TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
በዌራ ወረዳ በደረሰ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ። በሀላባ ዞን ዌራ ወረዳ ላይኛ በደኔ ቀበሌ በጦሮንቦራ ንዑስ ዛሬ ከረፋዱ 5፡00 ላይ የእሳት አደጋ ተከስቷል፡፡ ለጊዜው የአደጋው ምክንያት አልታወቀም ተብሏል። በአደጋው 11 መኖሪያ ቤቶች እንደተቃጣሉ እና ንብረት መውደሙ ተገልጿል። በአደጋው በሰው እና በእንስሳት ላይ እስካሁን ምንም አይነት ጉዳት እንዳልደረሰም። አደጋውን ለመቆጣጠር…
#UPDATE

በሀላባ ዞን ዌራ ወረዳ ላይኛ በደኔ ቀበሌ በደረሰው አደጋ ቤት ለተቃጠለባቸው እና ንብረት ለወደመባቸው አካላት ጊዜያዊ መጠለያ ውስጥ እንደሚገኙ ተገልጿል።

የአደጋው መንስኤም የተለያዩ እህሎች በተከመሩበት ቦታ በሶላር ባትሪ ቻርጅ የተሰካ የሞይባል ስልክ ፈንድቶ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

የዚህ አይነት አደጋዎች ሊከሰቱ እንደሚችሉ በተለያዩ አጋጣሚዎች ግንዛቤ የመፍጠር ስራ የተሰራ ቢሆንም በህብረተሰቡ ዘንድ አሁንም የጥንቃቄ ጉድለቶች እንደሚስተዋሉ ተጠቁሟል፡፡

በመሆኑም በጥንቃቄ ጉድለት ምክንያት መሰል የእሳት አደጋ እንዳይከሰት አስቀድሞ ለመከላከል ህብረተሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበትም የወረዳው አስተዳደር አሳስቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
* ቀይ መስቀል

በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የሃላባ ዞን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በዌራ ወረዳ እሳት አደጋ ቤት ንብረታቸው ለተቃጠለባቸው ወገኖች የአልባሳትና ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።

ቀይ መስቀል ለተጎጂ ቤተሰቦች ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች ብርድ ልብስ ፥ ከሰፍ ፥ ሸራ እና ሳሙና ነው ድጋፍ ያደረገው።

ማህበሩ እገዛ ለሚያስገልጋቸው ዜጎች የሚደረገውን ድጋፍ እንደሚያጠናክር አሳውቋል።

(ሀላባ ዞን ኮሚኒኬሽን)
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Metekel በኩጅ ቀበሌ ከተከሰተው ጭፍጨፋ ተርፈው በቡለን ከተማ ተጠልለው ለሚገኙ ዜጎች የተለያዩ ለዕለታዊ ፍጆታ የሚሆኑ የምግብ ገብዓቶችን እየቀረበ ነው። • ስንዴ 875 ኩንታል፣ • ዱቄት 1751 ኩንታል ፣ • ፓስታ እና የህጻናት አልሚ ምግብ ደግሞ 440 ኩንታል በአጠቃላይ 3 ሺህ 66 ኩንታል በቡለን ከተማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች መቅረቡን በብሄራዊ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።…
#Metekel

በመተከል ዞን ለተፈናቀሉ ዜጎች የፌዴራል አደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኮሚሽን ያደረገው ድጋፍ አየተሠራጨ ይገኛል።

ድጋፉ በቡለን ወረዳ ተፈናቅለው ቡለን ወረዳ ማዕከል ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች እየተሠራጨ መሆኑን የወረዳው ኮሙኒኬሽን አሳውቋል።

ኮሚሽኑ ከ2 ሺህ 180 ኩንታል በላይ የስንዴ ፣ የበቆሎ ፣ የፋፋ ዱቄት በቡለን ወረዳ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በመድረስ ላይ ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#NewsAlert

ነገ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት #አስቸኳይ_ጉባኤ እንደሚካሄድ ተገለጸ።

የክልሉ ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ አለምነሽ ይባስ እንዳሉት ምክር ቤቱ በነገው ዕለት በአሶሳ ከተማ አስቸኳይ ጉባኤውን ያካሂዳል።

በጉባኤው የመተከል ዞን የሠላም እና ጸጥታ ችግር ዋነኛው የምክር ቤቱ ትኩረት እንደሚሆን ምክትል አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ አለምነሽ አስታውቀዋል፡፡

ሌሎችም ክልላዊ እና ሃገራዊ ወቅታዊ ጉዳዮችን የውይይቱ አጃንዳ አድርጎ ይወያያል ብለዋል። (ENA)

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ዝግጅት !

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ገረመው ሁሉቃ ከኢ.ፒ.ድ ጋር በነበራቸው ቆይታ የሀገር አቀፉን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን በተመለከተ ተከታዮቹን ነጥቦች አንስተዋል ፦

• በ2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በኮሮና ምክንያት ፈተና ያልወሰዱ በአጠቃላይ 450 ሺህ የሚሆኑ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ዘንድሮ ፈተና ይወስዳሉ።

• ለፈተናው ብቻ የሚውል ቪሳት ሌሎች አጋዥ መሳሪያዎች ተገዝተው 1 ሺህ 184 ፈተና ጣቢያዎች ተቋቁመዋል።

• ለ270 ቴክኒሻኖች ስልጠና ተሰጥቷል።

• ለፈታኝ መምህራን 12ሺህ ላፕቶፖች ተዘጋጀቷል።

• 2 ትልልቅ ሰርቨሮችም በተገቢ ቦታ ላይ በመትከል ተማሪዎች እንዲለማመዱ ከ2008 እስከ 2011 ዓ.ም የተሰጡት የ12ኛ ክፍል ፈተናዎችም እዚያው ላይ ተጭነዋል።

• በትምህርት ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢ/ር ጌታሁን መኩሪያ አማካኝነት በእርዳታ የተገኙ 450 ሺህ ታብሌቶች እስከ ታኅሣሥ 30 ቀን 2013 ዓ/ም ወደ አገር ውስጥ ገብተው ለፈተናው ይውላሉ።

• ፈተናውም ጥር 30 የሚጠናቀቅ ይሆናል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Metekel

ሌፍተናንት ጄኔራል አስራት ዴኔሮ በጠ/ሚሩ የተቋቋመው ግብረ ኃይል የመተከል ዞንን የፀጥታ ማስከበር ስራ መረከቡን አስታውቀዋል።

ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እና የመከላከያ ሠራዊት አመራሮች የተካተቱበት ግብረ ኃይል በዞኑ የሕግ የበላይነትን የማረጋገጥ ስራውን ሙሉ በሙሉ ጀምሯል።

የፀጥታ ኃይሉን የሚመሩት ሌ/ጄኔራል አስራት ዴኔሮ እንደገለጹት፣ የንጹሃንን ሕይወት በማጥፋት ወንጀል የተሳተፉ ተጠርጣሪዎችን የማደን ስራው ቀጥሏል።

“በወንጀሉ የተሳተፉ ተጠርጣሪዎች በአጭር ጊዜ የሕግ ተጠያቂ ይሆናሉ” ሲሉም ተናግረዋል።

ችግሩን ከመሰረቱ ለመፍታት በአሁኑ ወቅት በየደረጃው ከሚገኙ የማኅበረሰብ አባላት እና አመራሮች ጋር ውይይት እየተካሄደ ሲሆን ወንጀለኞቹን በመለየት ለሕግ የማቅረቡ ስራም እንደሚቀጥል ሌፍተናንት ጄኔራሉ ተናግረዋል። (ኢዜአ)

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
በአ/አ የ8ኛ ክፍል ውጤት ይፋ ሆነ።

በአዲስ አበባ ከተማ የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ዛሬ አስታውቋል።

በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ዘግይቶ በ 2013 ዓ/ም በ156 መፈተኛ ጣቢያዎች ለ71,476 ተማሪዎች የተሰጠዉ የ2012 ዓ/ም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል።

ለፈተናው ከተቀመጡ ተማሪዎች መካከል 80 % ተማሪዎች ወደ ቀጣይ ክፍል መዛወራቸውን የአ/አ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ገልጿል።

የክልላዊ ፈተናዉ ውጤትም ለ10ሩም ክፍለ ከተማዎች ዛሬ ተሰራጭቷል።

ከነገ ማክሰኞ ጀምሮ ተማሪዎች ውጤታቸውን በየትምህርት ቤቶቻችው መመልከት ይችላሉ ተብሏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ታህሳስ 19 ቀን 2013 ዓ.ም

የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 4,171
• በበሽታው የተያዙ - 281
• ህይወታቸው ያለፈ - 3
• ከበሽታው ያገገሙ - 553

አጠቃላይ 123,145 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,912 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ 109,846 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።

231 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#TikvahFamilyMekelle

ዛሬ ከሰዓት የባንክ አገልግሎት መጀመሩን የመቐለ ቲክቫህ አባላቶቻችን አሳውቀዋል።

የንግድ ባንክ ቅርጫፎች ተከፍተው አገልግሎት ሲሰጡ ነበር።

እጅግ በርካታ ሰዎችም ገንዘብ ለማውጣት ረጅም ሰልፍ ተሰልፈው ነበር።

በተለይ በዋናው የንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የነበረው ሰልፍ እጅግ ከፍተኛ እንደነበር የመቐለ ቲክቫህ አባላት በስልክ ገልፀዋል።

ከኢፕድ ድረገፅ እንደተመለከትነው ደግሞ የመቐለ ከንቲባ አቶ አታኽልቲ ኃይለስላሴ የግል ባንኮች ተከፍተው አገልግሎት እንዲሰጡ ትዕዛዝ መተላለፉን አሳውቀዋል።

የቲክቫህ አባላት በከተማቸው የባንክ አገልግሎት አለመኖር ነዋሪውን ክፉኛ ችግር ላይ ጥሎት እንደነበር ነግረውናል። አሁን ባንክ መከፈቱ መልካም ቢሆንም ጫናው እንዲቃለል ሁሉም ባንኮች በፍጥነት ተከፍተው አገልግሎት እንዲሰጡ ጠይቀዋል።

በተጨማሪ በከተማው ያለው የዋጋ ንረት ለነዋሪዎች ከፍተኛ ፈተና ሆኗል፤ይህም በፍጥነት እንዲስተካከል ጠይቀዋል።

በፀጥታ በኩል አሁንም የሚታዩ ዘረፋዎች መኖራቸውን በመጠቆም ለህዝቡ በሰላም መንቀሳቀስ የደህንነት ስራው እንዲጠናከር አደራ ብለዋል።

በሌላ በኩል፦

የመቐለ ቲክቫህ አባላት ኔትዎክ በሌለባቸው የትግራይ ከተሞች የዘመድ አዝማዶቻቸውን ደህንነት ለማወቅ እንደተቸገሩ ገልፀዋል።

አንዳንዶችም በሰዎች ደብዳቤ በመላክ የእናት እና አባቶቻቸውን ደህንነት ለማወቅ ጥረት እያደረጉ እንደሆነ ነግረውናል።

ኔትዎርክ በሌለባቸው አካባቢዎች ኔትዎርክ ሲከፈት የተፈጠሩ ሁኔታዎችን በዝርዝር ለቲክቫህ አባላት እንደሚያጋሩ አሳውቀዋል።

በትግራይ የሚኖሩ እና በተለያዩ የሀገሪቱ የዩኒቨርሲቲ ሄደው የሚማሩ ተማሪዎች ጉዳይ እንዳሳሰባቸው በመግለፅ MoSE ለተማሪዎቹ ሊደረግ ስለታሰበው ነገር በሚዲያ ማብራሪያ እንዲሰጥ ጠይቀዋል።

@tikvahethiopia
#የቅዱስ_ገብርኤል_ንግስ_በዓል_ቁልቢ

ዓመታዊው የቁልቢ ገብርኤል ንግስ በዓል ያለምንም የፀጥታ ችግር በድምቀት ትላንት ተከብሯል።

በዓሉ ያለፀጥታ ችግር ይጠናቀቅ ዘንድ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ፣ የሀረር እና ኦሮሚያ ልዩ ኃይሎች ፣ የፌዴራል ፖሊስ እንዲሁም የቁልቢ ከተማ ፖሊስ በቅንጅት መስራታቸው ተገልጿል።

በዓሉ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ምንም የትራፊክ አደጋ አልተከሰተም።

በበዓሉ ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስና ሌሎችም ብፁዓነ ሊቃነ ጳጳሳት ተገኝተው ነበር።

*
*
በስርቆት ወንጀል የተከሰሱ 4 ግለሰቦች ፦

በቁልቢ ገብርኤል ንግስ በዓል በስርቆት ወንጀል የተከሰሱ አራት ግለሰቦች በእስራት እንዲቀጡ ተወስኖባቸዋል።

ግለሰቦቹ በንግስ በዓሉ ሞባይል ስልክና ሌሎች ቁሳቁሶችን ሲሰርቁ እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል።

አራቱ ግለሰቦች እስከ አንድ አመት ከስምንት ወር በሚደርስ እስራት ነው የተቀጡት።

#DirePolice #ENA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#የቅዱስ_ገብርኤል_ንግስ_በዓል_ሀዋሳ

ትላንት በሀዋሳ ከተማ የተከበረው የቅዱስ ገብርኤል ንግስ በዓል በታላቅ ድምቀት ያለምንም የፀጥታ ችግር ተከብሮ በሰላም ነው የተጠናቀቀው።

*
*

የስርቆት ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ ፦

በቅዱስ ገብርኤል የንግስ በዓል ላይ የስርቆት ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ በ1 አመት ከ 6 ወር እስራት ተቀጥቷል።

ከተበዳይ ወ/ሮ ኪኒኔ ዮሐንስ የእጅ ቦርሳ በመስረቅ የተያዘው ተከሳሽ አልጋ አዲሱን ነው የባህል አዳራሽ ክፍለ ከተማ ተንቀሳቃሽ ችሎት በ1 አመት ከ6 ወር እስራት የቀጣው።

ምንጭ፦ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ኮሚኒኬሽን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ጦር ማንኛውም አይነት ጥቃት ለመመከት 24 ሰዓት በተጠንቀቅ ላይ እንደሚገኝ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናገሩ።

አምባሳደሩ ይህን ያሉት ETHIO FM 107.8 ጣቢያ ሱዳን የኢትዮጵያን ድንበር በመጣስ ምዕራብ ጎንደር አካባቢ እያደረሰች ስላለው ጥፋት ተጠይቀው በሰጡት ምላሽ ነው።

አምባሳደር ዲና ፥ የሱዳን ኃይል የኢትዮጵያን ድንበር ጥሶ በመግባት በርካታ ህገወጥ ድርጊቶችን መፈፀሙን ተናግረዋል።

ይህም "የሀገር መከላከያ ሰራዊት በትግራይ ክልል እያደረገ ያለዉን የህግ ማስከበር ተልዕኮ እንደ ክፍተት ተጠቅመዉ ኢትዮጵያን እና ሱዳንን ወደ ግጭት እንዲያመሩ ከከሚፈልጉ ሃይሎች የመነጨ ነዉ" ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ ሉኣላዊነቷን ለማስጠበቅ ዝግጁ መሆኗን ያረጋገጡት አምባሳደር ዲና ፥ "ችግሩን በሰላማዊ መንገድ እንፈታለን ስንል ፍርሃት ከመሰላቸዉ ተሳስተዋል ፤ ማንኛዉንም ጥቃት ለመመከት የፀጥታ ሃይሉ 24 ሰዓት በተጠንቀቅ ላይ ይገኛል” ብለዋል፡፡

አምባሳደሩ ፥ "የኢትዮጵያን ዉድቀት፣ የኢትዮጵያን ችግር፣ የኢትዮጵያን ውጥንቅጥነት የሚመኙ ወገኖች ካሉ ተስፋ ቢቆርጡ ነው የሚሻላቸው ፥ ይህ የሚሳካ አይደለም " ሲሉ ተደምጠዋል።

የኢትዮጵያን ውድቀት የሚመኙ ሀገራት መኖራቸዉን የሚገልፁት አምባሳደር ዲና ፥ ኢትዮጵያ በነጻነቷ ከመጡባት ማንንም እንደማትምር ከታሪካችን መረዳት ይኖርባቸዋል ብለዋል።

የሱዳን ህዝብ እና የሱዳን መንግስት ከሚጎትታቸዉ ሃይል እራሳቸውን እንዲቆጥቡም አምባሳደር ዲና ሙፍቲ አሳስበዋል፡፡ #EthioFM

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT