TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.43K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በሀገራችን ኢትዮጵያ በኮቪድ-19 የተያዙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ከ160 ሺህ አለፈ !

ባለፉት 24 ሰዓት 6,030 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 841 ሰዎች ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል።

በተመሳሳይ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የ13 ሰዎች ሞት ሲመዘገብ 902 አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን 160,813 ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን ከነዚህ መካከል 2,386ቱ ህይወታቸው አልፏል ፤ 136,079 ከበሽታው አገግመዋል።

በአሁን ሰዓት 366 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#Purpose #Tikvah
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦብነግ) በምርጫ 2013 እንደሚሳተፍ አስታወቀ !

የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦብነግ) በመጪው 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ እንደሚሳተፍ አስታውቋል።

በቅርቡ በተወሰኑ የኦብነግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት የፓርቲው ግዜያዊ ሊቀመንበር ሆነው የተመረጡት አቶ ረያሌ ሃሙድ ፥ ኦብነግን የሚወክሉ እጩ አባላት መረጣ በመጠናቀቅ ላይ እንደሆነ ገልፀው በቅርብ ቀን በመላው ክልሉ የፖለቲካ ማኒፌስቶና የምረጡኝ ቅስቀሳ ፓርቲው እንደሚጀምር ለሶማሊ ክልል ቴሌቪዥን ገልፀዋል።

አክለው ህዝቡ ለወደፊት የሚሰጠውን ድምፅ ኦብነግ ይተማመንበታል ብለው ፤ 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ በጦር ካምፖች ውስጥ ይካሄዱ የነበሩት ምርጫዎች እንደሚለይ እምነታችን ነው ብለዋል።

በሌላ በኩል አቶ ረያሌ በሶማሊ ክልል እየታየ ያለውን የድርቅ ስጋት የፌዴራልና የክልሉ መንግሥት እንዲሁም አለም አቀፉ ማህበረሰብ ለድርቅ ስጋቱ አፋጣኝ መልስ እንዲሰጡ ጥሪ ማቅረባቸውን የሶማሊ ክልል ቴሌቪዥን ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አንቶኒ ብሊንከን ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር እንደተወያዩ ተገለፀ።

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ጋር መወያየታቸውን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ዛሬ አስታውቋል።

የውጭ ጉዳይ ኃላፊው በውይይቱ ወቅት በትግራይ ክልል ያለው የሰብአዊ እርዳናታና የሰብአዊ መብቶች ቀውስ አሜሪካንን እንደሚያሳስባት አጽንኦት ሰጥተው ከጠቅላይ ሚኒስተሩ ጋር መነጋገራቸው ተገልጿል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በአስቸኳይ ግጭቶች ቆመው የኤርትራ ወታደሮች እና የአማራ ክልል የጸጥታ ኃይሎችን ጨምሮ ከትግራይ ክልል እንዲወጡ አጥብቀው መጠየቃቸው ተገልጿል።

አንቶኒ ብሊንከን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ጋር ባደረጉት ውይይት በቅርቡ ኢትዮጵያ ወደ ትግራይ የሚደረጉ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦቶች ያለምንም ገደብ እንዲካሄዱ መፍቀዷን አድንቀዋል።

በተጨማሪ አሜሪካ ግጭቱ መፍትሔ እንዲያገኝ ለመርዳት ዝግጁ መሆኗንና በመላው ኢትዮጵያ የሚያስፈልግ ህይወት አድን የሰብአዊ እርዳታን በማቅረብ በኩል ያላትን ፈቃደኝነት ገልጸዋል።

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስተር አንቴኒ ብሊንከን እና ጠ/ሚር ዶክተር አብይ አህመድ አደረጉት ስለተባለው ንግግር በተመለከተ በኢትዮጵያ በኩል እስካሁን የተባለ ነገር የለም።

(ተጨማሪ በInstant View ያንብቡ)

https://telegra.ph/Secretary-Antony-Blinken-03-02
የሱዳን እና ግብፅ ነገር ...?

የግብፅ ጦር አዛዥ ካርቱም ፤ የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ካይሮ ናቸው።

ካርቱም ላይ ፦

ሰኞ ወደ ካርቱም ያመሩት የግብፅ ጦር አዛዥ ሌ/ጀ ሞሀመድ ፋሪድ ከሱዳን አቻቸው ሌ/ጀ ሞሀመድ አል ሁሴን ጋር የተለያዩ ወታደራዊ ስምምነቶችን ፈፅመዋል።

የግብፁ ጦር አዛዥ ማምሻውን በሰጡት መግለጫ ግብፅ እና ሱዳን ተመሳሳይ ብሄራዊ የደህንነት ስጋት ተደቅኖባቸዋል ፤ በጋራ መስራት የሚገባን ጊዜ አሁን ነው ብለዋል። እንዲሁም "ሱዳን ለምታቀርብልን ወታደራዊ ነክ ጥያቄዎች ሁሉ ምላሽ ለመስጠት ግብፅ ዝግጁ ናት" ሲሉ ተናግረዋል ።

የሰዳኑ አቻቸው እንዳሉት ደግሞ ሃገራቱ የጋራ አደጋ የተደቀነባቸው በመሆኑ በወታደራዊ መስክ ትብብራቸው ጠንክሯል ብለዋል።

ካይሮ ላይ ፦

የሱዳን ው/ጉ/ሚኒስትር ማርየም አል ሳዲቅ ግብፅ በማቅናት በዋናነት በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ከግብፅ መንግስት ሃላፊዎች ጋር ሲመክሩ ዉለዋል።

የህዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌትን እንዳይካሄድ ለማድረግ ያስችላል ያሉትን ምክክር አድርገዋል።

የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርየም አል ሳዲቅ ፥ ኢትዮጵያ ለብቻዋን የምታደርገውን ነገር እንድታቆም እንነግራታለን ፥ አካሄዷ ወደአላስፈላጊ አቅጣጫ ይዞን ሊሄድ ይችላልም ሲሉ ማስፈራሪያ አዘል ንግግር ሲያደርጉ ተደምጠዋል።

የግብፅ እና ሱዳን ሚኒስትሮች በጋራ በሰጡት መግለጫ አለም አቀፍ አሸማጋዮች በድርድሩ እንዲገቡ ግፊት ለማድረግ ተስማምተዋል።

(Selam Mulgeta ,Ustath Jemal Bashir)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
TIKVAH-ETHIOPIA
አልጀዚራ በትግራይ : በተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች የነዋሪዎች የውስጥ ሮሮ እና ብሶት የሚታዩ እውነታዎች ናቸው። የትግራይ ነዋሪዎች እንደሚገልፁት በኢትዮጵያ ሰሜኑ ክፍል ላይ የኤርትራ ወታደሮች እኩይ ተግባር ፈፅመዋል። አልጀዚራ በተንቀሳቀሰበት አካባቢ የትግራይ ነዋሪዎች ከምንም ነገር በፊት የሚያነሱት ጉዳይ የኤርትራ ወታደሮች የፈፀሙትን በደል ነው። የትግራይ ነዋሪዎች የኤርትራ ወታደሮች ከትግራይ…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
* Tigray

እድሜዋ ገና 18 ነው ፤ ስሟ ሞናሊዝ አብርሃ ይባላል።

የኤርትራ ወታደሮች ናቸው ካለቻቸው ሰዎች ጋር የገጠማትን ነገር ተናግራለች።

"የኤርትራ ወታደሮች ገብተው አያቴ ባለበት ሊደፍሩኝ ሞከሩ። ከአያቴ ጋርም ትግል ጀመሩ። ... እሱም እንቢ ብሎ በተከላከለበት ሰዓት መጥተው እኔን ሊደፍሩኝ ሞከሩ። አንዱ ወታደር እኔን ለማስደንገጥ ጥይት ተኮሰ ፤ ነገር ግን እጄን ነበር የመታኝ። ከዛም በኃላ ሌላ ጥይት ተኩሶ እግሬን አቆሠለኝ። ይህ ከሆነ በኃላ በወደኩበት ብዙ ደም ከፈሰሰኝ በኃላ ሰዎች መጥተው አዳኑኝ ፤ ሆስፒታልም መጥቼ እጄ ተቆርጧል።"

የሞናሊዛ ታሪክ ከተከሰቱት ክስተቶች መካከል አንዱ እንጂ ብዙዎች አሉ።

[Al Jazeera Tigray]
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#FDREDefenseForce

የልዩ ዘመቻዎች ኃይል የአየር ወለድ ስልጠና ማጠናቀቂያ የአየር ወለድ ዝላይ ትርኢት በዱከም አካሄደ።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ብርሃኑ ጁላን ጨምሮ ከፍተኛ የመከላከያ ሠራዊት አመራሮች በተገኙበት በአገር መከላከያ ሚኒስቴር የልዩ ዘመቻዎች ኃይል ማሰልጠኛ የአየር ወለድ ስልጠና ማጠናቀቂያ መርሐግብር በዱከም የአየር ወለድ ዝላይ ሜዳ ላይ አካሒዷል።

የዝላይ ትርኢቱ የልዩ ዘመቻዎች ኃይል አየር ወለድ የደረሰበትን ከፍተኛ አቅም የሚያሳይ መሆኑንና ሰልጣኞቹ ከአየር ወለድ ስልጠናው በተጨማሪ ልዩ ልዩ የኦፕሬሽናልና የውጊያ ስልጠናዎችን የወሰዱ መሆናቸው ተገልጿል።

በሌላ በኩል በልዩ ዘመቻዎች ኃይል ማሰልጠኛ ማዕከል ስር የሚገኘውን የአየር ወለድ ትምህርት ቤትን ለማጠናከር የአዲስ ህንጻ ግንባታ መሰረተ ድንጋይ ይቀመጣል ተብሏል።

በቢሾፍቱ የአየር ወለድ ትምህርት ቤት ጊቢ አጠቃላይ የአየር ወለድ የስልጠና ሂደት ጉብኝትና የመሰረተ ድንጋይ ማስቀመጥ መርሐግብሩ እንደሚካሔድ ነው የተገለጸው። (ኢዜአ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#OromoFederalistCongress

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ባወጣው መግለጫ :

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ባወጣው መግለጫ መንግስት በኃይል ዘጋብኝ ያላቸው ጽህፈት ቤቶቹ ተከፍተውና የታሰሩ አባሎቹ እንዲፈቱ በድጋሚ ጠይቋል።

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ አስፈላጊ ከሆነ የምርጫ መርሐ ግብሩ ተሻሽሎ እና የፖለቲካ ምህዳሩ ለሁሉም ዜጎች ተመቻችቶ ፣ ከሁሉም በላይ ደግሞ የተሳካ ብሔራዊ መግባባት ተደርጎ የተሳካ ብሔራዊ ምርጫ እንዲካሄድ ሲልም ጠይቋል።

ፓርቲው በመግለጫው ለዜጎቿ ሁሉ የምትሆን ኢትዮጵያ እንድትፈጠር በሚደረገው ሠላማዊ ትግል ጎን በፅናት እቆማለሁ ሲል አረጋግጧል።

* ዝርዝር መግለጫው ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#EthiopiaElection2013

አብን በተለያዩ አካባቢዎች የምርጫ ቅስቀሳ ማደረጉን ገለፀ።

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ለምርጫ 2013 የሚያደርገውን ዝግጅት አጠናክሮ መቀጠሉን ገልጿል።

አብን በም/ጎጃም ዞን ጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ ግንደወይን ከተማ እና በማቻከል ወረዳ ደጋሰኝና ደብረቀለም ታዳጊ ከተሞች ፣ እና በደቡብ ወሎ ዞን አማራ ሳይንት «ታሪክ እየጠበቅን ታሪክ ለመስራት ድምጻችንን ለአብን እንስጥ!» በሚል መሪ ቃል የካቲት 22 እና 23 ቀን 2013 ዓ.ም ይፋዊ የምርጫ ቅስቀሳ እንዳካሄደ አሳውቋል።

አብን ከየካቲት 14/2013 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ አካባቢዎች ይፋዊ የምርጫ ቅስቀሳ በማካሄድ ላይ ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የሱዳን እና ግብፅ ነገር ...? የግብፅ ጦር አዛዥ ካርቱም ፤ የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ካይሮ ናቸው። ካርቱም ላይ ፦ ሰኞ ወደ ካርቱም ያመሩት የግብፅ ጦር አዛዥ ሌ/ጀ ሞሀመድ ፋሪድ ከሱዳን አቻቸው ሌ/ጀ ሞሀመድ አል ሁሴን ጋር የተለያዩ ወታደራዊ ስምምነቶችን ፈፅመዋል። የግብፁ ጦር አዛዥ ማምሻውን በሰጡት መግለጫ ግብፅ እና ሱዳን ተመሳሳይ ብሄራዊ የደህንነት ስጋት ተደቅኖባቸዋል ፤ በጋራ መስራት…
የግብፁ ፕሬዜዳንት አል ሲ ሲ ሱዳንን ሊጎበኙ ነው።

የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርየም ሳዲቅ ኣልመሃዲ የግብፁ ፕሬዜዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲ ሲ ከከፍተኛ የሀገሪቱ ልዕካን ጋር በመጪዎቹ ቀናት ሱዳንን እንደሚጎበኙ አሳውቀዋል።

በጉብኝቱ አል ሲ ሲ ከአብድል ፈታህ አልቡርሃን ጋርም ይመክራሉ ተብሏል።

ምክክር የሚያደርጉትም ስለሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ፣ ስለ አካባቢ እና አለም አቀፋዊ ጉዳዮች እንደሆነ ተሰምቷል።

አብዱል ፈታህ አል ሲ ሲ በመጭው ቅዳሜ ነው ሱዳንን ይጎበኛሉ የተባለው።

በትላንትናው ዕለት የሁለቱ ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ግብፅ ካይሮ ላይ በህዳሴ ግድብ ድርድር ላይ ያላቸውን አቋም መግለፃቸው ፤ ካርቱም ላይ ደግሞ በጦር ኢታማዦር ሹሞቻቸው ወታደራዊ ስምምነት ማድረጋቸው ይታወቃል።

@tikvahethiopia
በኢራቅ ወታደራዊ ቤዝ ላይ የሮኬት ጥቃት ተፈፀመ።

በኢራቅ አል አንባር ግዛት በሚገኘው አይን አል አሳድ ኤር ቤዝ የሮኬት ጥቃት እንደተፈፀመበት ተሰማ።

ይህ የወታደሮች ቤዝ የኢራቅ እና የአሜሪካ ወታደሮች በጥምረት የሚገኙበት ነው።

አሁን በወጣው የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት አይን አል አሳድ ቤዝ በ10 ሮኬቶች ጥቃት እንደተፈፀመት ተገልጿል።

የአሜሪካ ጦርም ስለጥቃቱ ማረጋገጫ የሰጠ ሲሆን የኢራቅ የደህንነት ሰዎች ምርመራ እያደረጉ ነው ብሏል።

የኢራቅ ጦር ዘግየት ብሎ ባወጣው መግለጫ ጥቃቱ የከፋ ጉዳት እንዳላደረሰ ገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሳምንታዊ መግለጫ ፦

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ ሳምንታዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸው ላይ ከዚህ ቀደም በፍቃድ ይገቡ የነበሩ በትግራይ ሰብአዊ ድጋፍ የሚሰጡ ዓለም አቀፍ ረጅ ተቋማት አሁን ላይ በማሳወቅ ብቻ እየገቡ መሆኑን ገልጸዋል።

ከሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦት ጋር ተያይዞ መንግስት 70 በመቶውን ማቅረቡን አስረድተዋል።

በትግራይ ክልል የሚነሳውን የሰብአዊ መብት ጥሰት በተመለከተ የማጣራት ስራ እየተሰራ መሆኑንም አሳውቀዋል።

ከዚህ ጋር ተያይዞ የህግ ጥሰት ፈፅመዋል የተባሉ አካላትን ለህግ ለማቅረብ እየተሰራ ስለመሆኑም መግለጫቸውን ኤፍቢሲ (FBC) በድረገፁ አስነብቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Election2013

የአማራ ክልል ፕሬዜዳንት አቶ አገኘሁ ተሻገር የጎንደር ከተማ ሕዝብን ወክለው ለክልል ምክር ቤት ለመወዳደር በእጩነት ተመዘገቡ።

ፕሬዜዳንቱ የብልፅግና ፓርቲን ወክለው ነው በጎንደር ከተማ በሚገኘው ምርጫ ክልል 2 ነው በእጩነት የተመዘገቡት።

አቶ አገኘው ተሻገር በምዝገባው ወቅት የምርጫ ክልሉ ሠራተኞች በአግባቡ እንዳስተናገዷቸው ተናግረዋል።

አቶ አገኘሁ ቀጣዩ ምርጫ ዲሞክራሲያዊ እንዲሆን አንድም እንደ መንግሥት ሁለትም እንደ ፓርቲ ኀላፊነታቸውን እየተወጡ እንደሚገኙ ገልፀዋል።

የጎንደር ከተማ ምርጫ ክልል 2 ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሰለሞን ካሳይ እስካሁን በምርጫ ክልሉ የተመዘገቡ እጩ አቶ አገኘሁ መሆናቸውን በመጠቆም ሌሎች 3 እጩዎች በቀሪ ቀናት እንዲመዘገቡ ጥሪ ማቅረባቸውን አብመድ ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ጋዜጠኛ ግርማይ ገብሩ በቁጥጥር ስር ዋለ። የቢቢሲ የትግርኛ ቋንቋ አገልግሎት ጋዜጠኛው ግርማይ ገብሩ ዛሬ በመቐለ ከተማ በወታደሮች ቁጥጥር ስር መዋሉን ቢቢሲ አሳወቀ። የዓይን እማኞች ጋዜጠኛ ግርማይ ገብሩን ወታደሮች ከነበረበት ካፌ ይዘውት ሲሄዱ መመልከታቸውን ተናግረዋል። ቢቢሲ ጋዜጠኛው በምን ምክንያት በቁጥጥር ስር እንደዋለ የማውቀው ነገር የለም ብሏል። ነገር ግን ጋዜጠኛ ግርማይ እዛው መቐለ…
ጋዜጠኛ ግርማይ ገብሩ ከእስር ተፈታ።

መቐለ ውሰጥ በወታደሮች በቁጥጥር ሥር ውሎ የነበረው የቢቢሲ ሪፖርተር ግርማይ ገብሩ ዛሬ ከእስር ተለቀቀ።

ጋዜጠኛ ግርማይ ከእስር የተለቀቀው ለሁለት ቀናት በእስር ከቆየ በኋላ ምንም አይነት ክስ ሳይመሰረትበት ነው።

ጋዜጠኛዬ በምን ምክያት እንደታሰረ መረጃ የለኝም ብሏል ቢቢሲ።

ግርማይ ከተያዘ በኋላ መጀመሪያ ላይ በወታደራዊ ካምፕ ውስጥ የቆ ሲሆን በኋላ ላይ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ተዘዋውሮ ነበር ተብሏል።

ትግራይ ውስጥ ከግርማይ በተጨማሪ ታስረው ነበሩ የኤ ኤፍ ፒ ዜና ወኪልና የፋይናንሻል ታይምስ ዘጋቢ እና አስተርጓሚዎች ከእስር መለቀቃቸው ቢቢሲ በድረገፁ አስነብቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#FDREDefenseForce የልዩ ዘመቻዎች ኃይል የአየር ወለድ ስልጠና ማጠናቀቂያ የአየር ወለድ ዝላይ ትርኢት በዱከም አካሄደ። የኢፌዴሪ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ብርሃኑ ጁላን ጨምሮ ከፍተኛ የመከላከያ ሠራዊት አመራሮች በተገኙበት በአገር መከላከያ ሚኒስቴር የልዩ ዘመቻዎች ኃይል ማሰልጠኛ የአየር ወለድ ስልጠና ማጠናቀቂያ መርሐግብር በዱከም የአየር ወለድ ዝላይ ሜዳ ላይ አካሒዷል። የዝላይ ትርኢቱ…
#Update

ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ በልዩ ዘመቻዎች ኃይል ማሰልጠኛ ማዕከል ስር በሚገኘው የአየር ወለድ ትምህርት ቤት አዲስ ህንጻ ግንባታ መሰረተ ድንጋይ በቢሸፍቱ አየር ኃይል ጊቢ ውስጥ አስቀምጠዋል።

ህንጻው በ170 ሚሊዮን ብር ወጪ የሚገነባ ሲሆን በአንድ አመት ውስጥ ተሰርቶ እንደሚጠናቀቅ መገለፁን ከኢዜአ የተገኘው መረጃ ይጠቁማል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
እነሜ/ጄኔራል ገብረመድህን ፍቃዴ ክስ ሊመሰረትባቸው ነው።

የመከላከያ ሰራዊት ሬዲዮ ግንኙነትን በማቋረጥ ሰሜን ዕዝ ጦር ላይ ጥቃት እንዲደርስ አድርገዋል የተባሉት የመከላከያ ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ እነ ሜጀር ጄኔራል ገብረመድህን ፍቃዴ (ወዲነጮ) ክስ ሊመሰረትባቸው ነው፡፡

በዛሬው ዕለት በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ በተጠርጣሪዎቹ ላይ ክስ መመስረቻ ጊዜ ጠይቆ ተፈቅዶለታል፡፡

ክስ መመስረቻ የተጠየቀባቸው ተጠርጣሪዎች ፦

- የመከላከያ ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ ሜ/ጄኔራል ገብረመድህን ፍቃዴ፣
- ሜጀር ጄኔራል ይርዳው ገብረመድህን፣
- ብርጋዴር ጄኔራል አብርሃም መውጫ፣
- ኮሎኔል ገብረህይወት ደስታ፣
- ኮሎኔል ዮሃንስ በቀለ፣
- ኮሎኔል ዘመን ታመነ ፣
- ሻለቃ ገብረእግዚአብሄር ግርማይ፣
- ሌተናል ኮሎኔል ተክለ ኃይሉ፣
- ሌተናል ኮሎኔል ምሩጽ ወልደአረጋይ፣
- ሻለቃ ኃይለስላሴ ግርማይ እና ሻለቃ ብርኃኔ ገብሩ ናቸው፡፡

ከላይ የተዘረዘሩት ተጠርጣሪዎች በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ቡድን በተጠረጠሩበት ህገመንግስቱንና ህገመንግስታዊ ስርዓቱን ለመናድ ሙከራ ወንጀል ምርመራ ሲደረግባቸው ቆይቷል።

ምርመራው መጠናቀቁን ተከትሎ ዐ/ህግ ክስ መመስረቻ ጊዜ ጠይቆባቸዋል፡፡

ዐቃቤ ህግ ከጠየቀው 15 ቀናት ውስጥ 10 ቀናት ፍርድ ቤቱ በመፍቀድ ክስ እንዲመሰርት የምርመራ መዝገቡን መዝጋቱን አስታውቋል፡፡

ዐቃቤ ህግ በተጠቀሰው ጊዜ ከስ ካልመሰረተ በሌላ መዝገብ ተጠርጣሪዎቹ መብታቸውን መጠየቅ ይችላሉ ሲል ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia