የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ህዝበ ውሳኔ ፦
የኢትዮጵያ 11ኛው ክልል ሊመሰረት የሚያስችለው የሪፈረንደም (ህዝበ ወሳኔ) ምርጫ ሊደረግ 65 ቀናት ገደማ ይቀሩታል።
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ህዝበ ውሳኔውን የሚያደራጅ በቦርዱ ስር የፕሮጀክት ቢሮ አቋቁሞ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ወ/ሪት ሶሊያና ሽመልስ ለፋና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።
ይህ የፕሮጀክት ቢሮ ዋናው የሀገር አቅፍ ምርጫ በሚካሄድበት ወቅት ባሉ የኦፕሬሽናል ስራዎች እንዳይዋጥ የሚያስችል ነው።
እስከሁን በፕሮጀክት ቢሮው ፤ የህዝበ ውሳኔ በጀት ተዘጋጅቶ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተልኳል እንዲሁም የህዝበ ውሳኔው አክሽን ፕላን (እቅድ) ተዘጋጅቷል።
ቦርዱ ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የህዝበ ውሳኔ ምርጫ ያዘጋጀው በጀት 8 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ነው። ገንዘቡ ከሌሎች የህዝበ ውሳኔ ምርጫ ጋር ሲነፃፀር አነስተኛ ሲሆን ሪፈረንደሙ ከሀገር አቀፍ ምርጫው ጋር በአንድ ቀንና በአንድ አይነት ዝግጅት የሚካሄድ በመሆን የወጪ ብክነት አስቀርቷል ተብሏል።
ገንዘቡ በዋናው የምርጫ በጀቱ ውስጥ ስለሌለ ተጨማሪ በሚል ለተወካዮች ምክር ቤት አቅርቧል ፤ ምላሹን እየተጠባበቀ ይገኛል።
የሪፈረንደም ወጪ በቦርዱ አይሸፈንም ፤ ከዚህ በፊት የሲዳማ ክልል ሪፈረንደም ሲደርግ ወጪው የተሸፈነው በደቡብ ክልል ምክር ቤት ነበር።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የክልል ሪፈረንደም አሁን ላይ በምርጫ ምልክት መረጣ እና ውሳኔ ደረጃ ላይ ይገኛል። ምርጫ ቦርድ ከመራጩ ህዝብ ተወካዮች በኮሚቴ የቀረበለትን የባለ 6 እጆች ጥምረት ተቀብሎ መልሶ ለይሁንታ ልኮታል።
ምልክቱን ሲያፀድቁ የድምፅ መስጫ ወረቀት መታተም ይጀምራል።
የደቡብ ክልል የሚወከለው በ "ጎጆ" ነው።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
#Ethiopia🇪🇹 ዛሬ ከቀኑ በ10:00 ሰዓት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የማዳጋስካር አቻውን በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም የሚገጥም ይሆናል። ሀገራችን ኢትዮጵያ ለካሜሩኑ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጉዞ ለማለፍ 2 ወሳኝ ጨዋታዎች ይቀሯታል። ዛሬ ከማዳጋስካር ጋር የምታደርገው እና ከአንድ ሳምንት በኃላ መጋቢት 21 ከኮትዲቯር ጋር (በአቢጃን) የምታደርገው ነው። ሀገራችን…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ሁለት ጎል አስቆጥሯል።
በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከ #ማዳጋስካር አቻው ጋር እየተጫወተ የሚገኘው የሀገራችን ብሄራዊ ቡድን በኣማኑኤል ገ/ሚካኤል እና ጌታነህ አማካኝነት ሁለት ጎል ማስቆጠር ችሎ ጨዋታውን 2-0 በሆነ ውጤት እየመራ ነው።
ጨዋታውን ሂደት እና ውጤት በቲክቫህ ስፖርት በኩል መከታተል ትችላላችሁ @tikvahethsport
@tikvahethiopia
በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከ #ማዳጋስካር አቻው ጋር እየተጫወተ የሚገኘው የሀገራችን ብሄራዊ ቡድን በኣማኑኤል ገ/ሚካኤል እና ጌታነህ አማካኝነት ሁለት ጎል ማስቆጠር ችሎ ጨዋታውን 2-0 በሆነ ውጤት እየመራ ነው።
ጨዋታውን ሂደት እና ውጤት በቲክቫህ ስፖርት በኩል መከታተል ትችላላችሁ @tikvahethsport
@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኢትዮጵያ ሶስተኛ ጎል በአቡበክር ናስር አማካኝነት አገባች።
ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም #የማዳጋስካር አቻውን እያስተናገደ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በአቡበክር ናስር አማካኝነት 3ኛውን ጎል አግብቷል።
የመጀመሪያው የጨዋታው አጋማሽ በኢትዮጵያ የ3 ለ 0 መሪነት ተጠናቋል።
* ከላይ በቪድዮ የተያያዘው የጌታነህ ከበደ ሁለተኛ ጎል ነው።
More : @tikvahethsport
ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም #የማዳጋስካር አቻውን እያስተናገደ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በአቡበክር ናስር አማካኝነት 3ኛውን ጎል አግብቷል።
የመጀመሪያው የጨዋታው አጋማሽ በኢትዮጵያ የ3 ለ 0 መሪነት ተጠናቋል።
* ከላይ በቪድዮ የተያያዘው የጌታነህ ከበደ ሁለተኛ ጎል ነው።
More : @tikvahethsport
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ተጠናቀቀ | ኢትዮጵያ 4 - 0 ማዳጋስካር
ኢትዮጵያ ከማዳጋስካር ጋር ያደረገችውን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ 4 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፋለች። አራተኛው ጎል በሽመልስ በቀለ አማካኝነት የተገኘ ነው።
More : @tikvahethsport
ኢትዮጵያ ከማዳጋስካር ጋር ያደረገችውን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ 4 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፋለች። አራተኛው ጎል በሽመልስ በቀለ አማካኝነት የተገኘ ነው።
More : @tikvahethsport
አጫጭር የምርጫ 2013 መረጃዎች ፦
- ነገ መጋቢት 16/2013 ዓ/ም የ6ተኛው አጠቃላይ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ ይጀምራል። የመራጮች ምዝገባ ነገ ጀምሮ የሚጠናቀቀው ሚያዚያ 15 ቀን 2013 ዓ/ም ነው። (እንደምርጫ ቦርድ የጊዜ ሰሌዳ)
- የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የመራጮች ምዝገባ የሚያገለግሉ ቁሳቁሶችን ከትላንት ጀምሮ ለምርጫ ክልሎች ማሰራጨት ጀምሯል፡፡ ቦርዱ ለአንድ ወር ለሚቆየው የመራጮች ምዝገባ ለ673 የምርጫ ክልሎችና 50 ሺህ የሚሆኑ የምርጫ ጣቢያዎች የሚሆኑ የምርጫ ቁሳቁሶችን ነው ማጓጓዝ የጀመረው።
- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መጋቢት 14 ቀን 2013 ዓ.ም. ለመራጮች ምዝገባ ያለውን የቁሳቁስ ዝግጅት ለብዙኃን መገናኛ አካላት አስጎብኝቷል፤ በጉብኝቱ ወቅት የኮሚኒኬሽን ኃላፊዋ ወ/ሪት ሶሊያ ሽመልስ እንዲሁም የቦርዱ የሎጂስቲክ ድልድልና ሥርጭት ባለሙያ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
- በአፋር ክልል 8 ቀበሌዎች ሊከፈቱ የነበሩ 30 የምርጫ ጣቢያዎች እንዳይቋቋሙ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ውሳኔ አሳልፏል። በአካባቢው የሚኖሩ ዜጎች በአቅራቢያቸው ባለ ሌላ ቀበሌ መመዝገብ እና ድምጻቸውን መስጠት የሚችሉ መሆኑን አስታውቋል።
• በጋላእቶ/አዳይሌ
• በአዳይቱ/አዳይቱ
• በቴውኦ/አላሌ
• በጉርሙዳሊ/ዳንሌሄላይ
• በኡንዳፎኦ/ኡንዱፎ • በጋዳማይቱ/ጋርባኢሴ
• በአፍዓሶ/አፉአሴ
• በባላእቲ ጎና/መደኒ ቀበሌዎች ነው ሊከፈቱ የነበሩትን 30 የምርጫ ጣቢያዎች በአካባቢው እንዳይቋቋሙ የተወሰነው።
@Tikvahethiopia

#Attention አሰቦት ገዳም ዙሪያ የተነሳው እሳት ዛሬም ድረስ መቆጣጠር አልተቻለም ፤ እሳቱ አቅጣጫውን እየቀያየረ ለቁጥጥር አዳጋች አድርጎታል። ከቀናት በፊት የምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ደረጄ ብርሃኑ ለኢኦተቤ ቴቪ ፥ እሳቱ በሰው ኃይል ይጠፋል ብሎ ማሰብ የማይቻልበት ደረጃ መድረሱን አሳውቀው መንግሥት ተገቢውን ትኩረት በመስጠት ሌሎች አማራጮችን መጠቀም…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Attention
ይህ አጭር ቪድዮ የደብረ ወገገ አሰቦት ገዳም ሰደድ እሳትን የሚያሳይ ሲሆን ከምዕራብ ሐረርጌ ሀገረስብከት (EOTC TV) የተገኘ ነው።
ዛሬ ከሰዓት ላይ እንዳጋራናችሁ መረጃ እሳቱ በተለያየ አቅጣጫ እየተነሳ ለመቆጣጠር ፍፁም አስቸጋሪ ሆኗል ፤ በሰው ኃይል እሳቱን ማጥፋት ከባድ ስለሆነ ሌሎች አማራጮች እንዲፈለጉ ጥሪ ቀርቧል።
በሌላ በኩል ፦
በአንኮበር ወረዳ ወፍ ዋሻ ደን ላይ የተከሰተውን የእሳት አደጋ እስካሁን መቆጣጠር አልተቻለም።
ከጠዋቱ 12፡00 ጀምሮ በርካታ በጎ ፈቃደኛ የጎረቤላ ከተማ ወጣቶች ፣ የወረዳው መንግስት ሰራተኞችና እሳቱ በተከሰተበት አካባቢ ያሉ የዘጎ፣ የመሐልወንዝና የሐርአምባ ቀበሌ ነዋሪዎች ቦታው ድረስ በመሄድ እሳቱን ለማጥፋት የቆረጣ ስራና ልዩ ልዩ መንገዶች ሲጠቀሙ የነበሩ ቢሆንም እሳቱን ማጥፋት ከአቅም በላይ እንደሆነባቸው የአንኮበር ወረዳ አሳውቋል።
8 ሽህ 732 ነጥብ 28 ሄክታር ከሚሸፍነው ጠቅላላ ደን ውስጥ በአብዛኛው ማለትም 5 ሽህ 434 ነጥብ 78 ሄክታር (62.24%) በአንኮበር ወረዳ የሚገኘው የወፍ ዋሻ ጥብቅ ደን ከመጋቢት 13/2013 ዓ.ም እኩለ ቀን ጀምሮ በእሳት እየነደደ ይገኛል፡፡

የኤርትራ ጦር በአል ፋሽጋ ?
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) 'አል ፋሽጋ' አካባቢ የኤርትራ ወታደሮች ሰፍረዋል በማለት ሪፖርት አውጥቷል።
ይህ ቦታ ኢትዮጵያ እና ሱዳን በድንበር ጉዳይ የሚወዛገቡበት ነው።
የኤርትራ ጦር ሰፍረዋል የተባለው በአወዛጋቢው አል ፋሽጋ ልዩ ስሙ "ባርካት" በተባለ ቦታ እንደሆነ ነው የተገለፀው።
ብሉምበርግ በጉዳዩ ዙሪያ ከኤርትራ የኢንፎርሜሽን ሚኒስትር የማነ ገ/መስቀል ምላሽ ለማግኘት ስልክ ቢመታላቸውም ስልካቸው እንዳልተነሳለት አሳውቋል።
የተመድ ሪፖርት የወጣው ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ የኤርትራ ጦር ድንበር ተሻግሮ ወደ ኢትዮጵያ መግባቱን ለመጀመሪያ ጊዜ ካመኑ በኃላ ነው።
ትላንት ዶ/ር አብይ በፓርላማ በሰጡት ማብራሪያ ፥ ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር ወደ ጦርነት መግባት እንደማትፈልግ ገልፀዋል።
ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ ፥ "ሱዳን አሁን ባለችበት ሁኔታ ከጎረቤት ሀገር ጋር ለመዋጋት የሚያስችል ነገር ላይ አይደለም ያለችው በጣም ብዙ ችግር አለባት ፤ ኢትዮጵያም አሁን ባለችበት ሁኔታ ከሱዳን ጋር ለመዋጋት ብዙ ችግር አለባት ፤ ለሁለታችንም አይስፈልገንም በሰላም በንግግር መፍታት ነው የሚሻለው" ሲሉ ነው ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የተናግሩት።
የብሉምበርግ ዘጋባ : https://www.bloomberg.com/news/articles/2021-03-24/eritrea-forces-deployed-in-disputed-sudan-ethiopia-area-un-says
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT

#እጅግ_ከፍተኛ_ጥንቃቄ
ኢትዮጵያ ውስጥ የኮቪድ-19 ፅኑ ታማሚዎች 752 ደርሰዋል።
የኮቪድ - 19 ወረርሽኝ ኢትዮጵያ ከገባ ጊዜ አንስቶ ይህን ያህል የፅኑ ታማሚ ቁጥር አልተመዘገበም።
ባለፉት 24 ሰዓታት የ25 ሰዎች ህይወት ማለፉን ከጤና ሚኒስቴር የሕክምና አገልግሎት ዳይሬክተር ከሆኑት አቶ ያዕቆብ ሰማን (MoH) ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
በተጨማሪ ከተደረገው 7,659 የላብራቶሪ ምርመራ 1,981 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። ትላንት 1,052 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
ሁኔታው #አስከፊ ወደሆነ ደረጃ እየተሸጋጋረ ስለሆነ በምትችሉት አቅም ሁሉ እራሳችሁንና ቤተሰቦቻችን ከወረርሽኙ ጠብቁ እንላለን።

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ጊታ ፓስ በሶማሊ ክልል ፦
በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር የሆኑት አምባሳደር ጊታ ፓስ የተመራው ልዑክ በሶማሊ ክልል የአንድ ቀን የስራ ጎብኝት አድርጓል።
አምባሳደር ጊታ ጅግጅጋ ገራድ ዊልዋል አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የሶማሊ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ ናቸው አቀባበል ያደረጉላቸው።
አምባሳደር ጊታ በሶማሊ ክልል በነበራቸው ቆይታ ከክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ ጋር የተወያዩ ሲሆን፤ በክልሉ ያለው ወቅታዊ ሁኔታና አስተማማኝ ሰላም ፕሬዝዳንት ሙስጠፋ ገለፃ አድርገውላቸዋል።
አምባሳደሯና ልዑካቸው ከአለም የምግብ ድርጅት ኢትዮጵያ ዳይሬክተር ስቴቨን ዌሬ ጋር በመሆን በጅግጅጋ የሚገኘውን የአለም የምግብ ድርጅት የምግብ ማከማቻ መጋዘን ጎብኝተወል።
በአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት የተረዱ የምግብ ክምችትም ተዘዋውረው በመጎብኘት ገለፃም ተደርጎላቸዋል።
አምባሳደሯ በሶማሊ ክልል በነበራቸው የአንድ ቀን ይፋዊ የስራ ጉብኝት ከሶማሊ ክልል አደጋ ስጋት አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር አብዱልፈታህ ቢሂና ሌሎች የአሜሪካ ኢምባሲ ሰራተኞች በተገኙበት የቆሎጂ የተፈናቃዮች መጠለያ ጣቢያን ጎብኝተዋል።
በጉብኝታቸው ወቅት ከመጠለያ ጣቢያው ተወካዮች ጋር ተነጋግረዋል።
በሶማሊ ክልል የሚገኙትን ተፈናቃዮች ወደ ቀድሞው ህይወታቸው ለመመለስና እንደገና ለማቋቋም በሚሰራው ስራ አሜሪካ ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል አምባሳደር ፓስ።
በክልሉ ያለው የድርቅ አደጋ መልስ ለመስጠት የአሜሪካ መንግሥት ከክልሉ ይሰራል ብለዋል።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

ሰሜን ኮሪያ 2 የባላስቲክ ሚሳኤሎችን ወደ ጃፓን ባህር ላይ ተኮሰች።
ሰሜን ኮሪያ ጆ ባይደን የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ከሆኑ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሁለት የባሊስቲክ ሚሳኤሎችን በጃፓን ባህር ላይ እንደተኮሰች አሜሪካ እና ጃፓን ገለጹ።
በተመድ (UN) የፀጥታው ምክር ቤት ውሳኔ መሠረት ፒዮንግያንግ አስጊ መሳሪያዎች ተደርገው የሚቆተሩትን የባሊስቲክ ሚሳኤሎችን ከመሞከር ታግዳለች።
ጃፓን እና ደቡብ ኮሪያ ሙከራውን አውግዘዋል።
ይህ ሙከራ ሰሜን ኮሪያ ባሊስቲከው ያልሆኑ 2 ሚሳኤሎችን መተኮሷ ከተዘገበ ከጥቂት ቀናት በኋላ ነው።
በእስያ-ፓስፊክ አካባቢ ወታደራዊ ኃይሎችን በበላይነት የሚቆጣጠረው የአሜሪካ የፓስፊክ እዝ ሙከራው "የሰሜን ኮሪያ ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ መርሃ ግብር ለጎረቤቶቿ እና ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የሚያደርሰውን ሥጋት" አጉልቶ ያሳያል ብሏል።
ጃፓን በግዛቷ ውስጥ በሚገኝ የውሃ አካል ውስጥ ምንም ስብርባሪ እንዳልተገኘ ገልጻለች።
ይህን ሙከራ ተከትሎ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በጉዳዩ ላይ እስካሁን ያሉት ነገር የለም።
Via BBC

"...አፋጣኝ ፍትሕ ስጡን እና ከእስር ቤት ወጥተን ለምርጫው አስተዋፅኦ ማድረግ እንፈልጋለን" - አቶ እስክንድር ነጋ
የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) አመራሮች እስክንድር ነጋ፣ ስንታየሁ ቸኮል ፣ አስቴር ስዩም እና አስካለ ደምሌ ትላንት የከፍተኛ ፍርድ ቤት ችሎት ቀርበው ነበር።
ፍርድ ቤቱ ብይን መስጠት የሚችለው የጠቅላይ ፍርድ ቤቱን ውሳኔ ካወቀ በኋላ እንደሆነ በመጥቀስ ለሚያዝያ 11 ቀን 2013 ዓ.ም. ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።
አቶ እስክንድር ነጋ ፥ "አሁንም እድሎች ሙሉ በሙሉ አላለፉም፤ አፋጣኝ ፍትሕ ስጡን እና ከእስር ቤት ወጥተን ለምርጫው አስተዋፅኦ ማድረግ እንፈልጋለን" ሲሉ ጠይቀዋል።
የከፍተኛው ፍርድ ቤት ዳኞች በበኩላቸው ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ አፋጣኝ ምላሽ ከሰጠ እነርሱም ፈጣን ብይን እንደሚሰጡ ገልፀዋል።
አቶ ስንታየሁ ቸኮል ወቅቱ ዐብይ ፆም የሚጾምበት መሆኑን ጠቅሰው የምልኮ ስፍራ ወዳለበት የእስር ቤቱ ክፍል (ዞን) አራቱንም የህሊና እስረኞች እስር ቤቱ እንዲያዘዋውራቸው ጠይቀዋል። ይህ ካልሆነ በያሉበት የአምልኮ ስፍራ እንዲሰጣቸው ፍርድ ቤቱ ወህኒ ቤቱን ያዝዝ ዘንድ አሳስበዋል።
ወይዘሮ አስቴር ስዩም በበኩላቸው "የመደመር መንገድ የተባለው የጠቅላይ ሚንስትሩ መፅሐፍ እስር ቤት ውስጥ እየገባ ነው፤'ሀገር ስታምጥ' የተሰኘውን የእኔን መፅሐፍ ግን ማስገባት አልቻልኩም። ተከልክያለሁ። ለምን?" ሲሉ ጠይቀዋል።
ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/Balderas-Party-03-25

Telegraph
Balderas Party
"...አፋጣኝ ፍትሕ ስጡን እና ከእስር ቤት ወጥተን ለምርጫው አስተዋፅኦ ማድረግ እንፈልጋለን" - አቶ እስክንድር ነጋ የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ (ባልደራስ) አመራሮች እስክንድር ነጋ፣ ስንታየሁ ቸኮል ፣ አስቴር ስዩም እና አስካለ ደምሌ ትላንት የከፍተኛ ፍርድ ቤት ችሎት ቀርበው ነበር። ፍርድ ቤቱ ብይን መስጠት የሚችለው የጠቅላይ ፍርድ ቤቱን ውሳኔ ካወቀ በኋላ እንደሆነ በመጥቀስ ለሚያዝያ…
TIKVAH-ETHIOPIA
ሴናተር ክሪስ ኩንስ በኢትዮጵያ ፦ የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ጆ ባይደን በትግራይ ክልል ጉዳይ ግልፅ መረጃ ለማግኘት እንዲሁም በትግራይ ሰብዓዊ እርዳታ እንዲጠናከር ለማሳሰብ በሴናተክ ክሪስ ኩንስ የተመራ ልዑካ ወደ ኢትዮጵያ ልከዋል። ልዑኩ ትላንት ከሰዓት አዲስ አበባ የገባ ሲሆን ፥ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር ተወያይተዋል። በውይይቱ ኢትዮጵያ በትግራይ ክልል ስላለው…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የሴናተር ክሪስ ኩንስ የኢትዮጵያ ቆይታ ማብራሪያ ፦
By : Al Ain News Agency
ከአሜሪካ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን ወደ ኢትዮጵያ ተልከው ፣ በኢትዮጵያ የነበሩት ሴናተር ክሪስ ኩንስ የኢትዮጵያ ቆይታቸው ስኬታማ እንደነበር ገልጸዋል፡፡
ሴናተር ኩንስ ወደአሜሪካ ከተመለሱ በኋላ ከአሜሪካ ሴኔት የውጭ ግንኙነት ኮሚቴ ጋር በነበራቸው ስብሰባ ላይ ፣ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ እና ከሌሎች የኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለስልጣናት እንዲሁም የዓለማቀፍ ድርጅቶች ኃላፊዎች ጋር መወያየታቸውን ተናግረዋል፡፡
ሴኔቱ ኢትዮጵያን በተመለከተ በሚያሳልፈው ውሳኔ ላይ ለውጥ ለማድረግ የሚያስችል ሀሳብ እንዲሰጡ በውጭ ግንኙነት ኮሚቴው እንደተፈቀደላቸው ጠቅሰው ለዚህም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ በትግራይ ክልል ለተፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች የሚመለከታቸው አካላት ተጠያቂ እንደሚሆኑ መግለጻቸው ፣ በኢትዮጵያ ግዛት የኤርትራ ወታደሮች ስለመኖራቸው በይፋ መናገራቸውን ሴናተር ኩንስ በስብሰባው ላይ በአዎንታዊነት ጠቅሰዋል፡፡
ከሱዳን ጋር ላለው የድንበር ውዝግብ ዕልባት ለማምጣት እንዲሁም የታላቁን የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ አለመግባባት ለመፍታት የኢትዮጵያን ዝግጁነትም በአዎንታዊነት ነው ሴናተሩ ያነሱት፡፡
ይሁንና “አሁንም መፈታት ያለባቸው ጉዳዮች አሉ” ያሉት ሴናተሩ እነዚህም “የተሟላ የሰብዓዊ ድጋፍ ተደራሽነት፣ ግጭት ማቆም እና ነጻ፣ ፍትሀዊ ምርጫ የማድረግ ሽግግር” መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡ በነዚህ ጉዳዮች ላይ ከሴኔቱ ኮሚቴ ጋር በጋራ እንደሚሰሩና የተሻለ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል ያላቸውን ተስፋም ገልጸዋል፡፡

የፀጥታች ችግር ያላባቸው አካባቢዎች ፦ ባለፉት ቀናት ከፍተኛ የሆነ የፀጥታ መደፍረስ ፣ እና ከባድ የተኩስ ልውውጥ የነበረባቸው የአማራ ክልል አካባቢዎች ዛሬ ጋብ ብሎ ቢታይም አሁንም ግን አካባቢዎቹ ከስጋት ቀጠና አልወጡም። የሸዋሮቢት ከተማ ነዋሪዎች አሁንም የፀጥታ ስጋት እንዳለባቸው ለAMMA ተናግረዋል። ሱቆች፣ ሆቴሎች፣ እና ሌሎች አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ዝግ ናቸው። ዙጢ ከተማ ላይ የታጠቁ…
የጀውሃ ከተማ ፦
ጀውሃ ከተማ ከሰሞኑን በነበረው አለመረጋጋት እጅግ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል።
- የሰዎች ህይወት አልፏል (ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ሰዎች በአንድ ጉድጓድ እንደተቀረቡም የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል)
- የቀበሌ አስተዳደር ፣ የፖሊስ ፅ/ቤት ፣ የመንግስት መስሪያ ቤት ተቃጥሏል/ወድሟል ፤ አንድ ቤተ ክርስቲያን ላይ ጉዳት ደርሷል።
- የተለያዩ የግለሠብ ቤቶች እየተመረጡ እንዲወድሙ ሆኗል።
- በርካታ ዜጎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል።
- ህፃናት ፣ ነፍሰ ጡር ሴቶች ፣ ወጣቶች ፣ አዛውንቶች ራሳቸውን ከጥቃት ለማትረፍ በአንድ ትምህርት ቤት ውስጥ ተጠልለዋል።
- ጥቃት ሸሽተው ትምህርት ቤት ውስጥ የሚገኙ ዜጎች በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ፤ የህክምና ፣ የምግብ ችግር እያጋጠማቸው ይገኛል።
መረጃው ከአብመድ ዘገባ ላይ የተገኘ ነው።
ከሰሞኑን ከፍተኛ የሆነ የፀጥታ መደፍረስ የነበረባቸው አካባቢዎች ከዕለት ወደ ዕለት ሁኔታዎች እየተሻሻሉ ቢመጡም አሁንም ግን ከስጋት ያልተላቀቁ ቦታዎች እንዳሉ ይነገራል። አጠቃላይ ስለደረሰው ጉዳት፣ ስለጠፋው ህይወት፣ ስለወደመው ንብረት ዝርዝር መረጃ ይፋ አልተደረገም።

አጭር መረጃ ስለተሻሻለው የንግድ ህግ ፦
By : Haileyesus Seyume
ላለፉት 62 ዓመታት ያህል በስራ ላይ የነበረው የንግድ ህግ ዛሬ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተሻሽለ ፀድቋል።
- የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከሌሎች አዋጆች በተለየ እስከ 3 ወር ጊዜ ተወስዶ ተወያይቶ ነው ዛሬ ያፀደቀው
- 825 አንቀፆች ማሻሻያ ተደርጎባቸዋል፤
- የተሻሻለው አዋጅ ወቅቱን እና ቴክኖሎጂን ታሳቢ ያደረገ ነው ፤ ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ተሳፍቶ ለምታደርገው ጥረት የሚያቀል ነው።
- ማንኛውም ሰው ወደ ንግድ ስርዓት ለመግባት ይቸገርበት የነበረውን ረጅም አሰራር የሚያሳጥር ነው።
- የተሻሻለው ህግ የሚመለከተው የንግድ ስራን ብቻ ሲሆን የባንክ እና ሂሳብ ጉዳይ የሚመለከተው ከነበረው የንግድ አወጅ እንዲወጣ ተደርጎ ለብቻው እንዲታይ ተደርጓል።
- ማንኛውም ግለሰብ እና ድርጅት ባለው ካፒታል በንግድ ስርዓቱ ውስጥ ለመሳተፍ በፈለገበት ወቅት ሃሳቡን አቅርቦ በፈለገው ሞያ ላይ መሳተፍ ይችላል፤ ነገር በህግ የተከለከሉትን አይመለከትም።
- ማኛውም ሁለት እና ከዚያ በላይ የሆኑ ሰዎች በህብረት ስራ ማህበራት መስርተው በንግድ ላይ መሳተፍ ይችሉ ነበር ነገር ግን በግለሰብ ደረጃ ማህበር መመስረት አይቻልም ይህ እንዲቀር ተደርጎ ማንኛውም ግለሰብ ብቻውን ሆኖ የንግድ ህብረት ስራ ማህበር መስርቶ በንግድ ውስጥ እንዲንቀሳቀስ መብት ይሰጣል።
- የውጭ ባለሃብቶች በሀገር ውስጥ በተለያዩ የስራ መስኮች እንዲሰማሩ የሚያመቻችበት ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል።
- ከዚህ ቀደም ትናንሽ የሚባሉ ስራዎች (1ና 2 ሰው ተሳትፎ የሚሰራባቸው) በንግድ ስርዓት ውስጥ እንዲየልፉ ይገደዳሉ በዚህም ከትንሽ ተነስተው ወደ ትልቅ ደረጃ ለመድረስ የሚየስቡ ነጋዴዎች በስርዓቱ ምክንያት ከስራው ሲወጡ ነበር ይህን ለመቅረፍ በአዲሱ አዋጅ ትናንሽ ስራዎች ነጋዴ ተብለው እንዳይመዘገቡ እና ያለ ንግድ ፍቃድ ስራቸውን እንዲሰሩ የሚፈቅድ ነው ፤ በአዋጁ ላይ አንድ ወይም ሁለት ብሎ በቁጥር ተቀምጧል።
ለምሳሌ ፦
- እርሻ እና ከብት ማርባት
- የደን ልማት
- የእደጥበብ ስራዎችም በነጋዴ የሚለው ውስጥ እንዳይካተቱ ተደርገዋል።
ነገር ግን ካፒታል ያላቸው ወይም ተጨማሪ ስራቸውን ለመስራት የሚያስችል ከሆነ በዚህ ውስጥ አይስተናገዱም ፥ ካፒታላቸው ምን ያህል ነው የሚለው በቀጣይ በሚወጣ ዝርዝር የህግ አዋጅ የሚካተት ነው።
- ዛሬ ተሻሽሎ የፀደቀው አዋጅ ለ30 ዓመታት ስራ ላይ ይውላል ተብሎ የሚጠበቅ አዋጅ ነው።

#Attention ይህ አጭር ቪድዮ የደብረ ወገገ አሰቦት ገዳም ሰደድ እሳትን የሚያሳይ ሲሆን ከምዕራብ ሐረርጌ ሀገረስብከት (EOTC TV) የተገኘ ነው። ዛሬ ከሰዓት ላይ እንዳጋራናችሁ መረጃ እሳቱ በተለያየ አቅጣጫ እየተነሳ ለመቆጣጠር ፍፁም አስቸጋሪ ሆኗል ፤ በሰው ኃይል እሳቱን ማጥፋት ከባድ ስለሆነ ሌሎች አማራጮች እንዲፈለጉ ጥሪ ቀርቧል። በሌላ በኩል ፦ በአንኮበር ወረዳ ወፍ ዋሻ ደን ላይ…
#Update
አራተኛ ቀኑን የያዘው በአንኮበር ወረዳ ወፍ ዋሻ ደን ላይ የተከሰተው የእሳት አደጋ ዛሬም መቆጣጠር አልተቻለም፡፡
በአንኮበር ወረዳ በወፍ ዋሻ ደን ላይ መጋቢት 13/2013 ዓ.ም ጀምሮ የተከሰተውን የእሳ አደጋ ለመቆጣጠር ጥረት ቢደረግም አሁንም ግን መቆጣጠር አልተቻለም፡፡
እሳቱ አድማሱን እያሰፋ ወደ ታሪካዊው የእመ ምሕረት ተራራ እየተጠጋ ነው፡፡
እስከ ትናንት ምሽት ድረስ ከአጠቃላይ የደኑ ሽፋን ውስጥ 40 ያህል ሄክታር (0.45%) ውድመት መከሰቱን የወረዳው አስተዳደር አረጋግጧል፡፡
በሌላ በኩል ፦
አሰቦት ገዳም ዙሪያ የተነሳው እሳት በቁጥጥር ስር መዋሉን የገዳሙ አሐዱ ኤፍ ኤም 94.3 ሬድዮ ጣቢያ ዘግቧል።
እሳቱን መቆጣጠር የተቻለው በህብረተሰቡ እገዛ መሆኑ ተገልጿል።
በአራቱም አቅጣጫ በመናንያኑ መኖሪያ ከቤተክርስቲያኑ በ25 ሜትርና በ50 ሜትር ርቀት ላይ የእሳት አደጋው የደረሰ ሲሆን፤ ወጣቶች ብዙ ኪ.ሜ ርቀት ተጉዘው መጥተው እሳቱን ለማጥፋት ተባብረዋል።
በአደጋው ገዳሙ በአራቱም አቅጣጫ ጉዳት ያደረሰበት ሲሆን በድጋሚ የእሳት አደጋው እንዳይፈጥር ስጋት ያለ ሲሆን የሚመለከታቸው አካላት ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።