ኢሶዴፓ ራሱን ከመድረክ አገለለ።
በፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ የሚመራው የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኢሶዴፓ) እራሱን ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) በማግለል በቀጣዩ 6ኛው ብሔራዊ ምርጫ በተናጠል እንደሚወዳደር አስታውቋል።
የፓርቲው ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ እንዳረጋገጡት በተለይ ለፓርቲያቸው ከመድረክ ለመውጣት መወሰን ከኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ (ኦፌኮ) ጋር እየተፈጠረ የመጣው ልዩነት ዋነኛው ምክኒያት ነው ብለዋል።
የኦፌኮ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ሙላቱ ገመቹ በበኩላቸው ኢሶዴፓ በራሱ ፈቃድ ከመድረክ እየተገለለ መምጣቱ እውን ቢሆንም ፊቺው ግን ገና በይፋ በጠቅላላ ጉባኤ ያልተደመደመ ነው ብለዋል።
ኦፌኮ በመድረክ ስር በተለመደው ሁኔታ ይቀጥላል ያሉት አቶ ሙላቱ የተለያዩ ፓርቲዎች መድረክን በጥምረት ለመቀላቀል ጥያቄ እያቀረቡም ይገኛሉ ነው ያሉት።
ምንጭ፦ ዶቼ ቨለ
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

ዓለም አቀፍ የኮቪድ-19 ሪፖርት ፦
- በዓለም አቀፍ ደረጃ ባለፉት 24 ሰዓት 601,212 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ሲረጋገጥ ፥ 16,388 ሰዎች በበሽታው ሞተዋል።
- አሜሪካ የ3,908 ዜጎቿን ህይወት በ24 ሰዓታት ውስጥ አፍጥታለች፥ ይህን ተከትሎ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 443,769 ደርሷል።
- በUK ባለፉት 24 ሰዓታት የ1,239 ሰዎች ሞት ሲመዘገብ፤28,680 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
- ብራዚል ባለፉት 24 ሰዓታት 1,439 ዜጎቿን በዚህ አስከፊ ወረርሽኝ አጥታለች፥60301 ዜጎቿም በበሽታው ስለመያዛቸው አረጋግጣለች።
- በጀርመን የሟቾች ቁጥር በእጅግ መጨመር እያሳየ ሲሆን ባለፉት 24 ሰዓት የ862 ሰዎች ሞት ተመዝግቧል።
- ሜክሲኮ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 1,623 ዜጎቿን ስታጣ፥17,944 ዜጎቿን ለቫይረሱ መጋለጣቸውን ሪፖርት አድርጋለች።
- በስፔን ዳግም የኮቪድ-19 ሞቾች ቁጥር እያሻቀበ ይገኛል፤ትላንት የ515 ሰዎች ሞት ሲመዘገብ፤አጠቃላይ በበሽታው የሞቱ ሰዎች 57,806 ደርሰዋል።
- ጣልያን ባለፉት 24 ሰዓት 492 ዜጎቿን በኮቪድ-19 ስታጣ፥14,372 ዜጎቿ በቫይረሱ መያዛቸውን በምርመራ አረጋግጣለች።
- ደቡብ አፍሪካ በባለፉት 24 ሰዓታት የ555 ዜጎቿ ህይወት በአስከፊው ወረርሽኝ ስታጣ፤ 7,150 ዜጎቿ በቫይረሱ ተይዘዋል።
- በመላው አፍሪካ ትላንት 962 ሰዎች ሞተዋል፤ ከነዚህ መካከል 555 ከደ/አፍሪካ፣ 62 ከቱኒዝያ፣ 54 ከግብፅ፣ 17 ከሞሮኮ፣ 30 ከሊብያ፣ 13 ከጋና፣ 17 ከዛምቢያ ፣ 48 ከዝምባዌ፣ 38 ከሱዳን ይገኙበታል።
- በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለው ሪፖርት እንደሚያስረዳን 102,041,120 ሰዎች በቫይረሱ ተጠቅተዋል፥ የ2,201,044 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ 73,882,690 ሰዎች አገግመዋል።
#Purpose #Tikvah

የባልደራስ የሰልፍ ጥሪ እና የፖሊስ ምላሽ ፦
ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ በመጪው እሁድ በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያደርግ ትላንት በሰጠው መግለጫ ገልጿል።
ፓርቲው በእሁዱ ሰልፍ በ4 መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ መንግሥት ላይ ጫና ለመፍጠር አቅጃለሁ ነው ያለው፡፡
የፓርቲውን አመራሮች እስር፣ በአገሪቷ የተከሰተውን ማንነትን መሰረት ያደረገ ግድያ፣ የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ እየፈፀመ ነው የሚለውን የመሬት ወረራ እንዲሁም የሱዳን ኃይል የድንበር ጥሰትን መቃወም ዋነኞቹ አጀንዳዎቼ ናቸው ብሏል፡፡
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በበኩሉ ዛሬ ባሰራጨው መግለጫ ለጥር 23 በአዲስ አበባ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲያካሄድ እውቅና የተሰጠው አካል ያለመኖሩን ገልጿል።
ኮሚሽኑ በዕለቱ እውቅና የተሰጠው ሰልፍ እንዳለ በማስመሰል በማህበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው መረጃም ሀሰት ነው ብሏል።
የአዲስ አበባ ከተማ የከንቲባ ፅ/ቤት አስተዳደር ጉዳዩች ዘርፍ ጥር 18 ቀን 2013 ዓ/ም በቁጥር አ/አከፀ 18 /03/ 128 ለባልደረሳስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ በፃፈው ደብዳቤ ሰልፉ በልዩ ልዩ ምክንያቶች ተቀባይነት እንዳለገኘ ምላሽ የሰጠ ሲሆን ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በግልባጭ አሳውቋል ሲል ገልጿል።
ተቀባይነት ያላገኘ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ የህግ ተጠያቂነትን የሚያስከትል ነው ያለው የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥር 23 በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ እናደርጋለን የሚሉ ሆነ መረጃውን እያሰራጩ የሚገኙ አካላት ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ አሳስቧል፡፡
ይህንን መልዕክት ተላልፈው ሰልፍ ለማድረግ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ አካላት ላይ በህግ አግባብ እርምጃ ለመውሰድ እንደሚገደድም የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስጠንቅቋል።
ምንጭ፦ አ/አ ፖሊስ ኮሚሽን፣ ባልደራስ፣ አሐዱ ቲቪ

"ታይዋን ነጻ አገር ልሁን ካለች የሚከተለው ጦርነት ነው" - ዉ ኪን (የቻይና የመከላከያ ሚኒስትር ቃል አቀባይ)
(በቢቢሲ የቀረበ)
ታይዋን ነጻ አገር ለመሆን አንዳች ሙከራ ካደረገች ጦርነት እንደሚገጥማት ቻይና አስጠነቀቀች።
ከቻይና እንዲህ ጠንከር ያለ የጦርነት ማስጠንቀቂያ ሲመጣ ይህ ከረዥም ጊዜ በኋላ የመጀመርያው ነው።
ማስጠንቀቂያው የመጣው ቤጂንግ የጦር አውሮፕላኖችን ወደ ደሴቲቱ አካባቢ ካስጠጋችና ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን የታይዋን ድንበር አካባቢ ማድረጓ ከተዘገበ ከቀናት በኋላ ነው።
ይህ ብቻ ሳይሆን ታይዋንና አሜሪካ አዲስና ጠንካራ ግንኙነት ለመጀመር ከተነጋገሩ በኋላ ቻይና ይህን ማለቷ አዲስ ስጋት ፈጥሯል።
አዲሱ የባይደን አስተዳደር ባለፈው ሳምንት ከታይዋን ጋር ያለውን ግንኙነት እንደሚያጠናክር ገልፆ ነበር።
ባለፈው ሐሙስ ዋሺንግተን ታይዋንን በመከላከያው ዘርፍ መደገፏን እንደምትቀጥል የሚገልጽ መግለጫ አውጥቷል።
ቻይና ታይዋንን እንዳመጸች አንዲት ግዛቷ አድርጋ ነው የምትመለከታት። ታይዋን ግን ራሷን እንደ አንድ ሉአላዊት አገር ነው የምትመለከተው።
የቻይና የመከላከያ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ዉ ኪን ሐሙስ ዕለት በነበራቸው ጋዜጣዊ መግለጫ ጠንከር ያለ ሐሳብ ሰንዝረዋል።
"ቆፍጠን ብለን መናገር የምንፈልገው ነገር ቢኖር ታይዋኖች በእሳት እንዳይጫወቱ ነው። እሳቱ ይበላቸዋል፤ ታይዋን ነጻ አገር ልሁን ካለች የሚከተለው ጦርነት ነው" ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
ቻይና በታይዋን አቅራቢያ እያደረገች ያለችው ወታደራዊ እንቅስቃሴን "ትክክለኛ አካሄድ ነው፤ ብሔራዊ ሉአላዊነትንና ደኅንነትን ለማስጠበቅ የሚደረግ ነው፤ይቀጥላል" ብለዋል የቻይና መከላከያ ሰራዊት ቃል አቀባይ።
ቀጣዩን ያንብቡ : telegra.ph/BBC-01-29
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopaia

TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE በጅዳ ሹሜሲ የስደተኞች ማቆያ የነበሩ ዜጎች በዛሬው ዕለት ወደ አገር ተመለሱ። ወደ ሳዑዲ አረቢያ ህጋዊ ባልሆኑ መንገዶች ሲገቡ ተይዘው በሳዑዲ የተለያዩ ቦታዎች በሚገኙ የስደተኞች ማቆያ ጣብያ ውስጥ የሚገኙና ላለፉት ወራት ከኮሮና ወረርሽኝ ጋር ተያይዞ ወደ አገር መመለስ ያልቻሉ የነበሩ ዜጎችን ወደ አገር የመመለስ ስራ መጀመሩ ይታወቃል። በዚሁ መሰረት በጅዳ "ሹሜሲ" የህገወጥ ስደተኞች…
#Update
ተጨማሪ 282 ዜጎች ከሳዑዲ አረቢያ ወደ አገራቸው ተመለሱ።
ትላንት ሁለት መቶ ሰማኒያ ሁለት ኢትዮጵያዊያን ከሳዑዲአረቢያ ወደ አገራቸው ተመልሰዋል።
ወደ አገር የተመለሱት ዜጎች ሁሉም ወንዶች ናቸው።
Via Ministry Of Foreign Affairs Ethiopia
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ተጨማሪ 282 ዜጎች ከሳዑዲ አረቢያ ወደ አገራቸው ተመለሱ።
ትላንት ሁለት መቶ ሰማኒያ ሁለት ኢትዮጵያዊያን ከሳዑዲአረቢያ ወደ አገራቸው ተመልሰዋል።
ወደ አገር የተመለሱት ዜጎች ሁሉም ወንዶች ናቸው።
Via Ministry Of Foreign Affairs Ethiopia
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ደም እንለግስ ህይወት እናድን !
የፊታችን እሁድ ጥር 23 በብሄራዊ የደም ባንክ (ስታዲየም) የደም ልገሳ እንደሚደረገ አቡጊዳ ሮታራክት ክለብ ለቲክቫህ አሳውቋል።
ይህ የደም ልገሳ ለ51ኛ ዙር መሆኑ ተገልጾልናል።
'ታላቅ ስጦታ የሆነውን ደም እንለግስ፥ ህይወት እናድን' የሚሉት አዘጋጆቹ በአ/አ ከተማ ነዋሪ የሆናቸው የቲክቫህ አባላት ደም በመለገስ የሰው ህይወት ታድኑ ዘንድ ጥሪ አውርበውላችኃል።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT

#FaceBook
ፌስቡክ ተጠቃሚዎቹ የተለያዩ ማኅበራዊና ፓለቲካዊ ቡድኖችን እንዲቀላቀሉ የሚጠቁም መልዕክት ማስተላለፍ እንደሚያቆም አስታወቀ።
ይህ ውሳኔ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች በገጻቸው ላይ የሚያዩትን ፓለቲካ ነክ ይዘት ከመቀነስ ጋር የተያያዘ ነው።
የአሜሪካ ምርጫ ሲካሄድ ፌስቡክ ለሳምንታት ያህል ፓለቲካዊ መልዕክቶችን ቀንሶ ነበር። አሁን ይህንን አሠራር በሌሎች አገራትም እንደሚተገብር ተገልጿል።
የፌስቡክ መስራች ማርክ ዙከርበርግ "ሰዎች ፓለቲካና ግጭት መመልከት አይፈልጉም" ሲል ተናግሯል።
ማርክ ዙከርበርግ እንደሚለውም፤ ሰዎች ፌስቡክ ላይ የሚቀላቀሏቸው ቡድኖች "ጤናማና ቀና" እንዲሆኑ ይፈለጋል።
"ከፖሊሲያችን ጋር ባይጻረሩም ሰዎች እንዳይገቡ የምንፈልጋቸው ቡድኖች አሉ" ብሏል።
ማኅበራዊ እንዲሁም ፓለቲካዊ ቡድኖችን የፌስቡክ ተጠቃሚዎች እንዲቀላቀሉ የሚላኩ ማስታወቂያዎችን ረዘም ላለ ጊዜ እንዳገዱም ገልጿል።
"ውጥረትን ለማርገብና በማኅበረሰቡ ዘንድ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ውይይት እንዲኖር የጀመርነው ሥራ አንድ አካል ነው" ሲል መስራቹ መናገሩን ቢቢሲ በድረገፁ አስነብቧል።

የኦንላይን የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት አሰራር ስርአት (OTRLS) ነገ ይፋ ሊደረግ ነው።
የኢፌዴሪ ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አዲስ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት መስጫ የአሰራር ስርአት አልምቶ ወደ ስራ ለመግባት ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አሳውቋል።
ሚኒስቴሩ ነገ በስካይ ላይት ሆቴል የቀጥታ የበየነ መረብ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት አሰጣጥ ስርአቱን (online trade registration & licensing system) ያስመርቃል።
ስርዓቱ የንግዱ ማህበረሰብ እንግልት የሚቀንስና ሀገሪቱን በአለም አቀፍ ደረጃ በንግድ ስራ ፈቃድ አመቺነት (ease of doing business) ያላትን ደረጃ በማሻሻል ፣ በንግድ ስራ መጀመር (staring business) ሂደት ፣ በገጽታ ግንባታ እና በኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ተመራጭ በማድረግ እንዲሁም የዘርፉን ሀገራዊ የኢኮኖሚ አበርክቶ ከፍ በማድረግ አስተዋፅኦው የጎላ ነው ብሏል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ።
ከዚህ ጋር በተያያዘ ለዘርፉ አጋር አካላት፣ ለንግዱ ማህበረሰብ ተወካዮችና ለሚዲያ ባሉያዎች የቅድመ ምረቃ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ትላንት ሰጥቷል፡፡
የቀጥታ የንግድ ስራ ፈቃድ አገልግሎት አሰጣጥ ስርዓት ላለፉት 2 አመታት በሙከራ ትግበራ ላይ እንደነበር የኢፌዴሪ ንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገልጿል።

በትራፊክ አደጋ የ11 ሰዎች ህይወት አለፈ።
በሰበታ ከተማ በዛሬው እለት በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ11 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለፀ።
የትራፊክ አደጋው በዛሬው እለት ከቀኑ 8 ሰዓት አካባቢ መድረሱን የሰበታ ከተማ አስተዳደር አሳውቋል።
አደጋው በሰበታ ከተማ ዲማ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በተለምዶ ሀይሩፍ ተብሎ የሚጠራ የህዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ ተሽከርካሪ ከሲኖ ትራክ ጋር በመጋጨቱ የተፈጠረ ነው።
በአደጋውም የ11 ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ ፤ 7 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ የመቁሰል አደጋ መድረሱን የሰበታ ከተማ ጤና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብዱራዛቅ አህመድ መናገራቸውን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

#ArbaMinch
በነጭ ሳር ብሄራዊ ፓርክ ዙሪያ በአርባምንጭ ከተማ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው።
በብሄራዊ ፓርኩ ችግሮች እንዲሁም መፍትሄዎች ዙሪያ በቅንጅት መስራት የሚያስችል ስምምነት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።
የፌዴራል የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን ባዘጋጀው በዚሁ መድረክ ላይ በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ተገኝተዋል።
በመድረኩ ከህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ፣ የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠ/ሚ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ፣ በኦሮሚያ ክልል በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ የማኅበራዊ ክላስተር አስተባባሪ አቶ አዲሱ አረጋ ፣ በምክትል ርዕስ መስተዳድር ማዕረግ የደቡብ ክልል ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይለማሪያም ተስፋዬ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉበት እንደሚገኙ ኢዜአ ዘግቧል፡፡
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

Response to the Ethiopian Refugees UNFPA Sudan.pdf
4.3 MB
በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል የተካሄደውን ጦርነት ሸሽተው ወደ ሱዳን የተሰደዱ ዜጎችን የሚመለከት ወቅታዊ ዝርዝር ሪፖርት በ #UNFPA
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
ፊሊፖ ግራንዴ ኢትዮጵያ ይገኛሉ።
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ (UNHCR) ከፍተኛ ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ የተመራ ልዑካን ቡድን በኢትዮጵያ ይገኛል።
የልዑካን ቡድኑ ዛሬ ከሰላም ሚኒስትር ወ/ሮ ሙፍሪሃት ካሚል ጋር መወያየቱ ተገልጿል።
ሚኒስትሯ ለኮሚሽነሩ በሰብዓዊ ዕርዳታና ስደተኞች ጉዳይ ላይ በሀገሪቱ እየተከናወኑ ስላሉ ተግባራት ማስረዳታቸውን በሰላም ሚኒስቴር በኩል ይፋ የተደረገው መረጃ ያሳያል።