ለዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ፦
MoSHE የዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ የ2012 ተመራቂ ተማሪዎች ትምህርታቸውን በመቐለ ዩኒቨርሲቲ እንዲማሩ መልዕክት አስተላልፏል።
በ2012 ዓ/ም ተመራቂ የነበሩ ተማሪዎች ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ በጥገና ላይ ስለሆነ ትምህርታቸውን መቐለ ዩኒቨርሲቲ ተምረው እንደሚመረቁ MoSHE አሳውቋል።
ከታህሳስ 30 እስከ ጥር 1 የምዝገባ ጊዜ መሆኑም ተገልጿል።
የዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በተጠቀሱት ቀናት መቐለ ዩኒቨርሲቲ ኩሃ ግቢ ሪፖርት እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።
ጥር 2 ትምህርት ይጀምራል።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT

ግብጽ የኢትዮጵያን አምባሳደር ለማብራሪያ መጥራቷን ገለጸች !
የግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ አምባሳደር ማብራሪያ እንዲሰጡት መጥራቱን አህራም ዘግቧል።
አምባሳደሩ የተጠሩት የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ግብፅን በተመለከተ አስተያየት በመስጠታቸው ነው ተብሏል።
አህራም አምባሳደር ዲና የግብጽን ውስጣዊ ጉዳይ በመጥቀስ ሰሞኑን ማብራሪያ ሰጥተዋል ብሏል።
ይሁንና ቃል አቀባይ ዲና ከሰሞኑ በሰጧቸው መግለጫቸው ግብጽ የሚልን ቃል ከመጥቀስ ተቆጥበው ነበረ።
ቃል አቀባዪ በግብጽ የኢትዮጵያ አምባሳደር እንደነበሩ ይታወቃል።
ምንጭ፦ አል ዓይን ኒውስ

መልዕክት ፦
ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ :
የገና ስጦታ የልገሳ ጊዜ ከታህሳስ መጀመሪያ ጀምሮ እየተካሄደ ነው። ሜሪ ጆይ አረጋውያና ህፃናት በዓሉን በደስታ ያሳልፉት ዘንድ እርሶም ድጋፍ ያደረጉ ዘንድ መልዕክት አስተላልፏል።
ድጋፉን ፦
- በአልባሳት
- በቁሳቁስ
- በገንዘብ ማድረግ ይቻላል።
ሚሪ ጆይን በ 0987626262 or 0983636363 or 0911208518 ላይ ብትደውሉ ልታገኟቸው ትችላላችሁ።
@tikvahethiopia

ምስራቃዊ ሶሪያ ውስጥ በተፈፀመ ጥቃት የሰዎች ህይወት አለፈ!
በምሥራቃዊ ሶሪያ ውስጥ በአውቶብሶች ላይ በተፈጸመ ድንገተኛ ጥቃት ቢያንስ 28 ሰዎች ሳይሞቱ እንዳልቀረና ሁሉም ወታደሮች ሊሆኑ እንደሚችሉ ተገለጸ።
የሶሪያ ብሔራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ እንደገለጸው አውቶብሶቹ ዴር አል ዘር ተብሎ በሚታወቀው ግዛት ረቡዕ እለት ነው ኢላማ የተደረጉት።
በጥቃቱም በርካታ ዜጎች ተገድለዋል ብሏል ጣቢያው።
ነገር ግን አንዳንድ ምንጮችና ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ አውቶብሱ ውስጥ ወታደሮች እንደነበሩ እና የሟቾች ቁጥር ከዚህም በላይ ከፍ ሊል እንደሚችል አስታውቀዋል።
ከጥቃቱ በኋላ ወዲያው ኃላፊነቱን የወሰደ ቡድን አልነበረም።
መቀመጫውን UK ያደረገው የሶሪያ ሰብአዊ መብቶች ተቆጣጣሪ ድርጅት ጥቃቱን የፈጸመው #አይኤስ እንደሆነ በመግለጽ የሟቾች ቁጥር ደግሞ 37 ነው ብሏል።
ድርጅቱ በቦታው ላይ የነበሩ ምንጮችን በመጥቀስ ''ጥቃቱ በተቀናጀ መልኩ በአይኤስ አባላት የተካሄደ ነው ብሏል።
መንግስትን የሚደግፉ ታጣቂዎችና ወታደሮችን የጫኑ ሶስት አውቶብሶች ላይ ጥቃት ተፈጽሟል'' ሲል ነው መግለጫ ያወጣው። ~ BBC

የተሽከርካሪ ባለንብረቶች ህዝባቸውን እንዲያገለግሉ ጥሪ ቀረበ !
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ካሉት 6 ወረዳዎች በ5ቱ ወረዳዎች ወደ መቶ ሺ ተፈናቃዮች ይገኛሉ።
ለተፈናቃዮች የሰብዓዊ እርዳታ በወቅቱ ለማድረስ እየተቸገረ እንደሆነ የክልሉ የአደጋ ስጋት ኮሚሽን ለቪኦኤ አስታውቋል።
ለዚህ ምክንያቱ በአካባቢው ባለው የፀጥታ ስጋት የተሽከርካሪ ባለንብረቶች መምጣት ባለመፈለጋቸው ነው ተብሏል።
ኮሚሽኑ የአቅርቦት ችግር እንደሌለ ገልፆ ነገር ግን የትራንስፖርት ባለንብረቶች አንሄደም የማለት እንቢተኝነት እየታየባቸው እንደሆነ አሳውቋል።
ባለነብረቶች ህዝባቸውን እንዲያግዙ ፣ ህዝባቸውን እንዲታደጉ፣ ኢትዮጵያዊነታቸውን እንዲያሳዩ ለራሳቸው እና ለህዝባቸው ታሪክ አስመዝግበው እንዲያልፉ ጥሪ ቀርቧል።
መኪናቸውን አቁመው ህዝብ ቢያልቅ የታሪክ ተወቃሽ መሆን እንዳለ በማሰብ ህዝባቸውን እንዲያገለግሉ የክልሉ አደጋ ስጋት ኮሚሽን መልዕክት አስተላልፏል።
በሌላ በኩል ፦
ተፈናቃዮች ባሉባቸው ቦታዎች ነዋሪዎች ከ15-20 ተፈናቃይ እያስተናገዱ ነው።
በርካታ ተፈናቃይ መጠለያ አጥቶ በግለሠብ ቤት ውስጥ አርፏል።
ነዋሪዎች ማስጠለል ብቻ ሳይሆን ምግባቸውንም እየሸፈኑ እንደሚገኝ ተነግሯል።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አደጋ ስጋት ኮሚሽንም ተፈናቃዮችን እየተንከባከቡ ላሉ ነዋሪዎች ምስጋና ማቅረቡን ቪኦኤ ዘግቧል።

#BuleHoraUniversity
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ለቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንትነት ምደባ ሰጥቷል፡፡
ዶክተር ጫላ ዋታ የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ሆነዉ በቋሚነት መመደባቸውን ዩኒቨርሲቲው በይፋዊ ፌስቡክ ገፁ አሳውቋል።

TIKVAH-ETHIOPIA
#AdenAirport በየመን ኤደን ኤርፖርት በነበረው ጥቃት እስካሁን 26 ሰዎች መሞታቸውን ኤ ኤፍ ፒ አስነብቧል። በፍንዳታው ከ50 በላይ ሰዎች ቆስለዋል። አዲሱ ጠ/ሚ ማዒን አብዱልማሊክ ሰዒድ ጥቃቱን “በፈሪ ሽርተኞች የተቃጣ ነው” ያሉ ሲሆን ድርጊቱን “የግልበጣ ሙከራ” ብለውታል። እሳቸው ከነ ካቢኔያቸው ደህና መሆናቸውን በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ አስታውቀዋል፡፡ የመረጃ ሚኒስትሩ ሞሃማር…
3 የICRC አባላት ተደገሉ።
ትላንት በየመን 'ኤደን ኤርፖርት' በነበረው ፍንዳታ / ጥቃት ሶስት (3) የICRC ስታፍ አባላት መገደላቸው ተረጋግጧል።
ፍንዳታው በተከሰበት ወቅት የICRC አባላቱ ከሌሎች ሲቪሎች ጋር በኤደን ኤርፖርት ትራንዚት ላይ ነበሩ።
ከሟቾቹ መካከል ሁለቱ የየመኒ ዜጎች ሲሆኑ አንደኛው የሩዋንዳ ዜጋ ነው።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
ትላንት በየመን 'ኤደን ኤርፖርት' በነበረው ፍንዳታ / ጥቃት ሶስት (3) የICRC ስታፍ አባላት መገደላቸው ተረጋግጧል።
ፍንዳታው በተከሰበት ወቅት የICRC አባላቱ ከሌሎች ሲቪሎች ጋር በኤደን ኤርፖርት ትራንዚት ላይ ነበሩ።
ከሟቾቹ መካከል ሁለቱ የየመኒ ዜጎች ሲሆኑ አንደኛው የሩዋንዳ ዜጋ ነው።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
ኮማንደር ግርማይ ናይዝጊን ጨምሮ 6 ተጠርጣሪዎች ዋስትና ተፈቀደላቸው !
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አመራር የነበሩት ኮማንደር ግርማይ ናይዝጊን ጨምሮ 6 ተጠርጣሪዎች ዋስትና ተፈቀደላቸው።
ተጠርጣሪዎቹ ኮማንደር ግርማይ ናይዝጊ ፣ የቀድሞ የመከላከለያ ጡረተኛው ሌተናል ኮሎኔል ገብረማርያም አርያ ፣ ወይዘሮ ተክለብርሃን በርሄ፣ ዘረሰናይ ገብረዮሀንስ፣ የቀድሞ የመከላከለያ ጡረተኛው ብርጋዴል ጀነራል ሀየሎም ግብረስላሴ እና ዳንኤል ገብረመድህን ናቸው።
ተጠርጣሪዎቹ ላይ ከዚህ በፊት ፍርድ ቤቱ ዋስ ፈቅዶላቸው የነበረ ሲሆን መርማሪ ፖሊስ በይግባኝ መዝገቡ እንደገና እንዲታይ አድርጎ ነበር።
ይሁንና መርማሪ ፖሊስ ከዚህ በፊት በተሰጠው ጊዜ የሰራውን የምርመራ ስራ የገለጸ ሲሆን ÷ ተጠርጣሪዎችም 53 ቀን ሙሉ ያለአግባብ ታስረናል ሲሉ ፍትህ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።
መዝገቡን የመረመረው ፍርድ ቤትም የጊዜ ቀጠሮ የሚሰጠው የወንጀል ተሳትፎ አጣርቶ ማስረጃ ለማቅረብ እንጂ ተመሳሳይ ምርመራ ለማቅረብ አይደለም ብሏል።
ተጠርጣዎቹ 53 ቀን የታሰሩ በመሆኑና የተፋጠነ ፍትህ የማግኘት መብትን ባገናዘበ መልኩ ምርመራው ያልተሰራ በመሆኑ እንዲሁም ፍርድ ቤት የተጠርጣሪዎችን የሰብዓዊ መብት እና የተፋጠነ ፍትህ የማግኘት መብትን የማስከበር ሀላፊነት ያለው መሆኑን በምክንያትነት ጠቅሶ እያንዳንዳቸው በ10 ሺህ ብር ዋስ አስይዘው ከእስር እንዲፈቱ አዟል።
ከዚያም ባለፈ ከዚህ በፊት ችሎት ያስያዙት የዋስትና ብርም ካለ እንዲመለስላቸው ፍርድ ቤቱ ወስናል።
ተጠርጣሪዎቹም ከሀገር እንዳይወጡ እግድ እንዲጣል አዟል። (ኤፍ ቢ ሲ)

#Oromia
በኦሮሚያ ክልል 6 ዞኖች ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ የአንበጣ መንጋ ተከስቷል።
የኦሮሚያ ክልል እርሻና ተፈጥሮ ኃብት ልማት ቢሮ መንጋውን ለመከላከል በአውሮፕላን የተጋዘ የኬሚካል ርጭት እየተካሄደ መሆኑን አስታውቋል።
የአንበጣ መንጋው የተከሰተው በክልሉ ሁለቱ የባሌ ዞኖች ፣ ምስራቅ ሐረርጌ ፣ አርሲ፣ ጉጂና ቦረና ዞኖች ውስጥ ነው።
በተከሰተው የአንበጣ መንጋ እስካሁን የደረሰውን ጉዳት በባለሙያ ተጠንቶ ወደፊት የሚገለጽ መሆኑ ተጠቁሟል።
መንጋውን ለመቆጣጠር የተቀናጀ ስራ እየተሰራ ይገኛል ያለው ቢሮው ካለው ዝግጅት አንፃር ከአቅም በላይ እንደማይሆን ገልጿል። ~(ENA)

#China
ቻይና በአዲሱ የኮቪድ-19 ዝርያ የታይዘ የመጀመሪያውን ሰው ሪፖርት አደረገች።
ቫይረሱ የተገኘባት የ23 ዓመት እድሜ ያላት ተማሪ ስትሆን ከብሪታኒያ ወደ ቻይና ገብታ የኮሮና ምርምራ ሲደረግላት ነው ቫይረሱ እንዳለባት የተረጋገጠው።

#COVID19Ethiopia
የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :
• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 5,547
• በበሽታው የተያዙ - 408
• ህይወታቸው ያለፈ - 5
• ከበሽታው ያገገሙ - 226
አጠቃላይ 124,164 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,923 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ 112,096 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።
234 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

#Egypt #Ethiopia #Sudan በሕዳሴ ግድብ ዙሪያ በኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብፅ መካከል የሚደረገው ድርድር በሚቀጥለው #እሁድ ታህሳስ 25 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚቀጥልም አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገልፀዋል። አምባሳደሩ ይህን የገለፁት በሰጡት ሳምንታዊ መግለጫ ላይ ነው። ከታላቁ ህዳሴው ግድብ ድርድር ራሷን አግልላ የነበረችው #ሱዳን ወደ ድርድሩ እንደምትመለስ በቅርቡ ይፋ ማድረጓ ይታወቃል፡፡…
#Egypt #Ethiopia
አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ባለፈው ማክሰኞ በሰጡት መግለጫ ፥ “የአፍሪካ ቀንድና ምስራቅ አፍሪካ አካባቢ እንዲተራመስ የሚፈልጉ አካላት አሉ” ማለታቸውን ተከትሎ ግብጽ በኩል ቅሬታዎች እየመጡ ነው፡፡
“የሱዳንን ሰፊ መሬትን የያዙ አሉ፤ ግን ለሱዳን ተቆርቋሪ እየመሰሉ ይረብሻሉ” ያሉት አምባሳደር ዲና “ስማቸውን መናገር ግን አልፈልግም ፤ እናንተው ታውቋቸዋላችሁ” ሲሉ ማንነታቸውን በግልጽ ሳይጠቅሱ ማለፋቸው ይታወሳል፡፡
የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ “የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ በግብጽ የውስጥ ጉዳይ ላይ አስተያየት መስጠታቸው ተገቢ አይደለም” ብሏል፡፡
“አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ግብጽን በተመለከተ ኃላፊነት የጎደለው አስተያየት ሰጥተዋል” ያሉት የግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር አሕመድ ሀፊዝ “ግብፅ የግድቡን ግንባታ የምትቃወመው በሀገሪቱ ያለባትን ቀውስ ለማቀዝቀዝ ነው ማለታቸው ተገቢ አስተያየት አይደለም” ሲሉም ነው የገለጹት፡፡
አምባሳደር ዲና “የአፍሪካ ቀንድና ምስራቅ አፍሪካ አካባቢ እንዲተራመስ የሚፈልጉ አካላት አሉ ነው ያልነው ፣ ነገር ግን ሌባ እናት ልጇን ስለማታምን ይህንን የምናደርገው እኛ ነን ካሉ ምንም ማድረግ አንችልም” ብለዋል።

#FireAlert #DebreMarkos
ደብረ ማርቆስ ሆስፒታል አካባቢ ከሚገኘው ጉልት ገበያ ሱቆች ላይ በአሁኑ ሰዓት ከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ ተነስቷል።
ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሱቆች ተቃጥለዋል።
የከተማው ህዝብ በነቂስ ወጥቶ እሳቱን ለማጥፋት ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ የምስራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ ጽ/ቤት አስታውቋል።
@tikvahethmagazine @tikvahethiopia