TIKVAH-ETHIOPIA
ከትላንት በስቲያ በቁጥጥር ስር የዋለ የምግብ ዘይት ለሸማቾ ማህበራት እየተሰራጨ ነው ! የካቲት 6 ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ጀሞ ሚካኤል አካባቢ አንበሳ ጋራዥ ጎን በግለሰብ መጋዘን በህገወጥ መንገድ ተከማችቶ የተገኘው 2 ሚሊየን ጀሪካን ፓልም የምግብ ዘይት በሁሉም ክፍለ ከተሞች ለሚገኙ ሸማች ማህበራት እየተሰራጨ መሆኑን የአ/አ ፕሬስ ሴክሬተሪያት አሳወቀ። በቁጥጥር ስር የዋለው የምግብ ዘይት በሁሉም…
ዘይቱን ያከማቸው አካል ታወቀ !
ከሰሞኑ በግለሰብ መጋዘን በህገወጣ መንገድ የተከማቸው 2 ሚሊዮን ጀሪከን የፓልም ዘይት መያዙ ሲገለፅ ነበር።
ነገር ግን ይህ ዘይት በማን እንዴት ሊከማች እንደቻለ ይፋዊ መረጃ ከመንግስት በኩል ሳይሰጥ ቆይቷል።
ዛሬ ማለዳ ዘይቱን ያከማቸው አፍሪካ ሃ/የተ/የግ/ማህበርና የሮዛ ዳቦ ባለቤት እንደሆነ ተሰምቷል።
የላፍቶ ክ/ከተማ ነዋሪዎች በተለያየ ግዜ ለወረዳቸው እና ለክፍለ ከተማቸው ሲያሳውቁና ሲጠይቁ መቆየታቸው ተገልጿል።
ነዋሪው አቅርቦት በማጠሩ በተፈጠረው የዋጋ ውድነት የተነሳ ወደ አከፋፋይ ድርጅቱ አፍሪካ ሃ/የተ/የግ /ማህበር በመሄድ ቢጠይቁም ያገኙት የነበረው መልስ የውጭ ምንዛሪ ስላጣን መግዛት አልቻልንም፤ ከወደብ አልተነሣም፤ መንግስት ሁኔታዎችን አላመቻቸልንም የሚል ነበር።
ነገር ግን በድርጅቱ መጋዘን የፓልም ዘይት ሲወርድና ሲራገፍ ፤ እና ከመጋዘኑ በአሳቻ ሰዓት ወደ ተለያዩ አካባቢዎች እየተጫነ ሲጋዝ በተከታታይ ማየታቸውንና ድርጊቱ አግባብ አለመሆኑን በመረዳት ለክፍለ ከተማው መጠቆማቸው ተገልጿል።
በሌላ በኩል ፦
የአፍሪካ ኃ/የተ/የግ/ማ ለንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር የኢኒስፔክሽን እና ርጉላቶሪ ዳይሬክቶሬት በቀን 01/06/2013 በላከው ሪፖርት ድርጅቱ በጥር ወር ብቻ በአቃቂ ቃሊቲ እና ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተሞች ባጠቃላይ 1,846,532 ሊትር ፓልም ዘይት ማከፋፈሉን እና በመጋዘኑ የሚገኘው 14,003 ሊትር ብቻ በመሆኑ 3,552,376 ሊትር ፓልም የምግብ ዘይት ወደ አገር ውሥጥ ለማስገባት እንዲፈቀድለት መጠየቁ ታውቋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬተሪ በዚሁ ጉዳይ ያሰራጨው ዝርዝር መረጃ : telegra.ph/Addis-Ababa-Press-Sectary-02-16
@tikvahethiopia

ባንክ ቤት ውስጥ የማጭበርበር ድርጊት የፈፀመው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ !
በደብረ ማርቆስ ከተማ ቀበሌ 02 ልዩ ቦታው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሸዋበር ቅርንጫፍ ጥር 19 ቀን 2013 ተጠርጣሪው ወደ ባንክ በመሄድ ከሸዋበር ቅርንጫፍ በአቶ አየነው መሃሪ መላኩ ስም ከተከፈተው አካውንት 5 ሺ ብር እና ከዋናው ንግድ ባንክ 24 ሺ ብር በአጠቃላይ 29 ሺ ብር የማጭበርበር ወንጀል ፈጽሟል።
ተጠርጣሪው ወንጀሉን እንዴት ፈፀመው ?
የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽ/ቤት የሙስና ወንጀሎች ምርመራ ክፍል ሀላፊ ምክትል ኮማንደር አበበች አምሳሉ ሲያስረዱ ፦
ተጠርጣሪው ግለሰብ ባንክ በመሄድ የገንዘብ ወጪ ፎርም የሚሞሉ ግለሠቦችን ፎርሙን በሞባይል በማንሳት እና ፎርም ሞልተው ሲሳሳቱ የሚጥሉትን በማንሳት የአካውንት ቁጥሩን በመውሰድና ፊርማውን ጊዜ ሰጥቶ በመመለማመድ በተጨማሪም በአካውንት ባለቤቱ ስም የራሱን ፎቶ ግራፍ ያለበት ሀሠተኛ መታወቂያ በማዘጋጀት ወረፋ በሚበዛበት ጊዜ በመሄድ የማጭበርበር ተግባሩን ፈፅሟል።
በተጨማሪም የካቲት 5/6/2013 ዓ,ም ተጠርጣሪው ግለሠብ በአቶ ችሎት አበበ ጸጋዬ ስም የተዘጋጀ የሀሰት ሰነድ በማዘጋጀት 40 ሺ ብር ለማጭበርበር ሲሞክር ከባንኩ ሰራተኞች ለፖሊስ በደረሰ ጥቆማ መሠረት ተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር ውሎ አስፈላጊው የምርመራ ስራ እየተሰራ ነው ተብሏል።
ፖሊስ ህብረተሰቡ በእንደዚህ አይነት ወንጀል ሰለባ እንዳይሆን ገንዘብ ወጪ በሚያደርጉበት ግዜ ፎርሙን ከሰው እይታውጭ አድርጎ መሙላት እና ወረፋ በሚያሲዙበት ግዜ መታወቂያቸውን እንዲጠቀሙ ገልጸው የባንክ ሰራተኞችም ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስቧል።
መረጃው የደ/ማርቆስ ከተማ ፖሊስ ነው።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

የኑሮ ውድነቱ ነገር ...
በሀገራችን የሚታየው የኑሮ ውድነት የሰዎችን ህይወት በእጅጉ እየተፈተነው ይገኛል።
በሸቀጦች ዋጋ ላይ በየጊዜው የሚታየው ጭማሪም በርካቶች ህይወታቸው በፈተና እንዲሞላ እያደረገው ነው።
ከሰሞኑ ደግሞ የነዳጅ ምርቶች ላይ የዋጋ ክለሳ መደረጉ / የዋጋ ጭማሪ መደረጉ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ ሁኔታዎችን ይበልጥ አስቸጋሪ አድርጎታል።
በአንድ በኩል በየጊዜው የሚጨምረው የሸቀጦች ዋጋ በሌላ በኩል የሰሞኑ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ በኑሮ ላይ ከፍተኛ ጫና አሳድሯል።
እናትስ ምን ትላላችሁ ? ኑሮውስ እንዴት ይዟችኃል ? በአስተያየት መስጫው ላይ ሀሳባችሁን አስፍሩ።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT

የጋምቤላ ክልል የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ !
በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ዘግይቶ በ2013 ዓ.ም በክልሉ የተሰጠው የ2012 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ይፋ መደረጉን የጋምቤላ ክልሉ ትምህርት ቢሮ ዛሬ አስታወቀ፡፡
በክልሉ ለፈተናው ከተቀመጡ ተማሪዎች መካከል 98.5 በመቶ ተማሪዎች ወደ ቀጣይ ክፍል ተዛውረዋል።
የማለፊያ ነጥብ ለወንዶች 42 ሲሆን ለሴቶች ደግሞ 39 መሆኑ ተገልጿል።
ፈተናው ታርሞ ቢጠናቀቅም ካርድና ሮስተር ላይ የሚሞሉ መረጃዎች እንደተጠናቀቁ በቀጣይ ሳምንት በየትምህርት ቤቱ ካርድ እየተሰጠ ምዝገባ እንደሚከናወን ቢሮ ገልጿል።
የዘጠነኛ ክፍል ትምህርት መጋቢት 1 ለማስጀመር ቅድመ ዝግጅት መደረጉን የተገለፀ ሲሆን ዘንድሮ ወደ ዘጠነኛ ክፍል የተዛወሩት ከባለፈው 2011 ዓ.ም ጋር ሲነፃፀር የወንድ ተማሪዎች በ21 በመቶ የሴት ተማሪዎች በ19 በመቶ እድገት ማሳየቱን ተነግሯል።
መረጃው የጋምቤላ ክልል ፕሬስ ሴክሬተሪያት ነው።

ፌዴራል ፖሊስ በ3 አይሱዙ የጭነት መኪና በሕገ-ወጥ መንገድ ከአዲስ አበባ ሊወጣ የነበረ ዘይት በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ገለፀ !
በሦስት አይሱዙ የጭነት መኪና በሕገ-ወጥ መንገድ ከአዲስ አበባ ሊወጣ የነበረ ዘይት በቁጥጥር ሥር መዋሉን ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ማስታወቁን የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዘግቧል።
ቁጥጥር ሥር የዋለው ዘይት የካቲት 6 ቀን 2013 ዓ.ም ጀሞ ሚካኤል ልዩ ስሙ አንበሳ ጋራዥ አካባቢ በፌዴራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር ከዋለው 2 ሚሊዮን ሊትር በላይ ዘይት ቀድሞ ሊወጣ የነበረ መሆኑን ነው ፖሊስ የገለጸው።
"አፍሪካ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር" በተሰኘው ድርጅት ከውጭ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገባው የፓልም ዘይት በመንግሥት ፈቃድ ያገኘው በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ እንዲያከፋፍል ነበር ተብሏል።
ሆኖም በሦስት አይሱዙ የጭነት መኪና ተጭኖ ወደ ጅማ ሊወጣ ሲል በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ጅማ በር ፖሊስ ጣቢያ እና በፌዴራል ፖሊስ ትብብር በቁጥጥር ስር ውሏል።
በቁጥጥር ሥር የዋለው ዘይት 994 ጀሪካን ባለ 20 ሊትር እና 3 ሺህ ጀሪካ ባለ 3 ሊትር ፓልም ዘይት እንደሆነ ፌዴራል ፖሊስ አስታውቋል።
@TikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

"... ነጋዴዎች እና አንዳንድ የመንግስት የንግድ ተቋማት ጭምር ምርትን በመደበቅ ከፍተኛ ዋጋ በመጠየቅ የዋጋ ንረትን ፈጥረዋል" - የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ
By : Ahadu Radio 94.3
የአ/አ ከተማ ንግድ ቢሮ ከ1 መቶ በላይ የመንግስት የንግድ ተቋማት የዋጋ ንረት በመፍጠራቸው ምክንያት እርምጃ እንደተወሰደባቸው ገለፀ፡፡
ቢሮው በከተማዋ የተስተዋለው የዘይት ምርት እጥረት በነጋዴዎች በጅምላ ሻጮች ብቻ ሳይሆን በአንዳንድ የመንግስት የንግድ ተቋማትም ጭምር የተፈጠረ ነው ብሏል።
የቢሮው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዳንኤል መኤሳ፥በከተማዋ የተስተዋለው የዘይትና ሌሎች የፍጆታ ምርቶች እጥረት ከፍተኛ የዋጋ ንረትን በሚፈጥሩ የንግድ አካላት የተፈጠረ መሆኑን ገልፀዋል።
ጋላፊው ፥ ነጋዴዎቹ እና አንዳንድ #የመንግስት የንግድ ተቋማትም ጭምር ምርትን በመደበቅ ከፍተኛ ዋጋ በመጠየቅ የዋጋ ንረትን ፈጥረዋል ያሉ ሲሆን እስካሁን በተደረገው ክትትልና ቁጥጥር ከ1 መቶ በላይ የመንግስት የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ መውሰዱን ለሬድዮ ጣቢያው ገልፀዋል፡፡

ሱዳን ?
• ሱደን በምዕራብ ጎንደር ዞን ከቋራ እስከ አቡጢር ድረስ ሰፊ ቦታ በጉልበት ተቆጣጥራለች።
• ሱዳን በፈፀመችው ወረራ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል፤ ከ1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት የንብረት ዝርፊያ ተፈፅሟል።
• ከምድረገነት በቅርብ ርቀት በምትገኘው ሰላም በር ቀበሌ በርካታ የአካባበው ነዋሪዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል። የአርሶ አደሮችና የባለሀብቶች ሰብል ፣ ትራክተሮችና ካምፖች ውድመትና ዝርፊያ ተፈፅሞባቸዋል።
የሱዳን ታጣቂዎች አስካሁን ድረስ "በምድረ ገነት ከተማ" በማኅበረሰቡ ላይ ትንኮሳ እያደረጉ መሆኑን እና የአካባቢው ነዋሪዎችም ስጋት እንዳደረባቸውን የምድረ ገነት ከተማ ከንቲባ አይሸሽም ጓንቼ ተናግረዋል።
የአካባቢው መስተዳደር አካላት ፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶች ማኅበረሰቡን ለማረጋጋት ጥረት እያደረጉ መሆኑን ገልፀዋል።
የኢትዮጵያ መንግሥት በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ሱዳን ከጥቅምት 24 በፊት ወደነበረችበት እንድትመለስ እየሠራ ነው፡፡
ነገር ግን የመንግሥት ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ውጤታማነት የሚለካው ሱዳንን ወደነበረችበት መመለስ ሲቻል መሆኑን ተገልጿል።
"የእርሻ ጊዜ አልፎ" የሱዳን ታጣቂዎች ካደረሱት ጉዳት በላይ የከፋ ችግር እንዳይገጥም በተጀመረው አግባብ ፈጣን መፍትሔ እንዲገኝ ጥረቱ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ተጠይቋል።
በአካባቢው የሚኖረው ማኅበረሰብ የኢትዮጵያ መንግሥት የሚያሳልፈውን ውሳኔ በትግሥት እየተጠባበቀ መሆኑን ተሰምቷል።
መረጃው የተገኘው ከአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት/ ከምዕራብ ጎንደር ዞን ብልፅግና ፅህፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ከሆኑ አቶ ሁናለም አሻግሬ ነው።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

#Attention😷
በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት ከተደረገው 5,164 የኮቪድ-19 የላብራቶሪ ምርመራ 665 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ተረጋገጠ።
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የ14 ሰዎች ሞት ሲመዘገብ፤ 199 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
ኮቪድ-19 ወረርሽኝ በኢትዮጵያ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ 148,490 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ ከነዚህ መካከል ፣2,223 ሰዎች ሞተዋል፤ 129,145ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
አሁን ላይ 308 ሰዎች በፀና ታመው በህክምና ክትትል ላይ ይገኛሉ።
#Purpose #Tikvah

በሀገራችን የኮቪድ-19 ሟቾች ቁጥር እጨመረ ነው።
ባለፉት ቀናት ኢትዮጵያ ውስጥ በኮቪድ-19 የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር መጨመር አሳይቷል።
የካቲት 7፣ የካቲት 8 እና የካቲት 9 በአጠቃላይ የ42 ሰዎች ህይወት አልፏል።
ከዚህ በተጨማሪ በፅኑ ታመው ህክምና ያላይ ያሉ ሰዎች ቁጥር በፍጥነት አሻቅቧል። አሁን ላይ 308 ፅኑ ታማሚዎች አሉ።
ካለው የመተንፈሻ መሳሪያ እጥረት ሳቢያም ወረፋ በመጠብቅ ስቃይ ውስጥ የሚገኙ ወገኖቻችንም በርካታ ናቸው።
ውድ የቲክቫህ አባላት ለራሳችሁ እና ለቤተሰባችሁ ስትሉ ጥንቃቄያችሁን ጨምሩ ፤ ይበልጥ አጠናክሩ።
በየአካባቢው ከዚህ ቀደም የነበረው ጥንቃቄ እየላላ ፤ አንዳንድ ቦታ እርግፍ ተደርጎ እየተተው ፤ ጭራሽ ለሚያስተዳድሩት ህብረተሰብ አርአያ ይሆናሉ የሚባሉት የመንግስት አመራሮች ሳይቀር ምንም ነገር እንደሌለ / ኮቪድ-19 እንደጠፋ በሚመስል መልኩ ጥንቃቄ በጎደለው መልኩ እየተንቀሳቀሱ ነው።
ሞት እና ስቃይ ቤታትችን እስኪገባ አንጠብቅ!

#Update ዛሬ የካቲት 8 የነአቶ ጃዋር መሃመድ ጠበቆች በረሃብ አድማ ላይ የሚገኙ እስረኞች የህክምና ጉዳይ አስመልክቶ ጉዳዩን ለሚያየው የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ችሎት አቤቱታ አቅርበው ነበር። የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎትም እነአቶ ጀዋር መሀመድ በግል ሀኪሞቻቸው እንዲሁም በፈለጉት የግል ህክምና ተቋም መታከም እንደሚችሉ አፅንኦት ሰጥቶ ትዕዛዝ አስተላልፏል። ከቀናት…
አቶ በቀለ ገርባ ዛሬ ወደሆስፒታል ሲወሰዱ ምን ተፈጠረ ?
"አባቴ በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ አላውቅም" - ቦንቱ በቀለ
ትላንት የእነአቶ በቀለ ገርባ ጠበቆች በእስር ላይ የሚገኙትን የፖለቲከኞች የህክምና ጉዳይ አስመልክቶ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ችሎት አቤቱታ አቅርበው ነበር።
የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎትም እነአቶ በቀለ ገርባ በግል ሀኪሞቻቸው እንዲሁም በፈለጉት የግል ህክምና ተቋም መታከም እንደሚችሉ አፅንኦት ሰጥቶ ትዕዛዝ አስተላልፎ ነበር።
በፍርድ ቤቱ የተሰጠው ትእዛዝ አቶ በቀለ፣ አቶ ጃዋር፣አቶ ሃምዛ፣ አቶ ደጀኔ አ/አ ሜክሲኮ አካባቢ ላንድማርክ ጄነራል ሆስፒታል በአጃቢ አስፈላጊውን ጥበቃ ተደርጎ ህክምና እንዲወሰዱ የሚል ነው።
ነገር ግን በዛሬው ዕለት አቶ በቀለ ገርባ ወደ "ላንድማርድ ጄነራል ሆስፒታል" እንደሚወሰዱ ከተነገራቸው እና ከማረሚያ ከወጡ በኃላ የአጃቢ መኪኖቹና እሳቸውን የያዘው አምቡላንስ ከመንገድ ላይ ወደጦር ኃይሎች ሆስፒታል እንደወሰዷቸው ልጃቸው ቦንቱ ተናግራለች።
https://telegra.ph/BekeleGerba-02-16

Telegraph
#BekeleGerba
አቶ በቀለ ገርባ ወደ ሆስፒታል ሲወሰዱ ምን ገጠማቸው ? ትላንት የእነአቶ ጃዋር፣ የእነአቶ በቀለ ገርባ ጠበቆች በእስር ላይ የሚገኙትን ፖለቲከኞች የህክምና ጉዳይ አስመልክቶ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ችሎት አቤቱታ አቅርበው ነበር። የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎትም እነአቶ በቀለ ገርባ በግል ሀኪሞቻቸው እንዲሁም በፈለጉት የግል ህክምና ተቋም መታከም እንደሚችሉ አፅንኦት ሰጥቶ…
በሀዋሳ ከተማ በደረሰ የእሳት አደጋ ንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ ፦
በሐዋሳ ከተማ አስተዳደር በመሀል ከተማ ክፍለከተማ በአዲስ አበባ ቀበሌ በተለምዶ ቤተሰብ መምሪያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ያጋጠመ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ።
የሐዋሳ ከተማ ፓሊስ አዛዥ ኮማንደር ደረሰ ቡሳሮ የአደጋው መንስኤና የደረሰው የንብረት ውድመት በምርመራ ሂደት ላይ መሆኑን ገልፀዋል።
ኮማንደር ደረሰ በአካባቢው ህብረተሰብ ርብርብ ፣ በሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ የእሳት አደጋ መከላከያ እንዲሁም በፀጥታ ኃይሉ ርብርብ አደጋው ወደሌላ አካባቢ ሳይሰፋ መቆጣጠር መቻሉን ገልፀዋል።
መረጃው የሐ/ከ/አ/መ/ኮ/ጉ/መምሪያ ነው።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
በሐዋሳ ከተማ አስተዳደር በመሀል ከተማ ክፍለከተማ በአዲስ አበባ ቀበሌ በተለምዶ ቤተሰብ መምሪያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ያጋጠመ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ።
የሐዋሳ ከተማ ፓሊስ አዛዥ ኮማንደር ደረሰ ቡሳሮ የአደጋው መንስኤና የደረሰው የንብረት ውድመት በምርመራ ሂደት ላይ መሆኑን ገልፀዋል።
ኮማንደር ደረሰ በአካባቢው ህብረተሰብ ርብርብ ፣ በሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ የእሳት አደጋ መከላከያ እንዲሁም በፀጥታ ኃይሉ ርብርብ አደጋው ወደሌላ አካባቢ ሳይሰፋ መቆጣጠር መቻሉን ገልፀዋል።
መረጃው የሐ/ከ/አ/መ/ኮ/ጉ/መምሪያ ነው።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
አቶ በቀለ ገርባ ዛሬ ወደሆስፒታል ሲወሰዱ ምን ተፈጠረ ? "አባቴ በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ አላውቅም" - ቦንቱ በቀለ ትላንት የእነአቶ በቀለ ገርባ ጠበቆች በእስር ላይ የሚገኙትን የፖለቲከኞች የህክምና ጉዳይ አስመልክቶ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ችሎት አቤቱታ አቅርበው ነበር። የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎትም እነአቶ በቀለ ገርባ በግል ሀኪሞቻቸው እንዲሁም በፈለጉት የግል…
አቶ በቀለ ገርባ ወደ ቃሊት እንዲመለሱ መደረጉ ፦
አቶ በቀለ ገርባ ትላንት ወደ "ላንድ ማርክ ጄነራል ሆስፒታል" እንደሚወሰዱ ተገልፆላቸው ከቃሊቲ ከወጡ በኃላ ከመንገድ ላይ ወደ ጦር ኃይሎች ሆስፒታል እንዲወሰዱ መደረጋቸው መገለፁ ይታወሳል።
ወደ ሆስፒታሉ ከገቡ በኃላ ቤተስቦቻቸው ስላሉበት ሁኔታ እንደማያውቁ ገልፀውም ነበር።
ትላንት ምሽት ከጠበቆቻቸው እንደተሰማው ከሆነ ፥ አቶ በቀለ ገርባ ምንም እንኳን በጠና ቢታመሙም ፍርድ ቤት በግል የህክምና ተቋም ነው እንድታከም ያዘዘው ፤ በመንግስት ሆስፒታል ለመታከም እምነት የለኝም በማለት ህክምና ለማድረግ ፋቃደኛ ሳይሆኑ በመቅረታቸው ያለምንም ህክምና ወደ ቃሊቲ ማረሚያ እንዲመለሱ ተደርገዋል።

ችሎት !
በ2012 በጀት አመት ለደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ የቀለብ ጤፍ ለማቅረብ በውስን ጫራታ አሸናፊ ከሆነው የሞጣ ሁለገብ የገበሬወች ህብረት ስራ ዩኒየን ፤ 230 ኩንታል ጤፍ ወጭ በማድረግና ወደ ዩኒቨርስቲው ገቢ ሳያደርጉ የገባ በማስመሰል ፤ እነማይ ወረዳ ጠልማ ቀበሌ ነዋሪ ለሆነ ታደሰ ውባለ ለተባለ ጤፍ ነጋዴ በ655 ሺ 600 ብር ሸጠው ለግል ጥቅማቸው በማዋል የተጠረጠሩ አምስት ግለሰቦች የሚከተሉት ናቸው ፦
1ኛ ጳውሎስ ዋለልኝ ገረመው የደ/ማ ዩኒቨርስቲ መንቆረር አግሮ ኢንደስትሪ ኢንተርኘራይዝ የንብረት ክፍል ሀላፊ፤
2ኛ ደነቀው አላምር አዳነ ጤፉን የጫነ መኪና ሾፌር ፤
3ኛ እናውጋው ደሴ መንጋው የመኪናው እረዳት ፤
4ኛ አዲሱ እንግዳ አይተነው የኢንተርኘራይዙ የምግብ አቅርቦት ክትትልና ቁጥጥር ሽፍት ሀላፊ ፤
5ኛ በለጠ ጌጤ ተመስገን ሾፌር፤
ግለሰቦቹ በተጠረጠሩበት በስልጣን አላግባብ መገልገል የሙስና ወንጀል ፤ በምስራቅ ጎጃም ዞን ፓሊስ የሙስና ወንጀሎች ዋና ክፍል ምርመራው ሲጣራ ቆይቶ መዝገቡ ለሚመለከተው የፍትህ አካል ከተላከ በኃላ ተከሳሾች ጥፋተኛ መሆናቸውን በቀረቡ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎች ያረጋገጠው የአብክመ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ደብረ ማርቆስ ተዘዋዋሪ ችሎት የካቲት 5 ቀን 2013 ዓ/ም በዋለው ችሎት ፦
• 1ኛ ተከሳሽ በ4 ዓመት ከ5 ወር ፅኑ እስራትና በ3 ሺ ብር የገንዘብ ቅጣት፤
• 2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች እያንዳንዳቸው በ4 ዓመት ፅኑ እስራትና 3 ሺ ብር የገንዘብ ቅጣት፤
• 4ኛ እና 5ኛ ተከሳሾች እያንዳንዳቸው በ6 ወር ቀላል እስራትና በ2 ሺ ብር የገንዘብ ቅጣት እንዲቀጡ ተወስኖባቸዋል።
(የምስራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ)