#መቄዶንያ
መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር ከ 1.2 ቢሊዮን ብር በላይ የሚፈጅ ዘመናዊ ሆስፒታል እና የአረጋውያን መኖሪያ ህንፃ ግንባታ እያከናወነ ይገኛል።
አሁን ላይ ግንባታው በፎቶው የምትመለከቱት ደረጃ ላይ ደርሷል።
ይህ ህንፃ ሃምሳ በመቶ (50 %) የደረሰ ሲሆን ማህበሩ የህንፃውን ግንባታ ማጠናቀቀ እንዲችል ጠጠር፣ አሻዋ፣ ሲሚንቶ፣ ቁርጥራጭ ብርት፣ የፊኒሽንግ ቁሳቁሶችን እንደሚያስፈልጉት ለዚህም የሁሉም እገዛ እንደሚያስፈልገው አሳውቋል።
8161 ላይ " OK " ብሎ በመፃፍ ለተጀመረው ህንፃ ግንባታ የበኩልዎን አስተዋፅዎ ማድረግ እንደሚቻል ሜቄዶኒያ ገልጿል። ለበለጠ ዝርዝር መረጃ ደግሞ በ 0979797979 መደወል ይቻላል።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
ከአዲስ አበባ ወደ አማራ ክልል በመጓዝ ላይ የነበረ ተሳቢ መኪና ደጀን አካባቢ ተንሸራቶ በመውደቁ የትራንስፓርት መጉላላት መፍጠሩን የደጀን ከተማ አስተዳደር አስታወቀ ! ከአዲስ አበባ ወደ አማራ ክልል በመጓዝ ላይ የነበረው ተሳቢ መኪና ከደጀን ወጣ ብሎ በሚገኝ ደምበዛ በተባለ ስፍራ ከምሽቱ አንድ (1) ሰዓት ላይ ባጋጠመው መንሸራተት መንገድ ተዘግቷል። በዚህ ምክንያት ወደ አዲስ አበባም ሆነ ወደ ባህርዳር…
#update
ከአዲስ አበባ ከተማ ወደ አማራ ክልል በመጓዝ ላይ የነበረ ተሳቢ መኪና ደጀን አካባቢ ተንሸራቶ በመውደቁ ተከስቶ የነበረው የትራንስፓርት መጉላላት መፈታቱን የደጀን ከተማ አስተዳደር አስታወቀ።
ከአዲስ አበባ ወደ አማራ ክልል በመጓዝ ላይ የነበረው ተሳቢ መኪና ከደጀን ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኝ ደምበዛ በተባለ ስፍራ ትናንት የካቲት 01/2013 ዓ.ም ምሽት አንድ (1) ሰዓት ላይ ባጋጠመው መንሸራተት መንገድ መዘጋቱን ይታወቃል።
በዚህ ምክንያትም ወደ አዲስ አበባም ሆነ ወደ ባሕር ዳር ትራንፖርት ተስተጓጉሎ ነበር፡፡
በዛሬው ዕለት የካቲት 02 ቀን 2013 ዓ.ም ተሸከርካሪው ቦታ በመልቀቁ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴ መገባቱን የደጀን ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አበጀ አላምረው ተናግረዋል።
ችግሩ መፈታቱን እና ከሁለቱም አቅጣጫ የተለምዶው ሠላማዊ እንቅስቃሴ መቀጠሉን ነው ከንቲባው ያስታወቁት፡፡
ምንጭ፦ የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

#Facebook
ፌስቡክ የኮቪድ-19 ክትባት መርዛማ ነው ፣ አደገኛ ነው ፣ ኦቲዝም ያስከትላል በሚል ፖስት የሚደረጉ ፅሁፎችን እንደሚያነሳ በትላንትናው ዕለት አሳውቋል።

እነአቶ ዳጋቶ በ20 ሺህ ብር ዋስ እንዲለቀቁ ተወሰነ።
ዛሬ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተዘዋዋሪ ችሎት አቶ ዳጋቶ ኩምቤ (የቀድሞ የዎላይታ ዞን አስተዳዳሪ የነበሩ) እና አቶ ጎበዜ ጎዳና በ20 ሺህ ብር ዋስትና እንዲለቀቁ ወስኗል።
በ2ተኛው መዝገብ የታየው አቶ ጥጋቡ ደጀኔ በ30 ሺ ብር ዋስትና እንዲለቀቁ ተወስኗል።
Via Woldetsaadiqa Tamsggana
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዛሬ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተዘዋዋሪ ችሎት አቶ ዳጋቶ ኩምቤ (የቀድሞ የዎላይታ ዞን አስተዳዳሪ የነበሩ) እና አቶ ጎበዜ ጎዳና በ20 ሺህ ብር ዋስትና እንዲለቀቁ ወስኗል።
በ2ተኛው መዝገብ የታየው አቶ ጥጋቡ ደጀኔ በ30 ሺ ብር ዋስትና እንዲለቀቁ ተወስኗል።
Via Woldetsaadiqa Tamsggana
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
"... ባህር ዳርና አካባቢዋን ሽፍኖ የነበረዉ ጭጋግ ቀንሷል" - ጥላሁን ዉቤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ላሊበላ፣ ባሕርዳር እና ጎንደር የሚያደርገዉን በረራ እንዳቋረጠ ነው። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በትላንትናው ዕለት ባሰራጨው አጭር መልዕክት ለበረራዎች መቋረጥ ምክንያቱ የአየር መበከል እንደሆነ ገልፆ ነበር። ከአዲስ አበባ ወደ ባህር ዳር ለመጓዝ ተዘጋጅተዉ የነበሩ አንዲት መንገደኛ ሰሜን…
#Update
በኢትዮጵያ ወደ ሰሜንና ሰሜን ምዕራብ ከተሞች ተቋርጦ የነበረው የአየር በረራ ተጀመረ።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰሞኑን ተፈጥሮ ነበር ባለው አስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ምክንያት በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል በሚገኙ አብዛኞቹ ከተሞች የአየር በረራ ማቋረጡን አስታውቆ ነበር።
ከአዲስ አበባ ባህርዳር፣ ጎንደር እና ላሊበላ የአየር በረራ ትናንት መጀመሩን አየር መንገዱና ተሳፋሪዎች መግለፃቸውን ዶቼ ቨለ አስነብቧል።
አንድ የአየር መንገዱ ባልደረባ ፥ የአየር ሁኔታው የተሰተካከለ በመሆኑ እሁድ ወደ ላሊበላ በረራ መጀመሩን፣ ባህርዳርና ጎንደር ደግሞ ትናንት ሰኞ የበረራ አገልግሎት መቀጠሉን ገልፀዋል፡፡ ~ DW

ለመተከል ተፈናቃዮች የ5 ሚሊዮን ብር የምግብ ድጋፍ ተደረገ !
ከመተከል ዞን ቤት ንብረታቸው ወድሞባቸው በአማራ ክልል በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ተጠልለው የሚገኙ ተፈናቃዮች ቁጥር በአሁኑ ወቅት ወደ 70,000 ይጠጋል።
ጥረት ኮርፖሬት በአማራ ክልል ቻግኒ ራንች ካምፕ ለሚገኙ ተፈናቃዮች 5 ሚሊዮን ብር ወጭ የተደረገበት የፊኖ ዱቄት ድጋፍ አድርጓል።
የጥረት ኮርፖሬት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር አምላኩ አስረስ "ጥረት" ከዚህ በፊት ለክልሉ ከ152 ሚሊዮን ብር በላይ ለማህበራዊ ልማት ድጋፍ ማድረጉን ገልጸው በራንች ካምፕ ለሚገኙ ተፈናቃዮች 1 ሺህ 600 ኩንታል ፊኖ ዱቄት መደገፉን አስታውቀዋል።
ቻግኒ ራንች ጊዜያዊ መጠለያ ካምፕ የሚገኙ ተፈናቃዮች ከ48 ሺህ በላይ እንደሚሆኑ ሪፖርት ተደርጓል። (AMMA)

#WolaitaTelevision
የዎላይታ ዞን አስተዳደር ኮሚኒኬሽን በዛሬው ዕለት የዎላይታ ቴሌቭዥን የ "ሙከራ ስርጭት" መጀመሩን በይፋ ለህዝብ አሳውቋል።
እንደዞኑ የኮሚኒኬሽን ቢሮ መረጃ ከሆነ የዎላይታ ቴሌቪዥን ጣቢያ በኢትዮሳት - frequency -11165 ፣ Polarization - horizontal ፣ Symbol Rate-45000 HD ላይ ነው ማግኘት የሚቻለው።

እነ አቶ ጃዋር መሃመድ ለምንድነው የረሃብ አድማ እያደረጉ የሚገኙት ? የጤናቸው በሁኔታ ላይ ይገኛል ? የተካሄዱት ሰልፎች ጉዳይ ? * ዘግየት ብሎ ከ Oromo Prisoners Defense Team ባገኘነው ሪፖርት ላለፉት 12 ቀናት በረሃብ አድማ ላይ ከሚገኙት መካከል አቶ ሸምሰዲን ጠሃ በአድማው በመዳከሙ ምክንያት ከምሽቱ 3:00 ላይ ከቃሊቲ እስር ቤት ወደ ሆስፒታል በአንቡላንስ ተወስዷል። በአጠቃላይ…
#Update
ዛሬ ፖለቲከኞች፣ የሃይማኖት አባቶች እና ታዋቂ ሰዎች ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ተገኝተው እነ አቶ ጃዋር መሃመድ የረሃብ አድማቸውን እንዲያቆሙ ቢጠይቋቸውም ፈቃደኛ ሳይሆኑ መቅረታቸውን የተከሳሾች ጠበቃ አቶ ከድር ቡሎ ተናገሩ።
ከፖለቲከኞች የኦነግ ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ፣ አቶ ሌንጮ ለታ ፣ አቶ ባቴ ኡርጌሳ ፣ ከሃይማኖት አባቶች ደግሞ ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ ቃሊቲ ተገኝተው ቢለምኗቸውም ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።
ሌላኛው የእነ አቶ ጃዋር ጠበቃ አቶ ሙስጋኑ ሙለታ ፤ ፖለቲከኞቹ እና የሃይማኖት አባቶች የረሃብ አድማውን እንዲያቆሙ ሲጠይቁ በስፍራው እንደነበሩ ተናግረዋል።
"እነ አቶ ጃዋር መሃመድ በጣም ተዳክመዋል። ብዙ መናገር እንዲሁም መራመድ አይችሉም። ሰውነታቸው ዝሏል። ሃኪሞችም ብዙ አታውሩ ብለዋቸዋል" ሲሉ ገልጸዋል።
"ሽምግልና የሄዱ ሰዎች 'ምግብ ብሉ። በራሳችሁ ላይ ጉዳት አታደርሱ' ሲሉ ነበር የጠየቋቸው። ይሁን እንጂ ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል" ሲሉ አቶ ምስጋኑ ተናግረዋል። [BBC, Kamil Shemsu]

#Woldia
"...የታሪፍ ማሻሻያ ይደረግለን" - የባጃጅ አሽከርካሪዎች
ከሰሞኑን በተደረገ ቤንዚንና ናፍጣ ዋጋ ጭማሪ ዙሪያ ከወልዲያ ከተማ ባጃጅ አሽከርካሪዎች ጋር ዛሬ ውይይት መደረጉን ወልዲያ ኮሚኒኬሽን አሳውቋል።
በውይይቱ ከቤንዚን እና ናፍጣ የዋጋ ጭማሪ በተጨማሪም የተሽከርካሪዎች የመለዋወጫ እቃ መጨመሩ በነበረው ታሪፍ ለመስራት አላስቻለንም ያሉ አሽከርካሪዎቹ የታሪፍ ማሻሻያ እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል።
የወልዲያ ከተማ የትራንስፖርት መንገድ ደህንነት የስራ ቡድን መሪ አቶ አድኖ ገዳሙ ከተማ አስተዳደሩ የታሪፍ ማሻሻያ ማድረግ እንደማይችል ተናግረው የፌደራል መንግስቱ ታሪፍ እከሚልክ ይሰራበት በነበረው የተሽከርካሪ ታሪፍ መቀጠል አለበት ብለዋል።

"ኮሮናቫይረስ የተዛመተው ከላብራቶሪ አምልጦ ወጥቶ ነው የሚለው መላ ምት በእጅጉ ትክክል የማይመስል ነው" - ሳይንቲስቶች
ኮቪድ-19 ቻይናዋ ዉሃን ከተማ ከመከሰቱ አስቀድሞ በሽታው በስፋት ተሰራጭቶ መቆየቱን የሚያመለክት አንድም ማስረጃ አላገኘንም ሲሉ ወደቻይና ተጉዞ የበሽታውን ምንጭ እየመረመረ ያለው የሳይንቲስቶች ቡድን መሪ ተናገሩ።
በዓለም የጤና ድርጅት በቫይረስ ተላላፊ በሽታዎች አዋቂ ሳይንቲስቱ ፒተር ቤን ኤምባረክ ዛሬ ቻይና ዉሃን ከተማ ውስጥ ለጋዜጠኞች ገለጻ አድርገዋል።
መርማሪ ቡድናችን ያካሄደው ክትትል የሚጠቁመው በሽታው ከሌሊት ወፎች እንደመነጨ ነው ብለዋል፤ ነገር ግን የሌሊት ወፎቹ ዉሃን ውስጥ የነበሩ አይመስልም ሲሉ አክለዋል።
ዓለም አቀፉ የሳይንቲስቶች ቡድን በሽታው ሲጀምር የተቀሰቀሰበት ተብሎ ይጠረጠር የነበረውን የዉሃኑን ሁዋናን የአሳ ምግቦች ገበያ እና የዉሃን የቫይረስ ምርመር ተቋምና ቤተ ሙከራም ጎብኝተዋል።
የዓለም ጤና ድርጅቱ ሳይንቲስት ጨምረው ኮሮናቫይረስ የተዛመተው ከዉሃኑ ቤተ ሙከራ አምልጦ ወጥቶ ነው የሚለው መላ ምት በእጅጉ ትክክል የማይመስል ነው ስለዚህም ከአሁን በኋላ ቡድናችን ያን አይከታተልም ብለዋል።
የቻይና የጤና ኮሚሽን ባልደረባ ዶክተር ሊያንግ ዋንያን ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል ኮሮና ቫይረስ ዉሃን ላይ ከመከሰቱ በፊት በሌሎች አካባቢዎች ሲዛመት ቆይቶም ሊሆን ይችላል ማለታቸው ተጠቅሷል።
Via VOA

#Ethiopia😷
በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት ከተደረገው 4,981 የኮቪድ-19 የላብራቶሪ ምርመራ 572 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ተረጋገጠ።
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የ2 ሰዎች ሞት ሲመዘገብ ፤ 248 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
ኮቪድ-19 ወረርሽኝ በኢትዮጵያ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ 143,566 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ ከነዚህ መካከል ፣2,158 ሰዎች ሞተዋል፤ 126,004 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
አሁን ላይ 238 ሰዎች በፀና ታመው በህክምና ክትትል ላይ ይገኛሉ።

በሀገሪቱ የመጀመሪያ መሆኑ የተገለፀው ዘመናዊ የእናቶችና ህፃናት ሆስፒታል መጠናቀቁ ተገለፀ !
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተገነባው በሀገራችን የመጀመሪያው ትልቁና ዘመናዊ የእናቶችና ህፃናት ሆስፒታል መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዛሬ ምሽት ገልጿል።
ሆስፒታሉ ፦
- በ20,000 ካሬ ላይ ያረፈ፣
- 400 በላይ ተኝቶ መታከሚያ አልጋዎች ያሉት፣
- 100 የልህቀት ማዕከል አገልግሎት መስጫ ክፍሎች ያሉት፥
- በተመሳሳይ ሰአት ለ7 እናቶች የኦፕራሲዮን አገልግሎት መስጠት የሚያስችለው ዘመናዊና ወረቀት አልባ መስተንግዶ የሚሰጥ ዘመናዊ የህክምና ቁሳቁሶች የተሟሉለት ነው ተብሏል።
የእናቶች እና ህጻናት ሆስፒታሉ የካቲት 4 ቀን 2013 ዓ/ም በምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ተመርቆ ስራ ይጀምራል ተብሏል።
ግንባታው ቀድሞ ለ "መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ" ተብሎ የተጀመረ ሲሆን የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ በከተማው ትልቅ የአገልግሎት ችግር ያለበት የእናቶችና ህጻናት ጤና ቅድሚያ በመስጠት 700 ሚሊየን ብር በመመደብ ተጨማሪ ግንባታ በማድረግ እና ነባሩን ግንባታ በማሻሻል ወደ ሆስፒታልነት እንዲቀየር ማድረጉን የከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሴክሬተሪያት አሳውቋል።

የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ፦
ዛሬ የካቲት 2/2013 ዓ.ም ከቀኑ 6፡20 ጀምሮ 'ሰበር ዜና Breaking News' በሚል በማረሚያ ቤት በሚገኙት በአቶ ጃዋር መሃመድ እና በሌሎችም ግለሰቦች ዙሪያ የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ኮሚሽነር ደብዳቤ እንደጻፈ ተደርጎ በተለያዩ ማህበራዊ ትስስር ገጾች እየተናፈሰ ያለው ጉዳይ ፍጹም ስህተት እና ከእውነት የራቀ መሆኑን የፌዴራል ማረሚያ ቤት ባወጣው አጭር መግለጫ አሳውቋል።
በደብዳቤው የተካተቱ ቁጥር ፣ ቀን ፣ ሎጎ እንዲሁም ማህተም በፎቶ ሾፕ የተቀነባበሩ እንጂ ከፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን መዝገብ ቤት የወጣ ደብዳቤ እንዳልሆነ ማረሚያ ቤቱ አረጋግጧል።

#Lemlem_Hailu❤️#Ethiopia
በፈረንሳይ በተካሔደው የአለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ውድድር ኢትዮጵያዊቷ ለምለም ሐይሉ በ 3,000 ሜትር በ 8:32.55 በሆነ ደቂቃ በመግባት ውድድሯን በበላይነት አጠናቃለች። በዚሁ ውድድር ኢትዮጵያውያኑ ፋንቱ ወርቁ 4ኛ ፣ ፅጌ ገብረሰላማ 5ኛ ወጥተዋል።
ለምለም ሐይሉ ውድድሩን በበላይነት ስታጠናቅቅ ከፍተኛ ግምት ተሰጥቷት የነበረችውን ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሲፈን ሀሰን በመብለጥ ነው።
• ለምለም ሀይሉ በዚህ ውድድር የግሏን ምርጥ ሰዓትም አስመዝግባለች።
በሌላ በኩል ዛሬ በተካሄደ የሴቶች ውድድር በ800 ሜትር ሀብታም አለሙ ሁለተኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቃለች።
@tikvahethsport @tikvahethiopia