#Ethiopia❤️
በወንዶቹ ውድድር ከ1ኛ - 4ኛ ኢትዮጵያውያኑ አትሌቶች ተከታትለው ገቡ።
በፈረንሳይ እየተካሄደ ባለው የአለም አትሌቲክ የቤት ውስጥ ውድድር በ3,000 ሜትር ወንዶች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከ1ኛ እስከ 4ኛ ተከታትለው መግባት ችለዋል።
ጌትነት ዋለ 7:24.98 በሆነ ደቂቃ በመግባት ውድድሩን በበላይነት ሲያጠናቅቅ ሰለሞን ባረጋ ፣ ለሜቻ ግርማ እና በሪሁ ኣረጋዊ ተከታዩን ደረጃ በመያዝ ውድድራቸውን በአሸናፊነት አጠናቀዋል ።
@tikvahethsport @tikvahethiopia

#GudafTsegay
ጉዳፍ ፀጋይ ሪከርድ በመስበር ወድድሯን በበላይነት አጠናቀቀች።
በፈረንሳይ እየተካሄደ ባለው የአለም አትሌቲክ የቤት ውስጥ ውድድር ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ 3:53.09 በሆነ ደቂቃ በመግባት የ1,500 ሪከርድን (WR) በመስበር ውድድሯን በበላይነት አጠናቃለች።
#GudafTsegay❤️#Ethiopia

አጫጭር መረጃዎች #COVID19 ፦
- ባለፉት 24 ሰዓት ብቻ በመላው ዓለም 13,166 ሰዎች በኮቪድ-19 ሲሞቱ 383,614 ሰዎች በበሽታው ተይዘዋል።
- አሜሪካ በ24 ሰዓት 3,265 ዜጎቿን በወረርሽኙ አጥታለች፤ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 479,772 ደርሷል።
- UK 1,052 ዜጎቿን በ24 ሰዓት አጥታለች፤ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 113,850 ደርሷል።
- ብራዚል በ24 ሰዓታት ውስጥ የ1,340 ዜጎቿን ህይወት ስታጣ 51 ,733 ሰዎች በበሽታው ተይዘዋል።
- ሩስያ 530፣ ፈረንሳይ 508 ፣ ስፔን 766 ፣ ጣልያን 422፣ ጀርመን 674 ፣ ሜክሲኮ 531 ፣ ደቡብ አፍሪካ 396 ዜጎቻቸውን በ24 ሰዓት ውስጥ በአስከፊው ወረርሽኝ የተነጠቁ ሀገራት ናቸው።
- አህጉራችን አፍሪካ በኮቪድ-19 ሳቢያ የሞቱ ሰዎች ወደ 100 ሺህ እየተጠጉ ነው። ትላንት በአፍሪካ ደረጃ የ702 ሰዎች ሞት ሲመዘገብ 11,565 ሰዎች በበሽታው ስለመያዛቸው ተረጋግጧል።
ውድ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት የኮቪድ-19 ዛሬም የሰዎችን ህይወት እየቀጠፈ ነውና ጥንቃቄ አይለያችሁ፤ በየትኛውም ቦታ የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛ ማስኮን ማድረግ አይዘንጉ😷 ፣ ሰዎች በብዛት ከሚሰበሰቡበት ቦታ አይገኙ፣ የእጆን ንፅህን መጠበቅ አይዘንጉ!!
#Purpose #Tikvah
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የገንዘብ እጥረት ገጥሞታል ?
ከሰሞን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ "በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ሴክተር መ/ቤቶች በሙሉ የገንዘብ እጥረት በማጋጠሙ ከነዳጅ ክፍያ ውጭ አስተዳደሩ እንደማያስተናግድ" ፤ እንዲሁም "በከተማ አስተዳደሩ የካሽ እጥረት በመኖሩ ከየካቲት 1 ጀምሮ ምንም አይነት ክፍያ እንደማይሰጥ" የሚገልፁ ማስታወቂያዎች ሲዘዋወሩ ነበር።
በተጨማሪ አስተዳደሩ ባጋጠመው የገንዘብ እጥረት ስራ መስራት አቁሟል የሚሉ መረጃዎች ሲሰራጩ ታይቷል።
በዚህ ጉዳይ የከተማ አስተዳደሩ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ለገሰ ናዶ እንደገለፁት ሁሉም መረጃዎቹ ሀሰተኛ ናቸው።
የጥሬ ገንዘብ አስተዳደር ስርዓትን በማጠናከር የመንግስት ሀብት ውጤታማትን ለማሳደግ መምሪያው በልዩ ትኩረት እየሰራ ነው ብለዋል።
አክለው ጠንካራ ድጋፍና ክትትል በማድረግ የተሻለ የፋይናንስ አገልግሎት እየተሰጠ ይገኛል ሲሉ ገልፀዋል።
በ2013 በጀት ዓመት በከተማ ደረጃ ከተያዘው 2 ቢሊየን 54 ሚሊየን ብር በጀት ውስጥ 37 ፐርሰንት የሚሆነውን 800 ሚሊየን ብር ለካፒታል ፕሮጀክቶች መድቦ የከተማውን ልማት እና እድገት ቀጣይነት ለማረጋገጥ እየተሰራ መሆኑ ኃላፊው አሳውቀዋል።
በ2013 ዓ/ም በጀት ዓመት ወደ ስራ የገቡትን ጨምሮ ከ155 በላይ የካፒታል ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ፋይናንሻል ዕቅድ መሰረት እየተከናወኑ ይገኛሉ ብለዋል።
ከካፒታል ፕሮጀክቶች በተጨማሪ የቋሚና አላቂ ዕቃዎች አገልግሎትና ግዢ፣ የስራ ማስኬጃና የሰራተኛ ደመወዝ ወጪ እንዲሁም አጠቃላይ መምሪያው የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ከብክነት በፀዳ መንገድ የመንግስት ገንዘብ አጠቃቀም ውጤታማነት ላይ በማተኮር እየተሰራ እንደሚገኝም አቶ ለገሰ ገልፀዋል፡፡
@tikvahethiopia

የመምህራን 9 ወር የተጠራቀመ የደሞዝ ጭማሪ (JEG) ቅሬታ አስነሳ !
By : Addis Maleda Newspaper
በአገራችን የተለያዩ ክልሎች የሚገኙ መምህራን የዘጠኝ ወር የተጠራቀመ የደሞዝ ጭማሪ (JEG) መንግስት ቃል በገባልን መሰረት አልተከፈለንም ሲሉ ቅሬታቸውን አቅርበዋል።
ከሀምሌ 2011 ዓ/ም ጀምሮ እስከ መጋቢት 2012 አመት ያለው የዘጠኝ ወር ክፍያ እንዳልተከፈላቸውና የዘጠኝ ወሩን ውዝፍ (JEG) በ2013 በጀት አመት ተካቶ ይከፈላችኋል ተብሎ ቃል ቢገባላቸውም እስካሁን ምንም ክፍያ ሳይፈጸም የበጀት አመቱ አጋማሽ ላይ መደረሱን ነው የተናገሩት።
በአዲስ አበባ ለሚገኙ መምህራን ሙሉ በሙሉ (JEG) ሲከፈል የሌሎች ክልሎች ግን እስከ አሁን አለመከፈሉን ቅሬታቸውን ያቀረቡ መምህራን አክለው ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ም/ ፕሬዚዳንት ሽመልስ አበበ በበኩላቸው በክልል መምህራን በኩል የሚቀርቡት ጥያቄዎች አግባብነት ያላቸው እንደሆኑ ማህበሩ ያውቃል ሲሉ ገልጸዋል።
በአንድ ዘርፍ ላይ ያሉ ሰዎች ለአንዱ ተከፍሎ ለአንዱ የሚቀርበት አግባብ እንደሌለ ያስረዱት ፕሬዝዳንቱ መቼ እንደሚከፈል ነው እንጂ ያልታወቀው ክፍያው መፈፀሙ እንደማይቀር ጠቁመዋል።
በጉዳዩን በተመለከተ በአዲስ ማለዳ ጋዜጣ የተጠየቁት የገንዘብ ሚኒስቴር ህዝብ ግንኙነት ሰመሪታ እንደተናገሩት ጉዳዩ በበላይ አካላት እየታየ እንደሆነ ተናግረዋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

#TurkeyAnkara
በቱርክ አንካራ የተገነባው አዲሱ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጽህፈት ቤት ፤ በቅርቡ ከፍተኛ የመንግስት ባለሥጣናት በተገኙበት እንደሚመረቅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳውቋል።
ይህ የኤምባሲ ፅህፈት ቤት የመሰረት ድንጋይ የተቀመጠው በየካቲት 2009 ዓ/ም (ከ4 ዓመት ከፊት) በወቅቱ የኢትዮጵያ ፕሬዜዳንት በነበሩት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ አማካኝነት ነበር።

ችሎት !
በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ለአቶ ጃዋር መሀመድ አራት የሞባይል ሲም ካርድ ሊያቀብል ሲል በቁጥጥር ስር ውሏል የተባለው ግለሰብ ዋስትና ተፈቀደለት፡፡
ተጠርጣሪ ሀምዛ ጀማል አንድ በOMN ድርጅት ስም እና 3 በግለሰብ ስም የወጡ ሲም ካርዶችን ለአቶ ጃዋር መሀመድ ሊያቀብል ሲል በማረሚያ ቤቱ የጥበቃ አባላት በቁጥጥር ስር ውሏል ተብሎ ከአንድ ወር በላይ በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምርመራ ሲደረግበትና ለአራት ጊዜ ፍርድ ቤት ሲቀርብ ቆይቷል።
በምርመራው መርማሪ ፖሊስ ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት ምስክር ቃል መቀበሉን ከኢትዮ ቴሌኮም ሲም ካርዱ በማን ሰም ስለመውጣቱ ማስረጃ መሰብሰቡን ገልጾ ነበር፡፡
ምርመራ መዝገቡን አቃቤ ህግ እየተመለከተው መሆኑን እንዲሁም ተጨማሪ ምስክር ለመቀበል ተጨማሪ የምርመራ ቀናትን ጠይቆ የነበረ ሲሆን የተጠርጣሪ ጠበቃ በቂ ጊዜ ተሰጥቷል ተጨማሪ ጊዜ መጠየቁ አግባብ አደለም ሲል ተቃውሞ ተከራክሮ ነበር፡፡
የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት መርማሪ ያቀረበው የጊዜ ቀጠሮ ጥያቄ ተጨማሪ ጊዜ ለመስጠት አሳማኝ ምክንያት አይደለም ሲል አልተቀበለውም፡፡
እስካሁን የተከናወኑ የምርመራ ቀናት በቂ ናቸው ሲል ተጠርጣሪው የ30 ሺህ ብር ዋስ አስይዞ ከእስር እንዲፈታ ዋስትና ፈቅዷል፡፡
ምንጭ፦ ኤፍ ቢ ሲ

የቤንዚል ዋጋ ጨምሯል በሚል ያላግባብ ክፍያ የሚጠይቁ የባጃጅ አሽከርካሪዎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ከፖሊስ ማሳሰቢያ ተሰጠ !
በአሶሳ ከተማ አላግባብ እየተንቀሳቀሱ ያሉ የባጃጅ አሽከርካሪዎች ከድርጊታቸዉ ሊቆጠቡ እንደሚገባ የአሶሳ ከተማ አስተዳደር አሳሰበ።
የአሶሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮ/ር ቡሽራ አልቀሪብ ፥ በከተማው ያሉ አንዳንድ የባጃጅ አሽከርካሪዎች ከንግድና ኢንዱስትሪ ትራንስፖርት መምሪያ የተደረገ የተመን ለዉጥ ሳይኖር የቤንዚል ዋጋ ጨምሯል በሚል ምክንያት ከትላንት ጀምሮ በራሳቸዉ ጊዜ በመጨመር 5 ብር የማስከፈል ሁኔታ በመሞከር ይህ አልሆን ሲላቸዉም አድማ የማድረግ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ይታያል ፤ ይህ አግባብ ስላልሆነ ከድርጊታቸዉ ሊቆጠቡ ይገባል" ብለዋል፡፡
ኮ/ር ቡሽራ አክለዉ ባለባጃጆች ጥያቄ ቢኖራቸዉ እንኳን በህጋዊ መንገድ በማህበራቸዉ በኩል ከሚመለከተዉ አካል ጋር ጥያቄያቸዉን አቅርበዉ መነጋገር እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
ነገር ግን አግባብ ባልሆነ ሁኔታ የሚንቀሳቀሱት ላይ አስፈላጊዉን እርምጃ ለመዉሰድ ፖሊስ ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በመቀናጀት እየሰራ ነዉ፤ ተገልጋዩም መብቱን ማስከበርና አላግባብ የሚሰሩ አሽከርካሪዎችን መጠቆም ይገባል ማለታቸውን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ኮሚኒኬሽን ዘግቧል።
በነገራችን ላይ ሰሞኑ በተደረገው የነዳጅ ዋጋ ማስተካከያ ጋር ተያይዞ የነዳጅ ዋጋ ጨምሮ በድሮው ዋጋ ለመስራት እንቸገራለን ሲሉ በተለያዩ ከተሞች የታክሲ ሹፌሮች ፣ የባጃጅ አሽከርካሪዎች ቅሬታ እያሰሙ ይገኛሉ እስካሁን ግን በይፋ የተደረገ ምንም አይነት የታሪፍ ማስተካከያ የለም።

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ብልፅግና ዛሬ በይፋ ይቅርታ ጠየቀ።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ብልጽግና ፓርቲ በመተከል ዞን ለደረሰው ግድያና ውድመት በይፋ ይቅርታ ጠየቀ።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ጉባኤ ባለ ዘጠኝ ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል።
ጉባኤው በአሶሳ በክልሉ ወቅታዊ የፖለቲካና የሠላም ሁኔታ ላይ ለሶስት ቀናት ሲካሄድ እንደቆየ ኢዜአ አስነብቧል።
በዚህም በክልሉ መተከል ዞን በደረሰው አሳዛኝና ዘግናኝ ማንነት ተኮር ግድያና ውድመት ፓርቲው ይቅርታ ጠይቋል፡፡
የግል ፍላጎታቸውን ለማሳካት 'ብልፅግና አሀዳዊ ነው' በሚል የሀሰት ትርክት ከሁለት ቦታ በመርገጥ ህዝብን ሲበድሉ የነበሩ አመራሮች መኖራቸውን እንደገመገመ ተሰምቷል።
በቀጣይ የህግ የበላይነትን በማስከበር በወንጀል የተሳተፉ የስራ ኃላፊዎችን ተጠያቂ እንደሚሆኑ ተጠቁሟል። (ENA)