በእንግልት ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ተማፅኖ...
(በቢቢሲ)
በሳዑዲ አረቢያ እስር ቤቶች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ እንግልት እንደሚደርስባቸው በመግለጽ መንግሥት ወደ አገር ቤት እንዲመልሳቸው እየተማፀኑ ነው።
ጂዳ በሚገኝ እስር ቤት የሚገኙ ሶስት ኢትዮጵያውያን ስለሚደርስባቸው ስቃይ ለቢቢሲ የገለፁ ሲሆን ፣ በየጊዜው በፖሊስ ድብደባ እንደሚደርስባቸው ፣ በቂ ምግብ እንደማይሰጣቸውና መታረዛቸውን ጨምረው ገልፀዋል።
ወደ አገራችን መልሱን የሚሉት እነዚህ ኢትዮጵያውያን ከኢትዮጵያ ቆንስላ መጥቶ የሚጠይቃቸው ማንም እንደሌለ፣ በአንድ ወቅት ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ ቅጽ ቢሞሉም ከዚያ በኋላ ግን ማንም እንዳላነገራቸው ተናግረዋል።
የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ፥ በየሳምንቱ ከሳዑዲ አረቢያ፣ ከኩዌይት ፣ ከሌባኖስ እና ከሌሎችም የአረብ አገራት ኢትዮጵያውያን እየተመለሱ መሆኑን ገልፀዋል።
እስር ቤት ያሉና ቆንስላው ያላገኛቸው ኢትዮጵያውያን ወደ ኋላ እንደቀሩና እነርሱም በጊዜ ሂደት ወደ አገራቸው እንደሚገቡ አስረድተዋል።
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
#BREAKING - የአሜሪካ ብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ማት ፓቲንገር በፍቃዳቸው ስልጣናቸውን ለቀዋል። - የዋይት ሃውስ ምክትል ፕሬስ ሴክረተሪ ሳራ ማቲውስ በፍቃደኝነት ስልጣናቸውን ለቀዋል። - የዋይት ሃውስ የማህበራዊ ሴክረተሪ ኒኪ ኒኪታ በፍቃደኝነት ስልጣናቸው ለቀዋል። @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ስቲፍኒ ግሪሽሃም ስልጣናቸውን ለቀቁ።
የአሜሪካ ቀዳማዊት እመቤት የሜሊና ትራምፕ ቺፍ ኦፍ ስታፍ ስቲፍኒ ግሪሽሃም ከUS ካፒቶል ነውጥ ጋር በተያያዘ በገዛ ፍቃዳቸው ስልጣን ለቀዋል።
ስቲፍኒ ግሪሽሃም የዋይት ሃውስ ፕሬስ ሴክረተሪ ሆነውም አገልግለዋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

#NewsAlert
የአሜሪካ ምክር ቤቶች የጆ ባይደንን የምርጫ ውጤት አረጋገጡ።
የሁለቱ ምክር ቤት እንደራሴዎች የተሰጡትን የውክልና ድምጾች (ኤሌክቶራል ቮት) በመቁጠር ጆ ባይደን ቀጣዩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው መመረጣቸውን አረጋግጧል።
ኮንግረስ ጆ ባይደን እና ምክትላቸው ካማላ ሀሪስን የቀጣዮቹ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት እና ምክትል ፕሬዝዳንት በማድረግ ያገኙትን ድምጽ #አጽድቋል።
የተሰጡት የውክልና ድምጾች የጸደቁት የሁለቱ ምክር ቤት ተወካዮች በፔንሰልቫንያ እና አሪዞና ግዛቶች የቀረበውን ተቃውሞ ውድቅ ካደረጉ በኋላ ነው።
የአገሪቱ ሕዝብ እንደራሴዎች ተሰብስበው ቀጣዩ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የምርጫ ውጤት ዙሪያ በመነጋገር ላይ ሳሉ በድንገት በሺህ የሚቆጠሩ የዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎች ምክር ቤቱን ሰብረው ገብተው ነበር።
በዚህ የተነሳ ተቋርጦ የነበረው የምክር ቤቶቹ የጋራ ስብሰባ ተቃዋሚ ሰልፈኞቹ እንዲወጡ ከተደረገ በኋላ ቀጥሏል።
ዋሺንግተን ውስጥ የተሰናባቹ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎች የአገሪቱን ምክር ቤት ጥሰው መግባታቸውን ተከትሎ በተፈጠረ ፍጥጫ 4 ሰዎች ሞተዋል።
በተቀሰቀሰው ግርግር ሳቢያ የዋሺንግተን ከንቲባ በከተማዋ ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ የሰዓት እላፊ ገደብ ጥለዋል።
የካፒቶል ሂል አካባቢም ሙሉ በሙሉ ዝግ እንዲሆን ተደርጓል። ~ BBC
@tikvahethiopiaBot

#BREAKING
ፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ እ.ኤ.አ ጥር 20 ላይ የስልጣን ሽግግር እንደሚደረግ አሳውቀዋል።
አሁንም ቢሆን ግን ዶ. ትራምፕ በምርጫው ውጤት ሙሉ በሙሉ እንደማይስማሙ ገልፀዋል። ያም ቢሆን ሽግግሩ እ.አ.አ ጥር 20 እንደሚደረግ ገልፀዋል።
የአሜሪካ ምክትል ፕሬዜዳንት ማይክ ፔንስም ጆ ባይደን እ.ኤ.አ ጥር 20 የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ሆነው እንደሚሰየሙ አሳውቀዋል።
* ፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዋይት ሃውሱ ዳን ስካቪኖ በኩል ያሰራጩት መልዕክት ከላይ ተያይዟል።

#DonaldTrump
- ፌስቡክ
- ኢንስታግራም
- ትዊተር
- ስናፕቻት እነዚህ ሶሻል ሚዲያዎች የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ትራምፕ ምንም አይነት መልዕክት እንዳያስተላልፉ ወይም ፖስት እንዳያደርጉ አግደዋል።

#GadaSystem
የገዳ ስርዓት በዩኔስኮ የተመዘገበበትን አራተኛው ዓመት በቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲ ይከበራል።
ከ4 ዓመት ወዲህ የተከናወኑ ተግባራት የሚገመገሙበት መድረክ ጥር 1 እና 2 በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ እንደሚካሄድ ተገልጿል።
Via ENA
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

"...አዲሱ አይነት ቫይረስ በክትባቱ ላይ ያሰደረው ተጽእኖን የሚያመለክት ነገር የለም" - ዶ/ር ማሪያ ቫን ኬርሆቬ
ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ተገኘ የተባለው አዲስ አይነት የኮሮናቫይረስ ዝርያ ለሰዎች እየተሰጠ ያለውን ክትባት እንደሚቋቋም የሚያሳይ ምንም ምልክት እንደሌለ የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ።
የዓለም ጤና ድርጅት የቴክኒክ ኃላፊ ዶክተር ማሪያ ቫን ኬርሆቬ እንዳሉት በተለያየ አይነት የኮሮረናቫይረስ ዝርያዎች የተያዙ ሰዎች ተመሳሳይ የሆነ የበሽታውን ምልክት የሚያሳዩ ሲሆን አስካሁን የከፋ ምልክት አልታየም ብለዋል።
ነገር ግን አዲሱ የቫይረስ ዝርያ የበሽታውን የመስፋፋት ፍጥነት ከፍ ማድረጉን ዶክተሯ ተናግረዋል።
"አዲሱን አይነት ቫይረስ በክትባቱ ላይ ያሰደረው ተጽእኖን የሚያመለክት ነገር የለም። ይህ መልካም ዜና ነው። እስካሁን ያለን መረጃ ይህ ነው፤ ጥናቶች ግን እየተካሄዱ ነው" ብለዋል ዶክተር ቫን ኬርሆቬ። ~ BBC

ስቲፍኒ ግሪሽሃም ስልጣናቸውን ለቀቁ። የአሜሪካ ቀዳማዊት እመቤት የሜሊና ትራምፕ ቺፍ ኦፍ ስታፍ ስቲፍኒ ግሪሽሃም ከUS ካፒቶል ነውጥ ጋር በተያያዘ በገዛ ፍቃዳቸው ስልጣን ለቀዋል። ስቲፍኒ ግሪሽሃም የዋይት ሃውስ ፕሬስ ሴክረተሪ ሆነውም አገልግለዋል። @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ሚክ ሞልቬኒ ስልጣንናቸውን ለቀቁ።
በሰሜን አይርላድ የUS ልዩ መልዕክተኛ ሚክ ሞልቬኒ ከካፒቶል ነውጥ ጋር በታያያዘ በገዛ ፍቃዳቸው ስልጣናቸውን ለቀዋል።
ሚክ ሞልቬኒ የፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቺፍ ኦፍ ስታፍ እንደነበሩም ይታወቃል።
ለአራት ሰዎች ሞት ምክንያት ከሆነውና የአሜሪካንን የዴሞክራሲ ስርዓት ጥያቄ ውስጥ ከከተተው ከትላንቱ ክስተት በኃላ በገዛ ፍቃዳቸው ከትራምፕ አስተዳደር ራሳቸውን የሚያገሉና ስልጣናቸውን የሚለቁ ባለስልጣናት ቁጥር እየጨመረ ነው።
አሁን ላይ ስልጣናቸውን ከለቀቁት በተጨማሪ ሌሎችም የሚለቁ ይኖራሉ እየተባለ ነው።

#FDREDefenseForce
የሀገር መከላከያ ኃይል ስምሪት መምሪያ ኃላፊ ብ/ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው እንዳረጋገጡት ፦
- አቶ ተክወይኒ አሰፋ ፣
- ዶክተር ሰለሞን ኪዳኔ ፣
- አቶ ገ/መድህን ተወልደ ፣
- አቶ ወ/ጊዮርጊስ ደስታ ፤
- አምባሳደር አባዲ ዘሞ ፣
- ወ/ሮ ቅዱሳን ነጋ ፣
- አቶ ቴድሮስ ሃጎስ ፣
- ወ/ሮ ምህረት ተክላይ
- አቶ አብርሃም አደም መሃመድ በቁጥጥር ስር ውለዋል።
በሌላ በኩል አቶ ሴኮ ቱሬ ጌታቸው ፣ አቶ ዘርአይ አስገዶም ፣ አቶ አበበ ገ/መድህን እና አቶ ዳንኤል አሰፋ እርምጃ እንደተወሰደባቸው አሳውቀዋል።
@tikvahethiopia @tikvahethiopia

#COVID19Ethiopia
የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :
• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 4,670
• በበሽታው የተያዙ - 441
• ህይወታቸው ያለፈ - 1
• ከበሽታው ያገገሙ - 47
አጠቃላይ 127,227 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,966 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ 113,021 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።
226 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :
• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 4,670
• በበሽታው የተያዙ - 441
• ህይወታቸው ያለፈ - 1
• ከበሽታው ያገገሙ - 47
አጠቃላይ 127,227 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,966 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ 113,021 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።
226 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FDREDefenseForce
መከላከያ ሰራዊት ዛሬ ምሽቱን ይፋዊ በሆነ መገለጫ እርምጃ ከተወሰደባቸው የህወሓት አመራሮች ውጭ የነሱ ሹፌሮች እና ጥበቃዎቻቸው ይገኙበታል ብሏል።
እርምጃ የተወሰደባቸው /የተገደሉ/ አመራሮች ፦
1. አቶ ሴኩቱሬ ጌታቸው
2. አቶ ዘርአይ አስገዶም የቀድሞው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ስራ አስኪያጅና የብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር የነበሩ
3. አቶ አበበ አስገዶም የድምጸ ወያኔ ሃላፊ የነበሩ
4. አቶ ዳንኤል አሰፋ የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ሃላፊ የነበሩ ናቸው።
በቁጥጥር ስር የዋሉት 9 የህወሓት ቁልፍ አመራሮች ናቸው ያለው የመከላከያ ሰራዊት አመራሮቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በጫካ እና ዋሻ ለዋሻ ሲንቀሳቀሱ ነው ብሏል።
በቁጥጥር ስር የዋሉት ፦
- ወይዘሮ ቅዱሳን ነጋ የቀድሞ የክልሉ አፈጉባኤ የነበሩ
- ዶ/ር ሰለሞን ኪዳኔ የቀድሞ የትግራይ ክልል ከተማ ልማት ቢሮ ሃላፊና የአ/አ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊ የነበሩ
- አቶ ተክለወይኒ አሰፋ የማረት ስራ አስፈጻሚ የነበሩ
- አቶ ገብረመድህን ተወልደ የክልሉ ንግድ ቢሮ ሃላፊ የነበሩ
- አቶ ወልደጊዮርጊስ ደስታ የክልሉ መንገድ ትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊ የነበሩ
- አምባሳደር አባዲ ዘሙ በሱዳን የኢትዮጵያ የቀድሞ አምባሳደር የነበረና የህወሓት ፖለቲካ ክንፍ የተቀላቀሉ፣
- አቶ ቴዎድሮስ ሃጎስ የመለስ አመራር አካዳሚ ፕሬዚዳንትና የኢፈርት ቦርድ ሃላፊ የነበሩ
- ወይዘሮ ምህረት ተክላይ የክልሉ ምክር ቤት ህግ አማካሪ የነበሩ
- አቶ ብርሃነ አደም መሃመድ የክልሉ የንብረትና ግዢ ስራ ሂደት ሃላፊ የነበሩ ናቸው። ~ ENA

ሚክ ሞልቬኒ ስልጣንናቸውን ለቀቁ። በሰሜን አይርላድ የUS ልዩ መልዕክተኛ ሚክ ሞልቬኒ ከካፒቶል ነውጥ ጋር በታያያዘ በገዛ ፍቃዳቸው ስልጣናቸውን ለቀዋል። ሚክ ሞልቬኒ የፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቺፍ ኦፍ ስታፍ እንደነበሩም ይታወቃል። ለአራት ሰዎች ሞት ምክንያት ከሆነውና የአሜሪካንን የዴሞክራሲ ስርዓት ጥያቄ ውስጥ ከከተተው ከትላንቱ ክስተት በኃላ በገዛ ፍቃዳቸው ከትራምፕ አስተዳደር ራሳቸውን የሚያገሉና…
የአሜሪካ ባለስልጣናት ስልጣናቸውን እየለቀቁ ነው።
የትምህርት ሚኒስትር ቤትሲ ዴቫስ በገዛ ፍቃዳቸው ስልጣናቸውን ለቀዋል።
ለረዥም ጊዜ ያገለገሉት ሚስስ ቤትሲ ዴቫስ በመልቀቂያቸው ዶናልድ ትራምፕ የወንበዴዎችን አመጽ በማቀጣጠል እና ይሁንታን በመስጠት ወንጅለዋቸዋል።
የትራንስፖር ሚኒስትሯ ኤሌይን ቻዎ ሥልጣን ለቀዋል።
በሆነው ነገር ስለተረበሽኩ ከትራምፕ ጋር ለመሥራት እቸገራለሁ ብለዋል በመልቀቂያቸው።
ወ/ሮ ቻው በሴኔት የሪፐብሊካኑ ተጠሪ ሚች መከኔል ባለቤት ናቸው።
ከካቢኔ አባላት በተጨማሪ የዶናልድ ትራምፕ ልዩ ረዳቶቻቸውም መልቀቂያ እያስገቡ ነው።
የስቴት ዲፓርትመንቱ አማካሪ ደግሞ ትራምፕ ለአሜሪካ አይመጥኑም ማለታቸውን ተከትሎ ከሥራ ተሰናብተዋል። ~ BBC

ጋዜጠኛ ሀብቴ ያዕቆብ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።
የሲዳማ ሚድያ ኔትወርክ (SMN) መስራች እና አመራር ጋዜጠኛ ሀብቴ ያዕቆብ በድንገተኛ ህመም በሚኖርበት ደቡብ አፍሪካ በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ትላንት ታህሳስ 29 በሞት ተለይቷል፡፡
ጋዜጠኛ ያዕቆብ ከSMN መስራችነት ባለፈም የረጅም ጊዜ የሲዳማ ሕዝብ የመብት ተሟጋች እንደሆነ ተገልጿል።
እንዲሁም የሲዳማ ዳያስፖራ ኮሚውኒቲ መስራችና አመራር አባልም ነበር።
የሲዳማ ዳያስፖራ ኮሚውኒቲ (SDC) በጋዜጠኛው ህልፈት የተሰማውን ሀዘን ገልጿል።

#Boeing737
ቦይንግ ስለ #737_ማክስ አውሮፕላኑ ዲዛይን ከአሜሪካ የደኅንነት እና ጥንቃቄ ባለሙያዎች መረጃዎችን በመደበቅ ለተመሰረተበት የወንጀል ክስ 2.5 ቢሊዮን ዶላር ቅጣት ለመክፈል መስማማቱን ቢቢሲ በድረገፁ አስነብቧል።
የአሜሪካ ፍትህ ቢሮ ኩባንያው "ከግልጽነት ይልቅ ትርፍን" አስቀድሟል ብሏል።
ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን በኢትዮጵያ እና በኢዶኔዢያ ተከስክሶ የ346 ሰዎች ህይወት ማለፉ አይዘነጋም።

በአዲስ አበባ ከተማ የገና በዓል እንዴት አለፈ ?
የትራፊክ አደጋ ፦
በቀን 28 በትራፊክ አደጋ አንድ የሞት አደጋ ደርሷል። የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ነው አደጋው የደረሰው።
በዋዜማው ከባድ ሆነ ቀላል የትራፊክ አደጋ አልተመዘገበም።
በበዓሉ ዕለት የሞት አደጋ አልተመዘገበም። አንድ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል፤ አደጋው ንፋስ ስልክ ላፍቶ ወረዳ 11 ሃና ማርያም ኣካባቢ ነው የደረሰው።
የእሳት አደጋ ፦
ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 9 ሀዲድ ገበያ ተብሎ የሚጠራ አካባቢ በደረሰ የእሳት አደጋ ሃያ ሶስት (23) የሚደርሱ ሱቆች ተቃጥለዋል።
የአደጋው ምክንያት እየተጣራ ነው።
ኮልፌ ወረዳ 3 ኣካባቢ አጃንባ ኮንዶሚኒየም አንድ ብሎክ ቃጠሎ ደርሶበታል።
በአጠቃላይ የገና በዓል በአዲስ አበባ ከተማ የተረጋገ ሆኖ ማለፉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።