የትግራይ ክልል ሪፖርቶች ፦
- በኵሓ ህብረተሰብና በሆስፒታሉ ሰራተኞች ጥበቃ በጦርነቱ ወቅት ምንም ዘረፋ እና ጥቃት ያልደረሰበት ኵሓ ጠቅላላ ሆስፒታል
- ለትግራይ ክልል መልሶ ማቋቋም የተጀመረው ድጋፍ
- ወደ ትግራይ የገባው የኤርትራ ሰራዊት በርካታ የኮንስትራክሽን እቃዎችን ወደ ኤርትራ አሸጋግሯል መባሉ
- በትግራይ ከ4 ሺ 200 በላይ ማሽኖች ፣ ተሽከርካሪዎች ፣ አምቡላንሶች ፣ ገልባጮች ፣ ከባለቤቶቹ ውጭ መሆናቸው
- መላ ትግራይ 5ኛ ተከታታይ ቀን በጨለማ ውስጥ መሆኗ
- የመምህር የማነ ንጉስ በታጣቂዎች መገደል
- ባለፉት 3 ወራት በመቐለ ብቻ 29 የእሳት አደጋ መድረሱ፣ በአደጋው ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ ውድመት መድረሱ
[ለቲክቫህ አባላት የቀረበ]
(Tikvah - Family የካቲት 13 ቀን 2013 ዓ/ም)
https://telegra.ph/TikvahTigray-02-20

Telegraph
#TikvahTigray
በኵሓ ህብረተብ እና በሆስፒታሉ ሰራተኞች ጥበቃ ከዘረፋ እና ጥቃት የተረፈው ኵሓ ሆስፒታል : የኵሓ አጠቃላይ ሆስፒተል ባለፉት ወራት በትግራይ ክልል በነበረው አለመረጋጋት የንብረት ውድመት እና ስርቆት እንዳይደርስበት የሆስፒታሉ ሰራተኞች እና የኵሓ ነዋሪዎች ጥበቃ አድርገውለት በአሁን ሰዓት የ24 ሰዓት አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ተገልጿል። ይህ ሆስፒታል በተለይ በዓይን ህክምና ዘርፍ ለአማራ ፣ ለአፋር…
የዓለም ሎሬት ዶ/ር ጥበበ የማነ ብርሃን አረፉ።
በሕክምና ሞያ፣ በሀገር ሽማግሌነት፣ በርዳታ አስተባባሪነት እና በዕርቀ ሰላም ኮሚሽን አባልነት ሀገራቸውን ያገለገሉት የተከበሩ የዓለም ሎሬት ዶ/ር ጥበበ የማነ ብርሃን ማረፋቸው ተሰማ።
የኢትዮጵያ ጠ/ሚ አብይ አህመድ በዓለም ሎሬት ጥበበ የማነ ብርሃን ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገልፀው ለቤተሰቦቻቸው ፣ ለወዳጆቻቸውን እና ለኢትዮጵያ ህዝብ መፅናናትን ተመኝተዋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
የዓለም ሎሬት ዶ/ር ጥበበ የማነ ብርሃን አረፉ። በሕክምና ሞያ፣ በሀገር ሽማግሌነት፣ በርዳታ አስተባባሪነት እና በዕርቀ ሰላም ኮሚሽን አባልነት ሀገራቸውን ያገለገሉት የተከበሩ የዓለም ሎሬት ዶ/ር ጥበበ የማነ ብርሃን ማረፋቸው ተሰማ። የኢትዮጵያ ጠ/ሚ አብይ አህመድ በዓለም ሎሬት ጥበበ የማነ ብርሃን ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገልፀው ለቤተሰቦቻቸው ፣ ለወዳጆቻቸውን እና ለኢትዮጵያ ህዝብ መፅናናትን…
#Update
የዓለም ሎሬት ዶክተር ጥበበ የማነ ብርሃን ህይወታቸው ያለፈው በኮሮና ቫይረስ መሆኑን ጤና ሚኒስቴር ገለፀ።
የጤና ሚኒስቴር በተከበሩ የዓለም ሎሬት ዶክተር ጥበበ የማነ ብርሃን ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ሀዘን ገልጿል።
የተከበሩ የዓለም ሎሬት ዶ/ር ጥበበ የማነ ብርሃን በህክምና ሞያና ሌሎች ዘርፎች በትጋት ሀገራቸውን አገልግለዋል።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT

#Attention😷
"...በማዕከሉ ከኮቪድ ፅኑ ህሙማን መካከል በአማካይ ከአስሩ ስምንቱ ህይወታቸው እያለፈ ነው"
በኤካ ኮተቤ የኮቮድ-19 ህሙማን ማዕከል ከሚገኙ የፅኑ ህሙማን መካከል በአማካይ ከአስሩ ስምንቱ ህይወታቸው እያለፈ መሆኑ ማዕከሉ ገለፀ።
በኮቪድ 19 ኮሮና ቫይረስ የተያዙ ወጣቶችም እየሞቱ እንደሚገኝም ተገልጿል።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ የውስጥ ደዌ ሳንባ እና የፅኑ ህክምና ስፔሻሊስት ሐኪም ዶክተር ዳዊት ከበደ ለአዲስ ዘመን ንደገለፁት፤ ከቀን ወደ ቀን በቫይረሱ ምክንያት ወደ ፅኑ ህሙማን ክፍል የሚገቡ ታማሚዎች ቁጥር ተበራክቷል፤ የሚሞቱ ሰዎችም በዝተዋል።
በዚህም በአሁኑ ወቅት ከፅኑ ህሙማን ባለፈ በቫይረሱ የተያዙ ወጣቶችም ህይወት እያለፈ ነው።
እንደ ዶክተር ዳዊት ገለፃ፤ ከዕለት ወደ ዕለት የኮቪድ 19 ኮሮና ቫይረስ ህሙማን ቁጥር በከፍተኛ መጠን እየጨመረ ነው።
ይሄም ወደ ፅኑ ህሙማን የሚገቡ ሰዎችን ቁጥር እንዲጨምር ያደረገ ሲሆን ፤ ምንም አይነት ተጓዳኝ ህመም የሌሉባቸው እድሜያቸው በሃያና ሰላሳዎቹ የሚገኙ ወጣቶችም ፅኑ ህሙማን ክፍል ይገኛሉ፤ ህይወታቸውም እያለፈ ነው።
ምንጭ፦ አዲስ ዘመን

በመቐለ በ3 ወር 29 የእሳት አደጋ ተመዝግቧል።
ባለፉት ሶስት ወራት ብቻ በመቐለ ከተማ 29 የእሳት አደጋ መድረሱን የከተማው የእሳት አደጋ መከላከል እና ዝግጁነት ፅ/ቤት አስታውቋል።
የፅህፈት ቤቱ አስተባባሪ አቶ ሃብቶም ፀጋየ በ2012 ዓ.ም ከተመዘገቡት ባለፉት 3 ወራት የታየው አደጋ ከፍተኛው ነው ብለዋል።
29ኙ የእሳት አደጋዎች የመንግስት ተቋማት፣ መኖሪያ ቤቶች፣ የግል የንግድ ተቋማት፣ ሰው የሌለባቸው አካባቢዎች ያካትታል።
በአደጋዎቹ 162 ሺህ ሊትር ውሃ ጥቅም ላይ ውሏል።
በደረሱት አደጋዎች ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ ውድመት ደርሷል ፤ በፅ/ቤቱ በተደረገው የመከላከል ስራ ደግሞ ከ50 እስከ 60 ሚሊዮን ብር ማትረፍ ተችሏል።

የባቡር ሀዲድ ሲዘርፉ የነበሩ 9 ግለሰቦች ተያዙ !
በምስራቅ ሸዋ ዞን ቦሰት ወረዳው ከአዲስ አበባ ጂቡቲ የሚያገናኘውን ነባሩን የባቡር ሀዲድ መስመር ብረት ሲዘርፉ የነበሩ 9 ግለሰቦችን እጅ ከፍጅ መያዙን ፖሊስ አስታወቀ።
የም/ሸዋ ዞን ፖሊስ ሚዲያና ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር አስቻለው ዓለሙ ፥ ግለሰቦቹ በወረዳው ጠዴቾ ቀበሌ ገበሬ ማህበር የካቲት 11/2013 ዓ.ም ከሌሊቱ 11 ሰዓት ላይ የዘረፉትን የባቡር ሀዲድ ብረት ጭነው ሊጓዙ ሲሉ እጅ ከፍንች ተይዘዋል ብለዋል።
ተጠርጣሪ ግለሰቦቹ የሰረቁትን የባቡር ሀዲድ ብረት የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-82408 ኢት በሆነ ሲኖ ትራክ ተሽከርካሪ ጭነው ከአካባቢው ሊሰወሩ ሲሉ ህብረተሰቡ ለፖሊሰ በሰጠው ጥቆማ መሰረት ተይዘዋል።
ግለሰቦቹ ከዚህ ቀደም በቡድን ተደራጅተው ጨለማን ተገን በማድረግ ለረጅም ዓመታት ኢትዮጵያን ከጂቡቲ ሲያገኛኝ የነበረውን የባቡር ሀዲድ ብረት ብሎን በመፍታትና በመቆራረጥ ሲሸጡ መቆየታቸው የተደረሰባቸው መሆኑን አመልክተዋል።
ፖሊስ ግለሰቦቹን በቁጥጥር ስር አውሎ ለህግ ለማቅረብ ምርመራ እያካሄደ መሆኑን ተናግረዋል።
ነባሮቹ የባቡር ሀዲድ ብረቶች ለዘረፋ እየተጋለጡ መሆኑን በመረዳት የሚመለከተው አካል ቸል ሳይል አስቸኳይ መፍትሄ ሊፈልግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
ምንጭ ፦ ኢዜአ

#EthiopiaElection2013
በምርጫ 2013 ክልሎች የሚኖራቸው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ) የውክልና መቀመጫ፦
- የሲዳማ ክልል በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚኖረው መቀመጫ 19
- የደቡብ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውክልና 104 ደቡብ ክልል ላለፉት 26 ዓመታት ገደማ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የነበረው ውክልና ወይም መቀመጫ 123 ነበር፤ ሲዳማ ከደቡብ ክልል ወጥቶ ራሱን ከቻለ በኃላ ፣ ደቡብ የሚኖረው መቀመጫ ብዛት 104 ሆኗል።
- ኦሮሚያ ክልል በነበረበት 178፣
- አማራ ክልል በነበረበት 138፣
- ሶማሌ ክልል በነበረበት 23፣
- አዲስ አበባ ከተማ በነበረበት 23፣
- ቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል በነበረበት 9፣
- አፋር ክልል በነበረበት 8፣
- ጋምቤላ ክልል በነበረበት 3፣
- ሐረሪ ክልል በነበረበት 2 እንዲሁም ድሬዳዋ ከተማ በነበረበት 2 ሆነው ይቀጥላሉ።
6ኛው አጠቃላይ ምርጫ በትግራይ ክልል እንደማይከናወን ምርጫ ቦርድ ቀድሞ ያስታወቀ ሲሆን፣ ከሰሞኑ ምርጫ ቦርድ ይፋ ባደረገው የክልሎች የፓርላማ ውክልና ድርሻ ውስጥም የትግራይ ክልል አልተገለጸም።
ይሁን እንጂ ላለፉት አሥርት ዓመታት የትግራይ ክልል የፓርላማ ውክልና 38 እንደሆነ ይታወቃል።
ይህንን ከግምት በማስገባት ሥሌት ሲደረግ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አጠቃላይ መቀመጫ ብዛት ከነበረበት 547 አልተለወጠም።
(ከሪፖርተር ጋዜጣ)

በግልገል በለስ ከተማ ተጥሎ የነበረው የሠዓት እላፊ ማሻሻያ ተደረገበት!
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመተከል ዞን የጸጥታ ሁኔታ እየተሻሻለ በመምጣቱ የዞኑ መቀመጫ በሆነችው ግልገል በለስ ከተማ ተጥሎ የነበረው ሠዓት እላፊ ማሻሻያ ተደረገበት።
በዞኑ ሠላም እና ጸጥታ እያስከበረ የሚገኘው የተቀናጀ ግብረ ሀይል ከፍተኛ አመራሮች ከግልገል በለስ ከተማ ነዋሪዎች ተወካዮች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።
በውይይቱ ላይ በነዋሪዎች ተወካዮች ከቀረቡ ጥያቄዎች መካከል በከተማዋ የተጣለውን የሠዓት እላፊ ገደብ የተመለከተው ይገኝበታል።
የተቀናጀ ግብረ ሀይሉ በአካባቢው ያለውን የጸጥታ ሁኔታ በተሟላ መልኩ ለማስከበር በከተማዋ ከምሽቱ አንድ ሠዓት ጀምሮ መደበኛ እንቅስቃሴ ተገድቦ ቆይቷል።
በአሁኑ ወቅት የሠላምና ጸጥታ ሁኔታው እየተሻሻለ በመሆኑ በከተማዋ እስከ ምሽቱ 3፡00 ሠዓት ድረስ እንቅስቃሴ እንዲኖር በመወሰን ማሻሻያ ተደርጓል።
(ENA)

#EthiopiaElection2013 የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ነገ እሁድ በአዲስ አበባ ፣ በባሕር ዳር፣ ጎንደር፣ ደሴ እና ደብረ ብርሃን ከተሞች የምርጫ ቅስቀሳ ማስጀመሪያ መርኃ ግብር እንደሚያካሂድ አስታውቋል። ፓርቲው በአዲስ አበባ አብሮ ለመስራት ከተስማማቸው ፓርቲዎች ጋር (ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ፣ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት፣ የኢትዮጵያ ብሄራዊ አንድነት ፓርቲ) በጋራ…
#EthiopiaElection2013🗳
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ /አብን/ በአዲስ አበባ ከተማ የምርጫ ቅስቀሳ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ዛሬ አካሂዷል።
አብን ከአ/አ ከተማ በተጨማሪ በባህር ዳር፣ ጎንደር፣ ደሴ ፣ ደብረብርሃን ከተሞች የምረጡኝ ቅስቀሳ ዘመቻውን ዛሬ በይፋ እያስጀመረ ይገኛል።
አብን በአዲስ አበባው የምርጫ ቅስቀሳ ማስጀመሪያ ከዋና ጽህፈት ቤቱ በመነሳት መድረሻውን መስቀል አደባይ ያደረገ መርሃ ግብር አካሂዷል።
ይህ መርሃ ግብር አብን በአዲስ አበባ አብሯቸው ለመስራት ስምምነት ካደረገባቸው ፓርቲዎች ጋር በመሆን ያከናወነው ነው።
በመስቀል አደባባይ ንግግር ያደረጉት የአብን ሊቀመንነር ረ/ፕሮፌሰር በለጠ ሞላ አብን ከእህት ድርጅቶች ጋር በመሆን የሕዝብን አመኔታና ይሁንታ ወደ ፖለቲካ ውክልና የሚቀይርበትን ትልም ነድፎ ወደስራ ገብቷል ብለዋል።
ማንኛውም ዜጋ በሰላም እና በደኅንነት ወጥቶ የሚገባባት ፤ የሕግ የበላይነት የሰፈነባት ፣ ሰብአዊ መብቶች ፣ ፍትህ እና ርትዕ የተከበረባት፣ ያለልዩነትና መድልኦ በነፃነት መንቀሳቀስ፣ መኖርና ሰርቶ መበልፀግ የሚቻልባት ኢትዮጵያን ለመፍጠር ቆርጦ ተነስቷል ሲሉም ተናግረዋል።

ሲዳማ ክልል - 10ኛው የኢትዮጵያ ክልል ይፋዊ ምስረታ በዓል !
ነገ የሲዳማ ብሔራዊ ክልል ይፋዊ የምስረታ በዓል ይከበራል።
በዚህ የክልል ምስረት ይፋዊ በዓል ላይ ለመታደም በርካታ የፌደራል እንዲሁም የክልል መሪዎች ሀዋሳ ገብተዋል።
የሲዳማ ክልል ሀዋሳ ነዋሪዎች ፣ የከተማው አመራሮች እንግዶቻቸውን በመቀበል ላይ ይገኛሉ።
ምንጭ፦ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ነገ የሲዳማ ብሔራዊ ክልል ይፋዊ የምስረታ በዓል ይከበራል።
በዚህ የክልል ምስረት ይፋዊ በዓል ላይ ለመታደም በርካታ የፌደራል እንዲሁም የክልል መሪዎች ሀዋሳ ገብተዋል።
የሲዳማ ክልል ሀዋሳ ነዋሪዎች ፣ የከተማው አመራሮች እንግዶቻቸውን በመቀበል ላይ ይገኛሉ።
ምንጭ፦ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Attention😷
ባለፉት 24 ሰዓታት 6,005 የኮቪድ-19 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 949 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ተረጋገጠ።
በዚሁ በ24 ሰዓታት የ8 ሰዎች ሞት ሪፖርት ተደርጓል ፤ ትላንት 125 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
ኮቪድ-19 ወረርሽኝ በኢትዮጵያ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ 152,806 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ ከነዚህ መካከል ፣2,279 ሰዎች ሞተዋል ፤ 131,366 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
አሁን ላይ 370 ሰዎች በፀና ታመው በህክምና ክትትል ላይ ይገኛሉ።
#Purpose #Tikvah

በትግራይ ክልል በተመራቂዎች ላይ የተፈፀመው ጥቃት፦
ከቀናት በፊት በመቐለ የኒቨርሲቲ የተመረቁ የዓዲግራት እና መቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ በተፈፀመባቸው ጥቃት ህይወት አልፏል የቆሰሉም መኖራቸውን የዓይን እማኝ የሆኑ የቲክቫህ አባላት ገልፀዋል።
የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት በዚህ ጉዳይ ባለፉት ቀናት አስፈላጊ መረጃ ለመሰብሰብ ሞክረዋል።
ጥቃቱ የተፈፀመው "ዓዲመስኖ" የሚባል ቦታ ላይ መሆኑን በመኪናው ውስጥ የነበሩ አባላት ገልፀዋል።
በተማሪዎቹ መኪና ውስጥ ወደ አዲስ አበባ ይመለሱ የነበሩ 2 ፌዴራል ፖሊስ የፀጥታ አካላት ነበሩ እነሱን ጨምሮ የመኪናው ረዳት እንደተገደሉ አባላቶቻን ገልፀዋል።
በዚህ ጥቃት 3 ተመራቂዎች መሞታቸው ከመቐለ ዩኒቨርሲቲ ምንጮች ተገልጾልናል (የሟቾች ቁጥር ግን 6 መሆኑን ከጥቃቱ የተረፉ አባላት ገልፀዋል) በጥቃቱ የቆሰሉ በርካታ ሲሆኑ በመጀመሪያ ወደ ቆቦ ሆስፒታል ከዛም ወደ ወልዲያ ሆስፒታል ተዘዋውረው ህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።
በተማሪዎቹ ላይ ስለደረሰው ጥቃት ከMoSHE በኩል አንድ ስማቸውን የማንገልፅላችሁ ኃላፊ ጉዳዩን እሳቸውም እንደሰሙት ገልፀውልናል ዝርዝር መረጃ ከሌሎች የተቋሙ አመራሮች ለመቀበል ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም።
በተማሪዎች መኪና ላይ ከተፈፀመው ጥቃት በተጨማሪ አንድ ሌላ ኤፍኤስአር መኪና ላይ ጥቃት ተፈፅሞ እንደነበር በመኪና ውስጥ የነበረ አንድ ተመራቂ ገልጾልናል። ከጥቃቱ አምልጦ ቆቦ የገባው ይህ ተመራቂ በሹፌሩ እና ረዳቱ ላይ ጉዳት እንደደረሰ ነገር ግን እሱ ሊተርፍ መቻሉን አሳውቆናል።
በተፈፀመው ጥቃት ዙሪያ በቦታው የነበሩ እና ከጥቃቱ የተረፉ የቲክቫህ አባላት ከመነሻው ጀምሮ ምን እንደፈጠረ በዝርዝር አስረድተውናል ነገ እናጋራዋለን።
#TikvahFamily
@tikvahethiopia