TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የካቢኔ አባላትን ይፋ አደረገ !

የጊዜያዊ አስተዳደሩ የጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ገብረመስቀል ካሳ ዛሬ ለኢዜአ እንደገለጹት በክልሉ አዲስ የካቢኔ አባላት ተሹመው ስራ ጀምረዋል፡፡

ከሚያስፈልጉት 16 የካቢኔ አባላት መካከል 11 ተሿሚዎች በይፋ ስራ መጀመራቸውን አቶ ገብረመስቀል አስታውቀዋል፡፡

ያልተሟሉ የካቢኔ አባላት በቀጣይ ሳምንታት ተሟልተው ወደ ስራ እንደሚገቡ ተናግረዋል።

አስራ አንዱ (11) የካቢኔ አባላት ፡-

1. ዶ/ር ካህሣይ ብርሃኑ - የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ

2. ኢንጂነር አሉላ ሃብተአብ - የኮንስትራክሽን፣ መንገድ እና ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ

3. ዶክተር ፋሲካ አምደስላሴ - የጤና ቢሮ ኃላፊ

4. አቶ አበራ ንጉሴ - የፍትህ ቢሮ ኃላፊ

5. ወይዘሮ እቴነሽ ንጉሴ - የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ

6. አቶ ዮሴፍ ተስፋይ - የንግድ፣ ኢንዱስትሪ እና ከተማ ልማት ቢሮ ኃላፊ

7. ዶክተር ተስፋይ ሰለሞን - የትምህርት ቢሮ ኃላፊ

8. ዶክተር ገብረህይወት ለገሠ - የውሃ ጥናትና ዲዛይን ቢሮ ኃላፊ

9. አቶ ሰለሞን አበራ - የውሃ ሃብት ቢሮ ኃላፊ

10. አቶ አብርሃ ደስታ - የማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ

11. አቶ ገ/መስቀል ካሣ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የጽ/ቤት ኃላፊ

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#BuleHoraUniversity

የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የነባር የአንደኛ እና ከዛ በላይ የተማሪዎች ከነገ ማለትም ታህሣስ 16/2013 ጀምሮ ተማሪዎችን ይቀበላል፡፡

የዩኒቨርሲቲውን የቅበላ ዝግጅት የሚያሳዩ በፎቶዎችን ከላይ መመልከት ይቻላል።

በሌላ በኩል ፦

• ዶ/ር ጉሚ ቦሩ የቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዜዳንት ሆነው ተመድበዋል።

• ዶ/ር ታምሩ አኖሌ የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዜዳንት ሆነው ተመድበዋል።

• ዶ/ር ሮባ ደምቢ የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር እና ተማሪዎች አገልግሎት ምክትል ፕሬዜዳንት ሆነው ተመድበዋል።

• ኢንጂነር አብርሃም ባያብል የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ተቋማዊ ልማት ምክትል ፕሬዜዳንት ሆነው ተመድበዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#NEBE

ነገ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የመጪውን ምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ይፋ እንደሚያደርግ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር በድረገፁ ዘግቧል።

ምርጫ ቦርድ በምርጫ የጊዜ ሰሌዳው ላይ ከ47 የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ጋር ለመምከር ነገ በአዲስ አበባ ስብሰባ ጠርቷል።

በነገው ምክክር መድረክ ላይ ዝርዝር የምርጫ ክንውኖችን የያዘ የጊዜ ሰሌዳ ለፖለቲካ ፓርቲዎች እንደሚቀርብ የቦርዱ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ ሶልያና ሽመልስ ተናግረዋል።

Via Ethiopia Insider
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#COVID19Ethiopia

የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 5,503
• በበሽታው የተያዙ - 410
• ህይወታቸው ያለፈ - 12
• ከበሽታው ያገገሙ - 1,021

አጠቃላይ 121,399 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,882 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ 106,845 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።

236 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#WolaitaSodo ትላንት በወላይታ ሶዶ ከተማ 'መርካቶ ገበያ' በደረሰው የእሳት አደጋ ጉዳት የደረሰባቸውን ነጋዴዎች የዞኑ አስተዳደር ከመላው የወላይታ ህዝብ ጋር በመሆን ለመደገፍ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት ዶክተር እንድርያስ ጌታ አሳውቀዋል። በአደጋው የተጎዱ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋምና ዘላቂ መፍትሔ ለመፍጠር አንድ አቢይ እና የተለያዩ ንዑሳን ኮሚቴዎችን ተቋቁሟል…
#WoalitaSodo

በዎላይታ ሶዶ በተከሰተዉ የእሳት አደጋ ለተጎዱ ነጋዴዎች ጊዜያዊ አማራጭ የገበያ ቦታ እየተዘጋጀ ነዉ፡፡

በተለምዶ መናፈሻ ተብሎ የሚጠራዉ የቀድሞ የዎላይታ ዞን ፖሊስ መምሪያ ምድረ ግቢ ነዉ በአማራጭ ገበያ ቦታነት እየተዘጋጀ የሚገኘዉ፡፡

የከተማ አስተዳደሩ እና የዞኑ መንግስት ከተጎጂዎቹ ጋር ተወያይተው በተስማሙት መሰረት ነው ስራው የተጀመረው።

ነጋዴዎቹ በሚዘጋጅላቸዉ ጊዜያዊ ቦታ እየሠሩ ጎን ለጎን ነባሩ መርካቶ ገበያ ተገንብቶ የሚጠናቀቅ ይሆናል ብሏል ከተማ አሰተዳደሩ።

ነባሩ የመርካቶ ገበያ ግንባታ በዘመናዊ መልኩ ሳይቆይ የሚጀምር እንደሚሆን ተገልጿል።

Via Wolaita City Administration
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#PASSPORT

የኢሚግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ በቴክኒክ ችግር ምክንያት አቋርጦት የነበረውን የፓስፖርት አገልግሎት ከዛሬ ጀምሮ እንደሚቀጥል ገልጿል።

ኤጀንሲው ደንበኞች አገልግሎቱን ከዛሬ ታህሳስ 16 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ ማግኘት እንደሚችሉ በአጭር የፅሁፍ መልዕክት አሳውቋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#NEBE

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ 6ተኛ አገራዊ ምርጫን አስመልክቶ ከዚህ ቀደም ከተካሄዱ ምክክሮች በኋላ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን እንዲሁም መደረግ ስላለባቸው ተጨማሪ ጉዳዮች እና የጊዜ ሰሌዳን አስመልክቶ ከፓለቲካ ፓርቲዎች ጋር እየተወያየ ይገኛል።

ዛሬ የምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ይፋ ይደረጋል።

አሁን ላይ የቦርዱ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱኳን ሚደቅሳ የቀድሞ ምክክሮችን በማስከተል የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን ለፓርቲ አመራሮችና ተወካዮች በማቅረብ ላይ ናቸው።

#TikvahFamilyAA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#WolaitaSodo ትላንት በወላይታ ሶዶ ከተማ 'መርካቶ ገበያ' በደረሰው የእሳት አደጋ ጉዳት የደረሰባቸውን ነጋዴዎች የዞኑ አስተዳደር ከመላው የወላይታ ህዝብ ጋር በመሆን ለመደገፍ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት ዶክተር እንድርያስ ጌታ አሳውቀዋል። በአደጋው የተጎዱ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋምና ዘላቂ መፍትሔ ለመፍጠር አንድ አቢይ እና የተለያዩ ንዑሳን ኮሚቴዎችን ተቋቁሟል…
#UPDATE

በወላይታ ሶዶ ከተማ 'መርካቶ ገበያ' ደርሶ በነበረው የእሳት አደጋ 1.5 ቢሊዮን ብር የሚገመት ንብረት መውደሙን ተገለፀ።

42 ሺ የሚሆኑ ዜጎች በቀጥታና በተዘዋዋሪ በአደጋው ለቀውስ መጋለጣቸው ተነግሯል።

የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ከተጎጅዎች ጋር ውይይት አድርገዋል።

በአደጋው ሀብት ንብረታቸውን ያጡ ነጋዴዎች አደጋው በመከሰቱ ለከፍተኛ የስነ ልቦና ቀውስ መዳረጋቸውን በማንሳት ሀብታቸውን በማጣታቸው ቤተሰቦቻቸውን ጨምሮ በርካቶች ለከፋ ችግር ተጋላጭ በመሆናቸው ስጋት ገብቶናል ብለዋል።

የክልሉ መንግስትና ሁሉም ዜጋ ተገቢውን ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ጥሪ አቅርበዋል።

የደቡብ ከልል ምክትል ርዕስ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳው ከእለታዊ ድጋፍ ጀምሮ እስከ መልሶ ማቋቋል ድረስ የክልሉ መንግስት የድርሻውን እንደሚወጣ አረጋግጠዋል።

ተጊጂዎቹ ወደ ቀደመ ስራቸው እንዲመለሱ የማይክሮ ፋይናንስና የባንክ ብድር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር ይመቻቻል ብለዋል።

የመርካቶ ገበያ ማእከል ለተመሣሣይ አደጋ ተጋላጭ እንዳይሆን በዘመናዊ መንገድ እንዲገነባ ድጋፍ የክልሉ መንግስት ያደርጋል ብለዋል።

ለመነሻ እንዲሆን የደቡብ ክልል መንግስት የ10 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል።

Via Wolaita Zone Communication
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የሙለር ሪል እስቴት ባለቤት አቶ ሙልጌታ ተስፋኪሮስ በ1 መቶ ሺህ ብር ዋስ እንዲወጡ ፈቀደ !

አቶ ሙልጌታ ተስፋኪሮስ በተጠረጠሩበት የህወሓት ቡድንን በገንዘብ የመደገፍ ወንጀል የ1 መቶ ሺህ ብር ዋስ አስይዘው እንዲወጡ ተፈቀደላቸው፡፡

በእሳቸው መዝገብ ያሉ 2 ተጠርጣሪዎች ፦
- ሓይላይ መዝገበ
- ሳሙኤል አባዲ የ30,000 ብር ዋስ አስይዘው እንዲወጡ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት አዟል፡፡

ፖሊስ በተጠረጠሩበት ወንጀል በቂ ማስረጃ ያለማሰባሰቡን ፍርድ ቤቱ ገልጿል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ በዋስ ከእስር እንዲወጡ ቢፈቀድላቸውም ከሀገር እንዳይወጡ ፍርድ ቤቱ እግድ ጥሏል፡፡ (ኤፍ ቢ ሲ)

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ባደረገው ወይይት ቦርዱ ስላከናወናቸው ተግባራት ገለጻ አድርጓል።

በዚህም መመሪያዎችን በሚመለከት፣ የጸጥታና ተያያዥ ሥራዎች፣ የፖርቲዎች ምዝገባ የስርዓተ ጾታ አካታችነት እንዲሁም ኮቪድ 19 አስመልክቶ ስሰተሰሩ ሥራዎች የቦርዱ ሰብሳቢ ብርቱኳን ሚዴቅሳ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

https://telegra.ph/Tikvah-12-25-2

@TikvahethiopiaBot
#BREAKING

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ድምጽ መስጫ ቀን ግንቦት 28 እንዲሆን በረቂቅ የጊዜ ሰሌዳው ላይ አሳውቋል።

የአዲስ አበባ ከተማ እና የድሬደዋ ከተማ መስተዳድር የድምጽ መስጫ ቀን ሰኔ 5 መሆኑን ገልጿል።

ቦርዱ ዝርዝር የጊዜ ሰሌዳውን ይፋ አድርጓል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#BREAKING የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ድምጽ መስጫ ቀን ግንቦት 28 እንዲሆን በረቂቅ የጊዜ ሰሌዳው ላይ አሳውቋል። የአዲስ አበባ ከተማ እና የድሬደዋ ከተማ መስተዳድር የድምጽ መስጫ ቀን ሰኔ 5 መሆኑን ገልጿል። ቦርዱ ዝርዝር የጊዜ ሰሌዳውን ይፋ አድርጓል። @tikvahethiopia
#Tigray

ይህ የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ የትግራይ ክልልን አያካትትም ተብሏል።

የምርጫ ቢሮዎች መከፈት የክልል መስተዳድር አባላት ከፍተኛ ትብብር ስለሚያስፈልገው፤ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ይህንን ድጋፍ ለማድረግ ጊዜ ስለሚያስፈልገው እንዲሁም በክልሉ የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለምርጫ በሚስማማ መልኩ መመቻቸቱ ሲረጋገጥ በክልሉ የሚደረገው ምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ቦርዱ የሚያሳውቅ ይሆናል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የደቡብ ምዕራብ ህዝበ ውሳኔ !

ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የደቡብ ምዕራብ ህዝበ ውሳኔ ድምፅ መስጫ ቀን ግንቦት 28 ቀን 2013 ዓ/ም እንዲሆን ዛሬ ይፋ ባደረገው ረቂቅ የጊዜ ሰሌዳው አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia