TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.7K photos
1.44K videos
207 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Attention😷

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት ከተደረገው 5,001 የኮቪድ-19 የላብራቶሪ ምርመራ 733 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ተረጋገጠ።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የ15 ሰዎች ሞት ሲመዘገብ፤ 204 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

ኮቪድ-19 ወረርሽኝ በኢትዮጵያ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ 147,825 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ ከነዚህ መካከል ፣2,209 ሰዎች ሞተዋል፤ 128,946 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

አሁን ላይ 307 ሰዎች በፀና ታመው በህክምና ክትትል ላይ ይገኛሉ።

#Purpose #Tikvah
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የፖለቲከኞቹ የረሃብ አድማ ፦ - እነአቶ ጃዋር መሀመድ በረሃብ አድማ ዛሬ 18ኛ ቀናቸውን መያዛቸው - የፖለቲከኞቹ የጤና ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ - እነዶ/ር ኢሊሊ ጀማል ባለው ሁኔታ ተገደው ክትትል ማቆማቸው - ጠበቃ ከድር ቡሎ በተደጋጋሚ ውስኔ የተሰጠበት የፍርድ ቤት ትዕዛዝ መጣሱን መግለፃቸው - ICRC አባላት ፖለቲከኞቹ ያሉበትን ሁኔታ መጎብኘታቸው - አቶ በቀለ ገርባ ወደግል የህክምና…
#Update

ዛሬ የካቲት 8 የነአቶ ጃዋር መሃመድ ጠበቆች በረሃብ አድማ ላይ የሚገኙ እስረኞች የህክምና ጉዳይ አስመልክቶ ጉዳዩን ለሚያየው የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ችሎት አቤቱታ አቅርበው ነበር።

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎትም እነአቶ ጀዋር መሀመድ በግል ሀኪሞቻቸው እንዲሁም በፈለጉት የግል ህክምና ተቋም መታከም እንደሚችሉ አፅንኦት ሰጥቶ ትዕዛዝ አስተላልፏል።

ከቀናት በፊት አቶ በቀለ እያደረጉት በሚገኘው የረሃብ አድማ ምክንያት በጠና ታመው ወደ ህክምና ተቋም ሊወሰዱ ሲሉ እንዳይሄዱ ማረሚያ ቤቱ "ከላይ በመጣ" ትዕዛዝ ከልክሎ እንደነበር የህክምና ክትትል የሚያደርጉላቸው ዶ/ር ኢሊሊ ጀማል መግለፃቸው ይታወሳል።

በተጨማሪ ሀኪሞቻቸው ባለው ሁኔታ ተገደው ለእነአቶ ጃዋር የሚያደርጉትን የህክምና ክትትል ማቋረጣቸውን እንደገለፁ ይታወቃል።

https://telegra.ph/JawarMohammed-02-15
የሱዳን ተወረርኩኝ ክስ ?

ሱዳን የኢትዮጵያ ጦር ኃይል ድንበሬን ተሻግሮ "ወረራ ፈጽሞብኛል" ስትል ከሰሰች።

የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ትናንት የካቲት 7 ቀን 2013 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው ድርጊቱ በሁለቱ ሃገራት መካከል የነበረውን የድንበር ውዝግብ የሚያባብስ ነው ማለቱን ሮይተርስን ዋቢ አድርጎ ዶቼ ቨለ ዘግቧል።

ኢትዮጵያ የሱዳንን ድንበር ተሻግራ መግባቷ 'አሳዛኝ ነው' ያለው መግለጫው ውጤቱ አደገኛ እና ተቀባይነት የሌለው እንዲሁም በቀጣናው ደህንነት እና መረጋጋት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳድራል ብሏል።

ኢትዮጵያ የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ላይ እስካሁን ምንም የሰጠችው ምላሽ ባይኖርም ከዚህ ቀደም እጅግ በተደጋጋሚ ሱዳን የኢትዮጵያን ድንበር ጥሳ መግባቷን በመግለፅ የሀገሪቱ ጦር ስፍራውን ለቆ ወደነበረበት እንዲመለስ ስታሳስብ ነበር።

በተጨማሪ ኢትዮጵያ የድንበር ላይ ችግሩ በውይይት ይፈታ ዘንድ በቅድሚያ የሱዳን ጦር በኃይል የተቆጣጠራቸውን አካባቢዎች ለቆ መውጣት እንዳለበት ስታሳስብ ቆይታለች/አሁንም እያሳሰበች ትገኛለች።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
TIKVAH-ETHIOPIA
ኢዜማ አባሉ በጥይት ተመተው መገደላቸውን አሳወቀ። የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) የቢሾፍቱ ከተማ የአድአ ምርጫ ወረዳ 1 ሊቀመንበር የነበሩት ግርማ ሞገስ ትላንት እሑድ ምሽት በተተኮሰባቸው ጥይት መገደላቸውን ፓርቲው በይፋዊ ፌስቡክ ገፁ አሳወቀ። ኢዜማ አባሉ በማን እንደተገደለ/በግድያው ዙሪያ ዝርዝር መረጃ አልሰጠም። ፓርቲው የተፈፀመውን የግድያ ወንጀል ያወገዘው ሲሆን ተጨማሪ መረጃዎች…
"ትላንት የተገደሉት የኢዜማው አባል ማስፈራሪያ እና ዛቻ ይደርስባቸው ነበር"

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) የቢሾፍቱ ከተማ የአድአ ምርጫ ወረዳ 1 ሊቀመንበር አቶ ግርማ ሞገስ የተገደሉት መኖሪያ ቤታቸው አካባቢ በተተኮሰባቸው ጥይት መሆኑ ተገልጿል።

የኢዜማ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ናትናኤል ፈለቀ እንደገለፁት፥ አቶ ግርማ ከዚህ ቀደም በአካባቢው ከሚያደርጉት የፖለቲካ እንቅስቃሴ እንዲታቀቡ ማንነታቸውን ከማያውቋቸው ሰዎች ማስፈራሪያ እና ዛቻ ይደርስባቸው እንደነበር ለፓርቲው ሪፖርት አቅርበው ነበር።

ፓርቲውም በቀረበው ሪፖርት መሰረት ክትትል ሲያደርግ እንደነበርም ተናግረዋል።

ትላንት ምሽት የተፈፀመው ግድያ ሲደርስባቸው ከነበረው ማስፈራሪያና ዛቻ ጋር ይያያዛል ወይስ አይያያዝም ? የሚለውን ጉዳይ ማጣራት እንደሚያስፈልግው አቶ ናትናኤል ገልፀው ኢዜማ ማጣራቱ ተደርጎ እንዳበቃ በይፋ እንደሚገልፅ ዛሬ ምሽት ከቢቢሲ ሬድዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ አሳውቀዋል።

ኢዜማ ከግድያው ጋር በተያያዘ ከመንግስት ኃላፊዎች እና ከአካባቢው የፖሊስ ኃላፊዎች ጋር ንግግር እያደረገ እንደሚገኝ አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ከትላንት በስቲያ በቁጥጥር ስር የዋለ የምግብ ዘይት ለሸማቾ ማህበራት እየተሰራጨ ነው ! የካቲት 6 ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ጀሞ ሚካኤል አካባቢ አንበሳ ጋራዥ ጎን በግለሰብ መጋዘን በህገወጥ መንገድ ተከማችቶ የተገኘው 2 ሚሊየን ጀሪካን ፓልም የምግብ ዘይት በሁሉም ክፍለ ከተሞች ለሚገኙ ሸማች ማህበራት እየተሰራጨ መሆኑን የአ/አ ፕሬስ ሴክሬተሪያት አሳወቀ። በቁጥጥር ስር የዋለው የምግብ ዘይት በሁሉም…
ዘይቱን ያከማቸው አካል ታወቀ !

ከሰሞኑ በግለሰብ መጋዘን በህገወጣ መንገድ የተከማቸው 2 ሚሊዮን ጀሪከን የፓልም ዘይት መያዙ ሲገለፅ ነበር።

ነገር ግን ይህ ዘይት በማን እንዴት ሊከማች እንደቻለ ይፋዊ መረጃ ከመንግስት በኩል ሳይሰጥ ቆይቷል።

ዛሬ ማለዳ ዘይቱን ያከማቸው አፍሪካ ሃ/የተ/የግ/ማህበርና የሮዛ ዳቦ ባለቤት እንደሆነ ተሰምቷል።

የላፍቶ ክ/ከተማ ነዋሪዎች በተለያየ ግዜ ለወረዳቸው እና ለክፍለ ከተማቸው ሲያሳውቁና ሲጠይቁ መቆየታቸው ተገልጿል።

ነዋሪው አቅርቦት በማጠሩ በተፈጠረው የዋጋ ውድነት የተነሳ ወደ አከፋፋይ ድርጅቱ አፍሪካ ሃ/የተ/የግ /ማህበር በመሄድ ቢጠይቁም ያገኙት የነበረው መልስ የውጭ ምንዛሪ ስላጣን መግዛት አልቻልንም፤ ከወደብ አልተነሣም፤ መንግስት ሁኔታዎችን አላመቻቸልንም የሚል ነበር።

ነገር ግን በድርጅቱ መጋዘን የፓልም ዘይት ሲወርድና ሲራገፍ ፤ እና ከመጋዘኑ በአሳቻ ሰዓት ወደ ተለያዩ አካባቢዎች እየተጫነ ሲጋዝ በተከታታይ ማየታቸውንና ድርጊቱ አግባብ አለመሆኑን በመረዳት ለክፍለ ከተማው መጠቆማቸው ተገልጿል።

በሌላ በኩል ፦

የአፍሪካ ኃ/የተ/የግ/ማ ለንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር የኢኒስፔክሽን እና ርጉላቶሪ ዳይሬክቶሬት በቀን 01/06/2013 በላከው ሪፖርት ድርጅቱ በጥር ወር ብቻ በአቃቂ ቃሊቲ እና ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተሞች ባጠቃላይ 1,846,532 ሊትር ፓልም ዘይት ማከፋፈሉን እና በመጋዘኑ የሚገኘው 14,003 ሊትር ብቻ በመሆኑ 3,552,376 ሊትር ፓልም የምግብ ዘይት ወደ አገር ውሥጥ ለማስገባት እንዲፈቀድለት መጠየቁ ታውቋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ፕሬስ ሴክሬተሪ በዚሁ ጉዳይ ያሰራጨው ዝርዝር መረጃ : telegra.ph/Addis-Ababa-Press-Sectary-02-16

@tikvahethiopia
ባንክ ቤት ውስጥ የማጭበርበር ድርጊት የፈፀመው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ !

በደብረ ማርቆስ ከተማ ቀበሌ 02 ልዩ ቦታው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሸዋበር ቅርንጫፍ ጥር 19 ቀን 2013 ተጠርጣሪው ወደ ባንክ በመሄድ ከሸዋበር ቅርንጫፍ በአቶ አየነው መሃሪ መላኩ ስም ከተከፈተው አካውንት 5 ሺ ብር እና ከዋናው ንግድ ባንክ 24 ሺ ብር በአጠቃላይ 29 ሺ ብር የማጭበርበር ወንጀል ፈጽሟል።

ተጠርጣሪው ወንጀሉን እንዴት ፈፀመው ?

የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽ/ቤት የሙስና ወንጀሎች ምርመራ ክፍል ሀላፊ ምክትል ኮማንደር አበበች አምሳሉ ሲያስረዱ ፦

ተጠርጣሪው ግለሰብ ባንክ በመሄድ የገንዘብ ወጪ ፎርም የሚሞሉ ግለሠቦችን ፎርሙን በሞባይል በማንሳት እና ፎርም ሞልተው ሲሳሳቱ የሚጥሉትን በማንሳት የአካውንት ቁጥሩን በመውሰድና ፊርማውን ጊዜ ሰጥቶ በመመለማመድ በተጨማሪም በአካውንት ባለቤቱ ስም የራሱን ፎቶ ግራፍ ያለበት ሀሠተኛ መታወቂያ በማዘጋጀት ወረፋ በሚበዛበት ጊዜ በመሄድ የማጭበርበር ተግባሩን ፈፅሟል።

በተጨማሪም የካቲት 5/6/2013 ዓ,ም ተጠርጣሪው ግለሠብ በአቶ ችሎት አበበ ጸጋዬ ስም የተዘጋጀ የሀሰት ሰነድ በማዘጋጀት 40 ሺ ብር ለማጭበርበር ሲሞክር ከባንኩ ሰራተኞች ለፖሊስ በደረሰ ጥቆማ መሠረት ተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር ውሎ አስፈላጊው የምርመራ ስራ እየተሰራ ነው ተብሏል።

ፖሊስ ህብረተሰቡ በእንደዚህ አይነት ወንጀል ሰለባ እንዳይሆን ገንዘብ ወጪ በሚያደርጉበት ግዜ ፎርሙን ከሰው እይታውጭ አድርጎ መሙላት እና ወረፋ በሚያሲዙበት ግዜ መታወቂያቸውን እንዲጠቀሙ ገልጸው የባንክ ሰራተኞችም ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስቧል።

መረጃው የደ/ማርቆስ ከተማ ፖሊስ ነው።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የኑሮ ውድነቱ ነገር ...

በሀገራችን የሚታየው የኑሮ ውድነት የሰዎችን ህይወት በእጅጉ እየተፈተነው ይገኛል።

በሸቀጦች ዋጋ ላይ በየጊዜው የሚታየው ጭማሪም በርካቶች ህይወታቸው በፈተና እንዲሞላ እያደረገው ነው።

ከሰሞኑ ደግሞ የነዳጅ ምርቶች ላይ የዋጋ ክለሳ መደረጉ / የዋጋ ጭማሪ መደረጉ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ ሁኔታዎችን ይበልጥ አስቸጋሪ አድርጎታል።

በአንድ በኩል በየጊዜው የሚጨምረው የሸቀጦች ዋጋ በሌላ በኩል የሰሞኑ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ በኑሮ ላይ ከፍተኛ ጫና አሳድሯል።

እናትስ ምን ትላላችሁ ? ኑሮውስ እንዴት ይዟችኃል ? በአስተያየት መስጫው ላይ ሀሳባችሁን አስፍሩ።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
የጋምቤላ ክልል የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ !

በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ዘግይቶ በ2013 ዓ.ም በክልሉ የተሰጠው የ2012 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ይፋ መደረጉን የጋምቤላ ክልሉ ትምህርት ቢሮ ዛሬ አስታወቀ፡፡

በክልሉ ለፈተናው ከተቀመጡ ተማሪዎች መካከል 98.5 በመቶ ተማሪዎች ወደ ቀጣይ ክፍል ተዛውረዋል።

የማለፊያ ነጥብ ለወንዶች 42 ሲሆን ለሴቶች ደግሞ 39 መሆኑ ተገልጿል።

ፈተናው ታርሞ ቢጠናቀቅም ካርድና ሮስተር ላይ የሚሞሉ መረጃዎች እንደተጠናቀቁ በቀጣይ ሳምንት በየትምህርት ቤቱ ካርድ እየተሰጠ ምዝገባ እንደሚከናወን ቢሮ ገልጿል።

የዘጠነኛ ክፍል ትምህርት መጋቢት 1 ለማስጀመር ቅድመ ዝግጅት መደረጉን የተገለፀ ሲሆን ዘንድሮ ወደ ዘጠነኛ ክፍል የተዛወሩት ከባለፈው 2011 ዓ.ም ጋር ሲነፃፀር የወንድ ተማሪዎች በ21 በመቶ የሴት ተማሪዎች በ19 በመቶ እድገት ማሳየቱን ተነግሯል።

መረጃው የጋምቤላ ክልል ፕሬስ ሴክሬተሪያት ነው።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ፌዴራል ፖሊስ በ3 አይሱዙ የጭነት መኪና በሕገ-ወጥ መንገድ ከአዲስ አበባ ሊወጣ የነበረ ዘይት በቁጥጥር ሥር ማዋሉን ገለፀ !

በሦስት አይሱዙ የጭነት መኪና በሕገ-ወጥ መንገድ ከአዲስ አበባ ሊወጣ የነበረ ዘይት በቁጥጥር ሥር መዋሉን ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ማስታወቁን የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

ቁጥጥር ሥር የዋለው ዘይት የካቲት 6 ቀን 2013 ዓ.ም ጀሞ ሚካኤል ልዩ ስሙ አንበሳ ጋራዥ አካባቢ በፌዴራል ፖሊስ ቁጥጥር ስር ከዋለው 2 ሚሊዮን ሊትር በላይ ዘይት ቀድሞ ሊወጣ የነበረ መሆኑን ነው ፖሊስ የገለጸው።

"አፍሪካ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር" በተሰኘው ድርጅት ከውጭ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገባው የፓልም ዘይት በመንግሥት ፈቃድ ያገኘው በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ እንዲያከፋፍል ነበር ተብሏል።

ሆኖም በሦስት አይሱዙ የጭነት መኪና ተጭኖ ወደ ጅማ ሊወጣ ሲል በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ጅማ በር ፖሊስ ጣቢያ እና በፌዴራል ፖሊስ ትብብር በቁጥጥር ስር ውሏል።

በቁጥጥር ሥር የዋለው ዘይት 994 ጀሪካን ባለ 20 ሊትር እና 3 ሺህ ጀሪካ ባለ 3 ሊትር ፓልም ዘይት እንደሆነ ፌዴራል ፖሊስ አስታውቋል።

@TikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"... ነጋዴዎች እና አንዳንድ የመንግስት የንግድ ተቋማት ጭምር ምርትን በመደበቅ ከፍተኛ ዋጋ በመጠየቅ የዋጋ ንረትን ፈጥረዋል" - የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ

By : Ahadu Radio 94.3

የአ/አ ከተማ ንግድ ቢሮ ከ1 መቶ በላይ የመንግስት የንግድ ተቋማት የዋጋ ንረት በመፍጠራቸው ምክንያት እርምጃ እንደተወሰደባቸው ገለፀ፡፡

ቢሮው በከተማዋ የተስተዋለው የዘይት ምርት እጥረት በነጋዴዎች በጅምላ ሻጮች ብቻ ሳይሆን በአንዳንድ የመንግስት የንግድ ተቋማትም ጭምር የተፈጠረ ነው ብሏል።

የቢሮው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዳንኤል መኤሳ፥በከተማዋ የተስተዋለው የዘይትና ሌሎች የፍጆታ ምርቶች እጥረት ከፍተኛ የዋጋ ንረትን በሚፈጥሩ የንግድ አካላት የተፈጠረ መሆኑን ገልፀዋል።

ጋላፊው ፥ ነጋዴዎቹ እና አንዳንድ #የመንግስት የንግድ ተቋማትም ጭምር ምርትን በመደበቅ ከፍተኛ ዋጋ በመጠየቅ የዋጋ ንረትን ፈጥረዋል ያሉ ሲሆን እስካሁን በተደረገው ክትትልና ቁጥጥር ከ1 መቶ በላይ የመንግስት የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ መውሰዱን ለሬድዮ ጣቢያው ገልፀዋል፡፡

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ሱዳን ?

• ሱደን በምዕራብ ጎንደር ዞን ከቋራ እስከ አቡጢር ድረስ ሰፊ ቦታ በጉልበት ተቆጣጥራለች።

• ሱዳን በፈፀመችው ወረራ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል፤ ከ1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት የንብረት ዝርፊያ ተፈፅሟል።

• ከምድረገነት በቅርብ ርቀት በምትገኘው ሰላም በር ቀበሌ በርካታ የአካባበው ነዋሪዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል። የአርሶ አደሮችና የባለሀብቶች ሰብል ፣ ትራክተሮችና ካምፖች ውድመትና ዝርፊያ ተፈፅሞባቸዋል።

የሱዳን ታጣቂዎች አስካሁን ድረስ "በምድረ ገነት ከተማ" በማኅበረሰቡ ላይ ትንኮሳ እያደረጉ መሆኑን እና የአካባቢው ነዋሪዎችም ስጋት እንዳደረባቸውን የምድረ ገነት ከተማ ከንቲባ አይሸሽም ጓንቼ ተናግረዋል።

የአካባቢው መስተዳደር አካላት ፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶች ማኅበረሰቡን ለማረጋጋት ጥረት እያደረጉ መሆኑን ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ሱዳን ከጥቅምት 24 በፊት ወደነበረችበት እንድትመለስ እየሠራ ነው፡፡

ነገር ግን የመንግሥት ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ውጤታማነት የሚለካው ሱዳንን ወደነበረችበት መመለስ ሲቻል መሆኑን ተገልጿል።

"የእርሻ ጊዜ አልፎ" የሱዳን ታጣቂዎች ካደረሱት ጉዳት በላይ የከፋ ችግር እንዳይገጥም በተጀመረው አግባብ ፈጣን መፍትሔ እንዲገኝ ጥረቱ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ተጠይቋል።

በአካባቢው የሚኖረው ማኅበረሰብ የኢትዮጵያ መንግሥት የሚያሳልፈውን ውሳኔ በትግሥት እየተጠባበቀ መሆኑን ተሰምቷል።

መረጃው የተገኘው ከአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት/ ከምዕራብ ጎንደር ዞን ብልፅግና ፅህፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ከሆኑ አቶ ሁናለም አሻግሬ ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Attention😷

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት ከተደረገው 5,164 የኮቪድ-19 የላብራቶሪ ምርመራ 665 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ተረጋገጠ።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የ14 ሰዎች ሞት ሲመዘገብ፤ 199 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

ኮቪድ-19 ወረርሽኝ በኢትዮጵያ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ 148,490 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ ከነዚህ መካከል ፣2,223 ሰዎች ሞተዋል፤ 129,145ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

አሁን ላይ 308 ሰዎች በፀና ታመው በህክምና ክትትል ላይ ይገኛሉ።

#Purpose #Tikvah
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Attention😷

በሀገራችን የኮቪድ-19 ሟቾች ቁጥር እጨመረ ነው።

ባለፉት ቀናት ኢትዮጵያ ውስጥ በኮቪድ-19 የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር መጨመር አሳይቷል።

የካቲት 7፣ የካቲት 8 እና የካቲት 9 በአጠቃላይ የ42 ሰዎች ህይወት አልፏል።

ከዚህ በተጨማሪ በፅኑ ታመው ህክምና ያላይ ያሉ ሰዎች ቁጥር በፍጥነት አሻቅቧል። አሁን ላይ 308 ፅኑ ታማሚዎች አሉ።

ካለው የመተንፈሻ መሳሪያ እጥረት ሳቢያም ወረፋ በመጠብቅ ስቃይ ውስጥ የሚገኙ ወገኖቻችንም በርካታ ናቸው።

ውድ የቲክቫህ አባላት ለራሳችሁ እና ለቤተሰባችሁ ስትሉ ጥንቃቄያችሁን ጨምሩ ፤ ይበልጥ አጠናክሩ።

በየአካባቢው ከዚህ ቀደም የነበረው ጥንቃቄ እየላላ ፤ አንዳንድ ቦታ እርግፍ ተደርጎ እየተተው ፤ ጭራሽ ለሚያስተዳድሩት ህብረተሰብ አርአያ ይሆናሉ የሚባሉት የመንግስት አመራሮች ሳይቀር ምንም ነገር እንደሌለ / ኮቪድ-19 እንደጠፋ በሚመስል መልኩ ጥንቃቄ በጎደለው መልኩ እየተንቀሳቀሱ ነው።

ሞት እና ስቃይ ቤታትችን እስኪገባ አንጠብቅ!
#Purpose #Tikvah

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ዛሬ የካቲት 8 የነአቶ ጃዋር መሃመድ ጠበቆች በረሃብ አድማ ላይ የሚገኙ እስረኞች የህክምና ጉዳይ አስመልክቶ ጉዳዩን ለሚያየው የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ችሎት አቤቱታ አቅርበው ነበር። የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎትም እነአቶ ጀዋር መሀመድ በግል ሀኪሞቻቸው እንዲሁም በፈለጉት የግል ህክምና ተቋም መታከም እንደሚችሉ አፅንኦት ሰጥቶ ትዕዛዝ አስተላልፏል። ከቀናት…
አቶ በቀለ ገርባ ዛሬ ወደሆስፒታል ሲወሰዱ ምን ተፈጠረ ?

"አባቴ በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ አላውቅም" - ቦንቱ በቀለ

ትላንት የእነአቶ በቀለ ገርባ ጠበቆች በእስር ላይ የሚገኙትን የፖለቲከኞች የህክምና ጉዳይ አስመልክቶ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ችሎት አቤቱታ አቅርበው ነበር።

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎትም እነአቶ በቀለ ገርባ በግል ሀኪሞቻቸው እንዲሁም በፈለጉት የግል ህክምና ተቋም መታከም እንደሚችሉ አፅንኦት ሰጥቶ ትዕዛዝ አስተላልፎ ነበር።

በፍርድ ቤቱ የተሰጠው ትእዛዝ አቶ በቀለ፣ አቶ ጃዋር፣አቶ ሃምዛ፣ አቶ ደጀኔ አ/አ ሜክሲኮ አካባቢ ላንድማርክ ጄነራል ሆስፒታል በአጃቢ አስፈላጊውን ጥበቃ ተደርጎ ህክምና እንዲወሰዱ የሚል ነው።

ነገር ግን በዛሬው ዕለት አቶ በቀለ ገርባ ወደ "ላንድማርድ ጄነራል ሆስፒታል" እንደሚወሰዱ ከተነገራቸው እና ከማረሚያ ከወጡ በኃላ የአጃቢ መኪኖቹና እሳቸውን የያዘው አምቡላንስ ከመንገድ ላይ ወደጦር ኃይሎች ሆስፒታል እንደወሰዷቸው ልጃቸው ቦንቱ ተናግራለች።

https://telegra.ph/BekeleGerba-02-16