TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Metekel በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን "የጸጥታ ችግር" ጋር በተያያዘ እጃቸው እንዳለበት የተረጋገጠ ከፍተኛና በየደረጃው ያሉ አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋል እንደጀመሩ የክልሉ መንግስት ዛሬ ምሽት ገልጿል። እስካሁን ድረስ በቁጥጥር ስር የዋሉ ፦ • አቶ ቶማስ ኩዊ ፡- የኢፌዴሪ ሠራተኛ እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የማኅበራዊ ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ • አቶ አድጎ አምሳያ፡- የቀድሞው የክልሉ…
#Metekel

ዛሬ ጥዋት 2 የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

በቁጥጥር ስር የዋሉት የክልሉ ግዢ እና ንብረት ማስወገድ ዋና ዳይሬክተር ገመቹ አመንቴ እንዲሁም የገጠር መንገድና ትራንስፖርት ባለስልጣን ምክትል ዳይሬክተር አድማሱ ሞርካ ናቸው።

በትላንትናው ዕለት በኩጅ ቀበሌ የተፈጠው ችግር ከተከሰተ በኃላ እነዚህ ከፍተኛ አመራሮች #እጃቸው_አለበት ተብለው ተጠርጥረው ነው የታሰሩት።

አመራሮቹ ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉት ከህበረተሰቡ በተሰጠ ጥቆማ ነው።

በቀጣይም ከህብረተሰቡ በሚሰጥ ጥቆማ ለችግሩ መባባስ ድርሻ አላቸው የተባሉ የትኛውም የቤጉ ክልል አመራር ሆነ የፀጥታ አካል ተጣርቶ እርምጃ ይወሰድበታል ብሏል ክልሉ።

በትላንትናው ዕለት አምስት የክልሉ አመራሮች በቀጥጥር ስር እንደዋሉ መገለፁ ይታወሳል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የደረግ ባለስልጣናቱ እንዴት ጣልያን ኤምባሲ ገቡ ? (በ2017 በቲክቫህ ኢትዮጵያ ላይ የወጣ አጭር ፅሁፍ) © #ViceNews #ጋዜጠኛ_ደረጄ_ኃይሌ ነገሩ እንዲህ ነው ኢትዮጵያን ለ7 ቀናት ያስተዳደሩት ሌ/ጀነራል ተስፋዬ ገ/ኪዳን ወይም 'የተስፋዬዎች መንግስት' ሀገሪቷን መቆጣጠር ሲሳነው ይሸሻል። ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ሀገሪቷን በተቆጣጠረበት እለት አንዳንዱ የደርግ ባለስልጣን ከሀገር ይወጣል ወደ 13…
#UPDATE

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በእነ ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማሪያም የክስ መዝገብ የተከሰሱና በጣሊያን ኤምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ለ30 ዓመታት በጥበቃ ስር የነበሩ ሌ/ጀነራል አዲስ ተድላ እና ሌ/ኮሌኔል ብርሃኑ ባየህ ጉዳይ ላይ ብይን ሰጥቷል፡፡

በዚህም መሰረት ሌ/ጄነራል አዲስ ተድላና ሌ/ኮሎኔል ብርሃኑ ባየህ ከጣሊያን ኤምባሲ በአመክሮ እንዲለቀቁ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግና ለፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

ትዕዛዙ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል ለጣሊያን ኤምባሲ፣ እንዲሁም ለሌ/ጀነራል አዲስ ተድላና ለሌ/ኮሎኔል ብርሃኑ ባየህ እንዲደርስ ፍርድ ቤቱ አዟል፡፡ (ኢቲቪ)

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የካቢኔ አባላትን ይፋ አደረገ !

የጊዜያዊ አስተዳደሩ የጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ገብረመስቀል ካሳ ዛሬ ለኢዜአ እንደገለጹት በክልሉ አዲስ የካቢኔ አባላት ተሹመው ስራ ጀምረዋል፡፡

ከሚያስፈልጉት 16 የካቢኔ አባላት መካከል 11 ተሿሚዎች በይፋ ስራ መጀመራቸውን አቶ ገብረመስቀል አስታውቀዋል፡፡

ያልተሟሉ የካቢኔ አባላት በቀጣይ ሳምንታት ተሟልተው ወደ ስራ እንደሚገቡ ተናግረዋል።

አስራ አንዱ (11) የካቢኔ አባላት ፡-

1. ዶ/ር ካህሣይ ብርሃኑ - የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ

2. ኢንጂነር አሉላ ሃብተአብ - የኮንስትራክሽን፣ መንገድ እና ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ

3. ዶክተር ፋሲካ አምደስላሴ - የጤና ቢሮ ኃላፊ

4. አቶ አበራ ንጉሴ - የፍትህ ቢሮ ኃላፊ

5. ወይዘሮ እቴነሽ ንጉሴ - የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ

6. አቶ ዮሴፍ ተስፋይ - የንግድ፣ ኢንዱስትሪ እና ከተማ ልማት ቢሮ ኃላፊ

7. ዶክተር ተስፋይ ሰለሞን - የትምህርት ቢሮ ኃላፊ

8. ዶክተር ገብረህይወት ለገሠ - የውሃ ጥናትና ዲዛይን ቢሮ ኃላፊ

9. አቶ ሰለሞን አበራ - የውሃ ሃብት ቢሮ ኃላፊ

10. አቶ አብርሃ ደስታ - የማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ

11. አቶ ገ/መስቀል ካሣ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የጽ/ቤት ኃላፊ

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#BuleHoraUniversity

የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የነባር የአንደኛ እና ከዛ በላይ የተማሪዎች ከነገ ማለትም ታህሣስ 16/2013 ጀምሮ ተማሪዎችን ይቀበላል፡፡

የዩኒቨርሲቲውን የቅበላ ዝግጅት የሚያሳዩ በፎቶዎችን ከላይ መመልከት ይቻላል።

በሌላ በኩል ፦

• ዶ/ር ጉሚ ቦሩ የቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዜዳንት ሆነው ተመድበዋል።

• ዶ/ር ታምሩ አኖሌ የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዜዳንት ሆነው ተመድበዋል።

• ዶ/ር ሮባ ደምቢ የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር እና ተማሪዎች አገልግሎት ምክትል ፕሬዜዳንት ሆነው ተመድበዋል።

• ኢንጂነር አብርሃም ባያብል የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ተቋማዊ ልማት ምክትል ፕሬዜዳንት ሆነው ተመድበዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#NEBE

ነገ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የመጪውን ምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ይፋ እንደሚያደርግ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር በድረገፁ ዘግቧል።

ምርጫ ቦርድ በምርጫ የጊዜ ሰሌዳው ላይ ከ47 የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ጋር ለመምከር ነገ በአዲስ አበባ ስብሰባ ጠርቷል።

በነገው ምክክር መድረክ ላይ ዝርዝር የምርጫ ክንውኖችን የያዘ የጊዜ ሰሌዳ ለፖለቲካ ፓርቲዎች እንደሚቀርብ የቦርዱ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ኃላፊ ሶልያና ሽመልስ ተናግረዋል።

Via Ethiopia Insider
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#COVID19Ethiopia

የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 5,503
• በበሽታው የተያዙ - 410
• ህይወታቸው ያለፈ - 12
• ከበሽታው ያገገሙ - 1,021

አጠቃላይ 121,399 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,882 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ 106,845 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።

236 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#WolaitaSodo ትላንት በወላይታ ሶዶ ከተማ 'መርካቶ ገበያ' በደረሰው የእሳት አደጋ ጉዳት የደረሰባቸውን ነጋዴዎች የዞኑ አስተዳደር ከመላው የወላይታ ህዝብ ጋር በመሆን ለመደገፍ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት ዶክተር እንድርያስ ጌታ አሳውቀዋል። በአደጋው የተጎዱ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋምና ዘላቂ መፍትሔ ለመፍጠር አንድ አቢይ እና የተለያዩ ንዑሳን ኮሚቴዎችን ተቋቁሟል…
#WoalitaSodo

በዎላይታ ሶዶ በተከሰተዉ የእሳት አደጋ ለተጎዱ ነጋዴዎች ጊዜያዊ አማራጭ የገበያ ቦታ እየተዘጋጀ ነዉ፡፡

በተለምዶ መናፈሻ ተብሎ የሚጠራዉ የቀድሞ የዎላይታ ዞን ፖሊስ መምሪያ ምድረ ግቢ ነዉ በአማራጭ ገበያ ቦታነት እየተዘጋጀ የሚገኘዉ፡፡

የከተማ አስተዳደሩ እና የዞኑ መንግስት ከተጎጂዎቹ ጋር ተወያይተው በተስማሙት መሰረት ነው ስራው የተጀመረው።

ነጋዴዎቹ በሚዘጋጅላቸዉ ጊዜያዊ ቦታ እየሠሩ ጎን ለጎን ነባሩ መርካቶ ገበያ ተገንብቶ የሚጠናቀቅ ይሆናል ብሏል ከተማ አሰተዳደሩ።

ነባሩ የመርካቶ ገበያ ግንባታ በዘመናዊ መልኩ ሳይቆይ የሚጀምር እንደሚሆን ተገልጿል።

Via Wolaita City Administration
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#PASSPORT

የኢሚግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ በቴክኒክ ችግር ምክንያት አቋርጦት የነበረውን የፓስፖርት አገልግሎት ከዛሬ ጀምሮ እንደሚቀጥል ገልጿል።

ኤጀንሲው ደንበኞች አገልግሎቱን ከዛሬ ታህሳስ 16 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ ማግኘት እንደሚችሉ በአጭር የፅሁፍ መልዕክት አሳውቋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#NEBE

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ 6ተኛ አገራዊ ምርጫን አስመልክቶ ከዚህ ቀደም ከተካሄዱ ምክክሮች በኋላ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን እንዲሁም መደረግ ስላለባቸው ተጨማሪ ጉዳዮች እና የጊዜ ሰሌዳን አስመልክቶ ከፓለቲካ ፓርቲዎች ጋር እየተወያየ ይገኛል።

ዛሬ የምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ይፋ ይደረጋል።

አሁን ላይ የቦርዱ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱኳን ሚደቅሳ የቀድሞ ምክክሮችን በማስከተል የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን ለፓርቲ አመራሮችና ተወካዮች በማቅረብ ላይ ናቸው።

#TikvahFamilyAA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#WolaitaSodo ትላንት በወላይታ ሶዶ ከተማ 'መርካቶ ገበያ' በደረሰው የእሳት አደጋ ጉዳት የደረሰባቸውን ነጋዴዎች የዞኑ አስተዳደር ከመላው የወላይታ ህዝብ ጋር በመሆን ለመደገፍ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት ዶክተር እንድርያስ ጌታ አሳውቀዋል። በአደጋው የተጎዱ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋምና ዘላቂ መፍትሔ ለመፍጠር አንድ አቢይ እና የተለያዩ ንዑሳን ኮሚቴዎችን ተቋቁሟል…
#UPDATE

በወላይታ ሶዶ ከተማ 'መርካቶ ገበያ' ደርሶ በነበረው የእሳት አደጋ 1.5 ቢሊዮን ብር የሚገመት ንብረት መውደሙን ተገለፀ።

42 ሺ የሚሆኑ ዜጎች በቀጥታና በተዘዋዋሪ በአደጋው ለቀውስ መጋለጣቸው ተነግሯል።

የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ከተጎጅዎች ጋር ውይይት አድርገዋል።

በአደጋው ሀብት ንብረታቸውን ያጡ ነጋዴዎች አደጋው በመከሰቱ ለከፍተኛ የስነ ልቦና ቀውስ መዳረጋቸውን በማንሳት ሀብታቸውን በማጣታቸው ቤተሰቦቻቸውን ጨምሮ በርካቶች ለከፋ ችግር ተጋላጭ በመሆናቸው ስጋት ገብቶናል ብለዋል።

የክልሉ መንግስትና ሁሉም ዜጋ ተገቢውን ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ጥሪ አቅርበዋል።

የደቡብ ከልል ምክትል ርዕስ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳው ከእለታዊ ድጋፍ ጀምሮ እስከ መልሶ ማቋቋል ድረስ የክልሉ መንግስት የድርሻውን እንደሚወጣ አረጋግጠዋል።

ተጊጂዎቹ ወደ ቀደመ ስራቸው እንዲመለሱ የማይክሮ ፋይናንስና የባንክ ብድር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር ይመቻቻል ብለዋል።

የመርካቶ ገበያ ማእከል ለተመሣሣይ አደጋ ተጋላጭ እንዳይሆን በዘመናዊ መንገድ እንዲገነባ ድጋፍ የክልሉ መንግስት ያደርጋል ብለዋል።

ለመነሻ እንዲሆን የደቡብ ክልል መንግስት የ10 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል።

Via Wolaita Zone Communication
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia