TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Lemlem_Hailu❤️#Ethiopia

በፈረንሳይ በተካሔደው የአለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ውድድር ኢትዮጵያዊቷ ለምለም ሐይሉ በ 3,000 ሜትር በ 8:32.55 በሆነ ደቂቃ በመግባት ውድድሯን በበላይነት አጠናቃለች። በዚሁ ውድድር ኢትዮጵያውያኑ ፋንቱ ወርቁ 4ኛ ፣ ፅጌ ገብረሰላማ 5ኛ ወጥተዋል።

ለምለም ሐይሉ ውድድሩን በበላይነት ስታጠናቅቅ ከፍተኛ ግምት ተሰጥቷት የነበረችውን ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሲፈን ሀሰን በመብለጥ ነው።

• ለምለም ሀይሉ በዚህ ውድድር የግሏን ምርጥ ሰዓትም አስመዝግባለች።

በሌላ በኩል ዛሬ በተካሄደ የሴቶች ውድድር በ800 ሜትር ሀብታም አለሙ ሁለተኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቃለች።

@tikvahethsport @tikvahethiopia
#Ethiopia❤️

በወንዶቹ ውድድር ከ1ኛ - 4ኛ ኢትዮጵያውያኑ አትሌቶች ተከታትለው ገቡ።

በፈረንሳይ እየተካሄደ ባለው የአለም አትሌቲክ የቤት ውስጥ ውድድር በ3,000 ሜትር ወንዶች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከ1ኛ እስከ 4ኛ ተከታትለው መግባት ችለዋል።

ጌትነት ዋለ 7:24.98 በሆነ ደቂቃ በመግባት ውድድሩን በበላይነት ሲያጠናቅቅ ሰለሞን ባረጋ ፣ ለሜቻ ግርማ እና በሪሁ ኣረጋዊ ተከታዩን ደረጃ በመያዝ ውድድራቸውን በአሸናፊነት አጠናቀዋል ።

@tikvahethsport @tikvahethiopia
#GudafTsegay

ጉዳፍ ፀጋይ ሪከርድ በመስበር ወድድሯን በበላይነት አጠናቀቀች።

በፈረንሳይ እየተካሄደ ባለው የአለም አትሌቲክ የቤት ውስጥ ውድድር ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ 3:53.09 በሆነ ደቂቃ በመግባት የ1,500 ሪከርድን (WR) በመስበር ውድድሯን በበላይነት አጠናቃለች።

#GudafTsegay❤️#Ethiopia

@tikvahethsport @tikvahethiopia
አጫጭር መረጃዎች #COVID19

- ባለፉት 24 ሰዓት ብቻ በመላው ዓለም 13,166 ሰዎች በኮቪድ-19 ሲሞቱ 383,614 ሰዎች በበሽታው ተይዘዋል።

- አሜሪካ በ24 ሰዓት 3,265 ዜጎቿን በወረርሽኙ አጥታለች፤ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 479,772 ደርሷል።

- UK 1,052 ዜጎቿን በ24 ሰዓት አጥታለች፤ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 113,850 ደርሷል።

- ብራዚል በ24 ሰዓታት ውስጥ የ1,340 ዜጎቿን ህይወት ስታጣ 51 ,733 ሰዎች በበሽታው ተይዘዋል።

- ሩስያ 530፣ ፈረንሳይ 508 ፣ ስፔን 766 ፣ ጣልያን 422፣ ጀርመን 674 ፣ ሜክሲኮ 531 ፣ ደቡብ አፍሪካ 396 ዜጎቻቸውን በ24 ሰዓት ውስጥ በአስከፊው ወረርሽኝ የተነጠቁ ሀገራት ናቸው።

- አህጉራችን አፍሪካ በኮቪድ-19 ሳቢያ የሞቱ ሰዎች ወደ 100 ሺህ እየተጠጉ ነው። ትላንት በአፍሪካ ደረጃ የ702 ሰዎች ሞት ሲመዘገብ 11,565 ሰዎች በበሽታው ስለመያዛቸው ተረጋግጧል።

ውድ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት የኮቪድ-19 ዛሬም የሰዎችን ህይወት እየቀጠፈ ነውና ጥንቃቄ አይለያችሁ፤ በየትኛውም ቦታ የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛ ማስኮን ማድረግ አይዘንጉ😷 ፣ ሰዎች በብዛት ከሚሰበሰቡበት ቦታ አይገኙ፣ የእጆን ንፅህን መጠበቅ አይዘንጉ!!

#Purpose #Tikvah

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የገንዘብ እጥረት ገጥሞታል ?

ከሰሞን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ "በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ሴክተር መ/ቤቶች በሙሉ የገንዘብ እጥረት በማጋጠሙ ከነዳጅ ክፍያ ውጭ አስተዳደሩ እንደማያስተናግድ" ፤ እንዲሁም "በከተማ አስተዳደሩ የካሽ እጥረት በመኖሩ ከየካቲት 1 ጀምሮ ምንም አይነት ክፍያ እንደማይሰጥ" የሚገልፁ ማስታወቂያዎች ሲዘዋወሩ ነበር።

በተጨማሪ አስተዳደሩ ባጋጠመው የገንዘብ እጥረት ስራ መስራት አቁሟል የሚሉ መረጃዎች ሲሰራጩ ታይቷል።

በዚህ ጉዳይ የከተማ አስተዳደሩ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ለገሰ ናዶ እንደገለፁት ሁሉም መረጃዎቹ ሀሰተኛ ናቸው።

የጥሬ ገንዘብ አስተዳደር ስርዓትን በማጠናከር የመንግስት ሀብት ውጤታማትን ለማሳደግ መምሪያው በልዩ ትኩረት እየሰራ ነው ብለዋል።

አክለው ጠንካራ ድጋፍና ክትትል በማድረግ የተሻለ የፋይናንስ አገልግሎት እየተሰጠ ይገኛል ሲሉ ገልፀዋል።

በ2013 በጀት ዓመት በከተማ ደረጃ ከተያዘው 2 ቢሊየን 54 ሚሊየን ብር በጀት ውስጥ 37 ፐርሰንት የሚሆነውን 800 ሚሊየን ብር ለካፒታል ፕሮጀክቶች መድቦ የከተማውን ልማት እና እድገት ቀጣይነት ለማረጋገጥ እየተሰራ መሆኑ ኃላፊው አሳውቀዋል።

በ2013 ዓ/ም በጀት ዓመት ወደ ስራ የገቡትን ጨምሮ ከ155 በላይ የካፒታል ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ፋይናንሻል ዕቅድ መሰረት እየተከናወኑ ይገኛሉ ብለዋል።

ከካፒታል ፕሮጀክቶች በተጨማሪ የቋሚና አላቂ ዕቃዎች አገልግሎትና ግዢ፣ የስራ ማስኬጃና የሰራተኛ ደመወዝ ወጪ እንዲሁም አጠቃላይ መምሪያው የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ከብክነት በፀዳ መንገድ የመንግስት ገንዘብ አጠቃቀም ውጤታማነት ላይ በማተኮር እየተሰራ እንደሚገኝም አቶ ለገሰ ገልፀዋል፡፡

@tikvahethiopia
የመምህራን 9 ወር የተጠራቀመ የደሞዝ ጭማሪ (JEG) ቅሬታ አስነሳ !

By : Addis Maleda Newspaper

በአገራችን የተለያዩ ክልሎች የሚገኙ መምህራን የዘጠኝ ወር የተጠራቀመ የደሞዝ ጭማሪ (JEG) መንግስት ቃል በገባልን መሰረት አልተከፈለንም ሲሉ ቅሬታቸውን አቅርበዋል።

ከሀምሌ 2011 ዓ/ም ጀምሮ እስከ መጋቢት 2012 አመት ያለው የዘጠኝ ወር ክፍያ እንዳልተከፈላቸውና የዘጠኝ ወሩን ውዝፍ (JEG) በ2013 በጀት አመት ተካቶ ይከፈላችኋል ተብሎ ቃል ቢገባላቸውም እስካሁን ምንም ክፍያ ሳይፈጸም የበጀት አመቱ አጋማሽ ላይ መደረሱን ነው የተናገሩት።

በአዲስ አበባ ለሚገኙ መምህራን ሙሉ በሙሉ (JEG) ሲከፈል የሌሎች ክልሎች ግን እስከ አሁን አለመከፈሉን ቅሬታቸውን ያቀረቡ መምህራን አክለው ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ም/ ፕሬዚዳንት ሽመልስ አበበ በበኩላቸው በክልል መምህራን በኩል የሚቀርቡት ጥያቄዎች አግባብነት ያላቸው እንደሆኑ ማህበሩ ያውቃል ሲሉ ገልጸዋል።

በአንድ ዘርፍ ላይ ያሉ ሰዎች ለአንዱ ተከፍሎ ለአንዱ የሚቀርበት አግባብ እንደሌለ ያስረዱት ፕሬዝዳንቱ መቼ እንደሚከፈል ነው እንጂ ያልታወቀው ክፍያው መፈፀሙ እንደማይቀር ጠቁመዋል።

በጉዳዩን በተመለከተ በአዲስ ማለዳ ጋዜጣ የተጠየቁት የገንዘብ ሚኒስቴር ህዝብ ግንኙነት ሰመሪታ እንደተናገሩት ጉዳዩ በበላይ አካላት እየታየ እንደሆነ ተናግረዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#TurkeyAnkara

በቱርክ አንካራ የተገነባው አዲሱ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጽህፈት ቤት ፤ በቅርቡ ከፍተኛ የመንግስት ባለሥጣናት በተገኙበት እንደሚመረቅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳውቋል።

ይህ የኤምባሲ ፅህፈት ቤት የመሰረት ድንጋይ የተቀመጠው በየካቲት 2009 ዓ/ም (ከ4 ዓመት ከፊት) በወቅቱ የኢትዮጵያ ፕሬዜዳንት በነበሩት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ አማካኝነት ነበር።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia