#Ethiopia😷
በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት ከተደረገው 4,981 የኮቪድ-19 የላብራቶሪ ምርመራ 572 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ተረጋገጠ።
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የ2 ሰዎች ሞት ሲመዘገብ ፤ 248 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
ኮቪድ-19 ወረርሽኝ በኢትዮጵያ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ 143,566 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ ከነዚህ መካከል ፣2,158 ሰዎች ሞተዋል፤ 126,004 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
አሁን ላይ 238 ሰዎች በፀና ታመው በህክምና ክትትል ላይ ይገኛሉ።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

በሀገሪቱ የመጀመሪያ መሆኑ የተገለፀው ዘመናዊ የእናቶችና ህፃናት ሆስፒታል መጠናቀቁ ተገለፀ !
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተገነባው በሀገራችን የመጀመሪያው ትልቁና ዘመናዊ የእናቶችና ህፃናት ሆስፒታል መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዛሬ ምሽት ገልጿል።
ሆስፒታሉ ፦
- በ20,000 ካሬ ላይ ያረፈ፣
- 400 በላይ ተኝቶ መታከሚያ አልጋዎች ያሉት፣
- 100 የልህቀት ማዕከል አገልግሎት መስጫ ክፍሎች ያሉት፥
- በተመሳሳይ ሰአት ለ7 እናቶች የኦፕራሲዮን አገልግሎት መስጠት የሚያስችለው ዘመናዊና ወረቀት አልባ መስተንግዶ የሚሰጥ ዘመናዊ የህክምና ቁሳቁሶች የተሟሉለት ነው ተብሏል።
የእናቶች እና ህጻናት ሆስፒታሉ የካቲት 4 ቀን 2013 ዓ/ም በምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ተመርቆ ስራ ይጀምራል ተብሏል።
ግንባታው ቀድሞ ለ "መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ" ተብሎ የተጀመረ ሲሆን የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ በከተማው ትልቅ የአገልግሎት ችግር ያለበት የእናቶችና ህጻናት ጤና ቅድሚያ በመስጠት 700 ሚሊየን ብር በመመደብ ተጨማሪ ግንባታ በማድረግ እና ነባሩን ግንባታ በማሻሻል ወደ ሆስፒታልነት እንዲቀየር ማድረጉን የከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሴክሬተሪያት አሳውቋል።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ፦
ዛሬ የካቲት 2/2013 ዓ.ም ከቀኑ 6፡20 ጀምሮ 'ሰበር ዜና Breaking News' በሚል በማረሚያ ቤት በሚገኙት በአቶ ጃዋር መሃመድ እና በሌሎችም ግለሰቦች ዙሪያ የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ኮሚሽነር ደብዳቤ እንደጻፈ ተደርጎ በተለያዩ ማህበራዊ ትስስር ገጾች እየተናፈሰ ያለው ጉዳይ ፍጹም ስህተት እና ከእውነት የራቀ መሆኑን የፌዴራል ማረሚያ ቤት ባወጣው አጭር መግለጫ አሳውቋል።
በደብዳቤው የተካተቱ ቁጥር ፣ ቀን ፣ ሎጎ እንዲሁም ማህተም በፎቶ ሾፕ የተቀነባበሩ እንጂ ከፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን መዝገብ ቤት የወጣ ደብዳቤ እንዳልሆነ ማረሚያ ቤቱ አረጋግጧል።

#Lemlem_Hailu❤️#Ethiopia
በፈረንሳይ በተካሔደው የአለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ውድድር ኢትዮጵያዊቷ ለምለም ሐይሉ በ 3,000 ሜትር በ 8:32.55 በሆነ ደቂቃ በመግባት ውድድሯን በበላይነት አጠናቃለች። በዚሁ ውድድር ኢትዮጵያውያኑ ፋንቱ ወርቁ 4ኛ ፣ ፅጌ ገብረሰላማ 5ኛ ወጥተዋል።
ለምለም ሐይሉ ውድድሩን በበላይነት ስታጠናቅቅ ከፍተኛ ግምት ተሰጥቷት የነበረችውን ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሲፈን ሀሰን በመብለጥ ነው።
• ለምለም ሀይሉ በዚህ ውድድር የግሏን ምርጥ ሰዓትም አስመዝግባለች።
በሌላ በኩል ዛሬ በተካሄደ የሴቶች ውድድር በ800 ሜትር ሀብታም አለሙ ሁለተኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቃለች።
@tikvahethsport @tikvahethiopia

#Ethiopia❤️
በወንዶቹ ውድድር ከ1ኛ - 4ኛ ኢትዮጵያውያኑ አትሌቶች ተከታትለው ገቡ።
በፈረንሳይ እየተካሄደ ባለው የአለም አትሌቲክ የቤት ውስጥ ውድድር በ3,000 ሜትር ወንዶች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከ1ኛ እስከ 4ኛ ተከታትለው መግባት ችለዋል።
ጌትነት ዋለ 7:24.98 በሆነ ደቂቃ በመግባት ውድድሩን በበላይነት ሲያጠናቅቅ ሰለሞን ባረጋ ፣ ለሜቻ ግርማ እና በሪሁ ኣረጋዊ ተከታዩን ደረጃ በመያዝ ውድድራቸውን በአሸናፊነት አጠናቀዋል ።

#GudafTsegay
ጉዳፍ ፀጋይ ሪከርድ በመስበር ወድድሯን በበላይነት አጠናቀቀች።
በፈረንሳይ እየተካሄደ ባለው የአለም አትሌቲክ የቤት ውስጥ ውድድር ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ 3:53.09 በሆነ ደቂቃ በመግባት የ1,500 ሪከርድን (WR) በመስበር ውድድሯን በበላይነት አጠናቃለች።
#GudafTsegay❤️#Ethiopia

አጫጭር መረጃዎች #COVID19 ፦
- ባለፉት 24 ሰዓት ብቻ በመላው ዓለም 13,166 ሰዎች በኮቪድ-19 ሲሞቱ 383,614 ሰዎች በበሽታው ተይዘዋል።
- አሜሪካ በ24 ሰዓት 3,265 ዜጎቿን በወረርሽኙ አጥታለች፤ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 479,772 ደርሷል።
- UK 1,052 ዜጎቿን በ24 ሰዓት አጥታለች፤ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 113,850 ደርሷል።
- ብራዚል በ24 ሰዓታት ውስጥ የ1,340 ዜጎቿን ህይወት ስታጣ 51 ,733 ሰዎች በበሽታው ተይዘዋል።
- ሩስያ 530፣ ፈረንሳይ 508 ፣ ስፔን 766 ፣ ጣልያን 422፣ ጀርመን 674 ፣ ሜክሲኮ 531 ፣ ደቡብ አፍሪካ 396 ዜጎቻቸውን በ24 ሰዓት ውስጥ በአስከፊው ወረርሽኝ የተነጠቁ ሀገራት ናቸው።
- አህጉራችን አፍሪካ በኮቪድ-19 ሳቢያ የሞቱ ሰዎች ወደ 100 ሺህ እየተጠጉ ነው። ትላንት በአፍሪካ ደረጃ የ702 ሰዎች ሞት ሲመዘገብ 11,565 ሰዎች በበሽታው ስለመያዛቸው ተረጋግጧል።
ውድ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት የኮቪድ-19 ዛሬም የሰዎችን ህይወት እየቀጠፈ ነውና ጥንቃቄ አይለያችሁ፤ በየትኛውም ቦታ የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛ ማስኮን ማድረግ አይዘንጉ😷 ፣ ሰዎች በብዛት ከሚሰበሰቡበት ቦታ አይገኙ፣ የእጆን ንፅህን መጠበቅ አይዘንጉ!!
#Purpose #Tikvah
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT