TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
61.3K photos
1.55K videos
215 files
4.25K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ስለ34ኛው የአፍሪከ ህብረት መደበኛ የመሪዎች ጉባኤ ምን ማወቅ አለብኝ ?

- ጉባኤው ለሁለት ቀናት ሲካሄድ ቆይቶ ትላንት ምሽት ተጠናቋል።

- በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ጉባኤው በቪድዮ ኮንፈረንስ ነው የተካሄደው።

- "የአፍሪካን ባህል፣ ኪነት፣ ሙዚቃ ፣ ቋንቋና ትውፊት ይዘን አፍሪካን ወደምንፈልግበት እናደርሳለን" የሚል መሪ ቃል ነበረው።

- የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ፕሬዜዳንት ፌሌክስ ቺሲኬዲ አዲሱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል።

- አዲሱ ሊቀመንበር አዲስ አበባ ተገኘተው የAU ጉባኤ አዳራሽ ውስጥ ከቀድሞ ሊቀመንበር የደቡብ አፍሪካው ፕሬዜዳንት ራማፎሳ (እሳቸው ቨርቿል) ሆነው ርክክብ አድርገዋል።

- ከቻድ ሙሳ ፋኪ እንደገና የAU ዋና ኮሚሽነር ሆነው ተመርጠዋል። ምክትል ኮሚሽነር የሩዋንዳዋ ዶክተር ሞኒክ Nsanzabaganwa ሆነው ተመርጠዋል።

- የአፍሪካ ሰላም ጉዳይ፣ የኢኮኖሚ ውህደት፣ ዴሞክራሲና መልካም አስተዳደር በአፍሪካ ማስፈን ሌሎች አፍሪካን እየተፈታተኑ ያሉ ችግሮችን የሚያነሱ አጀንዳዎች ነበሩ። በዋነኝነት ኮቪድ-19 ወረርሽኝ መዋጋት፣ ክትባት ለሁሉም ማዳረስ የሚሉት ሃሳቦች ተነስተውበታል።

Via Ambassador Dina Mufti
Compiled By : Tikvah-Ethiopia
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#InterReligiousCouncilOfEthiopia

የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶችን፣የሀገር ሽማግሌዎችንና መማክርትን ያካተተ ልዑክ በወቅታዊ ሁኔታ ላይ ለመወያየት እና ድጋፍ ለማድረግ ወደ ትግራይ ክልል ማቅናቱን የጉባኤው ዋና ጸሃፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ ለኢዜአ ገለጹ።

ከዛሬ ጀምሮ ለ3 ቀናት የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶችን ፣የሀገር ሽማግሌዎች መማክርትን ያካተተ ልዑክ ወደ በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ ማቅናቱ ነው የታወቀው።

ልዑኩ በሚኖረው ቆይታ በክልሉ ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከህብረተሰቡ እንዲሁም ከባለድርሻ አካላት ጋር እንደሚወያይም ነው የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ጸሐፊ ገልጸዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ አርባ ምንጭ ገቡ።

ዛሬ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አርባ ምንጭ ገብተዋል።

ጉብኝቱ በአትሌቲክስ ስፖርት አርባ ምንጭ ከተማ ያላትን እንቅስቃሴ በመመልከት አስፈላጊ ድጋፍ እንደሚያደርግ ፕሬዝዳንቷ ተናግረዋል።

አርባ ምንጭ የገቡት የአትሌትክስ ፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ጨምሮ ከ44 በላይ የልዑካን ቡድን ናቸው።

የተለያዩ የአትሌቲክስ ፕሮጀክቶች ፣ የስልጠና ማዕከላት ፣ የቱሪስት መዳረሻዎች እንደሚጎበኙ የፌደሬሽኑ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ቢልልኝ መቆያ ገልፀዋል።

የጋሞ ዞን ከፍተኛ አመራሮችና የአካባቢው ነዋሪዎች ለቡድኑ አቀባበል ማድረጋቸውን ከጋሞ ዞን ኮሚኒኬሽን የደረሰን መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
393 ዜጎች ከሳዑዲ አረቢያ ወደ አገራቸው እንዲሸኙ ተደረገ።

በዛሬው ዕለት ሶስት መቶ ዘጠና ሶስት ኢትዮጵያዊያን ከሳኡዲ አረቢያ ሪያድ ከተማ ወደ አገራቸው እንዲሸኙ ማድረግ መቻሉን በሪያድ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ዛሬ ወደ አገር ከተሸኙት ዜጎቻችን ውስጥ 271 ሴቶች እና 90 ህጻናት እንዲሁም 32ቱ ደግሞ ወንዶች ናቸው።

ወደ ሳዑዲአረቢያ ህጋዊ ባልሆኑ መንገዶች ሲገቡ ተይዘው በሳዑዲ የተለያዩ ቦታዎች በሚገኙ የስደተኞች ማቆያ ጣብያ ውስጥ የሚገኙና ወደ አገር መመለስ ያልቻሉ የነበሩ ዜጎችን በስፋት ወደ አገር የመመለስ ስራው የቀጠለ ሲሆን፣ ሰሞኑን የዛሬዎቹን ተመላቾች ጨምሮ 3,167 ዜጎች ከሪያድ ወደ አገር ቤት መመለስ መቻሉን ኤምባሲው አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
የረሃብ አድማው 12ኛ ቀን መያዙ ተገለፀ።

እነ አቶ ጃዋር መሐመድ፣ በቀለ ገርባ፣ ሐምዛ አዳነ እና ሸምሰዲን ጠሃ የረሃብ አድማ ማድረግ ከጀመሩ 12 ቀናት እንደሆናቸው ከOromo Political Prisoners Defense Team ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ቢቢሲ በድረገፁ እንዳስነበው ከሆነ ደግሞ ከአራቱ በተጨማሪም በእነ አቶ ጃዋር መሐመድ የክስ መዝገብ ሥር የሚገኙ ተከሳሾች የረሃብ አድማውን ተቀላቅለዋል።

ተከሳሾቹ የአቶ ጃዋር መሐመድ ጠባቂዎች እና የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ ጋዜጠኛ መለሰ ዲሪብሳ ሲሆኑ አድማውን ከተቀላቀሉ 6 ቀናት አልፏቸዋል።

ይህን ያሳወቁት ከእነ አቶ ጃዋር መሐመድ ጠበቆች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ምስጋኑ ሙለታ ናቸው።

እነ አቶ ጃዋር መሐመድን ትናንት ጠዋት መጎብኘታቸውን የሚያስረዱት ጠበቃው ፥ "ትናንት 11ኛ ቀናቸው ነበር። በጣም ተዳክመዋል" ሲሉ ተናግረዋል።

የአቶ በቀለ ገርባ ባለቤት ወ/ሮ ሃና ረጋሳ ለቢቢሲ ፤ እነ አቶ በቀለ አሁንም በረሃብ አድማ ላይ እንደሚገኙ አረጋግጠዋል።

የጋዜጠኛ መለሰ ዲሪብሳ ባለቤት ታደለች መርጋ ፥ ባለቤቷ የረሃብ አድማውን መቀላቀሉን እና ለመጠየቅ ይዛለት የምትሄደውን ምግብ አልቀበልም እያላት መሆኑን ገልጻለች።

ጠበቃ አቶ ሙለታ፥ "አንዳንዶቹ በሰው ድጋፍ ነው ከክፍላቸው የሚወጡት። በተለየ ደግሞ ዘግይተው የረሃብ አድማውን የተቀላቀሉት በጣም ከብዷቸዋል" ሲሉ ተናግረዋል።

የእነአቶ ጃዋር ሃኪሞች "ምርመራ ካደረጉላቸው በኋላ ውሃ ካልወሰዱ አንዳንድ የሰውነት አካላቸው ሥራ ሊያቆም እንደሚችል ከነገሯቸው በኋላ ነው በግድ ውሃ እየወሰዱ ያሉት። ምግብ የሚባል ነገር አፋቸው ጋር እየደረሰ አይደለም" ሲሉ አስረድተዋል።

Via BBC & Oromo Political Prisoners Defense Team
@tikvahethiopia
12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና እስካሁን የሚሰጥበት ቀን ባይታወቅም ክልሎች ፣ ዞኖች ፣ ወረዳዎች ለፈተናው ዝግጅት እያደረጉ ነው።

በተለይ ፈተናው በሚሰጥበት ወቅት እክል እንዳይፈጠር ከወዲሁ ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነ ይሰማል።

ለአብነትም በአማራ ክልል የመቅደላ ወረዳ ትምህርት ፅ/ቤት የ12ኛ ክፍል ፈተና ያለምንም ችግር ለማጠናቀቅ ቅድመ ዝግጅት እያደረገ እንደሆነ ዛሬ አሳውቋል።

ፈተናው በኦንላይን የሚሰጥ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ የወረዳው ፅ/ቤት የዲሽ ተከላ ስራ መሰራቱን፣ በመብራት መጥፋት ፈተና እንዳይቋረጥ አስተማማኝ ጄኔሬተር መዘጋጁቱን ፣ የፈተና መፈተኛ ክፍሎች መብራታቸው በትክክል መስራቱን እንዳረጋገጠ እና ለፈተናው ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።

ትምህርት ፅ/ቤቱ ፈተናው በተለያዩ ምክንያቶች ወቅቱን ጠብቆ ባለመሰጠቱ በተማሪዎች ላይ መዘናጋት እና የስነ ልቦና ጫና ማሳደሩን ገልፆ ተማሪዎች ከዚህ ስሜት ውስጥ ወጥተው ከትምህርት ቤት ሳይርቁ ዝግጅት እያደረጉ እንዲቆዩ መልዕክት አስተላልፏል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ የመፈተኛ ታብሌቶች ግዥ ተፈፅሞ ት/ቤቶች ላይ ከደረሰ በሗላ 2 ሳምንት የመለማመጃ ጊዜ እንደሚሰጥ እና ለዚህም ለተማሪዎች የICT ባለሙያዎች እገዛ እንድሚያደርጉላቸው ተገልጿል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
የዕጩዎች_ምዝገባ_እና_የምርጫ_ክልል_ቢሮዎችን_መከፈት_አስመልክቶ_የተሰጠ_መግለጫ.pdf
133.7 KB
#EthiopiaElection

የዕጩዎች ምዝገባ እና የምርጫ ክልል ቢሮዎችን መከፈት አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የተሰጠ መግለጫ !

@tikvahethiopia
#Update

ዛሬ በሰሜን ሪጅን የቴሌኮም መሠረተ ልማት ጥገና እና አገልግሎትን በተመለከተ ኢትዮ ቴሌኮም ወቅታዊ መረጃ ሰጥቷል።

ኢትዮ ቴሌኮም እስካሁን ድረስ በተጠናቀቁ የጥገናና የኃይል አቅርቦት ስራዎች በሪጅኑ ካሉ ጣቢዎች መካከል 363ቱ ለአገልግሎት ዝግጁ ተደርገው የሞባይል ድምፅና የመደበኛ ስልክ አገልግሎት እንደጀመረ አስታውቋል።

- መቐለ
- ዓድዋ
- ዓዲግራት
- ሽረ እንደስላሰ
- ነጋሽ
- ዳንሻ
- ውቅሮ
- እደጋ ሀሙስ
- ኣዲሸሁ
- ኣዲጉደም
- አጉላ
- ውቅሮ ማራይ
- ተርካን
- ሁመራ
- ማይፀብሪ
- ማይካድራ
- ኮረም
- ኣላማጣ
- ማይጨው
- ሳምሪ
- ሰቆጣ
- ሄዋኒ
- ፍረወይኒ
- ሰለክለኻ
- ቤተመራ

በተጨማሪ በሪጅኑ የሚገኙ ባንኮች አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ ቅድሚያ በመስጠት እየተሰራ መሆኑን ገልፆ ከመቐለ እና ዓዲግራት በተጨማሪ በአሁን ወቅት በሽረ እንደስላሰ ፣ አክሱም፣ እና አድዋ ከተሞችና አካባቢዎቻቸው የሚገኙ ባንኮች የብሮድባንድ አገልግሎት እንዲያገኙ መደረጉን አሳውቋል።

በተመሳሳይም የድርጅት ደንበኞቹ የብሮድባንድ አገልግሎት ማግኘት እንዲችሉ ቅድሚያ ሰጥቶ የጥገና ሥራ እየሰራ መሆኑን ገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Ethiopia

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት ከተደረገው 5,147 የኮቪድ-19 የላብራቶሪ ምርመራ 656 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ተረጋገጠ።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የ8 ሰዎች ሞት ሲመዘገብ ፤ 137 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

ኮቪድ-19 ወረርሽኝ በኢትዮጵያ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ 142,994 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ ከነዚህ መካከል ፣2,156 ሰዎች ሞተዋል፤ 125,756 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

አሁን ላይ 225 ሰዎች በፀና ታመው በህክምና ክትትል ላይ ይገኛሉ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
እነ አቶ ጃዋር መሃመድ ለምንድነው የረሃብ አድማ እያደረጉ የሚገኙት ?
የጤናቸው በሁኔታ ላይ ይገኛል ?
የተካሄዱት ሰልፎች ጉዳይ ?

* ዘግየት ብሎ ከ Oromo Prisoners Defense Team ባገኘነው ሪፖርት ላለፉት 12 ቀናት በረሃብ አድማ ላይ ከሚገኙት መካከል አቶ ሸምሰዲን ጠሃ በአድማው በመዳከሙ ምክንያት ከምሽቱ 3:00 ላይ ከቃሊቲ እስር ቤት ወደ ሆስፒታል በአንቡላንስ ተወስዷል። በአጠቃላይ አድማውን እያደረጉ ያሉት 20 ሲሆኑ ሌሎችም ያሉበት ሁኔታ እጅግ በጣም አሳሳቢ መሆኑ ተገልጿል።

https://telegra.ph/TikvahFamily-02-08-2

@tikvahethiopia
ከአዲስ አበባ ወደ አማራ ክልል በመጓዝ ላይ የነበረ ተሳቢ መኪና ደጀን አካባቢ ተንሸራቶ በመውደቁ የትራንስፓርት መጉላላት መፍጠሩን የደጀን ከተማ አስተዳደር አስታወቀ !

ከአዲስ አበባ ወደ አማራ ክልል በመጓዝ ላይ የነበረው ተሳቢ መኪና ከደጀን ወጣ ብሎ በሚገኝ ደምበዛ በተባለ ስፍራ ከምሽቱ አንድ (1) ሰዓት ላይ ባጋጠመው መንሸራተት መንገድ ተዘግቷል።

በዚህ ምክንያት ወደ አዲስ አበባም ሆነ ወደ ባህርዳር ትራንፖርት መስተጓጎሉን ጉዳዩን በተመለከተ የደጀን ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አበጀ አላምረው ተናግረዋል።

አቶ አበጀ ፥ "የጭነት ተሽከርካሪ መኪናው የግንባታ ፌሮ ጭኖ በመጓዝ ላይ እንዳለ ተንሸራቶ በመውደቁ መንገድ ዘግቷል፤ በዚህም የትራንስፖርት መጉላላትን ፈጥሯል። መኪናው ከደጀን ከተማ በግምት 7 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ "ደምበዛ" በተባለ ስፍራ ሲደርስ ነው ክስተቱ የተፈጠረው" ብለዋል።

ያጋጠመውን ችግር ለመፍታት የክሬን አቅርቦት ባለመኖሩ ሎደር መላኩን ከንቲባው ገልጸዋል።

ምንጭ፦ የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
አንበጣ መንጋ በኮንሶ ዞን ተከሰተ።

የበረሃ አንበጣ መንጋው በቦረና ዞን ቴልተሌ ወረዳ ወደ ካራት ዙሪያ ወረዳ አባሮባ ቀበሌ በኮታራ ተራራ በኩል አድርጎ ወደ ኮንሶ ዞን መግባቱን የአከባቢ ነዋሪዎች ጠቁመዋል።

በአሁኑ ሰዓት በዙሪያ ወረዳው በመጨሎና ጃርሶ ቀበሌ ሰገን ሳዋቴ እርሻዎች አካባቢ ማደሩን የካራት ዙሪያ ወረዳ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ገሠሠ ኦላታ አስረድተዋል።

የጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ገሠሠ ኦላታ የሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላት ሁሉ የበረሃ አንበጣን በመከላከል ረገድ በትኩረት ልሰሩ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

በኮንሶ ዞን የካራት ዙሪያ ወረዳ የበረሃ አንበጣ የመከላከል ቅድመ ዝግጅት ተጠናክሮ እንዲቀጥል የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪና ት/ቤቶች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ በዩ ጋላሌ ገልፀዋል።

ህብረተሰቡ የአንበጣ መንጋ በመከላከል እንዲሳተፍ ጥሪ መቅረቡን ከኮ/ዞ/መ/ኮ/ጉ/መምሪያ የደረሰን መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ከያቤሎ ወደ ኮንሶ መስመር ...

ይህ የምትመለከቱት ቪድዮ ትላንት የካቲት 1 ቀን 2013 ዓ/ም አንድ የቤተሰባችን አባል ለስራ ጉዳይ በተጓዝንበት ከያቤሎ ወደ ኮንሶ መስመር በሚወስደው መንገድ ላይ የቀረፀው ነው።

ችግሩ ሳይባባስ እንዲሁም ጉዳት ሳያደርስ የሚመለከተው አካል ሁሉ አውቆት እርምጃ እንዲወስድ / መፍትሄ እንዲፈልግ ጥሪ መልዕክት ተላልፏል።

Video : 45 MB (WiFi)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
እሳት አደጋ በደብረ ማርቆስ ፦

በደብረ ማርቆስ ከተማ የእሳት ቃጠሎ ደርሶ በህብረተሰቡና በወጣቶች ተሳትፎ በቁጥጥር ስር ሊውል እንደቻለ ከደብረ ማርቆስ ከ/አስተዳደር ፖሊስ ጽ/ቤት ሰምተናል።

ዛሬ ከጥዋቱ በግምት 12:40 በሚሆንበት ግዜ ቀበሌ ዐ1 ልዩ ቦታው ከቄራ በተነሣ እሳት የንብረት ውድመት ተከስቷል።

ምንያህል ጉዳት እንደደረሰ እና የእሳት አደጋውን መንስኤ ለማወቅ ፖሊስ በማጣራት ላይ ይገኛል።

እሳቱን ለማጥፋት "ድሪባ ደፈርሻ መንገድ ስራ ድርጅት" የውሀ ቦቲ በመተባበሩ ለእሳቱ መጥፋት ትልቅ አስተዋጽኦ ማበርከቱን የከተማው ፖሊስ ፅ/ቤት አሳውቋል።

የከተማው ማህበረሰብ እና ወጣቶችም እሳቱ በደሌላ ሱቆች እና ወደ መነሀሪያ እንዲይዛመት በቁጥጥር ስር እንዲውል ከፍተኛ አስተዋጽ ማበርከታቸው ተገልጿል።

በአሁኑ ሰአት የእሳት አደጋውን ሙሉ ለሙሉ በቁጥጥር ስር ውሏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia