TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በየአካባቢው ስላሉ ግጭቶች ፦

ጠ/ሚር ዶክተር አብይ አህመድ በየቦታው የሚነሱ ግጭቶችን ለመፍታት ሕዝቡ ከመከላከያ ሰራዊት ጎን ሊቆም ይገባል አሉ።

በየቦታው እየታዩ ያሉ ግጭቶችን በተመለከተ ለተነሱ ጥያቄዎች ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲመልሱ በመከላከያ ሰራዊት ብቻ ችግሩን ሙሉ በሙሉ መፍታት እንደማይቻል ስለሆነም ሕዝቡ ወታደራዊ አገራዊ ግዴታን ከመወጣት ጀምሮ ከአገር መከላከያ ሰራዊት ጎን ሊቆም ይገባል ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ግጭትና ሞት በቀላል በምኞት አይቆምም ፤ ስራ ይፈልጋል ያሉ ሲሆን መከላከያ ሰራዊት ዜጎች ወደው እና ፈቅደው እንዲሳተፉ ያስፈልጋል ሲሉ ገልፀዋል።

"እስካሁን ያያነው በፌስቡክ ነው የሚሳተፉት ፤ ፉከራ ብቻ ነው፤ በአካል ሄዶ አንድም ሰው የሚሳተፍ የለም፤ ይህ ተቋም በሰው ሀብት መገንባትና መጠናከር ይኖርበታል" ብለዋል።

ሰላም ፣ ልማት ፣ ዕድገት ይምጣ ሲል ወጣቱ በእነዚህ ተቋማት መሳተፍም ይኖርበታል እና ያልተሳተፈበትን ችግር አልተፈታም ማለትም ተገቢ አይደለም ሲሉ ተናግረዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
"አንድ ቦታ ግጭት ሲፈጠር ዘለን መግባት አንችልም" - ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ

ለህብዝ ተወካዮች ም/ቤት ማብራሪያ እየሰጡ የሚገኙት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የትም ቦታ ላይ ችግር ሲፈጠር ሁሉንም ነገር ከፌዴራል መንግስት ጋር የማያያዝ ችግር አለ ፤ ይህ ደግሞ በሌላው ዜጋ ብቻ ሳይሆን በምክር ቤት አባላቱም ጭምር የሚታይ ነው ሲሉ ተደምጠዋል።

አሁን ባለው የሀገሪቱ ቅርፅ ውስጥ የፌዴራሉ መንግስት ስልጣን የተከለለ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንስተዋል።

"እየተከተልን ባለነው የፌዴራል ስርዓት ውስጥ አንድ ቦታ ግጭት ሲያጋጥም ክልሉ ና እርዳኝ ካላለው በስተቀር የፌዴራል መንግስት ዘሎ መግባት አይችልም" ብለዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
ችሎት !

እነ አቶ ስብሃት ነጋ ጉዳያችን በትግራይ ክልል ፍርድ ቤት ይታይልን ሲሉ አቤቱታ አቀረቡ፡፡

ይህን አቤቱታ ያቀረቡት ዛሬ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድቤት አራዳ ምድብ ችሎት ነው።

የጠቅላይ አቃቤ ህግ ቡድን በበኩላቸው የፌዴራል መንግስትን ስልጣን ለመጣል በሚል የሽብር አዋጁን በመተላለፍ በመላው ሀገሪቱ የተፈጸመ ወንጀል መሆኑን በመጥቀስ ተጠርጣሪዎቹ መቀሌ ሆነው በሰጡት ትዕዛዝ ባህርዳር እና ጎንደርን በሮኬት ማስደብደባቸው አንዱ ማሳያ ነው ብለዋል።

በተጨማሪም ተከሳሾቹ ስልጣን ተከፋፍለው በተለያዩ ቦታዎች የተፈጸመ ወንጀል ነው ያለው አቃቤ ህግ ዶክተር አዲስ አለም ባሌማ የድርጅቱ ስራ አስፈጻሚ ሆነው አዲስ አባባ ቁጭ ብለው ሲፈጽሙ የነበረው ወንጀል አንድ ቦታ አለመሆኑን ማመላከቻ ነው ብሏል በምላሹ።

ይህ የሚያሳየው በሃገሪቱ በተለያዩ ቦታዎች መፈጸማቸውን ስለሆነ በአካባቢ ስልጣን ሳይገደብ ጉዳያቸው መታየት ያለበት በፌዴራል ፍርድ ቤት ነው ሲል በጠበቆቻቸው ያነሱት መከራከሪያ ውድቅ እንዲደረግ ጠይቋል።

ፍርድቤቱ ምርምሮ ትዕዛዝ ለመስጠት ለመጋቢት 17 ቀን 2013 ዓ/ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ችሎቱ አቶ ስብሃት በግል ሃኪም እንዲታከሙ የታዘዘው ትዕዛዝ ተፈጻሚ እንዲሆን አዟል።

አምባሳደር አባይ ወልዱ ለዐይናቸው ህመም በግል እንዲታከሙ ያቀረቡት አቤቱታን ተቀብሎ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

https://telegra.ph/Ato-Sibhat-Nega-03-23
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር የኤርትራ ጦር የኢትዮጵያን ድንበር ተሻግሮ ትግራይ መግባቱን ዛሬ በነበራቸው ማብራሪያ አረጋግጡ።

ነገር ግን የኤርትራ ጦር የኢትዮጵያን ድንበር ተሻግሮ ኢትዮጵያ ውስጥ እንቅስቃሴ እያደረገ በእኛ ህዝብ ላይ በጥፋት በሚገለጽ የሚያደርጋቸውን ጥፋቶች በማንኛውም መንገድ አንቀበልም ብለዋል።

ይህንን የማንቀበለው የኤርትራ ጦር ስለሆነ ሳይሆን የእኛ ወታደርም ጥፋት አጥፍቶ ከሆነ አንቀበልም ሲሉ ገልፀዋል።

ዶ/ር አብይ ፥ ዘመቻው በግልጽ ከተለዩ ጠላቶች ጋር እንጂ ከህዝባችን ጋር አይደለም ሲሉ ተናግረዋል።

የኤርትራን ጉዳይ በተመለከተ ከኤርትራ መንግስት ጋር አራት አምስት ጊዜ ከፍተኛ አመራሮች ወደዚያም ወደዚህም ተልኮ ንግግር ሲደረግ መቆየቱን አሳውቀዋል።

የኤርትራ ጦር ይፈፅሟቸዋል ከሚባሉት በደሎች ጋር በተገናኘ፥ "ለኤርትራ መንግስት አቅርበናል፤ የኤርትራ መንግስት ይህንን በከፍተኛ መንገድ ነው የኮነነው፤ ማንም በዚህ ተግባር የሚሳተፍ የእኔ ወታደር ካለ እርምጃ እወስዳለሁ" ብሏል ሲሉ ዶ/ር አብይ አህመድ ገልፀዋል።

በሌላ በኩል ዶ/ር አብይ አህመድ የኤርትራን ህዝብ እና መንግስት ዳግም አመስግነዋል።

"የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በገዛ ወገኑ ክህደት ተፈጽሞበት የኤርትራ ህዝብና መንግስት ወደ እሱ የሄዱትን ወታደሮች የያዘበት፣ ወደፈለጉበት እንዲሄዱ የደገፈበት መንገድ የሁል ጊዜም የኢትዮጵያ ባለውለታ ያደርገዋል" ብለዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/Eritrea---Ethiopia-03-23
#Silte

በስልጤ ዞን አልቾ ውሪሮ ወረዳ በትላንትናው እለት በቡኔ ቀበሌ በደረሰ የቤት ቃጠሎ ከ78 ቤት ሙሉበሙሉ የወደመ ሲሆን በቤቶቹ ይኖሩ የነበሩ 450 ግለሰቦችን ቤት አልባ ከድርጓል።

ለጊዜው የእሳት አደጋው መነሻ በውል ባይታወቅም የ52 አባወራዎች ቤት ሙሉበሙሉ ሲወድም ከ57,500,000 ብር በለይ ንብረት ማውደሙን ተገልጿል።

በዕለቱ የነበረው የአየር ሁኔታ ነፋሻማና ወቅቱም በጋ መሆኑ ተደምሮ የእሳቱን ፍጥነት ለመቆጣጠር በጣም አስቸጋሪ ሁኔታ መፈጠሩን በስፍራው የነበሩ አባወራዎች ለወረዳው መንግስት ኮመንኬሽን ተነግሯል።

በባለፋት ተከታታይ የበጋ ወራት በወረዳችን ከ98 በላይ ቤቶች በእሳት አደጋ ወድመዋል።

@tikvahethiopia
#AlertEthiopia😷

በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወደአስከፊ ደረጃ እየተሸጋገረ ነው።

የፅኑ ታማሚዎች ቁጥር 693 ደርሷል።

ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ከተደረገው 7,092 የላብራቶሪ ምርመራ 1,692 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ በተመሳሳይ በ24 ሰዓታት ውስጥ 19 ሰዎች ሞተዋል።

ትላንት 1,019 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

በአጠቃላይ 190,594 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 2,693 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 149,590 ሰዎች አገግመዋል።

#Purpose #Tikvah
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር እና ሳይንስ፦

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ ዛሬ በጎጃም እና ሸዋ በሰው ሰራሽ ቴክኖሎጂ ዝናብ አዘነብን ማለታቸው ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኖ ውሏል።

ይህን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ተጨባጭ ሳይንስ ነው ?

የብሄራዊ ሚትሪዮሎጂ ምክትል ስራ አስፈፃሚ አቶ ክንፈ ኃ/ማርያም ዛሬ ምሽት በነበረው የቢቢሲ ሬድዮ ስርጭት፥ "...በቤጂንግ ኦሎምፒክ መክፈቻ ቀን ቻይና በዓሉን በብሩሃማ ቀን ለማክበር ብላ ተጠቅማበታለች። ያ ምን ማለት ነው ደመናማ ሆኖ በዛ ቀን ሊዘንብ የነበረውን በቤጂንግ ኦሎምፒክ አካባቢ በዝናብ መልክ ቀድሞ በማበልፀግ መክፈቻውንም መዝጊያውንም በብሩህ ቀን እንዲከበር አድርጋለች" ሲሉ በምሳሌ አስረድተዋል።

አቶ ክንፈ፥ "ደመናው ከሌለ ዝናቡን ማበልፀግ አይቻልም ፤ ደመናውን መፍጠር አንችልም፤ ዝናብ ለማበልፀግ ዝግጁ የሆነ ደመና በተፈጥሮ መምጣት አለበት ፤ ሳይንሱም እሱን ነው የሚነግረን ነው" ሲሉ ገልፀዋል።

በዚህ ቴክኖሎጂ ኢትዮጵያን በቴክኒክም በፋሲሊቲም እያገዙ የሚገኙት የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ (UAE) መንግሥት እና የሜትሪዮሎጂ ማዕከል ናቸው ተብሏል።

ቴክኖሎጂው እየተሞከረ ያለው ቀጥታ ከUAE በመጣ ኤርክራፍቱ እና ንጥረ ነገር መሆኑ ነው የተሰማው።

https://telegra.ph/Ethiopia-03-23-2
ዓዲግራት ዩኒቨርስቲ ዛሬ ማምሻውን በላከልን መልዕክት ነባር ተማሪዎቹ ከመጋቢት 28-30/2013 ድረስ ወደዩኒቨርስቲው እንዲገቡ ጥሪ አድርጓል።

ለዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ነባር ተማሪዎች በሙሉ ፦

የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች የሆናችሁ በሙሉ ተቋርጦ የነበረው የመማር ማስተማር ሂደት ለማስጀመር ዩኒቨርሲቲው በወሰነው መሰረት የመግብያ ቀን መጋቢት 28-30/2013 ዓ/ም መሆኑ ኣውቃችሁ በተጠቀሰው ቀን በዩኒቨርሲቲው ዋናው ግቢ ተገኝታችሁ እንድትመዘገቡ እናሳውቃለን።

ከሰላምታ ጋር!
የዓዲግራት ዩኒቨርስቲ ረጅስትራር ፅ/ቤት

#TikvahEthiopia
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#Ethiopia🇪🇹

ዛሬ ከቀኑ በ10:00 ሰዓት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የማዳጋስካር አቻውን በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም የሚገጥም ይሆናል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ ለካሜሩኑ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጉዞ ለማለፍ 2 ወሳኝ ጨዋታዎች ይቀሯታል።

ዛሬ ከማዳጋስካር ጋር የምታደርገው እና ከአንድ ሳምንት በኃላ መጋቢት 21 ከኮትዲቯር ጋር (በአቢጃን) የምታደርገው ነው።

ሀገራችን ኢትዮጵያ መልካሙ ሁሉ እንዲገጥማት እንመኛለን።

@tikvahethsport
በትግራይ_ክልል፣_አክሱም_ከተማ_የተፈጸመው_ከፍተኛ_የሰብአዊ_መብቶች_ጥሰት_ምርመራ_ሪፖርት.pdf
610.2 KB
የአክሱም ሪፖርት ፦

በኣክሱም ከተማ ትግራይ ክልል የደረሰውን ከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት እና በሲቪል ሰዎች ላይ የተፈጸመውን ጥቃት አስመልክቶ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ፣ የመጀመሪያ ደረጃ (ቀዳሚ) ሪፖርቱን ትላንት ለሊት ይፋ አድርጓል።

ከበርካታ ሳምንታት ጥረት በኋላ የምርመራ ባለሞያዎቹን ወደ አክሱም ከተማ መላክ መቻሉን ገልፆ ፤ ባለሞያዎቹ ከየካቲት 20 እስከ የካቲት 26 ቀን 2013 ድረስ በከተማዋ በመቆየት ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎችን፣ 45 የተጎጂ ቤተሰቦችን፣ የዓይን ምስክሮችን እና የሃይማኖት መሪዎችን አነጋግሯል። እንዲሁም 20 ሰዎች የተሳተፉበት የቡድን ውይይት ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር አድርጓል።

በተጨማሪ ከተጎጂ ቤተሰቦች፣ ከአክሱም ቅድስት ማርያም ሆስፒታል፣ ከአክሱም ሪፈራል ሆስፒታል፣ ከሚመለከታቸው የቀበሌ መስተዳደር አካላት እንዲሁም ከሃይማኖት ተቋማት አገልጋዮች የተለያዩ የምስል፣ የድምጽ እና ሌሎች የሰነድ ማስረጃዎችን አሰባስቧል።

ኢሰመኮ በዚህ ምርመራው ያሰባሰባቸው መረጃዎች በተለይ ከኅዳር 19 እስከ ኅዳር 21 ቀን 2013 ዓ.ም. በነበሩት ሁለት ቀናት ከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት እንደተፈፀመ አረጋግጧል።

- የአክሱም ከተማና አከባቢው ነዋሪዎች፣
- ከተለያዩ የትግራይ አከባቢዎች ጦርነት ሸሽተው በከተማዋ የተጠለሉ ተፈናቃዮች እና
- የኅዳር ፅዮን ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል ለማክበር ከተለያየ ቦታዎች የመጡ ሰዎችን ጨምሮ በአጠቃላይ ከአንድ መቶ በላይ ሲቪል ሰዎች በወቅቱ በአክሱም ከተማ በነበሩ #የኤርትራ_ወታደሮች መገደላቸውን ሪፖርቱ ያመለክታል።

*ሙሉ ሪፖርቱ ከላይ በPDF ፋይል ተያይዟል (በዝርዝር እንመለከተዋለን)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ኣክሱም ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን ጠራ። የኣክሱም ዩኒቨርሲቲ በ2013 ተመራቂ የነበሩ መደበኛ ተማሪዎቹን መጋቢት 5-6 ወደ ግቢ እንዲገቡ ጥሪ አቅርቧል። በ2013 ተመራቂ ያልሆኑ መደበኛ ተማሪዎቹን ደግሞ ከመጋቢት 15 -16 ወደ ግቢ እንዲገቡ ነው ጥሪውን ያቀረበው። የ2013 ተመራቂ ተማሪዎች የሆናችሁና በሽረና በዋናው ግቢ ትምህርታችሁን ስትከታተሉ የነበራችሁ ሪፓርት የምታደርጉት በዋናው ግቢ ሲሆን የጤና…
ማስታወሻ ለኣክሱም ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች :-

የኣክሱም ዩኒቨርሲቲ የ2013 ተመራቂ ያልሆናችሁ መደበኛ ተማሪዎች ከመጋቢት 15 -16 ወደ ግቢ እንዲገቡ ነው ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል።

በዚህም በሽረ እና በዋናው ግቢ ትምህርታችሁን ስትከታተሉ የነበራችሁ ሪፓርት የምታደርጉት በዋናው ግቢ ሲሆን የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች በነበራችሁበት ሪፓርት እንድታደርጉ ተብላችኋል።

@tikvahethiopia
#WFP

የዓለም የምግብ ፕሮግራም በትግራይ ክልል ለሚያከናውነው የሰብዓዊ መብት ድጋፍ 170 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልገው አስታወቀ።

በክልሉ በተካሄደው ውጊያ ምክንያት ዜጎች ለከፋ ሰብአዊ መብት ጥሰት ተዳርገዋል ያለው ፕሮግራሙ ለተጎጂዎች ድጋፍ በማድረግ ላይ መሆኑን ገልጿል።

ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ ለይ በክልሉ ለተፈናቀሉና ለምግብ እጥረት ለተዳረጉ ዜጎች ድጋፍ ለማድረግ 170 ሚሊዮን ዶላር ያስፈልገኛል ብሏል።

4.5 ሚሊዮን ዜጎች አስቸኳይ የሰብዓዊ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው የዓለም የምግብ ድርጅት ከነዚህ ውስጥ ለ1 ነጥብ 4 ሚሊዮን ዜጎች እየደገፈ መሆኑን አስታውቋል።

በትግራይ ክልል የተካሄደው ውጊያ የሰብል ስብሰባ በሚካሄድበት ወቅት መሆኑ የተጎጂ ዜጎች ቁጥር እንዲጨምር አድርጓል የሚለው ድርጅቱ ገበያዎች፣ሰብሎች እና ሌሎች መሰረታዊ መገልገያዎች ከጥቅም ዉጪ መሆናቸውን መግለፁን አል ዓይን ኒው በድረገፁ አስነብቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
"...እሳቱ በሰው ኃይል ይጠፋል ብሎ ማሰብ የማይቻልበት ደረጃ ደርሷል" -ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ደረጄ ብርሃኑ By : መ/ር አቤል አሰፋ-ኢኦተቤ ቴቪ ከትላንት ጀምሮ በደብረ ወገግ አሰቦት ገዳም የሰደድ እሳት ቃጠሎ ተነስቷል። በደብረ ወገግ አሰቦት ገዳም የተነሳው ሰደድ እሳት ለማጥፋት ከጭሮ /አሰበተፈሪ/፣ አሰቦት መኢሶ እና ከአካባቢው ወረዳዎች ወደ ሥፍራው የተጓዙ ምእመናን ከፍተኛ ጥረት ቢያደርጉም…
#Attention

አሰቦት ገዳም ዙሪያ የተነሳው እሳት ዛሬም ድረስ መቆጣጠር አልተቻለም ፤ እሳቱ አቅጣጫውን እየቀያየረ ለቁጥጥር አዳጋች አድርጎታል።

ከቀናት በፊት የምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ኅሩያን ቀሲስ ደረጄ ብርሃኑ ለኢኦተቤ ቴቪ ፥ እሳቱ በሰው ኃይል ይጠፋል ብሎ ማሰብ የማይቻልበት ደረጃ መድረሱን አሳውቀው መንግሥት ተገቢውን ትኩረት በመስጠት ሌሎች አማራጮችን መጠቀም ይገባዋል ሲሉ አስገንዝበው ነበር።

ዛሬ ሌሊት ሙሉ ለሙሉ ገዳሙ ሙሉ ዙሪያውን በእሳት ተከቦ እንዳደረ ወደ ገዳሙም የገባ እንደሆነ ጉዳዩን እየተከታተሉ ለህዝብ እያሳወቁ ከሚገኙ መካከል መምህር ኤፍሬም ዘደብረወግ የተባሉ ወንድም አሳውቀወል።

እንደ አዲስ በተለያየ አቅጣጫ እሳት እየተነሳ ነው ያለው። በጠፉ ቦታዎች ጭምር እንደ አዲስ እየተነሳ መሆኑ ተገልጿል።

በአራቱም አቅጣጫ በመናንያኑ መኖሪያ ከቤተክርስቲያኑ በ25 ሜትርና በ50 ሜትር ርቀት ላይ ደርሷል።

ወጣቶች ብዙ ኪ.ሜ ርቀት ተጉዘው መጥተው እሳቱን ለማጥፋት ከፍተኛ ተጋድሎ እያደረጉ ቢሆንም እሳቱ በሰው ኃይል የሚጠፋ አልሆነም።

እሳቱን በማጥፋት በርከታ ሰዎች እየተሳተፉ ቢሆንም እነሱ በመዳከማቸው አዲስ የሰው ኃይል ያስፈልጋል ፥ የሚችልም ወደቦታው እንዲሄድ ተጠይቋል።

ምግብ እንደሞከሮኒ፣ ፓስታ ፣ ዱቄት፣ ውሃ እና በቀላሉ እዛው የሚሰሩ የሚችሉ ነገሮችም ይሳፈልጋሉ።

ይህ እሳት በሰው ኃይል የማይጠፋበት ደረጀ በመድረሱ የሚመለከተው አካል ሁሉ በአስቸኳይ ሌሎች አማራጮችን እንዲፈልጉ ጥሪ ቀርቧል።

@tikvahethiopia
#SNNPRS

በካፋ ዞን ዴቻ ወረዳ ጉንድራ ገራ ቀበሌ ከሰሞኑ የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ የወረደው በረዶ ከ7 መቶ 80 ሄክታር በላይ ማሳ ላይ በነበሩ ቋሚና ዓመታዊ ሠብሎችና የቤት እንስሳት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን የዞኑ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

በጉዳቱ ሳቢያ ለችግር ለተጋለጡ ወገኖች ሠብዓዊ ድጋፍ የማድረስ ሥራ መጀመሩ ተገልጿል።

መጋቢት 8 ቀን 2013 ዓ.ም በዴቻ ወረዳ ጉንድራ ገራ ቀበሌ የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ የወረደው በረዶ ከ 6 መቶ 31 ሄክታር በላይ ማሳ ላይ የነበሩ ቡና ፣ ኮረሪማና እንሠትን የመሳሰሉ ቋሚ ሠብሎች ላይ ጉዳት ሲያደርስ ከ1 መቶ 53 ሄክታር በላይ በሆነ ማሳ ላይ የነበረ የበቆሎ ችግኝን ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጭ አድርጓል፡፡

በጉዳቱ ሳቢያም 312 እማወራና አባወራዎች ሥር የሚተዳደሩ ከ1 ሺ 5 መቶ 60 በላይ ሠዎች ለችግር ተዳርገዋል፡፡

በ780 የቀንድ ከብቶችና 556 የጋማ ከብቶች ላይም በረዶው ጉዳት አድርሷል ፡፡

በአካባቢው የጣለው በረዶ ከዚህ ቀደም ተከስቶ የማያውቅና ከባድ ነበረ ነው ተብሏል።

አደጋው በጉንድራ ገራ ብቻ ሣይሆን በጉንድራ ሸላ ቀበሌ ላይ የተከሰተ በመሆኑ ሠብዓዊ ድጋፍ ለማድረስ የሚያስችል የአደጋውን መጠን የመለየት ሥራ እየተሰራ ነው ተብሏል።

ምንጭ፦ ደ.ሬ.ቴ.ድ
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT