TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ማይክ ፔንስ የኮቪድ-19 ክትባት ተከተቡ !

የአሜሪካው ም/ፕሬዚደንት ማይክ ፔንስ በቴሌቪዥን የቀጥታ ሥርጭት እየታዩ የኮሮና ቫይረስ ክትባት ተከተቡ።

ምክትል ፕሬዚደንቱ ለተመልካቾች እና ለዶክተሮች "ምንም ነገር አልተሰማኝም" ብለዋል።

ምክትል ፕሬዚደንት ማይክ ፔንስ በቀጥታ ሥርጭት እየታዩ የመከተባቸው ዓላማ የክትባቱን ደህንነትና ውጤታማነት ለማስተዋወቅና በአሜሪካ ሕዝቦች ዘንድ መተማመንን ለመፍጠር እንደሆነ ዋይት ሃውስ አስታውቋል።

የ61 ዓመቱ ማይክ ፔንስ ከባለቤታቸው ካረን እና አዳምስ ጋር የመጀመሪያዎቹን ሁለት ዶዝ የፋይዘር/ ባዮንቴክ ክትባት የወሰዱት ዛሬ ከቀኑ 10 ሰዓት ነው።

አሜሪካ 95 በመቶ በሽታውን ይከላከላል የተባለውን የፋይዘር/ ባዮንቴክ ክትባት መከተብ የጀመረችው ባሳለፍነው ሰኞ ነበር።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ሆሳዕና ከተማ ምክትል ከንቲባ ተሾመላት።

የሆሳዕና ከተማ ምክር ቤት የ4ኛ ዙር 7ኛ የስራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤ ተካሂዶ ነበር።

አቶ ደጉ ከባሞ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የሆሳዕና ከተማ ከንቲባ በመሆን ተሹመዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#SNNPRS

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ተራዝሞ የነበረው የ2012 ዓ/ም 8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በሰላማዊ ሁኔታ መጠናቀቁን የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

በደቡብ ኦሞ ዞን አንድ ተማሪ ለወንድሙ ለመፈተን ሞክሮ እጅ ከፍንጅ ተይዞ ከመታሰሩ ውጭ ፈተናው ከኩረጃ በነፃ ሁኔታ መጠናቀቁን ቢሮ አሳውቋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከጸጥታ ጋር ተያይዞ በኮንሶ፣ ማሎኮዛ ወረዳ ፣ በአሌ ልዩ ወረዳ እና በቤንቺ ሼኮ ዞን ጉራ ፈርዳ ወረዳ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች በአቅራቢያቸው በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎቻቸውን አስፈትነዋል።

በጉራጌ ዞን እነርኖር ወረዳ ከመዋቅር ጥያቄ ጋር ተያይዞ 494 ተማሪዎች ፈተና ላይ እንዳይቀመጡ መደረጉ ተገልጿል።

በአጠቃለይ በ3,782 የመፈተኛ ጣቢያዎች ወደ 292,769 ተማሪዎች ፈተና ወስደዋል።

ምንጭ፦ የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 6_284
• በበሽታው የተያዙ - 544
• ህይወታቸው ያለፈ - 12
• ከበሽታው ያገገሙ - 1,108

አጠቃላይ 119,025 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,843 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ 100,859 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።

261 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#መልዕክት

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የሁሉም አባላት ድምፅ የሚሰማባት ሰፊው ቤታችን ነው።

ትልቁ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ስራም ከ1.1 ሚሊዮን በላይ አባላት መካከል የመረጃ ልውውጥ እንዲኖር ማድረግ ነው።

ቲክቫህ ፦

- የሚዲያ ባለቤቶች እና የሚዲያ ሰዎች፣
- የጋዜጠኞች፣
- የጤና ባለሞያዎች፣
- የገበሬዎች፣ የአርሶና አርብቶ አደሮች
- የመንግስት እና የግል ሰራተኞች ፣
- የገዢ ፓርቲ ደጋፊዎችና አመራሮች ፣
- የተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊዎችና አመራሮች፣
- የተማሪዎች፣
- የንግድ ሰዎችና ባለሃብቶች የሌሎችም በርካታ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን መሰባሰቢያ ቤት ነው።

ቲክቫህ ከመነሻው የሃሳብ ብዝሃነት ለሀገር እድገት ያለውን ከፍተኛ ሚና የሚረዱ ፣ ለሀገር የሚያስቡ፣ በሶሻል ሚዲያ ላይ ለሚፅፉት እያንዳንዱ ቃል ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚያደርጉ አባላትን ባለፉት ዓመታት ማፍራት ችሏል።

የእውነተኞቹ የቲክቫህ አባላት መገለጫ ብስለት፣ እርጋታ፣ መረጃ ማመዛዘን፣ የነገን የአብሮነትና ጉዞ ማሰብ፣ ለወገን መቆርቆር ነው።

ያለፈውን አንድ ወር የሀገራችን ማህበራዊ ሚዲያ የለየለት የውሸት እንዲሁም የጥላቻ መድረክ ሆኖ ማለፉን ሁሉም የቲክቫህ አባላት የሚያውቀው ነው።

እንዲህ ያሉ ወቅቶች በተደጋጋሚ ስለገጠሙ እና በእንዲህ ያለ የውጥረት ሰዓት ላይ ማህበራዊ ሚዲያዎች እንዴት እንደሚዘወሩ ለቲክቫህ አባላት አዲስ አልነበረም።

ለዚህም ነው ከጥቂቶች / ከአዲስ አባላት ውጭ ሁሉም አባል በሚባል ደረጃ እያንዳንዱን ሁኔታ በፍፁም እርጋታ ሲከታተል የነበረው።

ያልሰሙትን ሰምተናል፣ ያላዩትን አይተናል ፣ ያልተደረገውን ተደርጓል እያሉ የተገኘውን ተባራሪ ወሬ ሁሉ በማህበራዊ ሚዲያዎች ሲያሰራጩ የነበሩ አካላት በጊዜ ሂደት ምን ምን ጉዳዮችን ሲዋሹ እንደነበር ሁሉም አባላት በትዝብት ተመልክቷል።

ምንም ያለተረገጠና ውቅቱን ያልጠበቀ እንዲሁም ተባራሪ ወሬዎችን ለህዝብ ሲያሰራጩ የከረሙት የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎችም ብዙ የሀገራችን እናቶች ፣ ወላጆችን በሀሰት ዜና አስነብተዋል፣ ብዙ ቀናትንም ያለ እንቅልፍ በጭንቀት አሳድረዋል።

እውን እኛ ያለንባት #ኢትዮጵያ እንደ ማህበራዊ ሚዲያው ያለች ብትሆን ለአንድም ቀን እንኳን በሀገራችን ባላደርን ነበር።

ውድ አባላት የዛሬው መልዕክታችን ፦

• መረጃ ለቲክቫህ 1.1 ሚሊዮን አባላት ለማሳወቅ ስትልኩ ስለምታውቁት /ስላረጋገጣችሁት/ ጊዜውን እና ወቅቱ ስለመጠበቁ ገምግማችሁ እንዲሆን፤
• ሁሉም ወገን ወገን ፈጥሮ በሚሰራው ዘመቻ ተጠልፋችሁ እንዳትወድቁ በመጠንቀቅ፤
• የአእምሮ ጤናችሁን ከሚያቃውስ የስድድብ፣ የጥላቻ አካባቢዎች በመራቅ፤
• የምትናፍቋችሁን የቲክቫህ ትግራይ ክልል አባላት በትዕግስት የመልዕክት ልውውጥ ማድረግ እስኪጀምሩ በመታገስ፤
• ያላረጋገጣችሁትን ጉዳይ ባለመናገር ፣
• በየማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የሚነገረው ሁሉ እውነት ነው እያላችሁ ለሰው ከማጋራት በመቆጠብ ፣
• በተለመደው እርጋታችሁን ፣ ትዕግስታችሁን ፣ መከባበራችሁን ፣ የነገ አብሮነታችሁን እና ሀገራችሁን በማሰብ ወደፊት ትቀጥሉ ዘንድ መልዕክት እናስተላልፋለን።

ሌላው በትግራይ ክልል ያሉ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን የቲክቫህ አባላት ደህንነት ለማወቅ እየሰራን ነው፤ ስልክ የሚሰራባቸው አካባቢዎች ያሉ አባላቶችን እያገኘን ነው።

የትግራይ ክልል የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት #የኢንተርኔት ግንኙነት በሚያገኙበት ጊዜ ከዞን፣ ከወረዳ እስከ ቀበሌ ድረስ መረጃዎችን አዲስ በተዘረጋው የቲክቫህ አባላት የመረጃ ልውውጥ መድርክ www.tikvahethiopia.net ላይ ያሳውቃሉ ብለን እንጠብቃለን።

ሌሎችም የቲክቫህ አባላት www.tikvahethiopia.net በመመዝገብ ስለአካባቢያችሁ ጉዳይ ብቻ የምታውቁትን ማካፈል ትችላላችሁ። የአንድ ክልል፣ ዞን፣ ወረዳ መረጃ በሌሎች አባላት አይታይም!

Tikvah/Hope/ተስፋ
#TikvahFamily❤️

@tikvahethiopiaBOT
#እንዳትጭበረበሩ_ተጠንቀቁ !

በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች በሃሰተኛ ማስታወቂያዎች ሰዎችን #የሚጭበረብሩ አካላት እየበዙ መምጣታቸውን የሚገልፅ ጥቆማ ደርሶናል።

እጅግ ዘመናዊ ስልኮችን በአሁን ሰዓት በገበያ ላይ ካላቸው ዋጋ እጅግ በወረደ ዋጋ "የማስታወቂያ ጊዜ ቅናሽ ነው" በሚሉ ሰዎች የተጭበረበሩና ገንዘባቸውን የተበሉ የቲክቫህ አባላት መልዕክት አድርሰዋል።

እነዚህ ግለሠቦቹ የሚሰሩበት አድራሻ የማይታወቅ ፤ ስልክ ቆጥራቸው የውጪ ፣ በቅድሚያ ሙሉ ክፍያ እንዲሰጣቸው የሚጠይቁ፣ ምንም አይነት ማንነታቸውን የሚገልፅ መረጃ የሌላቸው ናቸው።

በኦንላይ "እጅግ በርካሽ ዋጋ" ዘመናዊ ስልክ አገኘሁ በሚል እንዳይጨረበሩ ግብይቶን በአግባቡ ከሚሰሩ ፣ አድራሻ እና ማንነታቸው ከሚታወቅ ሰዎች ብቻ ያድርጉ።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#AtoLilayHailemariam

የትግራይ የጊዜያዊ አስተዳደር ከፍተኛ አመራር አቶ ሊላይ ኃይለማርያም መብራት በዓደዋ እና አክሱም ከተሞች በዚህ ሳምንት እንደሚገባ ለኢፕድ አሳውቀዋል።

በትግራይ ክልል በሚቀጥለው ሳምንት የባንክ አገልግሎት በሰፊው እንደሚጀምር አሳውቀዋል።

አቶ ሊላይ ፥ "መቐለ በጥሩ እንቅስቃሴ ውስጥ ነው ያለችው። ወደ ቀደመ መልኳ ተቀይራለች" ብለዋል።

የመንግስት ተቋማትም አገልግሎት እንዲሰጡ እንዲከፈቱ መደረጉን ተናግረዋል።

በሰለማዊ መንገድ የሚንቀሳቀሰው ሁሉም ሰው ወደ ሥራ ገበታው እንደተመለሰ አሳውቀዋል።

ጥሪውን ተቀብለው ወደሥራ ያልገቡ ሠራተኞች ላይ በአገሪቷ ህግ መሠረት ዕርምጃ እንደሚወሰድ ተናግረዋል።

MORE : https://telegra.ph/AtoLilay-12-19

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#ASTU

የአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (ASTU) በተለያዩ መርሃግብሮች ሲያስተምራቸው የነበሩ ተማሪዎቹን በዛሬው ዕለት እያስመረቀ ይገኛል።

ዛሬ 1 ሺህ 300 ተማሪዎችን እያስመረቀ የሚገኘው፡፡

ከዚህ ውስጥ 1 ሺህ 228 በመጀመሪያ ዲግሪ ሲሆን 70 በሁለተኛ ዲግሪ እንዲሁም 2 ተመራቂዎች በሶስተኛ ዲግሪ ናቸው።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በጣልያን ኢምባሲ መኖር ከጀመሩ 26 ዓመት ያስቆጠሩት የደርግ ከፍተኛ ባለስልጣናት👇
በጣልያን ኤምባሲ የሚገኙት የደርግ ባለስልጣናት !

በጣሊያን ኤምባሲ በቁም እስር ላይ የሚገኙት የሞት ፍርደኞቹ ሁለት የደርግ ዘመነ መንግሥት ባለሥልጣናት በአመክሮ እንዲፈቱ የፌደራሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ጠየቀላቸው፡፡

ባለሥልጣናቱ በዘር የማጥፋት ወንጀል የተከሰሱ መሆኑን ተከትሎ ዐቃቤ ሕግ ያለው ሕጋዊ አካሄድ በአመክሮ እንዲፈቱ ቀድሞ ውሳኔውን ላሳለፈው ፍርድ ቤት ጥያቄ ማቅረብ ነው ብሏል፡፡

የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የፕሬስ ሴክሪታሪያት ኃላፊ አወል ሱልጣን ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የፍርደኞቹ ውሳኔ ከሞት ወደ እድሜ ልክ እንዲቀየር አፅድቀዋል ብለዋል፡፡

ይህን ተከትሎም ዐቃቤ ሕግ ሁለቱ ግለሰቦች ላለፉት ሰላሳ (30) ዓመታት በጣልያን ኤምባሲ በቁም እስር ላይ የቆዩ መሆናቸውን መነሻ በማድግ በአመክሮ ቢፈቱ ሲል ምክረ ሃሳቡን ለፍርድ ቤት አቅርቦ ውሳኔው እየተጠባበቀ ነውም ብለዋል፡፡

በኤምባሲው ተጠልለው የሚገኙት የቀድሞ ወታደራዊ መኮንኖች የ85 ዓመቱ ሌተናል ኮሎኔል ብርሃኑ ባይህ እና የ77 ዓመቱ ሌተናል ጀነራል አዲስ ተድላ ናቸው።

ምንጭ፦ አሐዱ ቴሌቪዥን
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በጣልያን ኢምባሲ መኖር ከጀመሩ 26 ዓመት ያስቆጠሩት የደርግ ከፍተኛ ባለስልጣናት👇
የደረግ ባለስልጣናቱ እንዴት ጣልያን ኤምባሲ ገቡ ?

(በ2017 በቲክቫህ ኢትዮጵያ ላይ የወጣ አጭር ፅሁፍ)

© #ViceNews #ጋዜጠኛ_ደረጄ_ኃይሌ

ነገሩ እንዲህ ነው ኢትዮጵያን ለ7 ቀናት ያስተዳደሩት ሌ/ጀነራል ተስፋዬ ገ/ኪዳን ወይም 'የተስፋዬዎች መንግስት' ሀገሪቷን መቆጣጠር ሲሳነው ይሸሻል።

ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ሀገሪቷን በተቆጣጠረበት እለት አንዳንዱ የደርግ ባለስልጣን ከሀገር ይወጣል ወደ 13 የሚጠጉ ባለስልጣናት ደግሞ የጣልያንን በር ያንኳኳሉ ጣልያንም አላሳፈረቻቸውም ኑ ግቡ ትላቸዋለች።

ከገቡት መካካል አንዳንዱ ወዲያው ወጣ ሌላውም ጥቂት ቀናትን ቆይቶ ወጣ። ካልወጡት መካከል ግን ድፍን 26 ዓመት (ይህ ፅሁፍ በወቅቱ ሲፃፍ 2017 ነበር) ሙሉ በኤምባሲው ውስጥ እየኖሩ የሚገኙት 2 ባለስልጣናት ይገኛሉ።

ሁለቱም ባለስልጣናት የሞት ፍርድ የተፈረደባቸው ሲሆኑ የጣልያን ህገ መንግስት የሞት ፍርድን ስለማያስፈፅም ሁለቱን የደርግ ባለስልጣናት ለኢትዮጵያ መንግስት አሳልፎ አልሰጠም።

የጣልያን ኤምባሲ ሰዎቹን ገፍቶ ማስወጣትም አይፈልግም።

የጣልያን መንግስትም ሰዎቹን እንደ በጎ ፍቃድ ታሳሪዎች ነው የሚቆጥራቸው።

የቀድሞ ባለስልጣናቱን 'ከሰብአዊ መብት አያያዝ' ጋር በተገናኘ የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ጠበቃዎች እንዲሁም መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ይጎበኟቸዋል።

ጣልያን ኤምባሲ ከገቡት እንዲሁም ገብተው ከወጡት መካከል ሜጀር ጀነራል ስዩም መኮንን (በማረፊያ ቤት ህይወታቸው አልፏል) ፣ ወሌ ቸኮል ፣ ፍሲካ ሲደልል ፣ ሽመልስ ማዘንጊያ ፣ ዶ/ር አለሙ አበበ ፣ ሸዋንዳኝ በለጠ ይገኙበታል።

በአሁን ሰዓት ጣልያን ኤምባሲ ውስጥ የሚኖሩት ሁለቱ (2) ባለስልጣናት አንዱ የቀድሞ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር የነበሩት ብርሀኑ ባየህ እንዲሁም በደርግ ስርዓት ከፍተኛ ተሰሚነት የነበራቸው ሌተናል ጀነራል ሀዲስ ተድላ (የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማጆር ሹም) ናቸው።

ሀይሉ ይመንህ ራሳቸውን አጥፍተዋል።

ሌፍተናንት ጀነራል ተስፋዬ ገብረኪዳን የኢትዮጵያ የአንድ ሳምንት ፕሬዘደንት በብርሀኑ ባየህ እንደተገደሉ ይነገራል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#AddisAbaba

ትላንት "በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ" የወጣቶች እና በጎ ፍቃድ ቢሮ አስተባባሪነት በቢሮዉ ስር ባሉ 10 ወረዳና የኦሮሚያ ፣ አዲስ አበባ ፣ ደቡብ ፣ አማራ እና ትግራይ ወጣቶች አደረጃጀትን በማስተባበር በሰሚት የጋራ መኖርያ አከባቢ በመገኘት የጤፍ አጨዳ ፕሮግራም አድርገዋል።

ከፕሮግራሙ መልስ በጤፍ አጨዳዉ ላይ ለተሳተፉት በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች የለሚ ኩራ ክ/ከ የወጣቶችና በጎ ፍቃድ ቢሮ ሀላፊ አቶ ባጫ ጂሬኛ ምስጋና በማቅረብ የወጣቱ ሀይል በቀጣይ በክፍለ ከተማዉ ለሚሰሩ ስራዎች ለይ ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪ አቅረበዋል።

Via Amanuel Eticha (TikvahFamily)
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ዛሬ የብሔራዊ ስቴዲዬም ሁለተኛዉ እና የማጠቃለያ ምዕራፍ ግንባታ ፊርማ ተካሂዷል።

የሁለተኛ ምዕራፍ ስራዉ ዋና አካል የጣራ መሸከሚያ ምሶሶ ኮንክሪት ሙሊት ስራ መጀመሩን ስፖርት ኮሚሽን አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ሀሰተኛ የብር ኖት ሲያዘዋውር የነበረ ግለሰብ ተያዘ።

አበርገሌ ወረዳ 16, 900 #ሃሰተኛ የብር ኖቶች ሲያዘዋውር ነበር የተባለ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ሥር መዋሉን የወረዳው ፖሊስ ለኢዜአ አስታወቀ።

ተጠርጣሪው በቁጥጥር ሥር የዋለው ሃሰተኛ የብር ኖቶቹን ይዞ ትናንት በወረዳው ወርቃዲኑ ጥንስስ ከተማ ለመገበያየት ሲሞክር ተደርሶበት ነው።

በአሁኑ ወቅት ተጠርጣሪው ምርመራ እየተደረገበት መሆኑም ተገልጿል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#EuropeanUnion

የአውሮፓ ህብረት ኢትዮጵያን ጨምሮ ለሦስት ሃገራት የ23 ነጥብ 3 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ ማድረጉን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

ከኢትዮጵያ በተጨማሪ የተደረገው ድጋፍ ሱዳን እና ኬንያን እንደሚያካትት ህብረቱ ባወጣው መግለጫ ገልጿል፡፡

ከ23 ነጥብ 7 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ ውስጥ 18 ነጥብ 8 ሚሊየን ዩሮው በኢትዮጵያ በትግራይ ክልል ድጋፍ ለሚሹ ዜጎች የሚውል መሆኑን ነው የጠቀሰው፡፡

እንዲሁም ሁለት ሚሊየን ዩሮው ደግሞ ለሱዳን የተደረገ ድጋፍ መሆኑን ጠቅሷል፡፡

በተጨማሪም 2 ነጥብ 9 ሚሊየን ዮሮ የሚሆነው ደግሞ በኬንያ የምግብ ዋስትና ለተጋረጠው አደጋ የሚውል መሆኑ ነው የገለጸው፡፡

የአውሮፓ ህብረት በፈረንጆቹ 2020 ለኢትዮጵያ ያደረገው ድጋፍ 63 ነጥብ 2 ሚሊየን ዩሮ መድረሱን ገልጿል፡፡

@tikvahethiopiaBot