የሀገረ አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ከነገ ጀምሮ የ2012 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ውጤትን አስመልክቶ የሚያቀርቡትን አቤቱታዎችን ማስተናገድ ይጀምራል።
ኤጀንሲው አቤቱታዎችን የሚያስተናግደው ከነገ መጋቢት 28/2013 ዓ/ም እስከ ሚያዚያ 5 ቀን 2013 ዓ/ም ድረስ ነው።
የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስርጭትን ከግምት በማስገባት ኤጀንሲው አቤቱታዎችን የሚያስተናግደው በድህረ ገፁ www.neaea.gov.et ላይ መሆኑን ያሳወቀ ሲሆን ፤ አቤቱታ ያላቸው ተፈታኞች ዘውትር በስራ ሰዓት በድህረገፁ በመግባት 'compliant' የሚለውን በመጫን በሚፈጠረው ቅፅ አቤቱታ ማቅረብ ይችላሉ ተብሏል።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT

ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) አረፉ፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርስቲ እና የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የበላይ ጠባቂ ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
ከአባታቸው ከባራምባራስ ተስፋ ተክሉ እና ከእናታቸው ከወይዘሮ ታህሣ ኃይሉ በ1930 ዓ.ም ግንቦት ወር በትግራይ ክልል ብዘት ወረዳ የተወለዱት ብፁዕነታቸው በተወለዱ በ83 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም ማረፋቸውን ቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት አሳውቋል።
በሌላ በኩል ቅዱስ ሲኖዶስ የብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) እረፍት አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።
ቅዱስ ሲኖዶስ በወሰነው መሠረት የብፁዕነታቸው የቀብር ሥነ ሥርዓት ነገ መጋቢት መጋቢት 29 ቀን 2013 ዓ.ም ከቅዳሴ በኀላ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቅዱሳን ፓትርያርኮች በተገኙበት ይፈጸማል፡፡
የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ መግለጫቸውን ያቀረቡ ሲሆን በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ብፁአን አባቶች እና የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻቸው በብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ ሽኝት እንዲገኙ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ዛሬ መጋቢት 28 ቀን 2013 ዓ.ም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ብፁአን ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት ጸሎተ ፍትሐት ይከናወናል ተብሏል። ~ EOTC TV
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

"...የጽኑ ህሙማን ቁጥር ካለው የህክምና አቅም በላይ ነው" - ዶ/ር ሚዛን ኪሮስ
ኢትዮጵያ በኮቪድ -19 በሚያዙና እና በፅኑ ህሙማን ቁጥር ከአፍሪካ ቀዳሚ መሆኗን በጤና ሚኒስቴር የኮቪድ -19 ምላሽ ግብረ-ሃይሎች አስተባባሪ ዶክተር ሚዛን ኪሮስ አስታወቁ።
የቫይረሱ ስርጭት በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ ምጣቱንም አመልክተዋል።
የበሽታው ስርጭት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ ስርጭቱ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ጠቋሚ ነው ብለዋል፡፡
የምርመራ ውጤቶች ከቀን ቀን የሚሊያዩ ቢሆንም ባለፉት ሶስት ሳምንታት በተለይ በአዲስ አበባ እና በሃዋሳ የቫይረሱ ስርጭት በከፍተኛ ደረጃ ማሻቀቡን አመልክተዋል።
በሚፈለገው ልክ ምርመራዎች እየተካሄዱ ባለመሆናቸው እንጂ በሌሎች ክልሎችም የበሸታው ስርጭት እየጨመረ ስለመምጣቱ ጠቋሚ ምልክቶች እንዳሉ ገልፀዋል።
የቫይረሱን አጠቃላይ ትክክለኛ ስርጭት ለማወቅ በቅርቡ ሰፊ ሀገራዊ ጥናት እንደሚካሄድ ጠቁመዋል፡፡
ባለፈው ወር ብቻ ከሚወሰዱ የደም ናሙናዎች ውስጥ ከመቶ ምርመራዎች ውስጥ በሃያ ስድስቱ ውስጥ ቫይረሱ መገኘቱን ያመለከቱት አስተባባሪው፣ በተመሳሳይ በቀን እስከ 2ሺ 300 የሚሆኑ ዜጎች በበሽታው እየተያዙ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
የጽኑ ህሙማን ቁጥርም ካለው የህክምና አቅም በላይ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
ወረርሽኙ ከጀመረ ወዲህ በበሽታው በቀንና በሳምንት የሚሞተው የሰው ቁጥር መጨመሩ የበሽታው ስርጭት እንደሀገር ከተፈጠረው የህክምና አቅም በላይ እየሆነ መምጣቱን የሚያሳይ መሆኑንም አስተባባሪው ጠቁመዋል፡፡ ~ EPA

TIKVAH-ETHIOPIA
"...የጽኑ ህሙማን ቁጥር ካለው የህክምና አቅም በላይ ነው" - ዶ/ር ሚዛን ኪሮስ ኢትዮጵያ በኮቪድ -19 በሚያዙና እና በፅኑ ህሙማን ቁጥር ከአፍሪካ ቀዳሚ መሆኗን በጤና ሚኒስቴር የኮቪድ -19 ምላሽ ግብረ-ሃይሎች አስተባባሪ ዶክተር ሚዛን ኪሮስ አስታወቁ። የቫይረሱ ስርጭት በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ ምጣቱንም አመልክተዋል። የበሽታው ስርጭት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ ስርጭቱ አሳሳቢ ደረጃ…
ዶክተር ሚዘን ኪሮስ በጤና ሚኒስቴር የኮቪድ -19 ምላሽ ግብረ-ሃይሎች አስተባባሪ ለኢፕድ ከተናግሩት ፦
"...የአስክሬን ምርመራዎች ቢካሄዱ እና የምርመራ አቅሙ ቢያድግ አሁን እየተመዘገበ ካለው በላይ ሞት ሊመዘገብ ይችላል። በጤና ሚኒስቴር በኩል እየተደረገ ያለው ሪፖርት የችግሩን ትክክለኛ ስፋት የማያሳይ መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል።
በዚህ አነስተኛ ሪፖርት እየተመዘገበ ያለው በበሽታው የሚያዙና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር የበሽታው ስርጭት ምን ያህል በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ መምጣቱን የሚጠቁም ነው።
ለበሽታው መቀነስ አስፈላጊ ናቸው ተብለው የሚታመኑ መሰረታዊ የመከላከያ መንገዶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሱ መምጣታቸው ለስርጭቱ መጨመር ትልቅ አስተዋፅኦ አበርክቷል።
ሰዎች መሰረታዊ የጥንቃቄ መንገዶችን ካልተከተሉ፣ ህግን የተከተሉ ጠንካራ እርምጃዎች ካልተወሰዱና የመንግስት ስብሰባዎች በውስን ቁጥር ካልተካሄዱ በቀጣይ በሽታው በከፍተኛ ደረጃ ዋጋ ሊያስከፍል ይችላል"
@tikvahethiopia

#ችሎት
ዐቃቤ ህግ በእነ ጃዋር መሀመድ ላይ በዝግ ችሎት ላሰማ ያለው የምስክር የአሰማም ሂደት ጥያቄ በፍርድ ቤት ውድቅ ተደረገ።
ዐቃቤ ህግ ባለፈው ቀጠሮው በምስክር ጥበቃ አዋጅ መሰረት ለምስክሮቼ ደህንነት ሲባል ከመጋረጃ በስተጀርባ እና በዝግ ችሎት ምስክሮቼን ላሰማ ሲል አቤቱታ አቅርቦ ነበር፡፡
ተከሳሾቹ የመከላከል መብታችንን የሚገድብ እና የዐቃቤ ህግ አቤቱታ ታማኝነት የለውም በማለት የዐቃቤ ህግ አቤቱታ ውድቅ እንዲደረግ አመልክተው ነበር።
የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ የጸረ ሽብርና የህገ መንግስት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ጥያቄውን መርምሮ ውድቅ አድርጎታል፡፡
ችሎቱ በዛሬው እለት ተሰይሞ አቶ ጃዋር መሀመድን ጨምሮ ሁሉም ተጠርጣሪዎች በተገኙበት ጉዳያቸውን ተመልክቷል፡፡
በዚህም ዐቃቤ ሕግ ባለፈው ቀጠሮ በምስክር ጥበቃ አዋጅ 699/2003 አንቀጽ 4 /1 ሸ እና ቀ መሰረት ለ146 ምስክሮች ጥበቃ ተደርጓል ብሎ ከመጥቀስ በዘለለ ምስክሮች ላይ የሚደርሰውን ጉዳት በማስረጃ ያላስደገፈ በመሆኑ በቂ ምክንያት ሆኖ አላገኘሁትም ሲል ፍርድ ቤቱ ምስክሮቹ በግልጽ ችሎት ምስክርነታቸውን እንዲሰጡ ብይን ሰጥቷል።
ነገር ግን ተከሳሾቹ የምስክር ዝርዝር ይገለጽልን ብለው ያቀረቡት አቤቱታን በተመለከተ ግን ፍርድ ቤቱ የምስክር ዝርዝር ለምስክሮች ደህንነትና መብት ጥበቃ ሲባል የምስክሮች ማንነት እንዳይገለጽ ሲል ጥያቄውን ውድቅ አድርጎታል።
በዚህ መሰረት የምስክሮች ዝርዝር ሳይገለጽ ምስክርነታቸው በግልጽ ችሎት እንዲሰማ ሲል ፍርድ ቤቱ ብይን መስጠቱን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

የእነአቶ እስክንድር ነጋ የፍርድ ሂደት ፦
ዛሬ መጋቢት 28 ረፋድ በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሁለተኛ ወንጀል ችሎት ሊዳኝ የነበረው የእነ አቶ እስክንድር ነጋ ጉዳይ ከሦስቱ ዳኞች መካከል አንዱ ባለመገኘታቸው ለሚያዝያ 6 ቀን 2013 ዓ.ም. ተራዝሟል።
ይግባኝ ለማከራከር የተቀጠረው መዝገብ ሳይከፈት በቀጥታ ለቀጣዩ ችሎት ተዘዋውሯል።
የተከሳሽ ጠበቆች ዳኞች ከቀትር በኋላ ተሟልተው እንዲቀርቡ፣ ይህ ካልተቻለም ነገ እንዲቀርቡ፣ እነኝህን አማራጮች ማድረግ ካልተቻለ ግን ችሎቱ ተከሳሾችን በነፃ እንዲያሰናብታቸው ጠይቀዋል። ሆኖም ዳኞች ውድቅ አድርገውታል።
ባሉበት እስር ቤት ሆነው በፕላዝማ የቀረቡት እነ እስክንድር ነጋ በበኩላቸው ጉዳዩ ከ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ጋር የተያያዘ መሆኑን እና ላለፉት ዘጠኝ ወራት ያለ ውሳኔ በቀጠሮዎች እየተጉላሉ መሆኑን ጠቅሰው አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።
ስድስት ኪሎ በሚገኘው ጠቅላይ ፍርድ ቤት በአካል መቅረብ ሲገባቸው ችሎቱን በፕላዝማ እንዲከታተሉ መደረጉም ስህተት እንደሆነ ተናግረዋል። በቀጣዩ ችሎት ፖሊስ በአካል እንዲያቀርባቸው ጠይቀዋል።
አፋጣኝ ፍትሕ እንዲሰጣቸው ከወራት በፊት ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንቷ በቀጥታ ደብዳቤ መፃፋቸውን አስታውሰዋል።
የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) አመራሮች እስክንድር ነጋ፣ ስንታየሁ ቸኮል፣ አስቴር ስዩም እና አስካለ ደምሌ የፊታችን ሚያዝያ 11 ቀን 2013 ዓ.ም. በከፍተኛው ፍርድ ቤት ችሎት እንደሚቀርቡ ከባልደራስ ያገኘነው መረጃ ያሳስያል።

የኦነግ ስራ አስፈፃሚ አባል አቶ አብዲ የፍርድ ሂደት ፦
አቶ አብዲ ረጋሳ ከተከሰሱበት ሶስት ክሶች 1 ውድቅ ሲደረግ በሌላኛው ፍርድ ቤት እየተመለከተው ነው።
ትላንት አቶ አብዲ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ወንጀል ችሎት ቀርበው ነበር ፤ የመከላከያ ምስክሮችን ለማሰማት በተያዘው በዚሁ ቀጠሮ ምስክሮች ባለመገኘታቸው ፍርድ ቤቱ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
ጠበቃቸው ቱሊ ባይሳ የመከላከያ ምስክሮች ያልቀረቡበት ምክንያት አስረድተዋል ፦
- ኮሎኔል ገመቹ አያና በፌዴራል ማረሚያ ቤት የቂሊጦ ማረሚያ የኦሮሚያ ጠ/ፍርድ ቤት በፃፈው ደብዳቤ የደረሰን ትዕዛዝ የተፈረመው በዳኛ ሳይሆን በህግ ኦፊሰር ነው ስለዚህ በዚህ ትዕዛዝ እንደማያቀርብ በማሳወቁ ነው። ኮሎኔል ገመቹ የታሰሩት በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ስለሆነ ፍርድ ቤቱ ኮሎኔሉ ለኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቀርበው የምስክርነት ቃላቸውን እንዲሰጡ መፍቀድ ነበረበት አይቀርብም የሚል ደብዳቤ ልካል።
- ሌላው ኦነግ ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ናቸው። የፍርድ ቤት ትዕዛዝ አውጥቶ የአቶ አብዲ ቤተሰቦች መጥሪያውን ይዘው ወደ አቶ ዳውድ ቤት ቢሄዱም የመንግስት ፀጥታ ኃይሎች አካባቢውን በመቆጣጠራቸው ወደ ቤት ገብተው መጥሪያ መስጠት እንዳይችሉ እንደተከለከሉ ቤተሰቦቻቸው ተናግረዋል።
አቶ አብዲ ረጋሳ ከታሰሩ ከ1 ዓመት በላይ ሲሆናቸው በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ፍርድ ቤቶች ሲቀርቡ ቆይተዋል።
3 ጊዜ የዋስትና መብት ተፈቅዶላቸው መዝገባቸውም ተዘግቶ ነበር።
More : https://telegra.ph/AtoAbdiRegassa-04-06

በአፋር እና ሱማሊ ክልል መካከል ያለው ውጥረት ፦
የአፋር ክልል መንግስት ፦
- በክልሉ "ሀሩቃ" በተባለ ቦታ ባለፈው አርብ በተሰነዘረ ጥቃት በትንሹ 30 ሰዎች መገደላቸውን እና ከ50 በላይ የአካባቢው ነዋሪዎች መቁሰላቸውን የአፋር ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።
- በአርቡ ጥቃት ከተገደሉት ውስጥ ሴቶች እና ህጻናት ይገኙበታል።
- የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል አባላት በዚያኑ ዕለት ምሽት "ገዋኔ" በተባለ ቦታ በከፈቱት ተኩስ ሁለት የክልሉ መንግስት ሰራተኞች መገደላቸውን አሳውቋል።
- ጥቃት ሲፈጽም ነበር የተባለ አንድ የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል አባል “እጅ ከፍንጅ” ተይዟል፤ ግለሰቡ በአሁኑ ወቅት “በፖሊስ ቁጥጥር ስር” ይገኛል። የአካባቢው ህብረተሰብ በወሰደው የመከላከል እርምጃ ሌሎች የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል አባላት ተገድለዋል።
- መሰል ጥቃቶች ከዚህ ቀደምም በአካባቢው በተደጋጋሚ ይከሰቱ ነበር ፥ መንስኤው ከሶማሌ ክልል መንግስት የመሬት ይገባኛል ጥያቄ ጋር የተያያዘ ነው።
የሱማሊ ክልል መንግስት ፦
- አርብ መጋቢት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ደአዋዲ እና ቀረፋ በተበሉ ቀበሌዎች ፤ ዛሬ መጋቢት 28 ጠዋት በደዋዲድ ፣ በገውረአን ፣ በቀላሌና በደንለሄላይ በሚባሉ 4 ቀበሌዎች በሚኖሩ ንፁሃን ነዋሪዎች ላይ የአፋር ክልል ልዩ ሀይል ግድያ፣ የአካል ጉዳትና የንብረት ውድመት ፈፅሟል ሲል ከሷል።
- አርብ መጋቢት 24 ቀን 2013 ዓ/ም ደአዋዲ እና ቀረፋ በተባሉ ቀበሌዎች በኑፁሃን ዜጎች ላይ በተፈፀመው ጥቃት ከ25 በላይ አርብቶ አደሮች ሲገደሉ ከ30 በላይ የሚሆኑ አርብቶ አደሮች ደግሞ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፤ ንብረትም ወድሟል ብሏል።
- ዛሬ መጋቢት 28 ቀን 2013 ዓ/ም ጠዋት የአፋር ክልል ልዩ ፖሊስ በአራት ቀበሌዎች በደዋዲድ፣ በገውረአን ፣ በቀላሌና በደንለሄ ላይ ስፊ ጥቃት በመፈፀም ለጊዜው ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ በርካታ ንፁሀንን ገድለዋል ብሏል።
- ጉዳዩ ወደለየለት ግጭት ከማምራቱ በፊት የአፋር ብሄራዊ ክልል መንግስት ያስብበት ፤ የፌደራል መንግስት የመፍትሔው አካል ለመሆን እንዲሰራ ብሏል።
** እስካሁን ድረስ በሁለቱ ክልሎች መካከል ስላለው እና የሰዎችን ህይወት እየቀጠፈ ስላለው ግጭት በፌዴራል መንግስቱ በኩል ምንም የተባለ ነገር የለም።
ተጨማሪውን ያንብቡ👇
https://telegra.ph/Afar-Somali-04-06-2

Telegraph
Afar-Somali
በሱማሊ እና አፋር ክልል መካከል ያለው ውጥረት ! ዛሬ የሱማሌ ክልል መንግስት የአፋር ክልላዊ መንግስት በክልሉ ነዋሪዎች ላይ እያደረሰ ያለውን ግድያና ማፈናቀል አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል። መግለጫው ሲጀምር ፥ "ባለፈዉ አርብ መጋቢት 24 - 2013 ዓ.ም ደአዋዲ እና ቀረፋ በተበሉ ቀበሌዎች ላይ እንዲሁም ዛሬ መጋቢት 28 ጠዋት በደዋዲድ ፣ በገውረአን ፣ በቀላሌና በደንለሄላይ በሚባሉ አራት የክልላችን…
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE ግብፅ በኪንሳሻ የተጀመረው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ውይይት ሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት ከመደረጉ በፊት ስምምነት ላይ ለመድረስ የመጨረሻው እድል ሊሆን ይችላል ብላለች። ግብፅ ይህን ያለቸው ግብፅ ፣ ኢትዮጵያና ሱዳን በታላቁ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ እየተደረገ የሚገኘውን ውይይት አስመልክታ ባወጣችው መግለጫ ነው። ዛሬ ሰኞ እንደሚጠናቀቅ በሚጠበቀው ውይይቱ 3ቱ ሃገራት በዕድሉ ተጠቅመው ከመጪው ክረምት…
#Update
በኪንሻሳ ሲካሄድ የነበረው የታላቁ የህዳሴ ግድብ የሶስትዮች ውይይት ያለስምምነት መጠናቀቁን የሱዳንና የግብጽ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሮች አስታውቀዋል፡፡
ኢትዮጵያ እስካሁን ውይይቱን በተመለከተ መግለጫ አላወጣችም፡፡
ሱዳን፣ ኢትዮጵያ በኪንሻሳው ውይይት ላይ ስምምነት ላይ ለመድረስ የሚያስቸግር ግትር አቋም አራምዳለች ብላ ስትከስ ፤ ግብጽ ደግሞ ኢትዮጵያ ሁሉንም የድርድር ሂደት አማራጮች ውድቅ ማድረጓን አስታውቃለች፡፡
የግብጽ የውጭ ጉዳይ ቃልአቀባይ አምባሳደር አህመድ ሀፌዝ በኪንሻሳ የተካሄደው ድርድር ምንም መሻሻል አላሳየም፤ድርድሩን ለመጀመርም ስምምነት ላይ አልተደረስም ብለዋል፡፡
ቃል አቀባዩ ኢትዮጵያ በሱዳንና በግብጽ በኪንሻሳ የሚመራና በ4 አካላት አደራዳሪነት ድርድሩ ይካሄድ የሚለውን ሀሳብ ባለመቀበሏ ስምምነት ሳይደረስ መውረቱን ገልጸዋል፡፡
ቀደም ሲል ኢትዮጵያ፣ ተመድ ፣ የአውሮፓ ህብረት፣ አሜሪካና የአፍሪካ ህብረት በህዳሴ ግድቡ ጉዳይ በአደራዳሪነት ይግቡ የሚለውን ሀሳብ እንደማትቀበል በውጭ ጉዳይ ሚኒቴሯ በኩል ማስታወቋ ይታወሳል፡፡
ምንጭ፦ አል ዓይን

#የቅጥር_ማስታወቂያ
የአማራ ክልል ጤና ቢሮ 265 ጠቅላላ ሀኪሞችን #በቋሚ_ቅጥር ለመቅጠር ማስታወቂያ አውጥቷል።
የትምህርት ደረጃ ፥ የመጀመሪያ ዲግሪ በጠቅላላ ሃኪም ሙያ የተመረቀ እና የሙያ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል።
የስራ ልምድ 0 ዓመት ፤ ደመወዝ 9,056 ብር ሲሆን መመዝገቢያ ቀን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ የስራ ቀናት በሁሉም ዞን ጤና መምሪያ እና ከተማ አስተዳደሮች ነው።
የፈተናው ቀን በቀጣይ ይገለፃል።
በሌላ በኩል ፦
ክልሉ 217 ጠቅላላ ሃኪሞችን በ3 ወር ኮንትራት መቅጠር ይፈልጋል።
የትምህርት ደረጃ ፥ የመጀመሪያ ዲግሪ በጠቅላላ ሃኪም ሙያ የተመረቀ እና የሙያ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል ፤ የስራ ልምድ 0 ዓመት ፤ ደመወዝ ፣ 9,056 ብር ሲሆን ምዝገባው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ የስራ ቀናት በሁሉም ዞን ጤና መምሪያ እና ከተማ አስተዳደሮች ነው።
የፈተና ቀን በቀጣይ ይገለፃል።

ፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት 1ኛ የምርጫ ጉዳዮች ችሎት የባልደራስ ለእውነተኛ እና ዴሞክራሲ ፓርቲ ሊቀ-መንበር እስክንድር ነጋን ጨምሮ አራት በእስር ላይ የሚገኙ አመራሮች በመጪው ምርጫ በዕጩነት መወዳደር የለባቸውም ሲል ምርጫ ቦርድ የሰጠውን ውሳኔ አፅንቷል።
ፍርድ ቤቱ በጉዳዩ ላይ ውሳኔ የሰጠው፣ ፓርቲው የቦርዱን ውሳኔ በመቃወም ለፍርድ ቤት ይግባኝ በማቅረቡ ነው።
ዳኞች የይግባኙን ተገቢነት መርምረው የብሄራዊ ምርጫ ቦርዱን ውሳኔ ያጸኑት በአብላጫ ድምጽ መሆኑን ኤፍቢ ሲ ዘግቧል።

"...ጦሩ በፍጥነት አብዬን ለቆ እንዲወጣ እንፈልጋለን" - መሬም አልሳዲግ አልመሀዲ
ዛሬ ሱዳን በአብዬ ግዛት የሚገኘው የኢትዮጵያ ሰላም አስካባሪ ኃይል ከቦታው ለቆ እንዲወጣ ተመድን መጠየቋን በይፋ አስታውቃለች፡፡
ሱዳን ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰቸው በኪንሻሳ የተካሄደው የግድብ የሶስትዮሽ ድርድር ያለስምምነት መጠናቀቁን ተከትሎ ነው።
የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ኃይል በተመድ ስር በመሆን በሱዳን እና በደቡብ ሱዳን መካከል በምትገኘውና ሁለቱ ሀገራት ይገባኛል ጥያቄ የሚያቀርቡባት "አብየ ግዛት" በፈረንጆቹ በ2011 ጀምሮ ሰላም ለማስከበር ሰፍሮ ቆይቷል፡፡
ኢትዮጵያ በዚች ግዛት ሰላም እንዲሰፍን ከ4 ሺህ በላይ ጦር ወደ ሰፍራው አቅነቶ ሰላም በማስከበር ላይ ይገኛል።
የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ መሬም አልሳዲግ አልመሀዲ ፤ በአብዬ ግዛት ላይ በተሰማራው የኢትዮጵያ ሰራዊት ላይ እምነት የለንም ያሉ ሲሆን ጦሩ በፍጥነት አብዬን ለቆ እንዲወጣ እንፈልጋለን ብለዋል።
ሚኒስትሯ ፥ ኢትዮጵያ በድርድሩ ላይ ግትር አቋም አሳይታለች ፤ በኬንሻሳ የተካሄደው የሶሰትዮሽ ድርድር ያለስምምነት የተጠናቀቀው ኢትዮጵያ ስላልፈለገች ነው ብለዋል።
አክለው ኢትዮጵያ በሱዳን ላይ ብዙ ፍላጎት አላት ፤ሱዳን ጥቅሟን ለማስከበር ብዙ አማራጮችን ትጠቀማለች ሲሉ ተናግረዋል።
"ኢትዮጵያ ያለችበትን የውስጥ ችግር ሱዳን ተረድታ ለረጅም ጊዜ ታግሳለች ፤ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን ተቀብለናል ከእንግዲህ ግን ይህ ያበቃል በቀጥታ ብሔራዊ ጥቅማችንን ማስከበር ላይ እናተኩራለን" ማለታቸውን አል ዓይን በድረገፁ አስነብቧል።
More : https://telegra.ph/Ministry-of-Foreign-Affairs-Sudan-04-06

"...በጃዋር ላይ የቀረቡት ክሶች ከማንነቱ እና ስብዕናው ጋር የማይገናኙ ናቸው" - ወ/ሮ አርፋሴ ገመዳ
"ስታር ትሪቢዩን" የተባለ የአሜሪካ ጋዜጣ ፥ ወይዘሮ አርፋሴ ገመዳ በባለቤታቸው አቶ ጃዋር መሃመድ ላይ የቀረቡት ክሶች ከማንነት እና ስብዕናቸው ጋር የሚገናኙ አለመሆናቸውን ስለመናገራቸው ዘግቧል።
"ህዝባችን ለረጅም ጊዜ የሰቆቃ ኑሮ የገፋ በመሆኑ ጃዋር የህዝቡ ህይወት እንዲሻሻል በሰላማዊ መንግድ ሲታገል የቆየ ነው" ያሉት ወይዘሮ አርፋሴ ፥ "ጃዋር ሚኒሶታን ለቆ ወደ ኢትዮጵያ የተመለሰው ለዚሁ አላማ ነበር" ብለዋል።
አቶ ጃዋር፥ ለህዝቡ ህይወት መሻሻል ሲል የአሜሪካን ዜግነት ትቶ ወደኢትዮጵያ በመመለስ በሰላማዊ ፖለቲካ ውስጥ በመሳተፉ በአሁኑ ጊዜ ሀገር አልባ ሆኗል ያሉት ወ/ሮ አርፋሳ፥ ለህዝባዊ አላማው ብሎ የአሜሪካን ዜግነቱን በመቀየሩ በጉዳዩ ላይ ጠንካራ የአሜሪካን መንግስትን ድጋፍ ለማግኘት እንዳልተቻለ ገልፀዋል።
ወይዘሮ አርፋሴ እና አቶ ጃዋር ፥ የአራት ዓመት ልጅ ያላቸው ሲሆን ልጁ አባቱ ለምን እንደጠፋ ለሚያነሳው ጥያቄ ምላሽ መስጠት አስቸጋሪ እና አሰቃቂው የህይወቴ አካል ነው ሲሉ ተናግረዋል።

#ItsMyDam🇪🇹
"...በጉዳዩ ላይ ይጮሃሉ ፣ ያስፈራራሉ ፣ ማስፈራሪያው ድሮም የነበረ ነው" - የውሃ ጥናት ባለሞያ ፈቅ አህመድ ነጋሽ
ኢትዮጵያ ባለፉት 10 ዓመታት በሀገር ውስጥ እና በውጭ የሚነሱ ጫናዎችን ተቋቁማ የመጀመሪያውን የውሃ ሙሌት አካሂዳለች።
አሁን ኢትዮጵያ ለሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት እየተዘጋጀች ነው።
ለ2ኛው ዙር የውሃ ሙሌት የተያዘው ጊዜ እየተቃረበ ሲመጣ የታችኞቹ ተፋሰስ ሀገራት በኢትዮጵያ ላይ ጫና እያበረቱ ይመጣሉ።
የውሃ ጥናት ባለሞያው ፈቅ አህመድ ነጋሽ ፥ "... ግድቡ እስከተገነባ ድረስ የውሃ ሙሌቱን መከልከል እንደማይቻል ግብፆቹም ሆነ ሱዳኖች ጠንቅቀው ያውቃሉ" ብለዋል።
ባለሞያው ፥ "...በጉዳዩ ላይ ይጮሃሉ ፣ ያስፈራራሉ ፣ ማስፈራሪያው ድሮም የነበረ ነው፤ ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ደግሞ ማስፈራሪያ ሲኖር ይፈራል ፤ ሀገራቶቹ ድንገት ወደግጭት ይገቡና ኃላ የራሳችን ችግር ይሆናል ብለው ስለሚፈሩ፥ ኢትዮጵያ ላይ ጫና ይፈጥራሉ የሚል እምነት ስላላቸው ነው"ሲሉ ገልፀዋል።
አክለውም፥ "የኢትዮጵያ ህዝብ ይህን እንደሉአላዊነት በቆጠረው ጉዳይ ላይ መስዋዕትነት ለመክፈል ዝግጁ ነው ፤ መሀል ላይ የሚፈጠሩ የፖለቲካ ጉዳዮች የሚያመጣቸው ውዥንብሮች ቢኖሩም ህዝቡ ግን ምንጊዜም ከድጋፍ ወደኃላ አይልም" ሲሉ ለዋልታ ቲቪ ተናግረዋል።