TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59K photos
1.5K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#TikvahFamilyWolaita

እሳቱ ቢቀንስም እስካሁን 'ሙሉ በሙሉ' እንዳልጠፋ የወላይታ ሶዶ ቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት አሳውቀዋል።

ፎቶው ከጥዋት 1:00 ሰዓት አካባቢ የነበረውን ሁኔታ የሚያሳይ ነው።

#Nebeyu
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#TikvahFamilyWolaita

ወላይታ ሶዶ "መርካቶ ገበያ" ረፋድ 4:00 ሰዓት አካባቢ እሳቱ በመጠኑም ቢሆን ከቀነሰ በኃላ የነበረው ሁኔታ በቪድዮው የምትመለከቱትን ይመስላል። እሳቱ አሁንም 'ሙሉ በሙሉ' አልጠፋም። #MesMed

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#Djibouti

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ በ38ኛው አስቸኳይ የኢጋድ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ጅቡቲ ገብተዋል።

ከጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ጋር የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎችን ያካተተ የልኡካን ቡድን ወደ ስፍራው አቅንቷል።

በሌላ በኩል ፦

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ከሱዳኑ አቻቸው አብደላ ሓምዶክና ከሶማሊያው ፕሬዝዳንት መሀመድ አብዱላሂ ፋርማጆ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን አስታውቀዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የ3 ሰዎችን ህይወት የቀጠፈው የቦንብ ፍንዳታ !

ጠዋቱ 2፡30 ሠዓት በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ቦታው ስልጤ መስኪድ ጀርባ ለልማት በፈረሰ ክፍት ቦታ ላይ ማንነታቸው ባልታወቁ ግለሰቦች ተጥሎ በተገኘ የእጅ ቦንብ የጎዳና ተዳዳሪ የሆኑ የ3 ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ በ5 ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

ከፍንዳታው ጋር በተያያዘ ያለው የምርመራ ሂደት እየተጣራ መሆኑ ተገልጿል። የምርመራ ውጤቱ እንደተጠናቀቀ ለህብረተሰቡ ግልጽ ይደረጋል ተብሏል።

በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የልዩ ልዩና የተደራጁ ወንጀሎች ምርመራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮማንደር አለማየሁ አያልቄ ባስተላለፉት በተለያዩ ቦታዎች እንደ አልባሌ በሚጣሉ ቦንቦችና ፈንጂዎች ንፁሀን ሰለባ መሆናቸውን አስታውሰው ህብረተሰቡ ምንነታቸው ያልታወቁ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት ከመነካካት በመቆጠብ ለሚመለከታቸው የፀጥታ አካላት ጥቆማ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

Via Addis Ababa Police Commission
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#WolaitaSodo

ዛሬ ጥዋት በወላይታ ሶዶ "መርካቶ ገበያ" የደረሰው የእሳት አደጋ ሙሉ በሙሉ ማለት በሚችል ደረጃ ከፍተኛ ውድመት አድርሷል።

አደጋው በበርካታ የንግድ ሱቆች እና ተቋሟት ላይ ውድመት አስከትሏል።

ጥዋት የተነሳውን የእሳት አደጋ መቆጣጠር እንደተቻለ የከተማው አስተዳደር ያሳወቀው ከ6:20 በኃላ ነው።

እሳቱ ወደ ሌሎች አከባቢዎች እንዳይዛመት የወላይታ ሶዶ ህብረተሰብ ከፍተኛ ርብርብ አድርጓል።

የከተማ አስተዳደሩ ህብረተሰቡ ላደረገው ቀና ትብብር ምስጋውን አቅርቧል።

የአደጋውን መንስኤ ፖሊስ እያጣራው ይገኛል።

Via Wolaita Sodo Administration
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#SUDAN #ETHIOPIA

ኢትዮጵያ እና ሱዳን የድንበር ውዝግባቸውን ለመፍታት በሚቀጥለው #ማክሰኞ ድርድር እንደሚጀምሩ የጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

የሱዳን ጠ/ሚ ጽ/ቤት ባወጣው መግለጫ እንዳለው ሐምዶክ እና ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው ዕለት ተገናኝተው በመጪው ማክሰኞ ታኅሳስ 13 ቀን 2013 ዓ.ም የሁለቱን አገሮች ድንበር ለማካለል የተቋቋመው ኮሚቴ በሚያደርገው ድርድር ላይ ተወያይተዋል።

ኢትዮጵያ እና ሱዳን 1,600 ኪሎ ሜትር የሚረዝም ድንበር ይጋራሉ።

ምንጭ፦ AFP / Deutsche welle
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#COVID19Ethiopia

የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 5,373
• በበሽታው የተያዙ - 457
• ህይወታቸው ያለፈ - 7
• ከበሽታው ያገገሙ - 827

አጠቃላይ 119,951 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,853 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ 102,980 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።

267 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ትላንት የተካሄደው የኢጋድ ስብሰባ ፦

* ዶ/ር አብይ አህመድ በኢትዮጵያ ስለተፈጠረው ሁኔታ 'ስለተወሰደው የህግ ማስከበር' ዘመቻ ሪፖርት አቅርበዋል።

1. የኢትዮጵያ መንግሥት የአገሪቱን አንድነት እና መረጋጋት ለማረጋገጥ የወሰደው እርምጃ ቆራጥነት የተሞላበት መሆኑን የአፍሪከ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋቂ ማሓመት ተናግረዋል።

የፌደራል መንግሥት የወሰደው እርምጃ "የአገሪቱን ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት ለማስከበር" መሆኑን ጠቅሰው፣ ይህም ሁሉም አገራት የሚጠበቅባቸው ሕጋዊ ኃላፊነት ነው ብለዋል።

በትግራይ ክልል የተከሰተው ቀውስ ተከትሎ ከፍተኛ መጠን ያለው መፈናቀል መከሰቱን ተናግረው ፤ በዚህ ረገድ ኢጋድ ለስደተኞችና ለተፈናቀሉ ሰዎች የተለየ ትኩረት በመስጠት ኢትዮጵያ ከምታደርገው የሰብአዊ ድጋፍ ጥረት ከጎኗ እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል።

የኢጋድ አባላት ለኢትዮጵያ መንግሥት ድጋፋቸውን መግለጻቸው ተነግሯል።

2. ዶክተር አብይ አህመድ የኢጋድ አባል ሀገራት መንግስት የወሰደውን የህግ ማስከበር እርምጃ ህጋዊነት በመረዳታቸውና እውቅና በመስጠታቸው እንዲሁም ኢትዮጵያን ለመደገፍ በመግለፃቸው ምስጋና አቅርበዋል።

3. ከኢጋድ ስብሰባ ጎን ለጎን ውይይት ያደረጉት ዶ/ር አብይ እና የሱዳን ጠ/ሚ ዶ/ር አብደላ ሃምዶክ በድንበር አካባቢ ያጋጠመው ችግር እንዲቆም እና ችግሩ በውይይት እንዲፈታ ተስማምተዋል። ሱዳን ውስጥ ስላለው ችግርም የሃሳብ ልውውጥ አድርገዋል፤ ዶ/ር አብይ ለሱደን መንግስት ድጋፋቸውን ሰጥተዋል።

4. የሱማሊያና ኬንያ መሪዎች በዶ/ር አብይ አህመድ አማካኝነት ውይይት አድርገዋል። ችግራቸውን በውይይት ለመፍታት፣ የዴፕሎማሲ ግንኙነታቸውን ዳግም መጀመር መስማማታቸውን ተነግሯል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ፣ ጅቡቲ ቴሌቪዥን፣ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን፣ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር
@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#SUDAN #UNHCR #Ethiopia

በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል የነበረውን ግጭት ሸሽተው ወደ ሱዳን የተሰደዱ የሀገራችን ዜጎች ከ50,000 ይበልጣሉ።

#UNHCR እና የሱዳን ባለስልጣናት በመነጋገር 14,000 ስደተኞችን ከሃምደያት እና አብድራፊ ድንበር ሃም ራኩባ ካምፕ አዘዋውረዋቸዋል። ቦታው ከኢትዮጵያ ድንበር 70 KM ይርቃል።

አብዛኞቹ ስደተኞች ሴቶች እና ህፃናት እንደሆኑ የUNHCR መረጃ ያሳያል።

https://www.unhcr.org/news/stories/2020/12/5fd60c0f4/growing-needs-thousands-displaced-ethiopians-sudan.html

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#EASA

የአውሮፓ የአቪየሽን ደኅንነት ኤጀንሲ የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች ከዚህ በኋላ ወደ ሰማይ ለመመለስ ዝግጁ ናቸው ሲል ለBBC አረጋግጧል።

የኤጀንሰው ኃላፊ እንደተናገሩት አውሮፕላኖቹ ከዚህ በኋላ ለመብረር አንዳችም ስጋት እንደሌለባቸው እርግጠኛ ሆነን መናገር እንችላለን ብለዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ኢቀመማ በትግራይ ክልል ውስጥ በግጭት ለተጎዱ ወገኖች የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ መቀጠሉን አሳውቋል !

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር በትግራይ ክልል ተከስቶ በነበረው ግጭት ለተፈናቀሉ እና ጉዳት ለደረሰባቸው 2000 ወገኖች ከብር 3 ሚሊዮን በላይ ወጪ በማድረግ ልዩ ልዩ ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች ድጋፍ አድርጓል፡፡

ማኅበሩ በትግራይ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ካደረገው ድጋፍ መካከል ብርድ ልብስ፣ ምንጣፍ የመመገቢያ እና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች እና መሠረታዊ መድኃኒት ድጋፍ ይገኝበታል፡፡

ኢቀመማ ግጭቱ ከተከሰተ በኋላ ከዓለም ዓቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ እና ከሌሎች ተባባሪ አካላት ጋር በመሆን ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች አስቸኳይ ሠብዓዊ ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱ ይታወቃል፡፡

ከዚህም መካከል የመጀመሪያ ደረጃ የህክምና እርዳታ ፣ የአምቡላንስ አገልግሎት፣ የተጠፋፉ ቤተሰቦችን የማገናኘት፣ የተለያዩ የምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች ድጋፍ ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

ማኅበሩ በመቀለ ከተማ ተፈጥሮ የነበረውን የንፁህ መጠጥ ውሀ እጥረትን ተከትሎ ለከተማዋ ነዋሪዎች መጠጥ ውሀ ድጋፍ እንደተደረገ ይታወቃል፡፡

(የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር)

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia