TIKVAH-ETHIOPIA
የሱዳኑ ጠ/ሚ ግብፅ ገቡ። የሱዳን ጠ/ሚ ዶ/ር አብደላ ሃምዶክ ከከፍተኛ ልዑካን ጋር በመሆን ዛሬ ግብፅ ካይሮ ገብተዋል። ሃምዶክ ካይሮ ኤርፖርት ሲደርሱ የግብፅ ጠ/ሚ ሙስጠፋ ማድቡሊና ሌሎች ባለስልጣናት ተቀብለዋቸዋል። ከሃምዶክ ጋር ወደ ግብፅ ካቀኑት የልዑካን ቡድን መካከል የውጭ ጉዳይ ፣ የፋይናንስ እና ኢኮኖሚ፣ የግብርና ደን፣ የንግድ፣ የውሃና መስኖ፣ የትራንስፖርት ፣ የኢንቨስትመንት ልዑካን…
#Update
የግብፁ ጠ/ሚር ሙስጠፋ ማዱቡሊ ሀገራቸው ፥ የኢትዮጵያን እድገት እንደማትቃወም ገልፀዋል ፤ ነገር ግን ኢትዮጵያ እድገቷ ሱዳንና ግብፅን በሚጎዳ መልኩ መሆን የለበትም ነው ያሉት።
ጠቅይላይ ሚኒስትሩ ይህ የተናገሩት ከሱዳን ጠ/ሚር ዶክተር አብደላ ሃምዶክ ጋር በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ነው።
በሌላ በኩል ፕሬዜዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲ ሲ ጠ/ሚ ዶ/ር አብደላ ሃምዶክን በቤተ መንግስታቸው ተቀብለው ውይይት አድርገዋል።
በውይይታቸው ከነበሩ አጀንዳዎች መካከል የህዳሴው ግድብ ጉዳይ እና የኢትዮ-ሱዳን ድንበር ውጥረት እንደነበረ ተሰምቷል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ መግለጫ ፦
[By : Deutsche Welle-Seyume Getu]
የ12ኛ ክፍል ፈተና መጠናቀቁን ተከትሎ የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ቶላ በሪሶ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸው ፦
- 14 ሴት ተማሪዎች ፈተና በመውሰድ ላይ ሳሉ ወልደዋል፤14ቱ ተማሪዎች በአቅራቢያቸው ወዳለው የጤና ተቋም ተወስደው ከወለዱ በኋላ እንዲያርፉ ተደርገው ፈተናውን ወስደዋል፡፡
- ፈተናው ያለ ፀጥታ ችግር «በተሳካ» ሁኔታ በመላው ክልል 336 የፈተና ጣቢያዎች ተሰጥቷል።
- 150,651 ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና እንደሚወስዱ ቢጠበቅም 148 ሺ 149 ተማሪዎች ማለትም 98.43 በመቶው ፈተናውን ወስደዋል።
- የኦሮሚያ ክልል ተፈታኞች በአገር አቀፍ ደረጃ ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች 36 በመቶ ድርሻ ይይዛሉ።
- በፈተናው ያልተገኙ የ2,362 ተማሪዎች እጣ ፈንታ በትምህርት ሚኒስቴር ይወሰናል።

ጥናት ፦
በብሪታንያ የተከሰተው ልውጡ ኮሮና ቫይረስ ዓይነት የያዘውን ሰው ከቀደሙት ዝርያዎች ይበልጥ ሊገድል የሚችል መሆኑን ጥናት አመልክቷል።
ጥናቱ በብሪታንያ የህክምና ጆርናል ላይ ታትሟል።
ይህ ጥናት እንደሚያሳየው /B.1.1.7/ የሚባለው ይህ የኮሮናቫይረስ ዝርያ የያዛቸው ሰዎች፣ ከሌሎቹ ዓይነቶች በንጽጽር ከ30% እስከ 100% በሚደርስ መጠን የህልፈት የሚያደርስ አቅም አለው።
የብሪታንያ ልውጥ ኮሮና ቫይረስ መጀመሪያ በሃገሪቱ ደቡባዊ ክፍል የተገኘው በመከረም ወር ሲሆን በአሁኑ ጊዜ ከመቶ ወደሚበልጡ ሃገሮች ተዛምቷል።
በሌላ በኩል ፦
የዓለም የጤና ድርጅት ኮቪድ-19ን ዓለማቀፍ ወረርሺኝ ብሎ ካወጀ ዛሬ አንድ ዓመት ሞልቶታል።
Via ቪኦኤ

#Attention😷
በሀገራችን ኮቪድ-19 በእጅጉ እያሻቀበ ነው።
በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ከተደረገው 7,065 የላብራቶሪ ምርመራ 1,332 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ በተመሳሳይ በ24 ሰዓታት ውስጥ 17 ሰዎች ሞተዋል።
ትላንት 805 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
በአጠቃላይ 171,210 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 2,483 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 140,840 ሰዎች አገግመዋል።
በአሁን ሰዓት 428 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።
#Purpose #Tikvah
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT

የትግራይ ክልል ሪፖርቶች ፦
- የትግራይና አማራ ክልል አስተዳደር እና ወሰን ጉዳይ በውይይት እንዲፈታ የትግራይ አስተዳደር ዝግጁ መሆኑን መግለፁ።
- በ3 ቀናት ብቻ ከ70 ሺ በላይ ሰዎች ከምዕራብ ትግራይ መፈናቀላቸውን የትግራይ አስተዳደር ማሳወቁ።
- የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ሕወሓት የሚያሰራጫቸው የውሸት መረጃዎች ለአስተዳደሩ ፈተና እንደሆኑበት ማሳወቁ።
- አንቶኒ ብሊንከን በትግራይ "የዘር ማጥፋት/ማፅዳት" ፤ የአማራ ክልል እና የኤርትራ ኃይሎች ከትግራይ ይውጡ ለታቸው።
- የአማራ ኃይል ትግራይ ውስጥ እንደሌለ አሁን የተያዙት ቦታዎች በታሪክ የትግራይ አለመሆናቸውን መግለፁና ሰፊ የሰው ቁጥር ተፈናቅሏል ስለሚባለው ጉዳይ "ፕሮፖጋንዳ" ነው ማለቱ።
- የአቶ ደመቀ መኮንን እና የሙሳ ፋኪ ውይይት።
- የአውሮፓ ኅብረት በኢትዮጵያ ጉዳይ።
- የዓለም ባንክ ለትግራይ መልሶ ማቋቋም ድጋፍ እንደሚያደርግ መግለፁ።
[ለቲክቫህ አባላት የቀረበ]
መጋቢት 2 ቀን 2013 ዓ/ም
አዲስ አበባ ፣ ኢትዮጵያ
https://telegra.ph/Tigray-Report-Tikvah-03-11

Telegraph
Tigray Report [Tikvah]
የትግራይ እና አማራ ወሰን ጉዳይ በውይይት እንዲፈታ የትግራይ አስተዳደር ዝግጁ መሆኑን መግለፁ ፦ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ሙሉ ነጋ በትግራይ እና አማራ ክልል መካከል ያለው የአስተዳደር እና ወሰን ችግር ከአማራ ክልል ጋር በመነጋገር ለመፍታት አስተዳደራቸው ዝግጁ መሆኑን ገልፀዋል። ዶ/ር ሙሉ ፥ “በዚህ ወቅት ከትግራይ ህዝብ ጎን ሆኖ ከማረጋጋት ይልቅ በችግር ላይ ችግር…
TIKVAH-ETHIOPIA
#Attention😷 በሀገራችን ኮቪድ-19 በእጅጉ እያሻቀበ ነው። በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ከተደረገው 7,065 የላብራቶሪ ምርመራ 1,332 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ በተመሳሳይ በ24 ሰዓታት ውስጥ 17 ሰዎች ሞተዋል። ትላንት 805 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል። በአጠቃላይ 171,210 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 2,483 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤…
የዛሬ እውነታዎች (መጋቢት 2/March 11) ፦
የኮቪድ ነገር እጅግ በጣም አሳሳቢ ነው። ዛሬ በተደረገው ምርመራ እንደ ሀገር በሽታው የመገኘት ምጣኔ 19 በመቶ ሲሆን በሽታው የመግኘት ዕድል በጣም ከፍተኛ የሆነበቸው አራት ከተሞች ፦
1. ሐዋሳ - 42%
2. ድሬዳዋ - 27%
3. አሶሳ - 23.5%
4. አዲስ አበባ - 20%
ሁሉም (17) ሞቶች ከአዲስ አበባ ናቸው።
እነዚህ ቁጥሮች በዓለም ጤና ድርጅት መመዘኛ ወደ complete shutdown የሚወስዱ እና እጅግ ከፍተኛ የጥንቃቄ እርምጃ የሚያስፈልጋቸው ናቸው::
አሁንም ፦
1. የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ በአግባቡ መጠቀም
2. የእጅ ንፅህና መጠበቅ
3. አላስፈላጊ መሰባሰብ መተው
4. ርቀትን ጠብቆ መንቀሳቀስ ያስፈልጋል።
ያዕቆብ ሰማን
የሕክምና አገልግሎት ዳይሬክተር
ጤና ሚኒስቴር
#SPHMMC

ሰሞኑ በሀገራችን በተፈፀሙ ጥቃቶች በርካቶች ተገድለዋል ፦ "...ልክ ፀሎት ይደረግ ተብሎ ፤ በፀሎት ሲጀመር የታጠቁ ኃይሎች መጥተው ኢሰብዓዊ ጭፍጨፋ አደረጉ" - በአማሮ ልዩ ወረዳ ዳኖ ቀበለ የተፈፀመው ጥቃት ዓይን እማኝ ከሰሞኑ ጥቃት ካስተናገዱ አካባቢዎች አንዱ የአማሮ ልዩ ወረዳ፣ ዳኖ ቀበሌ በእርቅ ላይ በነበሩ ሰዎች ላይ ተፈፀመው ነው። በጥቃቱ በርከቶች ሞተዋል፤ ብዙዎችም ቁስለኛ ሆነዋል። …
እንደ ኦሮሚያ ፖሊስ መረጃ ከሆነ ፦
- በ27/06/2013 ዓ/ም በሆሮጉድሩ ወለጋ ዞን አቤ ዶንጎሮ ወረዳ ዳቢስ ቀበሌ 22 ሰዎች በታጣቂዎች ተገድለዋል።
- በ30/06/2013 ዓ/ም በሆሮጉድሩ ወለጋ ዞን ጃርቴ ጃርዴጋ ወረዳ በሀሩዳኢ ቀበሌ 20 ሰዎች በታጣቂዎች ተገድለዋል።
በአጠቃላይ በሁለቱ የሆሮጉድሩ ወለጋ ዞን ወረዳዎች 42 ንፁሃን ዜጎች በታጣቂዎች ተገድለዋል። በርካቶች ደግሞ ቁስለኛ ሆነው ሆስፒታል ገብተዋል።
ከቅዳሜ የካቲት 27/2013 ዓ.ም ጀምሮ በተከታታይ ቀናት የተፈፀመው ጥቃት ማንነትን መሰረት ያደረገ ሲሆን ሕፃናት እና ሴቶችን ጨምሮ ዜጎች በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉበት ነው።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

"...ክትባቱ የደም መርጋት አያመጣም" - የአውሮፓ ህብረት
ኮቪድ-19 እንዲከላከል ተብሎ የተሠራው የኦክስፎርድ-አስትራዜኔካ ክትባት የደም መርጋት አደጋን ይጨምራል የተባለው ሃሰት ነው ሲል የአውሮፓ ሕብረት የመድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ።
የአውሮፓ ሕብረት ይህን ያለው ዴንማርክና ኖርዌይን ጨምሮ አንዳንድ ሃገራት ክትባቱን ለዜጎቻቸው መስጠት ማቆማቸውን ተከትሎ ነው።
ሃገራቱ ክትባቱን መስጠት ያቆሙት ጥቂት ሰዎች ከተከተቡ በኋላ የደም መርጋት ምልክት አሳይተዋል ተብሎ ነው።
የEU የመድሃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን እንደሚለው የደም መርጋት የታየባቸው የተከተቡ ሰዎች ቁጥር ካልተከተቡ ሰዎች ቁጥር ጋር ተመሳሳይ ነው።
ባለስልጣኑ ክትባዩ የደም መርጋት አደጋን ይጨምራል የተባለው ሃሰት ነው ሲልም አሳውቋል።
አስትራዜኔካ በቃል አቀባዩ አማካይነት የክትባቱ ደህንነት በብዙ ምርምርና ፈተና የተረጋገጠ ነው ብሏል።
በዩናይትድ ኪንግደም የመድኃኒት ተቆጣጣሪው ባለሥልጣን ክትባቱን ከደም መርጋት ጋር ግንኙነት እንዳለው የሚያሳይ ምንም መረጃ የለም ብሏል።
ስለዚህ ሰዎች በተጠየቁ ጊዜ ሄደው ክትባቱን እንዲወስዱ እንመክራለን ነው ያለው።
ምንጭ፦ ቢቢሲ

በድሬዳዋ ነገ የኮቪድ-19 ክትባት መሰጠት ይጀመራል።
ኢትዮጵያ ከተረከበችው 2.2 ሚሊዮን የኮቪድ-19 ክትባት 6 ሺህ የሚሆን ክትባት ወደ ድሬዳዋ ከተማ ገብቷል።
ክትባቱ በነገው እለት በሀገር አቀፍ ደረጃ መሰጠት የሚጀምር ሲሆን በድሬዳዋ አስተዳደርም በነገው እለት በሳቢያን የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የሚሰጥ ይሆናል።
የድሬዳዋ ከተማ ጤና ቢሮ ሀላፊ የሆኑት ወ\ሮ ለምለም በዛብህ ፥ ክትባቱ በ2 ዙር መሰጠት እንደሚጀምርና የመጀመሪያ ዙር ክትባት ከተሰጠ በኋላ ከ8 እስከ 12 ሳምንት ባለው ውስጥ ሁለተኛው ዙር ክትባት ቀድመው ለተከተቡ አካላት በድጋሚ እንደሚሰጥ አሳውቀዋል።
ክትባቱ በዋናነት የጤና ተቋም ላይ ላሉ ባለሞያዎች ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች እንደሚሰጥ ተገልጿል።
በአሁን ሰአት በድሬዳዋ የኮቪድ 19 ስርጭት በከፍተኛ ሁኔታ እየተሰራጨ መጥቷል፤ የማሟቾች ቁጥርም እየጨመረ ይገኛል ፤ ነዋሪው ህብረተሰብ ከምን ጊዜውም በላይ የበሽታውን አስከፊነት ከግምት ውስጥ በማስገባት መጠንቀቅ ይገባዋል ተብሏል።
Via Diredawa Health Bureau

ትላንት በአክሱም የእንቅስቃሴ ማቆም እና የስራ አድማ ተደርጎ ነበር።
By : Mulgeta Atsebha
የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች እና ዲፕሎማቶች አክሱም ይገባሉ የሚል ወሬ መናፈሱን ተከትሎ ትላንት በአክሱም ከተማ እንቅስቃሴ እና ስራ የማቆም አድማ ተደርጎ ነበር።
አምባሳደሮች እና ዲፕሎማቶች ግን ወደ አክሱም እንዳልሄዱ ታውቋል።
ከትላንት በስቲያ አምባሳደሮች እና ዲፕሎማቶች መቐለ ከተማ መግባታቸውን ተከትሎ እንቅስቃሴ የማድረግ እቀባ እና ስራ የማቆም አድማ ተደርጎ ነበር። ይህ የሆነው እንግዶቹ ትግራይ ወደቀደመው ሁኔታ ተመልሳለች የሚባለው ትክክል አይደለም፤ አሁንም መፍትሄ ያስፈልጋል የሚለውን ሃሳብ እንዲረዱት ለማድረግ ነው ተብሏል።
ተቃውሞው የተጠራው በ "ትግራይ ሚዲያ ሃውስ/TMH" ቴሌቪዥን ጣቢያ በተሰራጨ መልዕክት እና በፅሁፍ መልዕክት እንደሆነም ተሰምቷል።
በመቐለ ከተማ ስራ ዘግተው የነበሩ የንግድ ተቋማት "ታሽጓል" የሚል ወረቀት እንዲለጠፍባቸው ተደርጓል።
ከታሸጉ የንግድ ተቋማት ጋር በተያያዘ የትግራይ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ኢተነሽ ንጉሰ ተጠይቀው ዝርዝር መረጃ እንደሌላቸው አሳውቀዋል።
ከተቃውሞ ጋር በተያያዘም ወ/ሮ ኢተነሽ ፥ "ህዝባችን በችግር ውስጥ እያለ ፤ ወደ መረጋጋት እና ወደመደበኛ ስራ ለመመለስ ጥረት እየተደረገ ስራ ማቆም ችግር ያባብሳል እንጂ ችግሩን ይፈታዋል ብለን አናምንም፤ ጥያቄም ካለ ስራ እየተሰራ ማቅረብ ነው ለህዝባችን የሚያዋጣው" ብለዋል።
መቐለ ከትላንት ጀምሮ ወደቀደመ መደበኛ እንቅስቃሴዋ ተመልሳለች።

የ20 ሚሊዮን ብር የሎተሪ አሸናፊው ሳይታወቅ ጊዜው ሊያበቃ ነው። የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር ሃያ (20) ሚሊየን ብር የሚያሸልመው የሎተሪ እጣ የአሸናፊው ጊዜ ነገ እንደሚያበቃ አስታወቀ። ጳጉሜ 2012 የወጣው የእንቁጣጣሽ ሎተሪ እስካሁን ድረስ አሸናፊው አልታወቀም። የእጣ ቁጥሩ ከወጣ 6 ወራቶች ቢያስቆጥርም ፣ እስካሁን ድረስ አሸናፊ ሆኖ የቀረበ እና ሽልማቱን የወሰደ ግለሰብ እንደሌለ የብሄራዊ…
#Update
የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር "የ20 ሚሊዮን ብር የሎተሪ አሸናፊዉ" መገኘቱ አሳውቋል።
አስተዳደሩ የእንቁጣጣሽ ሎተሪ እድለኛ መታወቁን የገለፀው ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ሬድዮ ነው።
የአርባ ምንጭ ነዋሪ የሆነዉ ክንዴ አስራት በእንቁጣጣሽ ሎተሪ በገዛቻዉ 3 ሎተሪ ትኬቶች የ12 ሚሊዮን ብር አሸናፊ መሆኑን የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ ነዋይ ተናግረዋል፡፡
ዕድለኛዉ የሎተሪ ሽልማት የጊዜ ገደብ ሊጠናቀቅ አራት ቀናት ሲቀረዉ እንደተገኝም ታዉቋል፡፡
እድለኛው ለተፈናቃዮች ከአርባ ምንጭ ያሰባሰበውን የተለያየ አይነት ያላቸው አቃዎች ገቢ ለማድረግ ወደ ዱራሜ በመሄድ ላይ ሳለ በገዛው ሎተሪ ነው አሸናፊ መሆን የቻለው፡፡
ወጣቱ የሁለት ልጆች አባት ሲሆን ቋሚ ገቢ የሌለው እና የተለያዩ ስራዎችን በመስራት እንደሚተዳደር ነው ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 በዘገባው የገለፀው።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ መግለጫ ፦ የእጩዎች ምዝገባ መጠናቀቅን አስመልክቶ በዛሬው እለት ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ መገለጫ ሰጥቷል። በመግለጫው ፦ - ሁሉም ህጋዊ ሰውነት ያላቸው ፓርቲዎች በራሳቸው ወይም በፈጠሩት ትብብር/ህብረት አማካኝነት 53 የፖለቲካ ፓርቲዎች 49 ምርጫ መወዳደሪያ ምልክት ውስደዋል። - ምርጫ ምልከት ከወሰዱ 49 ፓርቲዎች ውስጥ 47 ፓርቲዎች እጩዎቻቸውን አስመዝግበዋል። …
#Update
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ እስካሁን በተገኘው መረጃ እጩዎችን ያስመዘገቡ ፓርቲዎች ዝርዝር ዛሬ ይፋ አድርጓል።
ይህ ዝርዝር ጊዜያዊ ሲሆን ሊቀየር እንደሚችልም ጠቁሟል።
47 ፓርቲዎች በድምሩ 8,209 እጩዎችን አስመዝግበዋል።
በግል የሚወዳደሩ 125 እጩዎች ተመዝግበዋል።
የትኞቹ ፓርቲዎች እጩ አስመዘገቡ ? ከላይ ይመልከቱ።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ እስካሁን በተገኘው መረጃ እጩዎችን ያስመዘገቡ ፓርቲዎች ዝርዝር ዛሬ ይፋ አድርጓል።
ይህ ዝርዝር ጊዜያዊ ሲሆን ሊቀየር እንደሚችልም ጠቁሟል።
47 ፓርቲዎች በድምሩ 8,209 እጩዎችን አስመዝግበዋል።
በግል የሚወዳደሩ 125 እጩዎች ተመዝግበዋል።
የትኞቹ ፓርቲዎች እጩ አስመዘገቡ ? ከላይ ይመልከቱ።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የአማራ ክልል ፕሬዜዳንት አቶ አገኘሁ ተሻገር በተለያዩ ክልሎች በአማራ ተወላጆች ላይ የሚደርሰው ግፍ እና በደል እንዲቆም የክልሉ መንግስት እየሰራ እንደሚገኝ ገለፀዋል።
አቶ አገኘው ይህን የገለፁት ትላንት የ6 ወር ሪፖርት ሲያቀርቡ ነው።
በአማራ ክልል ተወላጆች ላይ የሚፈፀመው ግድያው እና መፈናቀሉ በቶሎ መፍትሄ ካልተገኘለት ወደፊት አስጊ ደረጃ ላይ ይደርሳል ሲሉም አቶ አገኘሁ አስገንዝበዋል።
አቶ አገኘሁ ፥ "በአማራ ተወላጆች ላይ የሚደርሰው ግፍና በደል እንዲቆም በቀጣይ የማይሰራ ከሆነ የክልሉ ህዝብ የሚደርሰውን ግፍ እንዲሁም በደል ለመከላከል እና ለማስቆም ወደሌላ አቅጣጫ እንዳይሄድ ችግሮች በተከሰቱባቸው ቦታዎች በጥንቃቄ ከሌሎች አካላት ጋር በመሆን መፍትሄ ካልመጣ ለወደፊቱ አስጊ ሁኔታ ሊደርስ ይችላል" ብለዋል።
የክልሉ መንግስት በዚህ ጉዳይ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ የገለፁ ሲሆን እስካሁን ባለው ሂደትም ተከታታይ ጥረቶች እየተደረጉ መሆናቸውን አሳውቀዋል።
https://telegra.ph/Ato-Agegnehu-Teshager-03-12

Ato Agegnehu Teshager
የአማራ ክልል ፕሬዜዳንት አቶ አገኘሁ ተሻገር በ6 ወር ሪፖርታቸው ፦ የአማራ ክልል ፕሬዜዳንት አቶ አገኘሁ ተሻገር በተለያዩ ክልሎች በአማራ ተወላጆች ላይ የሚደርሰው ግፍ እና በደል እንዲቆም የክልሉ መንግስት እየሰራ እንደሚገኝ ገለፀዋል ፤ ግድያው እና መፈናቀሉ በቶሎ መፍትሄ ካልተገኘለት ወደፊት አስጊ ደረጃ ላይ ይደርሳል ሲሉ አስገንዝበዋል። አቶ አገኘሁ ፥ "በአማራ ተወላጆች ላይ የሚደርሰው ግፍ እና…
"...ወደ ፖለቲካው ሃይማኖትን ይዤ አልመጣሁም" - በግል ለፓርላማ የሚወዳደሩት ኡስታዝ ከሚል ሸምሱ
By : Ahadu FM 94.3
6ተኛው ሀገራዊ ምርጫ ሊካሄድ ወራት የቀሩት ሲሆን በምርጫው የሚሳተፉ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ዝግጅት እያደረጉ ይገኛሉ፡፡
ከእነዚህም ውስጥ አንዱ በግላቸው ለፓርላማ የሚወዳደሩት ኡስታዝ ከሚል ሸምሱ ናቸው፡፡
የሃይማኖት መምህር የሆኑት ኡስታዝ ከሚል ሸምሱ ወደ ፖለቲካው ስመጣ ሃይማኖቴን ይዤ ሳይሆን ለሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ አንደበት ለመሆን ነው ብለዋል፡፡
ከዚህ ቀደም የነበረው ፓርላማ የተለየ ሃሳብ የማይንፀባረቅበት መሆኑን ያነሱት ኡስታዝ ከሚል ፓርላማው አሳታፊ ሊሆን ይገባል የሚል እምነት እንዳላቸው ገልፀዋል።
ምርጫው ላይ ለመወዳደር ዝግጅት እያደረጉ መሆኑን የገለፁት ኡስታዝ ከሚል ፖለቲካ ሙያ ነው ለምርጫው ስወዳደርም እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ እንጂ ሃይማቴን ተገን አድርጌ ለእምነቱ ተከታዮች ብቻ አይደለም ብለዋል።

ኢትዮጵያ ዜጎቿን ከሳዑዲ አረቢያ ማስወጣቷን ቀጥላለች።
ኢትዮጵያ ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ በችግር ላይ የወደቁ ዜጎችን በተከታታይ እያስወጣች ወደሀገራቸው እንዲመለሱ እያደረገች እንደሆነ ይታወቃል።
በዛሬው ዕለት 292 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረብያ ጂዳ ወደ ሀገራቸው ኢትዮጵያ ተመልሰዋል።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ኢትዮጵያ ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ በችግር ላይ የወደቁ ዜጎችን በተከታታይ እያስወጣች ወደሀገራቸው እንዲመለሱ እያደረገች እንደሆነ ይታወቃል።
በዛሬው ዕለት 292 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ አረብያ ጂዳ ወደ ሀገራቸው ኢትዮጵያ ተመልሰዋል።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
“የትግራይ ጉዳይ ያሳስበናል” - IMF
By : https://am.al-ain.com/ (አል ዓይን)
በትግራይ ያጋጠመውን ሰብአዊ ቀውስ የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) በትኩረት እየተከታተለው መሆኑን የድርጅቱ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጅዮርጅየቫ ተናገሩ፡፡
ዳይሬክተርዋ ከToday News Africa’s የአለም አቀፍ ጉዳዮች ዘጋቢ ሳይሞን አቴባ ጋር በነበራቸው ቃለ ምልልስ እንዳሉት ከሆነ፤ በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል የተከሰተው ቀውስ ከሰብኣዊ እርዳታ በተጨማሪ የኢኮኖሚ ምላሽ የሚያስፈልገው ነው ብለዋል፡፡
“የትግራይ ጉዳይ ያሳስበናል” ያለው ሁኔታ በቅርበት እየተከታተልነው ነው ፤ በእንደዚህ አይነት ሰብአዊ ቀውስ ዜጎች ያልተገባ ዋጋ ሊከፍሉ አይገባም ሲሉ ተናገረዋል የአለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ማኔጂንግ ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጅዮርጅየቫ፡፡
ክሪስታሊና ጅዮርጅየቫ አሁን በሀገሪቱ ያለው አጠቃላይ የኢኮኖሚ ሁኔታና የሚፈጥረው ተፅእኖ ድርጅታቸው IMF በትኩረት እየተከታተለው መሆኑ በመናገር፤ ሀገሪቱ የኢኮኖሚ ጫናውን ተቋቁማ መቀጠል እንድትችል አስፈላጊውን ምክረ ሀሳብ ለመስጠት ድርጅታቸው ዝግጁ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
ማኔጂንግ ዳይሬክተርዋ የኢትዮጵያ ጥሩ መሆን ለተቀረው አህጉረ አፍሪካ ወሳኝ ነው ብለዋል።

ወንድ ህፃናትን የደፈሩ ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ ፦
#አርባ_ምንጭ :
በ10 ዓመት ህጻን ላይ የግብረ-ሰዶም ወንጀል የፈጸመ ግለሰብ በ18 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን የአርባ ምንጭ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አሳወቀ፡፡
ተከሳሽ አቶ ተመኘሁ ጣሰው የተባለ በከተማው የድልፋና ቀበሌ ነዋሪ የሆነ የ39 ዓመት ግለሰብ በቀበሌው ነዋሪ የሆነውን የ10 ዓመት ህጻን ላይ የግብረ - ሰዶም ወንጀል መፈጸሙን ፍርድ ቤቱ በሰነድና በሰው ማስረጃ አረጋግጧል።
ወንጀሉን ለየት የሚያደርገው በአከባቢው ያልተለመደ እና የግል ተበዳይን በተደጋጋሚ በማስፈራራት ተከሳሽ ወንጀሉን እየፈጸመ መቆየቱና በመጨረሻ በአርባ ምንጭ ከተማ ሼቻ ቀበሌ "ገሮ መኝታ ቤት" ወንጀሉን እየፈጸመ እያለ በአከባቢው ህብረተሰብ ጥቆማ ሊያዝ መቻሉ ነው።
በወንጀል ህግ ቁጥር 631 ንዑስ 1 ሀ መሠረት በአቃቤ ህግ ክስ ቀርቦ ፍርድ ቤቱ ተከሳሽ ወንጀሉን ስለመፈጸሙ የሰውና የሰነድ ማስረጃ በማጣራት በ18 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ተወስኗል።
#ማዕከላዊ_ጎንደር ፡
በአማራ ክልል በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ዐቃቤ ሕግ መምርያ የግብረ ሰዶም ወንጀል የፈፀመውን ግለሰብ በእስራት ቀጥቷል።
ተከሳሽ አቶ የምስራች ዓባይ ጥር 28 ቀን 2013 ዓ.ም. ከቀኑ 5:00 ላይ ታች አርማጭሆ ወረዳ ሙሴ ባንብ ቀበሌ የ8 ዓመት ሕፃን ወንድ ልጅ አስገድዶ ደፍሯል፡፡
የሙሴ ባንብ ንዑስ ወረዳ ፍርድ ቤት የተከሳሽን የወንጀል ድርጊት በሰው እና በሕክምና ማስረጃ ማረጋገጥ ችሏል፡፡
ተከሳሽ የወንጀል ሕግ ቁ631/1/ለ/ ላይ የተደነገገውን በመተላለፉ በ10 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል፡፡
መልዕክት ፦
ወላጆችና አሳዳጊዎች ህጻናት ለወንጀል ተጋላጭ እና ራሳቸውን ለመከላከል ስለማይችሉ የጥቃት ሰለባዎች እንዳይሆኑ የልጆቻቸሁን አዋዋል ልትከታተሉና ልትቆጣጠሩ ይገባል።
በህጻናት ላይ የተለየና አጣራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥም ለሚመለከተው አካል ጥቆማ ስጡ።
[ይህ መረጃ የተሰባጠረው ከአርባ ምንጭ ኮሚኒኬሽን ፣ የአርባ ምርጭ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፕሬዜዳንት አቶ አለማየሁ አልታዬ እና ከአዲስ ዘይቤ /Addis Zeybe/ ደረገፅ ነው]