TIKVAH-ETHIOPIA
በእስር ላይ የሚገኙት ፖለቲከኞች እና እየተካሄደ የሚገኘው የትዊተር ዘመቻ ! አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ ጀዋር መሀመድ፣ አቶ ሀምዛ ቦረና እና ሌሎችም እስረኞች የረሀብ አድማ ከጀመሩ ዛሬ 6ተኛ ቀናቸውን ይዘዋል። ይህን ተከትሎ ዛሬ ከምሽቱ 2:00 ሰአት ጀምሮ እስከ ምሽቱ 5:00 ሰአት የሚቆይ የትዊተር የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ እየተካሄደ ነው። የዘመቻው እየተካሄደ ያለው #OromoYellowMovement…
በረሃብ አድማ ላይ የሚገኙ እስረኞች ሁኔታ ፦
ኢሰመኮ በእነአቶ ጃዋር መሐመድ መዝገብ የተከሰሱ እስረኞች እና ሌሎች እስረኞችን ሁኔታ መመልከቱን በዛሬው መግለጫ አሳውቋል።
ኮሚሽኑ ጥር 25 በቃሊቲ ማረሚያ ቤት እና በቂሊንጦ ጊዜያዊ ማቆያ በመገኘት እስረኞችን የጎበኘ ሲሆን፣ ከእነ አቶ ጃዋር መሐመድ በተጨማሪም፣ የኮሎኔል ገመቹ አያና እና የአቶ ጥላሁን ያሚ አያያዝ ላይ ክትትል ማድረጉን ገልጿል።
በክትትሉም ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት እና ከቂሊንጦ ጊዜያዊ ማቆያ ቤት አስተዳደሮች እንዲሁም ከእስረኞቹ ተነጋግሪያለሁ ብሏል።
ኢሰመኮ ጥር 25 በቃሊቲ ማረሚያ ቤት በተገኘበት ወቅት፣ አቶ ጃዋር መሐመድ፣ አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ ሀምዛ አዳነ (ቦረና) እና አቶ ሸምሰዲን ጣሃ ከጥር 19 ጀምሮ በረሃብ አድማ ላይ ነበሩ።
የረሃብ አድማው ዓላማ “መንግስት በሕዝብ እና በፓርቲያቸው ላይ እያደረሰ ያለውን አፈና እና የመብት ጥሰት ለመቃወም፣የኮሎኔል ገመቹ አያናን አላግባብ የሆነ አያያዝ እና እንግልት እንዲቆም ለመጠየቅ እና የችሎት ሂደታቸውን ለመከታተል ወደ ፍርድ ቤት በሚመጡ እና እነሱን ለመጠየቅ ወደ ማረሚያ ቤት በሚመጡ ሰዎች ላይ የሚፈጸም እስር እና ወከባ እንዲቆም ለመጠየቅ” መሆኑን እስረኞቹ ለኢሰመኮ ገልጸዋል።
ቃሊቲ ማረሚያ ቤት አስተዳደር በበኩሉ ለረሃብ አድማው በምክንያትነት የተጠቀሱ አብዛኛዎቹ ጉዳዮች ማረሚያ ቤቱን የማይመለከቱ መሆኑንና እስረኞችን ለመጠየቅ የሚመጡ ሰዎች ላይ ወከባ እንደማይፈጽም ገልጿል።
አስተዳደሩ አክሎም የረሃብ አድማው በእስረኞቹ ላይ የከፋ ጉዳት እንዳያስከትል፣ በተለይ ከመካከላቸው ሁለቱ የጤና ችግር ስላለባቸው በቋሚነት መድኃኒት የሚወስዱ በመሆኑ ቅርብ የህክምና ክትትል እንደሚደረግላቸው አስረድቷል።
*ተጨማሪ ከላይ ከተያያዘው መግለጫ ያንብቡ።
@tikvahethiopia

በኤርትራ የአሜሪካ ኤምባሲ ያጋራው መረጃ ፦ በኤርትራ የአሜሪካ ኤምባሲ ፥ ዩናይትድ ስቴትስ ‹‹በትግራይ ክልል የኤርትራ ወታደሮች እንዳሉ የሚያሳይ ተጨባጭ መረጃ አለኝ፤ የሰብኣዊ መብት ጥሰትንም እየፈፀሙ ነው›› በማለት በአስቸኳይ እንዲወጡ መጠየቋን የሚገልፅ በJan 28 በአሶሼትድ ፕሬስን ላይ የወጣ መረጃን ዛሬ ጥዋት በፌስቡክ ገፁ አጋርቷል። ዩናይትድ ስቴትስ ፥ በክልሉ የተፈፀሙ ፆታዊ ጥቃት፣…
የኤርትራ ምላሽ ፦
የኤርትራ መንግስት ዛሬ በኤርትራ የአሜሪካ ኤምባሲ ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ የተጋራውን መግለጫ እንደማይቀበለው ገለፀ።
የኤርትራ የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገ/መስቀል ዛሬ በአሜሪካ ኤምባሲ የፌስቡክ ገፅ ላይ የወጣውን መግለጫና ሀገሪቱን በሚመለከት እየተሰራጨ ያለውን ሀሰተኛ እና ግምታዊ ውንጀላ ሀገራቸው እንደማትቀበለው ገልፀዋል።
ኤርትራ በትግራይ ውሥጥ ወታደሮቿ እንደሚገኙ/በትግራይ ክልል ጦርነትም እንደተሳተፈች በተደጋጋሚ በተለያየ መልኩ ቢገለፅም የሀገሪቱ መንግስት ጉዳዩን እያስተባበለ ይገኛል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

#Ethiopia
የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :
• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 5,065
• በበሽታው የተያዙ - 726
• ህይወታቸው ያለፈ - 10
• ከበሽታው ያገገሙ - 999
አጠቃላይ 140,883 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ2,136 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ 125,241 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።
225 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

#Tigray
ከትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዶ/ር ኣርኣያ ይርጋ የተገኘ መረጃ ፦
- ከጦርነቱ በፊት በትግራይ 264 የሚጠጉ የጤና ተቋማት ነበሩ (24 የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል፣ 14 አጠቃላይ ሆስፒታል፣ 2 ሪፈራል ሆስፒታል እና 224 ጤና ጣቢያዎች) የክልሉ ጤና ቢሮ ሊደርስባቸው የቻለው 19 ሆስፒታሎች ሲሆን 16ቱ ሙሉ በሙሉ ስራ እየሰሩ ነው። 4ቱ ምንም አይነት አገልግሎት የሚሰጡበት ሁኔታ ላይ አይደሉም፤ ሆስፒታሎቹ ጉዳት የደረሰባቸው ወይም የፀጥታ ስጋት ያለበት አካባቢ ያሉ ናቸው (ፍረወይኒ ሆስፒታል፣ ሃውዜን ሆስፒታል፣ እንጥጮ ሆስፒታል፣ ኣብይ ኣዲ ሆስፒታል)
- በትግራይ ክልል በነበረው ጦርነት ከፍተኛ ውድመት የደረሰባቸው ሆስፒታሎች አሉ። የወደሙ ሆስፒታሎች እንደአዲስ ተሰርተው አገልግሎት እንዲሰጡ እየተሰራ ነው።
- ከፍተኛ ውድመት ከደረሰባቸው ሆስፒታሎች መካከል ውቅሮ ሆስፒታል ፣ ኣብይ ኣዲ ሆስፒታል ፣ ኣድዋ ሆስፒታል ፣ ሰለክለካ ሆስፒታል (ሽረ አካባቢ) ይገኙበታል። እነዚህ ሆስፒታሎች በፍጥነት (በአንድ ሳምንት) ተጠግነው ወደ ስራ እንዲገቡ ለማድረግ ከጤና ሚኒስቴር ጋር ጥረት እየተደረገ ነው።
- በክልል ትግራይ 20 ሺህ የጤና ባለሞያዎች ከጦርነቱ በፊት ስራ ላይ ነበሩ፤ በጦርነቱ ምክንያት 1,024 ተፈናቅለው ቀያቸውን ለቀዋል፣ 3,066 ስራ ላይ ናቸው፤ የተቀሩት ሪፖርት ያላደረጉ (ወደ ሱዳን የተሰደዱ፣ ወደ መሀል ሀገር፣ አ/አ የሄዱ) ባለሞያዎች ናቸው።
- መቐለ ውስጥ ኣይደር እና መቐለ አጠቃላይ ሆስፒታል 24 ሰዓት አገልግሎት እየሰጡ ነው። ከመቐለ ውጭ ዓዲግራት ፣ መሆኒ ፣ ማይጨው እና ኣዲጉደም ፣ ሽረ ሆስፒታሎች 24 ሰዓት ለ7 ቀን አገልግሎት እየሰጡ ነው።

የቀጠለ ...
ከዶ/ር ኣርኣያ ይርጋ (የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ) ፦
- ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ በመቐለ የሚገኙ 9 ጤና ጣቢያዎች ባለሞያዎቻቸው ደህንነታቸው ተጠብቆ አሁን እየሰጡት ካለው የ12 ሰት አገልግሎት ወደ 24 ሰዓት ለማሳደግ እየተሰራ ነው።
- በትግራይ ከጦርነት በኃላ ባጋጠመው የመድሃኒት እጥረት እና የጤና አገልግሎት ጉዳት ዓለም አቀፍ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የመድሃኒት አቅርቦት እገዛ በማድረግ አስተዋፅኦ እያደረጉ ነው። በተጨማሪ እነዚህ ተቋማት የመኪና ክራይ በመፈፀም፣ ተንቀሳቃሽ ክሊኒክ በማቋቋም ፣ የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ በማቅረብ እያገዙ ነው።
- የመድሃኒት እጥረት ለመቅረፍ ቢሮው ከፌዴራል ጤና ቢሮ ጋር በመሆን 55 ለሚሆኑ የጤና ተቋማት የመድሃኒት፣ ክትባት፣ የኤች አይቪ እና የቲቢ መድሃኒቶች ስርጭት አደርጓል። ከዚህ ቀደም ጤና ተቋማት የመድሃኒት ወጪን በውስጣዊ ገቢያቸው (በራሳቸው በጀት) ይሸፍኑ ነበር፤ ከጦርነቱ በኃላ ባጋጠመው ችግር ሙሉ በሙሉ በኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር ወጪው እንዲሸፈን ተደርጓል።
- በትግራይ ከጦርነቱ በፊት 269 አምቡላንሶች ነበሩ፤ ጦርነቱ ካለቀ በኃላ ሪፖርት የተደረጉት 24 ብቻ ናቸው። በሂደት ሹፌሮች ቤታቸው ያስቀመጡትን አምጥተዋል፣ የተወሰኑ አምቡላንሶች በተሽከርካሪ እጥረት መከላከያው ጋር ቆይተው የተመለሱ አሉ ፣ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ከክልሎች ጋር ባደረገው ውይይት ክልሎቹ ወደ 60 አምቡላንስ በሥጦታ መልክ ለትግራይ ለመስጠት ቃልገብተዋል ፤ እስካሁን 60ዎቹ አምቡላንሶች ወደመቐለ አልደረሱም በሂደት ላይ ነው።
- የመቐለ እና አክሱም የደም ባንኮች ስራ ላይ ይገኛሉ። ኣክሱም አካባቢ መብራት ባለመኖሩ ችግሮች ነበሩበት። መቐለ እና አካባቢው ያለውን ህዝብ በማስተባበር የደም ማሰባሰብ ዘመቻ ለማድረግ እቅድ ተይዟል።

የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ይገኛሉ ፦
#WolaitaSodoUniversity
ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ እለተ ዛሬ 29 ቀን 2013 ዓ.ም በመደበኛ እና በተከታታይ የትምህርት መርሃ-ግብር በቅድመ ምረቃ እና በድህረ ምረቃ ያሰለጠናቸውን 5,310 ተማሪዎችን እያስመረቀ ይገኛል።
#WoldiaUniversity
የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ላለፋት ዓመታት በተለያዩ ትምህርት መስኮች ሲያሰለጥናቸው የቆዩ ተማሪዎቹን ዛሬ በሼህ ሙሃመድ ሁሴን አሊ ኣላሙዲን ስታዲየም እያስመረቀ ይገኛል።
በመደበኛው፣ በተከታታይ እና በክረምት መርሃግብር ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ 2785 የሚሆኑ እጩ ተመራቂ ተማሪዎችን ነው እያስመረቀ የሚገኘው።
ከጠቅላላ ተመራቂዎች ውስጥም 926 ሴቶች ናቸው።
#BahirdarUniversity
ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መድኮች ሲያስተምራቸው የቆያቸውን 5,117 ተማሪዎችን በፔዳ ካምፓስ በማስመረቅ ላይ ይገኛል።
4,203 የሚሆኑት የመጀመሪያ ዲግሪ (ቅድመ ምረቃ ፕሮግራም) የተማሩ ናችው። 759 በሁለተኛ ድግሪይ የተማሩ፣10 የፒኤችዲ ተመራቂዎች ይገኙበታል።
በሌላ በኩል በህክምና ስፔሻሊቲ የተመረቁ 40 የሚሆኑ ሰልጣኞች ዛሬ እየተመረቁ ነው።
ከአጠቃላይ ተመራቂዎቹ ውስጥ 1,623 የሚሆኑት ሴቶች ናቸው።
#DebarkUniversity
ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች በመጀመሪያ ዲግሪ ያሰለጠናቸውን 773 ተማሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ በማስመረቅ ላይ ይገኛል፡፡
#MizanTepiUniversity
ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ከ2 ሺህ በላይ ተማሪዎችን እያስመረቀ ይገኛል።
በሌላ በኩል፦
ሂልኮ የኮምፒዩተር ሳይንስ እና ቴክኖሎጅ ኮሌጅ ነገ ጥር 29/2013 ዓ/ም ተማሪዎቹን ያስመርቃል።

የተማሪዎችን የትምህርት ማስረጃ ትክክለኝነት የሚያረጋግጥ ቴክኖሎጂ ተግባራዊ ሊደረግ ነው !
በኢትዮጵያ ከመንግስት እና ከግል ትምህርት ተቋማት የተመረቁ ተማሪዎችን ማስረጃ ትክክለኛነት ማረጋገጥ የሚያስችል ቴክኖሎጂ ተግባራዊ ሊደረግ መሆኑ የከፍተኛ ትምህርት አግባብነት እና ጥራት ኤጀንሲ ዋና ዳሬክተር ዶ/ር አንዱዓለም አድማሴ ተናገሩ።
ዶ/ር አንዱዓለም ይህን ያሳወቁት ከፋና ብሮድካስቲንግ ጋር በነበራቸው ቆይታ ነው።
አሰራሩ ተቋማት እና ግለሰቦች ሰራተኞችን ለመቅጠር በሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ እንዳይታለሉ ይረዳል ብለዋል ዶ/ር አንዱዓለም።
በኢትዮጵያ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን ሀሰተኛ እና የተሳሳተ የትምህርት ማስረጃን ትክክለኛነቱን ለማረጋገጥ የሚጠይቀው ሂደት ረጅም በመሆኑ አድካሚ ሆኖ ቆይቷል።
አሁን ግን ከተለያዩ ተቋማት ጋር ጥምረት በመፍጠር በቴክኖሎጂ የተደገፈ የተደራጀ መረጃ ለሚፈልግ አካል ለመሰጠት ስራዎች መጠናቀቃቸውን አሰታውቀዋል።
ስራውን ለማስጀመር የኤጀንሲው ሰራተኞች በቂ ስልጠና መውሰዳቸውን ገልፀዋል፡፡
የህግ ተጠያቂነት እንዲኖረውም ከጠቅላይ አቃቢ ህግ ፣ ከፌዴራል ፖሊስ ፣ ከፀረ ሙስና ኮሚሽን ፣ ከጠቅላይ ፍርድ ቤት እና ከቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ሚኒስቴር እንዲሁም ከ ብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት ኤጀነሲ ጋር በጋራ እየተሰራ ይገኛል ነው ያሉት፡፡
ስራዎቹ ተጠናቀው በቅርቡ ተግባራዊ እንደሚሆኑም ገልፀዋል፡፡
ምንጭ፦ ኤፍ ቢ ሲ

#Ethiopia ኢትዮጵያ በሳዑዲ አረቢያ በችግር ላይ የሚገኙ ዜጎቿን ማስወጣቷን ቀጥላለች። በዛሬው ዕለት 336 ኢትዮጵያዊያን ከሳኡዲ አረቢያ ሪያድ ከተማ ወደ አገራቸው እንዲሸኙ መደረጉን በሪያድ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጀ ይገልጻል። ዛሬ ወደ አገር የተሸኙት ዜጎች ሁሉም ወንዶች ናቸው። @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Update
ትላንት ሦስት መቶ ሰላሳ ስድስት (336) ኢትዮጵያዊያን ከሳዑዲ አረብያ ሪያድ ከተማ ወደ አገራቸው መመለሳቸውን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳውቋል።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ትላንት ሦስት መቶ ሰላሳ ስድስት (336) ኢትዮጵያዊያን ከሳዑዲ አረብያ ሪያድ ከተማ ወደ አገራቸው መመለሳቸውን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳውቋል።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የፊቤላ የምግብ ዘይት ፋብሪካ እሁድ ሊመረቅ ነው። በምዕራብ ጎጃም ዞን "ቡሬ ከተማ" በቀን ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሊትር በላይ የተጣራ የምግብ ዘይት ማምረት የሚችል ፋብሪካ በመጭው እሁድ ተመርቆ ምርቱን ሊያቀርብ ነው። ፋብሪካው የዘይት ምርቱን፥ “ቅድሚያ ለሀገር ውስጥ ገበያ በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ የማረጋጋት ስራ ይሰራል” ተብሏል። ፊቤላ ኢንዱስትሪያል ሃ/ተ/የግል ድርጅት ለኢዜአ እዳሳወቀው ፥…
#Update
ዛሬ ባለሃብቱ አቶ በላይነህ ክንዴ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል ፦
የበላይነህ ክንዴ ኮርፖሬት የቦርድ ሰብሳቢ አቶ በላይነህ ክንዴ ዛሬ እንደተናገሩት የኮርፖሬቱ አካል የሆነውና በአማራ ክልል ቡሬ ከተማ የተገነባው ፊቤላ ኢንዱትሪል ኮምፕሌክስ የግንባታ ስራው ተጠናቆ በነገው ዕለት ይመረቃል፡፡
በዋናነት የምግብ ዘይት የሚያመርተው ይህ ፋብሪካ ደረቅ እና ፈሳሽ ሳሙና እንዲሁም ማርጋሪን ያመርታል፡፡
በ30 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው ይህ ፋሪብካ 4 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ወጪ የተደረገበት ሲሆን ፤ ሙሉ ለሙሉ ወደስራ ሲገባ በቀን 1500 ቶን ዘይት በማምረት የሀገሪቱን 60 በመቶ የምግብ ዘይት ፍላጎትን እንደሚሸፍን ተናግረዋል፡፡
ፋብሪካው ሀገሪቱ ለምግብ ዘይት ግዢ የምታወጣውን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ በማስቀረት የላቀ ጠቀሜታ እንደሚኖረውም አቶ በላይነህ ጠቁመዋል፡፡
ፋብሪካው በዘርፉ የቴክኖሎጂ ደረጃ የደረሰበትን ዘመናዊ መሳሪያዎች እንደሚጠቀም የጠቆሙት ሰብሳቢው ፤ ጥራት ያለው ዘይት በማምረትም የህብረተሰቡን የጤና ችግሮች የጠበቀ ምርት ያመርታል ብለዋል።
አቶ በላይነህ ክንዴ አሁን ላይ ከ3,000 በላይ ሰራተኞች በስራ ላይ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡
ፋብሪካው ምርቱን በሁሉም የሀሪቱ ክፍሎች በተመጣጣኝ ዋጋ እንደሚያቀርብ የጠቅሱት አቶ በላይነህ ፤ ዘይቱ ከሰኞ የካቲት 1 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ለገበያ ይቀርባል ብለዋል፡፡ (ኢ.ፕ.ድ)

"...ትምህርት ቤቶች ዳግም ሊዘጉ የሚችሉበት እድል አለ" - የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ
በትምህርት ቤቶች የኮሮና ቫይረስ መከላከያ መንገዶች በአግባቡ ተግባራዊ ባለመደረጋቸው ትምህርት ቤቶች ዳግም ሊዘጉ የሚችሉበት እድል መኖሩን የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።
ትምህርት ቢሮው ይህን ያሳወቀው በባህር ዳር ከተማ "እንድናገለግሎ ማስክዎን ያድርጉ" የሚል ንቅናቄ በተጀመረበት ወቅት ነው።
በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ተዘግተው የነበሩ ትምህርት ቤቶች ተገቢው ጥንቃቄ እየተደረገ ትምህርት እንዲቀጠሎ ተደርጎ መከፈታቸው ይታወሳል።
ምንም እንኳን ትምህርት ቤቶች ቢከፈቱም በኮሮና ቫይረስ መከላከያ ላይ ያለው አተገባበር በታሰበው መልኩ እየሄደ አይደለም ተብሏል።
ተማሪዎች ትምህርት ቤት ዳግም የተከፈተ ሰሞን ጥሩ ጥንቃቄ ያደረጉ የነበር ሲሆን አሁን ላይ ትኩረት እያጡ መከላከያውም እየተረሳ መሆኑ ተገልጿል።
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ሙላው አበበ ፥ አሁን እየታየ ያለው መዘናጋት እና ግዴለሽነቱ ካልቆመ ትምህርት ቤቶች ተመልሰው ሊዘጉ እንደሚችሉ አሳስበዋል።
ምክትል ቢሮ ኃላፊው አክለው ፥ በክልሉ ውስጥ ያሉ ትምህርት ቤቶች የኮሮና ቫይረስ መከላከያን ተግባራዊ በማድረግ ሊመጣ እና ሊያጋጥም ከሚችለው አደጋ እራስን መጠበቅ እንደሚገባ ተናግረዋል።

#EthiopianAirlines
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አፍሪካ አህጉር የኮቪድ-19 ክትባት ማጓጓዝ ጀመረ።
በኮቪድ-19 ወረርሺኝ ወቅት የኮቪድ-19 ቁሳቁስን ሲያጓጉዝ የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አሁን ደግሞ የቫይረሱን ክትባት ማጓጓዝ መጀመሩን በፌስቡክ ገፁ አሳውቋል።
በሌላ የኢትዮጵያ አየር መንገድ መረጃ ፦
በአንዳንድ የሀገር ውስጥ መዳረሻዎች ባጋጠመው አስቸጋሪ የአየር ጠባይ ምክንያት ዛሬ ወደ ላልይበላ፣ ጎንደር እና ባህር ዳር ይደረጉ የነበሩ በረራዎች እንደተስተጓጎለበት ገልጿል።
አየር መንገዱ የአየር ሁኔታው መሻሻሉን የሚገልጽ መረጃ ከብሄራዊ ሚቲዎሮሎጂ አገልግሎት ሲደርሰው በረራውን እንደሚቀጥል ገልጿል።
Via Ethiopian Airlines