TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
56.9K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በእድሳት ምክንያት ተዘግቶ የቆየው "አምባሳደር ፓርክ" ተመረቀ !

የአ/አ "አምባሳደር ፓርክ" በ49 ሚሊየን ብር እድሳት ተደርጎለት በዛሬው ዕለት ተመርቋል፡፡

በ1 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው የአምባሳደር ፓርክ የእድሳት ስራ በ25 ወራት መጠናቀቁ ተገልጿል፡፡

በተመሳሳይ በ4 ሄክታር ቦታ ላይ በ101 ሚሊየን ብር የተገነባውና በመጀመሪያው የአዲስ አበባ ከንቲባ ስም የተሰየመው የቢትወደድ ወልደፃዲቅ ጎሹ መታሰቢያ ፓርክም በዛሬው ዕለት ተመርቋል፡፡

በሁለቱም ፓርኮች ምርቃት ላይ ላይ የአ/አ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች ተገኝተዋው እንደነበር ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬተሪያት የተገኘው መረጃ ያሳያል።

Photo : Abbas Shah (File)
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የእጩዎች ምዝገባ ለ4 ቀናት ተራዘመ!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለ6ተኛው አጠቃላይ ምርጫ የእጩዎች ምዝገባን እያከናወነ እንዳለ የሚታወቅ ነው።

• የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር
• የድሬደዋ ከተማ መስተዳድር
• የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል
• የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ብሔራዊ ክልል
• የጋምቤላ ብሔራዊ ክልል
• ሃሪሪ ብሔራዊ ክልል ለእጩዎች ምዝገባ የተቀመጠው የጊዜ ገደብ መሰረት የካቲት 08- 21 ድረስ እንደሚከናወን ማሳወቁ ምዝገባም መካሄድ መጀመሩ አዘነጋም።

ቦርዱ የእጩዎች ምዝገባ ሂደትን በመገምገም የምርጫ ክልል ቢሮዎች ለመከፈት በመዘግየታቸው ፣ የትራንስፓርት መጓተት የተወሰኑ የምርጫ ክልሎች ላይ የምዝገባ ቀንን በማራዘሙ እና የፖለቲካ ፓርቲዎች በተለያዩ ምክንያቶች እጩዎችን ለመመዝገብ ችግር ስላጋጠመን ይራዘምልን ብለው መጠየቃቸውን ገልጿል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከላይ የተጠቀሱት ምክንያቶች አሳማኝ ናቸው ያለ ሲሆን የመጀመሪያ ዙር ምዝገባ በጀመሩት ከላይ በተጠቀሱት ክልሎች/የከተማ መስተዳድሮች ላይ የሚካሄደው የእጩዎች ምዝገባ ለ4 ቀናት ያህል እስከ የካቲት 25 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ መራዘሙን ዛሬ አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AddisAbaba

ተደብቆ ወደ አዲስ አበባ የገባ ስናይፐር፣ ብሬን፣ ሽጉጥና ከ5 ሺህ በላይ ልዩ ልዩ ጥይቶች ተያዙ።

የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ባደረገው ክትትል ከጭነት ጋር ተመሳስሎ በረቀቀ መንገድ ተደብቆ ወደ አዲስ አበባ የገባ ስናይፐር፣ ብሬን ፣ ሽጉጥ ፣ ከ5ሺህ በላይ ልዩ ልዩ ጥይቶች እንደተያዘ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሸን አስታውቋል፡፡

መነሻውን ጎንደር ያደረገ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 አ/አ 99483 አይሱዙ ተሽከርካሪ በጉሌሌ ክፍለ ከተማ በቀድሞ ወረዳ 8 ልዩ ቦታው መንደር ሰባት ተብሎ በሚጠራ አካባቢ የካቲት 19 ቀን 2013 ዓ/ም ከሌሊቱ 10፡00 ሰዓት መያዙ ነው የተገለጸው።

በተደረገው ክትትልም 2 ብሬን ፣ 2 ስናይፐር ፣ 38 ትልቁ እና 25 ትንሹ ኢኮልፒ ሽጉጦች ፣ 5992 የክላሸ ኮቭ ጥይት ፣ 892 የኢኮልፒ ሽጉጥ ጥይት ፣ 5 የስናይፐር ጥይት ፣ የብሬን እግር እና ሁለት የብሬን ዝናር ህገወጥ የጦር መሳሪያውን ሲያዘዋወሩ ከተገኙ ሁለት ተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተደረገ ነው ተብሏል።

በተመሳሳይ ዜና በደቡብ ወሎ ዞን ኮምቦልቻ ከተማ በህገ ወጥ መንገድ 2 ሺህ ተተኳሽ የክላሽንኮቭ ጥይቶችን በድብቅ ሲገበያዩ የተገኙ ሦስት ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የከተማዋ ፖሊስ ማስታወቁን ኢዜአ ዘግቧል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#EthiopiaElection2013

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሀይማኖት መምህርነታቸውና በሚሰጧቸው ማህበራዊ ሂሶች የሚታወቁት ሙአዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በመጪው 6ተኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ በግላቸው እንደሚወዳደሩ አሳውቁ።

ሙአዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ለኢትዮጵየ ቼክ ድረገፅ በሰጡት ቃል ፥ "...በስድስተኛው አገር አቀፍ ምርጫ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እወዳደራለሁ" ብለዋል።

"ሀሳብ ከመስጠት ባለፈ በሂደቱ ተሳታፊ መሆን ይገባል ብዬ ስላመንኩ በምርጫው ለመሳተፍ ወስኛለሁ" የሚሉት ሙአዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል በአዲስ አበባ ከተማ በወረዳ 12/13 ምርጫ ክልል በግል ተወዳዳሪነት ዕጩ ሆነው አስረድተዋል።

ለምን በግል ለመወዳደር ፈለጉ በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ፥ "...ከፓርቲ ፖለቲካ ይልቅ ግላዊ ፖለቲካ የተሻለ ነው ብየ ስለማምን ነው" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ምንጭ፦ www.ethiopiacheck.org
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ወልርድ ቪዥን በትግራይ ከልማት ስራ ከሚሰራበት ገንዘቡ ቀንሶ በችግር ላይ ላሉ ወገኖች የገንዘብ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል !

ወርልድ ቪዥን የሰሜን ኢትዮጵያ ቅርንጫፍ በትግራይ የልማት ስራዎችን ከሚያከናውንበት በጀት 19 ሚሊዮን ብሩን በጦርነቱ ምክንያት ለችግር የተጋለጡ ዜጎች ድጋፍ ለማድረግ ስራውን ጀምሯል።

ወርልድ ቪዥን ባለፉት ቀናት በእንደርታ ወረዳ ለሚገኙ ዜጎች 4.5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ያደረገ ሲሆን በውቅሮ ኽልተ አውላዕሎ ለሚገኙ 590 የተቸገሩ ዜጎች ከ1.3 ሚሊዮን ብር በላይ የገንዝብ ድጋፍ አድርጓል።

ለአንድ ሰው 2,200 ብር ነው ወርልድ ቪዥን እየሰጠ የሚገኘው።

በአጠቃላይ በትግራይ ድርጅቱ በ7 ወረዳዎች ላይ የሚሰራ ሲሆን ለዚህ ድጋፍ 19 ሚሊዮን ብር መድቧል፤ በቀጣይ ወደ ሽረ፣ አላማጣ፣ ዓዲግራት እና ሌሎች ያልደረሰባቸው ቦታዎች በመድረስ ድጋፍ እንደሚያደርግ አሳውቋል።

ድርጅቱ እያደረገ ያለው ድጋፍ በቂ በለመሆኑ ሌሎች ዓለም አቀፍ ተቋማት እና ባለሀብቶች አፋጣኝ እርዳት ለትግራይ ህዝብ ማድረስ ይገባቸዋል ብሏል። ያለው ችግር መጠነ ሰፊ በመሆኑ ሁሉም ሊተባበር ይገባል ብሏል።

የወልርድ ቪዥን የሰሜን ኢትዮጵያ ቅርንጫፍ ተጠባባቂ ዳይሬክተር አቶ ተስፋይ አስፋ ፥ እንደድርጅት ሰራተኞች ከ10-15 ፐርሰንት ከደሞዝ ላይ ድጋፍ ለማድረግ ቃል እንደገቡ ገልፀዋል፤ ከደሞዛቸው ተቆርጦ ለትግራይ እገዛ ለማድረግ የወሰኑት በትግራይ ክልል ብቻ የሚሰሩ የወልድ ቪዥን ሰራተኞች ሳይሆኑ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ያሉ ሰራተኞች ናቸው።

ከዚህ በተጨማሪ በትግራይ ያሉ ባለሃብቶችን በማስተባበር ድጋፍ እንዲያደርጉ ገንዝብ የማሰባሰብ ሁኔታ እየተመቻቸ መሆኑ ተገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
2ኛው ዙር የደን ምንጣሮ ሊጀመር ነው #GERD🇪🇹

ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ውሃው በሚተኛበት ስፍራ ሁለተኛ ዙር የደን ምንጣሮ ስራ በመጪው መጋቢት ወር እንደሚጀመር የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ቴክኒክና ሙያ ስራ እድል ፈጠራ ኢንተርፕራይዞች ኤጀንሲ መግለፁን ኢዜአ ዘግቧል።

የህዳሴው ግድብ 2ኛ ዙር የውሃ ሙሌት ስራ ለማስጀመር ውሃው በሚተኛበት ስፍራ የሚገኘውን አካባቢ ምንጣሮ ስራ የሚከናወነው ክልሉ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋር ስምምነት በማድረግ ነው ተብሏል።

ሁለተኛ ዙር የደን ምንጣሮ ከመጪው መጋቢት እስከ ሚያዚያ ወር 2013 ዓ.ም. ይከናወናል።

የደን ምንጣሮ ስራው ከግድቡ ግራ እና ቀኝ በኩል የሚገኙ በመተከል ዞን ሰዳል፣ ሸርቆሌ እና ወምበራ ወረዳዎች የሚከናወን ሲሆን አራት ሺህ 854 ሄክታር ይሸፍናል።

ለደን ምንጣሮ ስራው 81 ሚሊዮን ብር መመደቡን ተገልጿል

ስራውን ለማከናወን በ500 ኢንተርፕራይዞች የታቀፉ ከ5 ሺህ በላይ የክልሉ ስራ አጥ ወጣቶች ናቸው።

ከባህር ጠለል በላይ ከ560 እስከ 595 ሜትር ከፍታ ላይ በሚከናወነውን የደን ምንጣሮ አንድ ኢንተርፕራይዝ እስከ 10 ሄክታር መሬት ድረስ ይሸፍናል ተብሏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ሟቾች ቁጥር ከ900 አለፈ! ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 25,158 የላብራቶሪ ምርመራ 1,206 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ21 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 531 ሰዎች አገግመዋል። በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 58,672 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 918 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 21,307…
በኢትዮጵያ 2013 ዓ/ም ከገባ በኃላ ከፍተኛው የኮቪድ-19 ኬዝ ተመዘገበ።

ኢትዮጵያ ውስጥ ባለፉት 24 ሰዓታ 1006 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ዶ/ር ሊያ ታደሰ በዕለታዊ ሪፖርታቸው አሳውቀዋል።

ይህ ቁጥር 2013 ዓ/ም ከገባ በኃላ የተመዘገበ ከፍተኛው ኬዝ መሆኑን ከዚህ ቀደም ሪፖርት የተደረጉትን ኬዞች መለስ ብለን በማየት ተረድተናል።

ኢትዮጵያ በኮቪድ-19 የሚያዙባት ዜጎቿ ቁጥር ከዕለት ወደዕለት እየጨመረ ሄዷል፤ የሟቾች እና የፅኑ ታማሚዎችም ቁጥር እንዲሁ በእጅጉ እየጨመረ ነው።

ኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሀገራችን ከገባ ጊዜ አንስቶ 158,053 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከነዚህ መካከል የ2,354ቱ ህይወት አልፏል፤ 134,736 ሰዎች አገግመዋል።

በአሁን ሰዓት በሀገራችን ኢትዮጵያ 377 ሰዎች በፅኑ ታመው ህክምና ክትትል ላይ ናቸው።

#Tikvah #Purpose
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አክሱም ዩኒቨርሲቲ ለ12ኛ ጊዜ ተማሪዎቹን አስመረቀ።

አክሱም ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ለ12ኛ ጊዜ 2,867 ተማሪዎችን በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ መርሃግብር አስመርቋል።

ተመራቂዎቹ 1848 ወንዶች ሲሆኑ 1,019 ሴቶች ናቸው።

አክሱም ዩኒቨርሲቲ ጥቅምት ወር ላይ ኮቪድ-19 ወረርሽኝ በመከላከል ተማሪዎቹን ለመቀበል ዝግጅት ካጠናቀቀ እና ተማሪዎቹን አስተምሮ ለማስመረቅ ከተዘጋጀ በኃላ በትግራይ ክልል በተፈጠረው አለመረጋጋት የተማሪዎች የምረቃ ጊዜ ከሚገባው ጊዜ በላይ መራዘሙን የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ፕሬዜዳንት ፕሮፌሰር ገብረእየሱስ ብርሃነ ተናግረዋል።

የዛሬዎቹ ተመራቂ ተማሪዎች ከባድ ውጣ ውረድ በትእግስት ተሻግረው ለምረቃ በመብቃታቸው ከፍተኛ ደስታ እንደተሰማቸው ፕ/ር ገብረእየሱስ ተናግረዋል።

በምርቃት ስነሥርዓቱ ላይ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ም/ስራ አስፈፃሚ አቶ አበበ ገ/ህይወት ተገኝተው ነበር።

#Mekelle #Tigray

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
አክሱም ዩኒቨርሲቲ ለ12ኛ ጊዜ ተማሪዎቹን አስመረቀ። አክሱም ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ለ12ኛ ጊዜ 2,867 ተማሪዎችን በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ መርሃግብር አስመርቋል። ተመራቂዎቹ 1848 ወንዶች ሲሆኑ 1,019 ሴቶች ናቸው። አክሱም ዩኒቨርሲቲ ጥቅምት ወር ላይ ኮቪድ-19 ወረርሽኝ በመከላከል ተማሪዎቹን ለመቀበል ዝግጅት ካጠናቀቀ እና ተማሪዎቹን አስተምሮ ለማስመረቅ ከተዘጋጀ በኃላ በትግራይ ክልል በተፈጠረው…
አክሱም ዩኒቨርሲቲ ከ1ኛ እስከ 4ኛ ዓመት ተማሪዎቹን በራሱ ዩኒቨርሲቲ ሊጠራ መሆኑን አሳወቀ !

በአክሱም ዩኒቨርሲቲ የደረሰው ዝርፊያና ጉዳት ከፍተኛ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዜዳንት ፕሮፌሰር ገብረእየሱስ ብርሃነ ዛሬ በነበረው የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ምረቃ ስነስርዓት ላይ ሲናገሩ ተደምጠዋል።

ዩኒቨርሲቲውን ወደነበረበት የቀድሞ ሁኔታ ለመመለስ ጥረት እየተደረገ መሆኑ ያሳወቁት ፕሮፌሰሩ የሁሉም አካላት ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

ከ1ኛ እስከ 4ኛ ዓመት የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች በአጭር ጊዜ ዩኒቨርሲቲው ዝግጅቱን አጠናቆ ተቋርጦ የነበረውን የመማር ማስተማር ሂደት ለማስቀጠል ወደ አክሱም ዩኒቨርሲቲ እንደሚጠራቸው ፕ/ር ገብረእየሱስ አሳውቀዋል።

በአክሱም ዩኒቨርሲቲ ላይ በደረሰው ውድመት እና ዝርፊያ ዛሬ ዩኒቨርሲቲው ያስመረቃቸው ለ12ኛ ጊዜ ያስመረቃቸው ተማሪዎች ያላጠናቀቁትን ትምህርት መቐለ ዩኒቨርሲቲ ገብተው በመማር ነው አጠናቀው የተመረቁት።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከ7 ወር እስር በኃላ ከእስር የተለቀቁት ፖለቲከኛ ፦

አቶ አመንቴ ግሺ (የቦሮ ዴሞክራክ ፓርቲ ሊቀ መንበር) ከ7 ወራት በኃላ ከአሶሳ ዞን ማረሚያ ቤት ከእስር መለቀቃቸውን ፓርቲው አስታውቋል፡፡

አቶ አመንቴ ግሺ  ባለፈው ዓመት 3 ጊዜ  ታስረዋል።

የፓርቲው ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት አቶ ዩሐንስ ተሰማም ከእስር ተለቀዋል፡፡

ቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከሚንቀሳቀሱት የፓለቲካ ፓርቲዎች መካከል አንዱ ነው።

የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የፓርቲውን ሊቀመንበርን ጨምሩ የተለያዩ አመራሮቹ በመታሰራቸው ፓርቲው ለምርጫ በሚያደርገው እንቅስቃሴ ላይ ተዕጽኖ ማሳደሩን  ሲገልጽ ቆይቷል፡፡

የቦዴፓ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ዶ/ር መብራቱ አለሙ ፓርቲአቸው በሰላማዊ መንገድ የሚንቀሳቀስ እና ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድም ዕውቅና ያለው መሆኑን ገልጸው  በአመራሩ ላይ የሚደረገው ወከባ መቆም አለበት ሲሉ አስረድተዋል። 

የተቋዋሚ የፖለቲካ ፓርዎች የሚያቀርቡትን ቅሬተን በተመለከተ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አብዱልአዚም ሙሐመድ ፥ በክልሉ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች በክልሉ በነበሩት ግጭቶች ውስጥ የተሳተፉ ስለመኖቸራው ገልጸው ፥ የፓለቲካ ፓርቲም ሆነ ግለሰብ በወንጀል ድርጊት የሚሳተፍ ከሆነ ህግ የማስከበር ስራ እንሰራንል ማለታቸውን ዶቼቨለ ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ወደኢትዮጵያ የሚገባው መኪና ቁጥር አሽቆለቆለ !

ወደ ኢትዮጵያ የሚገባው የመኪና ቁጥር ላለፉት ስድስት ወራት ብቻ በአሥር እጥፍ ማሽቆልቆሉን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘገበ።

በያዝነው በጀት ዓመት የመጀመርያ 6 ወራት 10.7 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ ተሽከርካሪዎች ወደ አገር ውስጥ የገቡ ሲሆን፣ ባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ቁጥሩ 105 ሚሊዮን ዶላር አካባቢ እንደነበር ማወቅ ተችሏል።

ለመቀነሱ ዋነኛ ምክንያቶች የሆነው መንግሥት በመኪኖች ላይ የሚጥለው ኤክሳይዝ ታክስ ምጣኔ መጨመሩና የውጭ ምንዛሪ እጥረት መሆናቸውን ሪፖርተር አስረድቷል።

ወደ አገር ውስጥ የሚገባው የተሽከርካሪ መጠን በመቀነሱ ፣ መንግሥት የሚያገኘው የግብር ገቢ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳደረ ሲሆን ፣ ባለፉት ስድስት ወራት የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ኮሚሽን ከኤክሳይዝ ታክስ ያገኘው ገቢ በግማሽ ቢሊዮን ብር ሊቀንስ መቻሉን የተቋሙ ሪፖርት አመልክቷልከመኪና በተጨማሪ ወደ አገሪቱ የሚገባው የነዳጅ ምርቶች ላይ ቅናሽ ተስተውሏል፡፡

በ2013 የመጀመርያ ስድስት ወራት 147 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ የነዳጅ ምርቶች ወደ አገር ውስጥ የገቡ ሲሆን፣ የ37 በመቶ ቅናሽ ሊያሳዩ ችለዋል፡፡

በአጠቃላይ ለመቀነሱ ዋናኛ ምክንያት ወደ አገር ውስጥ የሚገባው የበጀት ነዳጅ መጠን መቀነሱ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡ 

https://telegra.ph/Reporter-News-Paper-02-28
የአማራ ባንክ ምስረታ ጉባኤ ተካሄደ።

የአማራ ባንክ አክሲዮን ማኅበር የምስረታ ጉባዔዉን በአዲስ አበባ ከተማ አካሂዷል።

አማራ ባንክ 188 ሺህ ባለአክስዮኖች ያሉት ሲሆን 5 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር በላይ የተከፈለ ካፒታል እና ቃል የተገባ 7 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር በላይ የገንዘብ መጠን አለው።

የተከፈለው ካፒታል መጠን 12 አዳዲስ ባንኮችን የማቋቋም አቅም ያለው ሲሆን ቃል የተገባው ካፒታል ደግሞ በኢትዮጵያ 16 አዳዲስ የግል ባንኮችን የማቋቋም አቅም እንዳለው ነው የተገለፀው።

ብሔራዊ ባንክ መስከረም 27 ቀን 2013 የውክልና ገደብ ያነሳበትን መመሪያ መሰረት በማድረግ የመስራች ጉባኤውን በውክልና ለማካሄድ በተደረሰው ስምምነት መሰረት ውክልና ለአደራጆች የመስጠት ሂደቱ ተከናውኗል።

በውጤቱም 88 ሺህ 645 ባለአክስዮኖች 3 ነጥብ 8 ቢሊየን የተፈረመ ካፒታል ውክልና መስጠታቸውን ተከትሎ የመስራቾች ጠቅላላ ጉባኤን ማካሄድ ተችሏል።

የመስራቾች ጉባኤ ላይ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አገኘው ተሻገር ፣ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ዣንጥራር አባይ ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ሀላፊዎች ፣ አደረጆች እና ባለአክስዮኖች ተገኝተው ነበር።

ምንጭ፦WaltaTV
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አዲስ አበባ ለትግራይ የ100 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገች !

የአዲስ አበባ ከተማ ለትግራይ የ100 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገች።

በተጨማሪም 35 ሚሊየን ብር የሚገመት የቢሮ ቁሳቁስ፣ 3 አምቡላንስ እና 2 መኪናዎችን ድጋፍ አድርጋለች።

ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ዛሬ መቐለ በመገኘት ለትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ ድጋፉን ማስረከባቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬተሪያት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia