TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.1K photos
1.5K videos
211 files
4.09K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#GondarUniversity

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ስራ አመራር ቦርድ ታኅሳስ 14 ቀን 2013 ባደረገው ስብሰባ ለዶ/ር በላይ ተሰማን እና ዶ/ር ውዱ ተመስገንን የሙሉ ኘሮፌሰርነት ማዕረግ እንዲሰጣቸው ወስኗል።

ዩኒቨርሲቲው ኘሮፌሰር በላይ ተሰማ እና ኘሮፌሰር ውዱ ተመስገን ለዚህ ስኬት በመብቃታቸው የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፏል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
TIKVAH-ETHIOPIA
#TikvahFamilyBulenWoreda ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ቡለን ወረዳ ከትላንት ሌሊት ጀምሮ እስከ ጠዋት በዘለቀው ጥቃት ከ 96 በላይ ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን የቡለን ወረዳ በኩጂ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑ የቲክቫህ አባላት ገልጸዋል። እስካሁን ድረስ በግልጽ ስለተፈጸመውም ጥቃት ይህ ነው የሚባል መረጃ ከሚመለከታቸው አካላት የተሰማ ነገር የለም። የምን ያህል ሰው ህይወት እንዳለፈም በውል…
#UPDATE

በመተከል ዞን የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት ቃል አቀባይ ኮ/ል አያሌው በየነ ዛሬ በቡለን ወረዳ ንጹሃን መገደላቸውን እንዳረጋገጡ አል ዓይን በድረገፁ አስነብቧል።

ቃል አቀባዩ የሟቾቹ ቁጥር ከ100 ሊበልጥም ሊያንስም ይችላል ብለዋል፡፡

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ማምሻውን ባወጣው መግለጫ በቡለን ወረዳ ኩጂ ቀበሌ በንፁሃን ላይ አሳዛኝ ጥቃት መፈፀሙን አሳውቋል።

ምን ያህል ንፁሃን እንደተገደሉ አልገለፀም።

የክልሉ መንግስት በጥቃቱ በሰዎች እና ንብረት ላይ ጎዳት መድረሱንም ገልጿል።

መከላከያ ሰራዊት ፣ እና የክልሉ ፀጥታ አካላት በጥቃት አድራሾቹ ላይ እርምጃ እየወሰዱና አካባቢውን እያረጋጉ ነው ብሏል።

በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ ቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት አሁንም በ www.tikvahethiopia.net ላይ የደህንነት እና የፀጥታ ስጋት እንዳለባቸው እያሳወቁን ይገኛሉ።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#COVID19Ethiopia

የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 5,096
• በበሽታው የተያዙ - 351
• ህይወታቸው ያለፈ - 6
• ከበሽታው ያገገሙ - 1,006

አጠቃላይ 120,989 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,870 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ 105,824 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።

253 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Metekel

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን "የጸጥታ ችግር" ጋር በተያያዘ እጃቸው እንዳለበት የተረጋገጠ ከፍተኛና በየደረጃው ያሉ አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋል እንደጀመሩ የክልሉ መንግስት ዛሬ ምሽት ገልጿል።

እስካሁን ድረስ በቁጥጥር ስር የዋሉ ፦

• አቶ ቶማስ ኩዊ ፡- የኢፌዴሪ ሠራተኛ እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የማኅበራዊ ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ

• አቶ አድጎ አምሳያ፡- የቀድሞው የክልሉ ምክትል ርዕሰ-መስተዳድር

• አቶ ሽፈራው ጨሊቦ፡-የቀድሞ የክልሉ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ዳይሬክተር

• አቶ ባንዲንግ ማራ፡- የመተከል ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ

• አረጋ ባልቢድ፡- የመተከል ዞን የቀድሞ አመራር የነበሩ

#BenishangulGumuz #MetekelZone

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#Eritrea

ጎረቤታችን ኤርትራ ትላንት የመጀመሪያውን የኮሮና ቫይረስ ሞት አስተናግዳለች።

ሟቹ የ50 ዓመት እድሜ ያለው ወንድ #ደቀምሓረ ሆስፒተል ውስጥ የኮቪድ-19 ህክምና ሲደረግለት የነበረ ነው።

የዛሬ ሪፖርትን ጨምሮ በአጠቃላይ በኤርትራ ውስጥ 877 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ሲረጋገጥ የ1 ሰው ህይወት አልፏል፤ 599 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#BenishangulGumuz

የኢትዮጵያ መንግሥት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ያለውን ችግር ከመሠረቱ ለመፍታት አስፈላጊውን የተቀናጀ ኃይል እንዲሠማራ ማድረጉን ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ ዛሬ ጥዋት አሳወቁ።

በክልሉ መተከል ዞን ውስጥ በዜጎች ላይ እየተፈጸመ ያለው ጭፍጨፋ እጅግ አሳዛኝ ሆኗል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

በተፈጸመው ኢሰብአዊ የሆነ ተግባርም በእጅጉ ማዘናቸውን ገልፀዋል።

ጠ/ሚሩ ችግሩን በተለያዩ መንገዶች ለመፍታት የተደረገው ጥረት የሚፈለገውን ውጤት አላመጣም ብለዋል። መንግስት አሁን ላይ የተቀናጀ ኃይል እንዲሰማራ ማድረጉን በፌስቡክ ገፃቸው አሳውቀዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ሀገር መከላከያ ሰራዊት በወሰደው እርምጃ 42 ታጣቂዎች ተደመሰሱ !

በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ በኩጂ ቀበሌ በትናንትናው ዕለት በንጹኃን ዜጎች ላይ #ጥቃት ያደረሱ የታጠቁ ኃይሎች ላይ ሀገር መከላከያ ሰራዊት ተከታትሎ በወሰደው እርምጃ 42ቱ መደምሰሳቸውን የክልሉ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ከደቂቃዎች በፊት አሰውቋል።

የመከላከያ ሠራዊት በወሰደው እርምጃ ታጣቂዎቹ ለጥፋት ሲጠቀሙባቸው የነበሩ በርካታ የጦር መሳሪያዎችን እና ቀስቶችን በቁጥጥር ስር አዉሏል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#SecurityAlert

በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ ኤማንጂ፣በኖሽ፣ ዶቢ ቀበሌዎች አሁንም ከፍተኛ የደህንነት ችግር እንዳለባቸውን የቲክቫህ አባላት አሳውቀዋል።

ትላንት ለሊቱን በዶቢ ቀበሌ የተኩስ ድምፅ ሲሰማ እንደነበረ ጠቁመዋል። ስለደረሰው ጉዳት አጣርተው እንደሚያሳውቁን ገልፀዋል።

በተጠቀሱት አካባቢዎች ነዋሪው ቤት ንብረቱን ጥሎ እየሸሸ መሆኑንም አባላቶቻችን መልዕክት አድርሰዋል።

www.tikvahethiopia.net ላይ በየአካባቢው ያለውን የፀጥታ እንዲሁም ደህንነት ስጋት ልታሳውቁን ትችላላችሁ።

#TikvahFamilyBulenWoreda

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#TikvahFamilyBulenWoreda

ትላንት ለሊቱን በዶቢ ቀበሌ ከፍተኛ የተኩስ ድምፅ ሲሰማ ነበር።

በቀበሌው በተፈፀመው ጥቃት የአምስት ሰዎች ህይወታቸው እንዳለፈ በቡለን ወረዳ የቲክቫህ ኢትጵያ አባላት አሳውቀዋል።

አሁን በስልክ ያገኘናቸው የዶቢ ቲክቫህ አባላት የሟቾችን ስርዓተ ቀብር በስጋት ውስጥ ሆነው እያከናወኑ እንደሆነ ተናግረዋል።

ጥቃት አድራሾቹ ከበኩጂ ቀበሌ የተበተኑ የታጠቁ ኃይሎች እንደሆኑ የቲክቫህ አባላት በ www.tikvahethiopia.net ላይ ገልፀዋል።

አንድ አባላችን እንደገለፁልን ወደ #ዶቢ የገቡት ታጣቂዎች እስከ 300 የሚደርሱ ናቸው።

የመከላከያ ሰራዊት መረጃው ደርሶት በመግባት ምሽግ ይዞ ጥቃቱን ባይከላከል የሟቾች ቁጥር ሊጨምር ይችል ነበር ብለውናል።

አንድ የመከላከያ አባልም መጠነኛ ጉዳት ደርሶበታል።

የመተከል ዞን የቲክቫህ አባላት ለአካባቢው እንዲህ መሆን አመራሮችን ተጠያቂ ያደርጋሉ።

መንግስት ውስጡን እንዲፈትሽም በተደጋጋሚ አሳውቀዋል።

ነዋሪው ተስፋ ቆርጧል ፥ ግፍ እና መከራ አድክሞታል እጅግ በጣም አስቸኳይ መፍትሄ ይፈልጋል ብለዋል።

አሁንም ቢሆን በወረዳው የተለያዩ ቀበሌዎች ውስጥ ከፍተኛ የደህንነት ስጋት በመኖሩ የሚመመለከተው አካል ንፁሃንን እንዲታደግ አባላቶቻችን እየተማፀኑ ነው።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#የእሳት_አደጋ_በጅግጅጋ

በጅግጅጋ ከተማ በ ቀበሌ 02 በልዩ ስሙ ድብኡራሾ ሱቅ ተብሎ በሚታወቀው ቦታ ትላንት ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ የእሳት አደጋ ተከስቶ ነበር።

መነሻ መንስዔው ያልታወቀው እሳቱ የተነሳው ከአንድ ሱቅ መሆኑ ተገልጿል።

በሰው ህይወት ላይ ምንም አይነት ጉዳት እንዳልደረሰ የተገለፀ ሲሆን እሳቱ በፍጥነት በመዛመቱ 7 የንግድ ቦታዎች ላይ ከፍተኛ አደጋ አድረሷል።

ድምሩ ወደ 1.2 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ንብረት ነው።

#እሳት_አደጋ_በመቅደላ_ወረዳ

ትላንት ምሽት በደቡብ ወሎ ዞን መቅደላ ወረዳ የእሳት አደጋ ተከስቶ ነበር።

የእሳት አደጋው መነሀሪያ ሸድ ላይ የተከሰተ ነበር።

በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት የሌለ ሲሆን በንብረት ላይ የደረሰውን የጉዳት መጠን እና ተያያዥ ጉዳዮች እየተጣራ ነው።

ምንጭ፦ አዲስ ዘይቤ ድረገፅ፣ የመቅደላ ወረዳ ኮሚኒኬሽን
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Metekel በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን "የጸጥታ ችግር" ጋር በተያያዘ እጃቸው እንዳለበት የተረጋገጠ ከፍተኛና በየደረጃው ያሉ አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋል እንደጀመሩ የክልሉ መንግስት ዛሬ ምሽት ገልጿል። እስካሁን ድረስ በቁጥጥር ስር የዋሉ ፦ • አቶ ቶማስ ኩዊ ፡- የኢፌዴሪ ሠራተኛ እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የማኅበራዊ ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ • አቶ አድጎ አምሳያ፡- የቀድሞው የክልሉ…
#Metekel

ዛሬ ጥዋት 2 የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከፍተኛ አመራሮች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

በቁጥጥር ስር የዋሉት የክልሉ ግዢ እና ንብረት ማስወገድ ዋና ዳይሬክተር ገመቹ አመንቴ እንዲሁም የገጠር መንገድና ትራንስፖርት ባለስልጣን ምክትል ዳይሬክተር አድማሱ ሞርካ ናቸው።

በትላንትናው ዕለት በኩጅ ቀበሌ የተፈጠው ችግር ከተከሰተ በኃላ እነዚህ ከፍተኛ አመራሮች #እጃቸው_አለበት ተብለው ተጠርጥረው ነው የታሰሩት።

አመራሮቹ ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉት ከህበረተሰቡ በተሰጠ ጥቆማ ነው።

በቀጣይም ከህብረተሰቡ በሚሰጥ ጥቆማ ለችግሩ መባባስ ድርሻ አላቸው የተባሉ የትኛውም የቤጉ ክልል አመራር ሆነ የፀጥታ አካል ተጣርቶ እርምጃ ይወሰድበታል ብሏል ክልሉ።

በትላንትናው ዕለት አምስት የክልሉ አመራሮች በቀጥጥር ስር እንደዋሉ መገለፁ ይታወሳል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የደረግ ባለስልጣናቱ እንዴት ጣልያን ኤምባሲ ገቡ ? (በ2017 በቲክቫህ ኢትዮጵያ ላይ የወጣ አጭር ፅሁፍ) © #ViceNews #ጋዜጠኛ_ደረጄ_ኃይሌ ነገሩ እንዲህ ነው ኢትዮጵያን ለ7 ቀናት ያስተዳደሩት ሌ/ጀነራል ተስፋዬ ገ/ኪዳን ወይም 'የተስፋዬዎች መንግስት' ሀገሪቷን መቆጣጠር ሲሳነው ይሸሻል። ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ሀገሪቷን በተቆጣጠረበት እለት አንዳንዱ የደርግ ባለስልጣን ከሀገር ይወጣል ወደ 13…
#UPDATE

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በእነ ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማሪያም የክስ መዝገብ የተከሰሱና በጣሊያን ኤምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ለ30 ዓመታት በጥበቃ ስር የነበሩ ሌ/ጀነራል አዲስ ተድላ እና ሌ/ኮሌኔል ብርሃኑ ባየህ ጉዳይ ላይ ብይን ሰጥቷል፡፡

በዚህም መሰረት ሌ/ጄነራል አዲስ ተድላና ሌ/ኮሎኔል ብርሃኑ ባየህ ከጣሊያን ኤምባሲ በአመክሮ እንዲለቀቁ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግና ለፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

ትዕዛዙ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል ለጣሊያን ኤምባሲ፣ እንዲሁም ለሌ/ጀነራል አዲስ ተድላና ለሌ/ኮሎኔል ብርሃኑ ባየህ እንዲደርስ ፍርድ ቤቱ አዟል፡፡ (ኢቲቪ)

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የካቢኔ አባላትን ይፋ አደረገ !

የጊዜያዊ አስተዳደሩ የጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ገብረመስቀል ካሳ ዛሬ ለኢዜአ እንደገለጹት በክልሉ አዲስ የካቢኔ አባላት ተሹመው ስራ ጀምረዋል፡፡

ከሚያስፈልጉት 16 የካቢኔ አባላት መካከል 11 ተሿሚዎች በይፋ ስራ መጀመራቸውን አቶ ገብረመስቀል አስታውቀዋል፡፡

ያልተሟሉ የካቢኔ አባላት በቀጣይ ሳምንታት ተሟልተው ወደ ስራ እንደሚገቡ ተናግረዋል።

አስራ አንዱ (11) የካቢኔ አባላት ፡-

1. ዶ/ር ካህሣይ ብርሃኑ - የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ

2. ኢንጂነር አሉላ ሃብተአብ - የኮንስትራክሽን፣ መንገድ እና ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ

3. ዶክተር ፋሲካ አምደስላሴ - የጤና ቢሮ ኃላፊ

4. አቶ አበራ ንጉሴ - የፍትህ ቢሮ ኃላፊ

5. ወይዘሮ እቴነሽ ንጉሴ - የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ

6. አቶ ዮሴፍ ተስፋይ - የንግድ፣ ኢንዱስትሪ እና ከተማ ልማት ቢሮ ኃላፊ

7. ዶክተር ተስፋይ ሰለሞን - የትምህርት ቢሮ ኃላፊ

8. ዶክተር ገብረህይወት ለገሠ - የውሃ ጥናትና ዲዛይን ቢሮ ኃላፊ

9. አቶ ሰለሞን አበራ - የውሃ ሃብት ቢሮ ኃላፊ

10. አቶ አብርሃ ደስታ - የማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ

11. አቶ ገ/መስቀል ካሣ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የጽ/ቤት ኃላፊ

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#BuleHoraUniversity

የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የነባር የአንደኛ እና ከዛ በላይ የተማሪዎች ከነገ ማለትም ታህሣስ 16/2013 ጀምሮ ተማሪዎችን ይቀበላል፡፡

የዩኒቨርሲቲውን የቅበላ ዝግጅት የሚያሳዩ በፎቶዎችን ከላይ መመልከት ይቻላል።

በሌላ በኩል ፦

• ዶ/ር ጉሚ ቦሩ የቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዜዳንት ሆነው ተመድበዋል።

• ዶ/ር ታምሩ አኖሌ የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዜዳንት ሆነው ተመድበዋል።

• ዶ/ር ሮባ ደምቢ የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር እና ተማሪዎች አገልግሎት ምክትል ፕሬዜዳንት ሆነው ተመድበዋል።

• ኢንጂነር አብርሃም ባያብል የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ተቋማዊ ልማት ምክትል ፕሬዜዳንት ሆነው ተመድበዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia