TIKVAH-ETHIOPIA
መቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን አስመረቀ ! መቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን በዛሬው ዕለት አስመርቋል። ዩኒቨርሲቲው ያስመረቃቸው 3290 ተማሪዎች በመጀመሪያ ዲግሪ ሲሆን ፤ 1 ደግሞ በሶስተኛ ዲግሪ መሆኑ ታውቋል። ከጠቅላላው ተመራቂዎች መካከል 30% እንዲሁም በጤና መስክ ከተመረቁት መካከል ደግሞ 38% ሴቶች መሆናቸው ከኢፕድ የተገኘው መረጃ ያሳያል። @tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#MekelleUniversity
ዛሬ መቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን አስመርቋል።
በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ ዶ/ር ሙሉ ነጋ እንዲሁም የዩኒቨርሲቲው ፕሬዜዳንት ፕሮፌሰር ፈትየን ኣባይን ጨምሮ የዩኒቨርሲቲው የቦርድ አባላት ተገኝተው ነበር።
የዛሬውን የምርቃት ድባብ የሚያሳዩ ፎቶዎች ከላይ ተያይዘዋል።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

#Tigray
የሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ የተመድ (UN) ከባድ ተሽከርካሪዎች ትላንት ትግራይ ክልል መግባታቸው ተገልጿል።
ትግራይ የገቡት ሰማንያ ከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎች ሲሆኑ 579 ሜትሪክ ቶን እህል አቅርበዋል።
እርዳታውን የጫኑት የተመድ መኪኖች ያቀኑት #ኤርትራውያን ስደተኞች ወደሚገኙበት ኣዲ ሓሩሽ እና ማይ ኣይኒ መጠለያ ጣቢያዎች ነው።
ተመድ (UN) እርዳታው ለ35 ሺህ ገደማ ስደተኞች #ለአንድ ወር እንደሚበቃ መግለፁን ከዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

#COVID19Ethiopia
የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :
• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 5,276
• በበሽታው የተያዙ - 475
• ህይወታቸው ያለፈ - 13
• ከበሽታው ያገገሙ - 1,782
አጠቃላይ 118,481 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,831 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ 99,751 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።
273 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

በዓዲግራት እና ውቅሮ ከተሞች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ዳግም ጀመረ !
በዓዲግራት እና ውቅሮ ከተሞች ተቋርጦ የነበረው የመብራት አገልግሎት ዛሬ ማምሻውን እንደጀመረ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አሳውቋል።
የሽረ፣ አክሱም እንዲሁም የአድዋ ከተሞች ኃይል እንዲያገኙ እየተሰራ መሆኑንም ተቋሙ ገልጿል።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
በዓዲግራት እና ውቅሮ ከተሞች ተቋርጦ የነበረው የመብራት አገልግሎት ዛሬ ማምሻውን እንደጀመረ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አሳውቋል።
የሽረ፣ አክሱም እንዲሁም የአድዋ ከተሞች ኃይል እንዲያገኙ እየተሰራ መሆኑንም ተቋሙ ገልጿል።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#Hawassa
ታህሳስ 19 ቀን 2013 ዓ/ም በሲዳማ ክልል በሀዋሳ ከተማ የሚከበረውን ዓመታዊው የቅዱስ ገብርኤል በዓል በተሳካ ሁኔታ እንዲከበር የቅድመ ዝግጅት ስራው በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ተገልጿል።
በዓሉ ሰላምና ፀጥታው ተጠብቆ ያለምንም እንከን በደማቅ ሁኔታ እንዲከበር ከተማ አስተዳደሩ ይህን ስራ በባለቤትነት የሚሰራ አብይ ኮሚቴ አቋቁሞ ስራዎችን እያከናወነ እንደሆነ አሳውቋል።
የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ለማከናወን የተቋቋመው አብይ ኮሚቴ ትላንት ውይይት ማካሄዱን የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ኮሚኒኬሽን አሳውቋል።

#FDREDefenseFORCE
የህወሓት አመራሮች የሚገኙበትን ለጠቆመ የ10 ሚልዮን ብር ሽልማት ማዘጋጁትን የኢፌዴሪ ሀገር መከላከያ ሠራዊት ማስታወቁን የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዘግቧል።
ሌ/ጀነራል አስራት ዴኔሮ እንደተናገሩት የህወሓት አመራሮችን በአጭር ጊዜ በቁጥጥር ስር ለማዋል የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ሽልማቱ መዘጋጀቱን ገልፀዋል።
በዚህም የመከላከያ ሠራዊት በህግ የሚፈለጉትን የህወሓት አመራሮች ያሉበትን ቦታ ለጠቆመ የ10 ሚሊዮን ብር ሽልማት እንደሚሰጥ አመልክተዋል።

ተመድ ለትግራይ ክልል መርጃ $35.6 ሚሊዮን ለግሷል !
ተመድ በአገር ውስጥ ለተፈናቀሉ እንዲሁም የሱዳንን ድንበር ተሻግረው ለስደት ለተዳረጉ ኢትዮጵያውያን መርጃ እንዲውል $35.6 ሚሊየን ለገሰ።
የ$13 ሚሊየን ወጪ የተደረገው ከተመድ ማዕከላዊ የአስቸኳይ ግብረ ምላሽ ድጎማ ነው ፤ የሚውለውም ኢትዮጵያ ውስጥ ለተፈናቀሉ ዜጎች ሲሆን ፤ ተጨማሪ $5 ሚሊየን ሱዳን በቅርቡ በስደተኛነት ለገቡቱ መርጃ ይውላል።
በተከታይ $12 ሚሊየን ከኢትዮጵያ የተመድ ሰብዓዊ እርዳታ ድጎማና $5.6 ከሱዳን የተመድ ሰብዓዊ እርዳታ ድጎማ ወጪ ሆኗል።
በእርዳታ ክፍፍሉ ወቅት ለሴቶች፣ ሕጻናት፣ አረጋውያን እና የግብረ አካል ጉዳተኞች ቅድሚያ እንደሚሰጥ ተመድ ገልጿል።
ተመድ በማያያዝም ፥ "እንዲህ ያሉት ግጭቶች አንዴ ከቁጥጥር ውጪ ከሆኑ ለማስቆም በእጅጉ አዋኪ ነው ። የተቀጠፉ ሕይወቶች አይመለሱም ፤ ዘላቂ ዕርሮዎችንም ይፈጥራሉ። በአሁኑ ወቅት ሕጻናት ከእርዳታ ተገልለዋል። ያልተገደበ ተደራሽነት እንዲኖረን እንሻለን" ብሏል። (SBS)

#FDREDefenseFORCE የህወሓት አመራሮች የሚገኙበትን ለጠቆመ የ10 ሚልዮን ብር ሽልማት ማዘጋጁትን የኢፌዴሪ ሀገር መከላከያ ሠራዊት ማስታወቁን የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዘግቧል። ሌ/ጀነራል አስራት ዴኔሮ እንደተናገሩት የህወሓት አመራሮችን በአጭር ጊዜ በቁጥጥር ስር ለማዋል የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ሽልማቱ መዘጋጀቱን ገልፀዋል። በዚህም የመከላከያ ሠራዊት በህግ የሚፈለጉትን የህወሓት አመራሮች…
#FDREDefenseForce
መከላከያ ሰራዊት በህግ እየፈለጋቸው የሚገኙት የህወሓት #አንኳር አመራሮች መበታተናቸውን አሳውቋል።
ሰራዊቱ የህወሓት አመራሮች የተደበቁበትን ለጠቆመው 10 ሚሊዮን ብር ማበረታቻ እንደሚሰጥ ገልጿል።
ጥቆማ ለሚያደርሰው አካል ደህንነቱ ተጠብቆ ማበረታቻው በሚስጥር ይሠጠዋል ብሏል።
ሀገር መከላከያ ሰራዊት እየፈለኳቸው ነው ያላቸውን የህወሓት አንኳር የነበሩትን አመራሮች የተደበቁበትን በአካል መጠቆም እንደሚቻልም ገልጿል።
በተጨማሪ የጥቆማ መቀበያ ስልክ ቁጥሮች ይፋ አድርጓል፦ 09 43 47 13 36 እና 012 5 50 43 48

#AddisAbaba
የኦሮሞ ታጋዮች ፋውንዴሽን በአዲስ አበባ በ1 ቢሊየን ወጪ ብር ባለ 15 ወለል ህንፃ ሊያስገነባ መሆኑ አስታውቋል።
ፋውንዴሽኑ የኦሮሞ ታጋዮችን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ለመቅረፍ የሚሰራ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በ2008 ዓ.ም የተመሰረተው ፋውንዴሽኑ የራሱን ባለ 15 ወለል ህንፃ በ1 ቢሊየን ብር በአዲስ አበባ ካዛንችስ አካባቢ የሚገነባ ይሆናል፡፡
ለሚያስገነባው ህንጻም በዛሬው እለት ከኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ጋር ስምምነት ተፈራርሟል፡፡
የግንባታ ስራው በሁለት አመት ተኩል ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሏል፡፡
ምንጭ፦ ኤፍ ቢ ሲ

#EthiopianAirlines
ከአዲስ አበባ ወደ ባሕር ዳር ከተማ በረራ ነገ እንደሚጀመር የኢትዮጵያ አየር መንገድና ኤርፖርቶች ድርጅት የባሕር ዳር ቅርንጫፍ አሳውቋል።
የአየር መንገዱ ደንበኞች የተንቀሳቃሽ ስልክ መተግበሪያን በመጠቀም ወይም ወደ 6787 ደውለው ትኬት በመቁረጥ ጊዜያቸውንና ገንዘባቸውን እንዲቆጥቡ መልእክት ተላልፏል።
ምንጭ፦ አብመድ

ማይክ ፔንስ የኮቪድ-19 ክትባት ተከተቡ !
የአሜሪካው ም/ፕሬዚደንት ማይክ ፔንስ በቴሌቪዥን የቀጥታ ሥርጭት እየታዩ የኮሮና ቫይረስ ክትባት ተከተቡ።
ምክትል ፕሬዚደንቱ ለተመልካቾች እና ለዶክተሮች "ምንም ነገር አልተሰማኝም" ብለዋል።
ምክትል ፕሬዚደንት ማይክ ፔንስ በቀጥታ ሥርጭት እየታዩ የመከተባቸው ዓላማ የክትባቱን ደህንነትና ውጤታማነት ለማስተዋወቅና በአሜሪካ ሕዝቦች ዘንድ መተማመንን ለመፍጠር እንደሆነ ዋይት ሃውስ አስታውቋል።
የ61 ዓመቱ ማይክ ፔንስ ከባለቤታቸው ካረን እና አዳምስ ጋር የመጀመሪያዎቹን ሁለት ዶዝ የፋይዘር/ ባዮንቴክ ክትባት የወሰዱት ዛሬ ከቀኑ 10 ሰዓት ነው።
አሜሪካ 95 በመቶ በሽታውን ይከላከላል የተባለውን የፋይዘር/ ባዮንቴክ ክትባት መከተብ የጀመረችው ባሳለፍነው ሰኞ ነበር።
ምንጭ፦ ቢቢሲ