልል ፍትህ ቢሮ አቃቤ-ህግ በመሆን ፤ በመቐለ ዩኒቨርስቲ ለ12 አመታት የህግ ትምህርት ክፍል ረዳት ፕሮፌሰር በመሆን አገልግለዋል፡፡

- በዩኒቨርስቲዉ የስርዓተጾታ ጥናት ኢንስቲትዩት ዳይሬክተርና የህግና ስነ-መንግስት/Governance/ ኮሌጅ ዲን በመሆን አገልግለዋል፡፡

- የመቐለ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንትንት ሆነው ከመሾማቸዉ በፊት የትግራይ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት በመሆን እያገለገሉ ነበር፡፡

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ ዩኒቨርሲቲ ካሉ የቤተሰብ አባለቱ እንደሰማው ለዩኒቨርሲቲው ፕሬዜዳንትነት ውድድር ሲደረግ ነበር። ተወዳዳሪዎችም የተለያዩ ሃሳቦቻቸውን ሲያቀርቡ ነበር የቆዩት።

ዶክተር ፋና ፕሬዜዳንት ከመሆናቸው በፊት ፕሮፌሰር ፈትየን ኣባይ ጊዜያዊ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዜዳንት በመሆን ሲሰሩ ነበር።

ፕሮፌሰር ፈትየን ኣባይ የኃላፊነት ቦታውን ተረክበው የነበረው ከግንቦት 28/2005 ጀምሮ እስከ መስከረም 5 ቀን 2013 ዓ/ም ዩኒቨርሲቲውን የመሩት ፕ/ር ክንደያ ገ/ህይወት የስራ ኃላፊነቱ ከተነሳላቸው በኃላ እንደነበር አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
#UnitedNationsSecurityCouncil

የተመድ የፀጥታው ም/ቤት በኢትዮጵያ የትግራይ ክልል ባለው ጉዳይ ላይ ዛሬ በዝግ ይወየያል።

የተመድ፥ የእርዳታ ዘርፍ ኃላፊ ማርክ ሎውኮክ ለተፈናቃዮች እርዳታ ከማቅረብ አንጻር ያሉትን ችግሮች በተመለከተ ለ 15ቱ የፀጥታው ም/ቤት አባላት ገለጻ ያደርጋሉ፡፡

የዛሬው ስብሰባ በአሜሪካ የተጠራ ነው።

ከዚህ በፊትም የካቲት 25/2013 ዓ.ም በተመሳሳይ ጉዳይ ስብሰባ የተካሔደ ሲሆን ፣ በፀጥታው ም/ቤት ቋሚ አባላት ሩሲያና ቻይና እንዲሁም በተለዋጭ አባሏ ህንድ ተቃውሞ የጋራ መግለጫ ሳይወጣ መቅረቱ ይታወሳል ሲል አል ዓይን በድህረ ገፁ አስነብቧል።

@tikvahethiopia @tikavhethiopiaBOT
#Russia #Ethiopia

ኢትዮጵያና ሩስያ በሰላማዊ የኑክሌር ኃይል አጠቃቀም ዙሪያ የጋራ መግባቢያ ስምምነቶችን በሞስኮ መፈራረማቸውን ተሰምቷል።

የመግባቢያ ስምምነቱ የኑክሌር ኃይል በተመለከተ አዎንታዊ የሕዝብ አስተያየትን ለማስያዝ እና በኢትዮጵያ የኑክሌር ኃይል መስክ በትምህርት እና በስልጠና ትብብር መሥራት ላይ ያተኮረ ነው።

ስምምነቱን የፈረሙት አምባሳደር አለማየሁ ተገኑ እና የሩስያ የኑክሌር ኃይል ትብብር ኮርፖሬሽን ምክትል ዳይሬክተር ኒኮላይ ስፓስኪ መሆናቸውን በሩስያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አሳውቋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
TIKVAH-ETHIOPIA
የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና መሰጠት ተጀመረ። በኮቪድ -19 ወረርሽኝ ምክንያት "በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ትምህርት ቤት ጅዳ" እስከ አሁን ሳይሠጥ የቆየው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ዛሬ 3/08/2013 መሠጠት ጀምሯል። ፈተናው የፊታችን ረቡዕ ይጠናቀቃል። በሀገር ውስጥ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ከየካቲት 29 - መጋቢት 2 ድረስ መሰጠቱ ፤ በአጭር ጊዜም ፈተናው ታርሞ ውጤትና የመቁረጫ ነጥብ ይፋ…
#Update

ሲሰጥ የነበረው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ተጠናቀቀ።

በኢትዮጵያ ዓለም ዐቀፍ ት/ቤት ለተማሪዎች ሲሰጥ የቆየውን የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ተጠንቋል።

ሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ለተማሪዎቹ አዲስ ፈተና አዘጋጅቶ በመላክ ከሚያዚያ 3 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ እስከትላንት ሚያዚያ 6 ድረስ ፈተናው ሲሰጥ ቆይቷል።

ኤጀንሲው ኃላፊ መድቦ ፈተናውን እንደተቆጣጠረ ተገልጿል።

የትምህርት ቤቱ ዳይሬክተር አቶ አበበ ጫላ ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ ፈተናው ትላንት በሰላም ስለመጠናቀቁ ተናገረዋል።

የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የ2013 የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ነጥብ በቅርቡ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።

@tikvahuniversity @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
"...ሀገራችን ከመቼውም ጊዜ በላይ ወደ ፈጣሪ በመቅረበ በይቅርታና በንስሃ የሚመላለሱ ልጆች ያስፈልጓታል" - ሊቀ ትጉሀን ቀሲስ ታጋይ ታደለ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከመጪው አርብ ጀምሮ ሃገር አቀፍ የጸሎትና ምህላ መርሃ ግብር ሊጀመር መሆኑን ዛሬ አስታወቀ። ጉባኤው ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ እንደገለጸው ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይን፣ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ መስፋፋትን፣ መጪው ሀገራዊ…
#Update

ሀገራዊ የፀሎት እና ምህላ እወጃ መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው።

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የሀገራዊ ፀሎት እና ምዕላ ማስጀመሪያ እና ማወጃ መርሃ ግብር ዛሬ ሚያዚያ 7 እያካሄደ ነው።

በመርሀ ግብሩ ላይ ፕሬዜዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ፣ ከሁሉም የቤተ እምነቶች የተወኩሉ የእምነት አባቶች ፣ ሁሉንም ማህበረሰብ ይወክላሉ የተባሉ የሀገር ሽማግሌዎች ፣ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ፣ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ አባላት ፣ ታዋቂ ግለሰቦች ተገኝተዋል ተብሏል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#EthiopianAirlines

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ጅማ የሚያደርገውን በረራ ለ2 ቀናት ማቋረጡን ገልጿል።

አየር መንገዱ በረራውን ያቋረጠው የጂማ አውሮፕላን ማረፊያ ለ ሁለት ቀናት [ሚያዝያ 11 እና 12 ቀን 2013 ዓ.ም] እድሳት ስለሚደረግለት ነው ብሏል።

እድሳቱ ከተጠናቀቀ በኋላ መደበኛ በረራው ከሚያዝያ 13 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ የሚቀጥል መሆኑን አሳውቋል።

@tikvahethiopia
"የኑሮ ውድነት ችግርን ለመፍታት ያለውጭ ምንዛሬ ፈቃድ (ፍራንኮ ቫሉታ) ስኳር ፣ ምግብ ዘይት ፣ ስንዴ ፣ ሩዝ ፣ የዱቄት ወተት ከውጭ ሀገር እንዲገቡ ተወስኗል። 250 ሺህ ዶላር (የውጭ ሀገር ገንዘብ) ያላቸው ምንጩን በብሔራዊ ባንክ እያረጋገጡ ማስገባት ይችላሉ።" - አቶ መላኩ አለበል የንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
ዛሬ ከ5 ሺህ 500 በላይ ተተኳሽ ጥይቶችን በህገ ወጥ መንገድ ይዘው ሲንቀሳቀሱ የተገኙ አራት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ነው ከ5 ሺ 500 በላይ የክላሽንኮቭ ተተኳሽ ጥይቶችን በህገ ወጥ መንገድ ይዘው ሲንቀሳቀሱ የተገኙ አራት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር የዋሉት።

የመጀመሪያው ፦

ከማሽላ እህል ጋር ቀላቅለው 5 ሺህ 106 ጥይቶች ይዘው የተገኙ ሁለት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

በታርጋ ቁጥር ኮድ 3-7277 አዲስ አበባ በሆነ የጭነት አይሱዙ ከቆቦ ከተማ ወደ ከሚሴ ከተማ እህል አስመስለው ጭነው ለማለፍ ሲሞክሩ ነው ዛሬ በወልድያ ጉምሩክ መቆጣጠሪ ጣቢያ ተደርሶባቸው የተያዙት።

ግለሰቦቹ አሽከርካሪውና ረዳቱ መሆናቸው ተገልጿል።

ሁለተኛው ፦

በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር በደሃና ወረዳ 456 የክላሽንኮቭ ጥይቶችን በህገ ወጥ መንገድ ይዘው ሲንቀሳቀሱ የተገኙ 2 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ዛሬ በቁጥጥር ስር ያዋሉት ግለሰቦቹ ከሰቆጣ -ባህር ዳር ይጓዝ በነበረ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ተተኳሽ ጥይቱን በህገ ወጥ መንገድ ደብቀው ለማሳለፍ ሲሞክሩ ነው።

ሊደረስባቸው የተቻለው በወረዳው 022 ቀበሌ በሚገኘው ኬላ የፀጥታ አካላት ባደረጉት ድንገተኛ ፍተሻ ነው።

ግለሰቦቹ በህግ ቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በምርመራ የማጣራት ስራ ተጀምሯል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
የኮቪድ-19 ሪፖርቶች ፦

- በደቡብ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ከተደረገ 630 የላብራቶሪ ምርመራ 78 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ 1 ሰው ህይወቱ አልፏል ፤ 103 ሰዎች አገግመዋል።

- በሱማሊ ክልል በ24 ሰዓታት ከተደረገው 31 የላብራቶሪ ምርመራ 18 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ 2 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

- በድሬዳዋ ከተማ በ24 ሰዓታት ከተደረገው 168 የላብራቶሪ ምርመራ 95 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። 1 ሰው አገግሟል።

- አማራ ክልል በ24 ሰዓት ውስጥ ከተደረገ 246 የላብራቶሪ ምርመራ 83 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል ፤ ከ83ቱ 68ቱ ከባህር ዳር ናቸው። በ24 ሰዓት 1 ሰው ህይወቱ አልፏል፤ 11 አገግመዋል።

- ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓታት ከተደረገው 170 የላብራቶሪ ምርመራ 52 ሰዎች ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል ፤ 23 ሰዎች አገግመዋል።

- ኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 805 የላብራቶሪ ምርመራ ተደረጎ 166 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል ፤ 8 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

- ሃረሪ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 80 የላብራቶሪ ምርመራ ተደረጎ 37 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል ፤ 3 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

- ሲዳማ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 160 የላብራቶሪ ምርመራ ተደረጎ 63 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል ፤ 1 ሰው ህይወቱ አልፏል።

* ያልተካተቱ ሪፖርቶች ይፋ የሚደረጉ ከሆነ ዘግየት ብላችሁ ይህንኑ ፖስት ተመልከቱ።

#Purpose #Tikvah

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የቤት ቁልፍ መረከቢያ ፕሮግራም - Tikvah.pdf
የቤት ቁልፍ መረከቢያ ፕሮግራም 2.pdf
163.5 KB
የ40/60 መኖሪያ ቤት ቁልፍ መረከቢያ ፕሮግራም #2 :

የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በ40/60 የቤት ልማት ፕሮግራም ካስገነባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች መካከል ለተጠቃሚዎች ያስተላለፋቸውን ቤቶች ቁልፍ ለቤት ባለቤቶች ከመጋቢት 6 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ እያስረከበ ይገኛል።

ሚያዚያ 2 የቁልፍ መረከቢያ ፕሮግራም ከዚህ ቀደም ይፋ መደረጉ ይታወቃል።

ከባለፈው የቀጠለው የቤት ቁልፍ መረከቢያ ፕሮግራም ከላይ በPDF ተያይዟል።

በተገለፀው ፕሮግራም የቤታችሁን ቁልፍ እንድትረከቡ ጥሪ ቀርቧል።

የቤት ቁልፍ ለመረከብ የትኞቹን ሰነዶች መሟላት አለባቸው ?

- የቤት ሽያጭ ውል
- የባንክ ብድር ውል/ሙሉ ክፍያ ከሆነ የተከፈለበት ደረሰኝ
- የቤት ቁልፍ መረከቢያ ቅፅ/ፎርም
- የቤቱን ባለቤት ማንነት የሚገልፅ የታደሰ መታወቂያ
- በውክልና ከሆነ የውክልና ማስረጃና የተወካይ ማንነት የሚገልፅ የታደሰ መታወቂያ

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
TIKVAH-ETHIOPIA
የኮቪድ-19 ሪፖርቶች ፦ - በደቡብ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ከተደረገ 630 የላብራቶሪ ምርመራ 78 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ 1 ሰው ህይወቱ አልፏል ፤ 103 ሰዎች አገግመዋል። - በሱማሊ ክልል በ24 ሰዓታት ከተደረገው 31 የላብራቶሪ ምርመራ 18 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ 2 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል። - በድሬዳዋ ከተማ በ24 ሰዓታት ከተደረገው 168 የላብራቶሪ ምርመራ…
የኮቪድ-19 የፅኑ ታማሚዎች ቁጥር ከ1 ሺህ አለፈ።

የዛሬ የኮቪድ-19 ዕለታዊ ሪፖርት እንደሚያሳየው አሁን ላይ 1,031 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

ባለፉት 24 ሰዓት 33 ሰዎች በኮቪድ-19 መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል።

በተመሳሳይ ከተደረገው 8,878 የላብራቶሪ ምርመራ 2,149 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

ትላንት 1,288 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

በአጠቃላይ 236,554 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 3,285 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 175,879 ሰዎች አገግመዋል።

#Purpose #Tikvah
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
"...ችግሩ የተፈጠረው ሰልጥነው ስራ ያልጀመሩ እና የጀመሩ አስፈፃሚዎችን ለመለየት ጊዜ በመውሰዱ ነው" - ወ/ሪት ሶሊያና ሽመልስ

በምርጫ አስፈፃሚነት እየሰሩ ያሉ የምርጫ አስፈፃሚዎች ከክፍያ ጋር በተያያዘ ባለፉት ቀናት በርካታ ጥያቄዎችን እያነሱ ይገኛሉ።

ጥያቄያቸውም "ክፍያ አልተከፈለንም" የሚል ነው።

በጉዳዩ ዙሪያ የፅሁፍ መልዕክት ያስቀመጥንላቸው የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር ወይዘሪት ሶሊያና ሽመልስ ፥ ችግሩ የተፈጠረው ሰልጥነው ስራ ያልጀመሩ እና የጀመሩ አስፈፃሚዎችን ለመለየት ጊዜ በመውሰዱ መሆኑን ገልፀዋል።

ወ/ሪት ሶሊያና ፥ "... አንዳንዶቹ ሰልጥነው ስራ ጥለው የሄዱ እና እየሰሩ ያሉ አሉ ፤ ይህን በመለየት እንከፍለን ፤ ትንሽ መታገስ ብቻ ነው የሚያስፈልገው" ሲሉ ምላሽ ሰጥተውናል።

#TikvahFamily
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
“...ወደ ጦርነት የሄደነው ግልጽ የሆነ ግብ ይዘን ነው፤ ግባችንን አሳክተናል ፤ ቢላደን ሞቷል ፤...የሁልጊዜው ጦርነት መቆሚያው ጊዜ ነው" - ጆ ባይደን

የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ባይደን ባይደን “ረጅሙ ጦርነት አብቅቷል” የአሜሪካ ወታደሮች አፍጋኒስታንን በመስከረም ይለቃሉ ሲሉ ተናግረዋል።

አሜሪካ መስከረም 11/2021 2,500 የሚሆኑ ወታደሮችዋን ነው ከአፍጋኒስታን የምታስወጣው።

ቀነ ገደቡ ፣ ባለፈው ዓመት የትራምፕ አስተዳደር እና የታሊባን መሪዎች ከተስማሙበት ግንቦት 1 ለወራት ዘግይቶ የሚፈጸም ነው።

ከ20 ዓመታት በኋላ ፣ ወደ ትሪሊዮን ዶላሮች ካወጣችበት ፣ 2 ሺ 300 አሜሪካውያንን ህይወት ካጣችበት እና በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ የአፍጋን ዜጎች ህይወታቸውን ከተነጠቁበት በኋላ አሜሪካ ጦርነቱ ይበቃል ብላለች።

ጆ ባይደን ፥ "... ወደ ጦርነት የሄደነው ግልጽ ግብ ይዘን ነው፡፡ ግባችንን አሳክተናል፡፡ ቢላደን ሞቷል፡፡ አልኬዳ በኢራቅ እና አፍጋኒስታን ውስጥ ተመናምኗል፡፡ ስለዚህ ይህ የሁልጊዜው ጦርነት መቆሚያው ጊዜ ነው" ብለዋል።

በሌላ በኩል : የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን አስቀድሞ ይፋ ባልተደረገ ጉብኝት አፍጋኒስታን ካቡል ገብተዋል።

ሚኒስትሩ አሜሪካ የቀሩትን ወታደሮች የምታስወጣ ቢሆንም ከአፍጋኒስታን ጋር ያላት ግንኙነት እና አጋርነት እንደሚቀጥል ቁርጠኝነቷን ገልፀዋል።

ብሊንከን ፤ ከአፍጋኒስታን ፕሬዝዳንት አሽራፍ ጋኒ እና ሌሎች ባለስልጣናት ጋር የተወያዩ ሲሆን ፥ "አጋርነታችን እየቀያየረ ነው ነገር ግን ዘላቂ አጋርነት ሆኖ ይቆያል" ማለታቸውን ቪኦኤ ዘግቧል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
ለሰዎች ህይወት ማለፍ ምክንያት እንዳይሆኑ ይጠንቀቁ !

[Purpose - Tikvah]

የህመም ስሜት ከተሰማዎት ፣ የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ - 19) ምልክት ከታየቦት ወይም እራሶን በኮቪድ-19 ከጠረጠሩ እባክዎትን በቤትዎ በመቆየት ወረርሽኙ እየተዛመተ ያለበትን ፍጥነት በመቀነስ ኃላፊነትዎን ይወጡ።

በቤትዎ ሲቆዩ ሌሎች ቤተሰቦችዎን ለመጠበቅ እራስዎን ለይተው ይቀመጡ።

በሽታው ከሚታሰበው በላይ የሰዎችን ህይወት እያጠፋ፣ ልጆችን ያለእናት እና አባት እያስቀረ፣ ወላጆችን ያለ ልጅ እያስቀረ፣ በርካቶችንም በህመም እያሰቃየ ነው።

ዘውትር የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ (ማስክ) ማድረግዎን፣ ሰዎች ከተሰበሰቡበት ቦታ አለመገኘትዎን ፣ በየትኛውም አጋጣሚ የእጆችዎን ንፅህና መጠበቅዎን ፣ በየትኛውም ቦታ አካላዊ ርቅትዎን መጠበቅዎን እንዳይዘነጉ።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#MoSHE

የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በ2013 ዓ/ም አዲስ የዩኒቨርስቲ ገቢ ተማሪዎች የዩኒቨርስቲ ምርጫቻውን በዩኒቨርስቲዎች ልየታ መሰረት እንዲያስተካክሉ ማሳሰቢያ አስተላልፏል።

ይህን ማስፈንጠሪያ በመጫን ያንብቡ https://telegra.ph/MoSHE-04-16 ወይም ከላይ በቪድዮ የተያያዘው ይመልከቱ።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#Tigray

የሰኞው የአድዋ ከተማ ግድያ :

• "የኤርትራ ወታደሮች ሰኞ ዕለት በአድዋ ከተማ ነዋሪዎች ላይ ድንገተኛ ጥቃት ከፍተው 3 ሰዎች ገድለዋል ፤ 19 አቁስለዋል" - አምነስቲ ኢንተርናሽናል

• "... የኤርትራ ወታደሮች በአድዋ ሰላማዊ ዜጎችን ገድለዋል ፥ በወቅቱ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጣልቃ ባይገባ ኖሮ ተጨማሪ ሰላማዊ ዜጎች ይገደሉ ነበር" - የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ባለስልጣን

• የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገ/መስቀል ፤ የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ መኖር አለመኖራቸውን በተመለከተ በቀጥታ ምላሽ ባይሰጡም በአጠቃላይ "የኤርትራ ወታደሮች ሰላማዊ ሰዎችን በፍፁም አይገድሉም" ብለዋል።

• “የህወሃት ደጋፊዎች እና ምንጮች የሚናገሩትን ማረጋገጥ አልችልም” - ቢለኔ ስዩም

የፔካ ሐቪስቶ ቃለምልልስ :

• "...በጉብኝቴ ወቅት የኤርትራ ወታደሮች ከትግራይ ክልል መውጣታቸውን የሚያረጋግጥ ምስክር ማየትም ሆነ መስማት አልቻልኩም" - ፔካ ሐቪስቶ

የተመድ ፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ :

• "...የኤርትራ ወታደሮች መውጣታቸውን የሚያመለክት ነገር የተባበሩት መንግሥታት ተቋማትም ሆኑ ሌሎች ከእኛ ጋር አብረው የሚሰሩ የሰብአዊ እርዳታ ድርጅቶች አላዩም" - ማርክ ሎውኮክ

• በትግራይ የአስገድዶ መድፈርና ጾታዊ ጥቃቶችን የተመለከቱ ሪፖርቶችን ተከትሎ የኤርትራ ወታደሮች 'በአስቸኳይ' ከኢትዮጵያ ለቀው እንዲወጡ ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ ጠይቀዋል።

• አምባሳደር ታዬ ትላንት በፀጥታው ም/ቤት ስለቀረበው ገለፃ ፥ “ገለጻው የመንግስትንና የሌሎች ሰብዓዊ አጋሮችን ጥረት ዝቅ ያደረገ እና የሚያደናቅፍ” ነው ብለዋል።

ያንብቡ : telegra.ph/Tigray-Report-04-16

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
አሜሪካ ለኢትዮጵያ የ20 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ይፋ አደረገች።

አሜሪካ ያደረገችው የ20 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ለኢትዮጵያ የጤና ዘርፍ እንደሚውል ተሰምቷል።

ይህ ከአሜሪካ የበሽታዎች መከላከል ማዕከል (CDC) ይፋ የተደረገው ድጋፍ ኮቪድ -19ን ለመከላከል እና የአገሪቱ የህብረተሰብ ጤና አቅምን ለማጠናከር እንደሚያግዝ ነው የተገለፀው።

መረጃው በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ነው።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT