የእሳት አደጋ ፦
#ሐረማያ_ዩኒቨርሲቲ
በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ህንፃ 3 የሚባለው የድህረ ምረቃ ተማሪዎች ከሚኖሩበት ህንፃ የኤሌክትሪክ መቆጣጠሪያ ላይ የተነሳ የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር ውሏል።
በእሳት አደጋው በንብረት ላይ ጉዳት ያደረሰ ቢሆንም በሰው ላይ ምንም ጉዳት አለማድረሱን የዩኒቨርሲቲው ሕዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት አስታውቋል።
#መካነ_ሠላም_ከተማ
በደቡብ ወሎ ዞን መካነሠላም ከተማ ድንገት የተከሰተ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት አድርሷል።
መንስኤው ያልታወቀው የእሳት አደጋ በግምት ከለሊቱ 8፡00 ሰዓት አካባቢ የተከሰተ ሲሆን በሸቀጣ ሸቀጥ ሱቆች ላይ ፣ በሴቶች የውበት ሳሎን እና በልብስ ስፌት ቤቶች ላይ ነው ጉዳት ያደረሰው፡፡
ከአምስት (5) በላይ ሱቆች እና ሌሎች የገበያ ቤቶች በእሳት አደጋው የተጎዱ ሲሆን የሱቅ እቃዎች ፣ የተለያዩ ማሽኖች እና ከ1 መቶ ሺህ ብር በላይ ጥሬ ገንዘብ ተቃጥሏል፡፡
Via @TIKVAHETHMAGAZINE
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

መቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን አስመረቀ !
መቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን በዛሬው ዕለት አስመርቋል።
ዩኒቨርሲቲው ያስመረቃቸው 3290 ተማሪዎች በመጀመሪያ ዲግሪ ሲሆን ፤ 1 ደግሞ በሶስተኛ ዲግሪ መሆኑ ታውቋል።
ከጠቅላላው ተመራቂዎች መካከል 30% እንዲሁም በጤና መስክ ከተመረቁት መካከል ደግሞ 38% ሴቶች መሆናቸው ከኢፕድ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

#TikvahFamilyMekelle
ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በስልክ ያገኘናቸው የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች የሆኑ የቲክቫህ አባላት ከብዙ ውጣ ውረድ በኃላ ለዚህ ቀን በመብቃታቸው ደስ እንደተሰኙ ገልፀውልናል።
እጅግ በጣም ፈታኝ እና አስቸጋሪ በነበሩ ወቅቶች የመቐለ ነዋሪዎች አብሯቸው ስለነበሩ ፣ አይዞአችሁ እኛ አለንላችሁ ስላሏቸው ፣ ለእራሳቸው እየተቸገሩ ከሚበሉት ላይ ቀንሰው ስላካፈሏቸው ፣ ከሚጠጡት ቀንሰው ስላጠጧቸው፣ ፍቅር ስላስተናገዷቸው ፣ እንደልጆቹ ስለተንከባከባቸው ምስጋና እንድናደርስላቸው ጠይቀውናል።
እኛም ምንም እንኳን የመቐለ ነዋሪዎች በኢንተርኔት መቋረጥ ይህንን መልዕክት ባያዩትም ምስጋናውን አድርሰናል።
#Congratulations

TIKVAH-ETHIOPIA
አቶ ጃዋር እና አቶ በቀለ ዛሬ ህዳር 18/2013 ፍርድ ቤት አልቀረቡም። አቶ ጃዋር መሃመድ እና አቶ በቀለ ገርባ ለደህንነታቸው ሲባል የፍርድ ሂደታቸው የሚታይበት ቦታ ጊዜያዊ ችሎት ተቋቁሞ ወዳሉበት አካባቢ እንዲሆንላቸው ጠይቀዋል። ምክንያት ? እነ አቶ ጃዋር ችሎት እየቀረቡ ያለሆነው የተከሰሱበት ጉዳይ አወዛጋቢ ፣ በሀገሪቱ ፖለቲካ ውስጥ ካላቸው ሚና እና ሲነዛ ከነበረው የሚዲያ ፕሮፖጋንዳ አንፃር…
ችሎት !
ዛሬ ታህሳስ 8 የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ የህገመንግስት እና የፀረ ሽብር ወንጀሎች ጉዳይ ችሎት የእነ አቶ ጀዋር መሀመድን ጉዳይ ተመልክቷል፡፡
ከዚህ በፊት እነ አቶ ጃዋር መሃመድ ባቀረቡት የጽሁፍ አቤቱታ ለደህንነታችን ስለምንሰጋ ችሎቱ በአቅራቢያችን ይሁንልን ሲሉ መጠየቃቸው ይታወሳል፡፡
ይህንን የመረመረው ችሎቱ ጥያቄያቸውን ውድቅ በማድረግ በዚሁ ችሎት ጉዳያቸው እንዲታይ አዝዟል፡፡
ለጥር 4 ቀን 2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
ምንጭ፦ ኤፍ ቢ ሲ

#DrAbrhamBelay
ዶክተር አብርሃም በላይ በዓዲግራት እና ውቅሮ ከተሞች የመብራት አገልግሎት በሁለት ቀናት ውስጥ እንደሚጀምር አሳወቁ።
ዶ/ር ኣብርሃም ይህን ያሳወቁት በዓዲግራት ከተማ ከአገር ሽማግሌዎች ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት እንደሆና ኢዜአ ገልጿል።
በውይይቱ ላይ የአገር ሽማግሌዎች ተቋርጦ የቆየው በተለይ የመብራት ፣ ቴሌኮም እና የውሃ አቅርቦት #በአፋጣኝ ወደ አገልግሎት እንዲመለስ ጠይቀዋል።
ዶ/ር አብርሃም መብራት በሁለት ቀን ውስጥ እንደሚጀመር ገልፀው ሌሎች መሰረተ ልማቶችን መልሶ የመገንባት ስራ በመከናወን ላይ መሆኑን አብራርተዋል።

በሐመር ወረዳ የአንበጣ መንጋ ተከስቷል !
በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን ሐመር ወረዳ ሁለት ቀበሌዎች የበረሃ አንበጣ መንጋ ተከስቷል።
የአንበጣ መንጋውን ለመከላከል ርብርብ እየተደረገ መሆኑን የክልሉ መንግስት አስታውቋል።
አርሶ አደሩ የደረሱ ሰብሎችን ከማሳ ላይ ፈጥኖ መሰብሰብ እንደሚገባም ተገልጿል። #SRTA
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን ሐመር ወረዳ ሁለት ቀበሌዎች የበረሃ አንበጣ መንጋ ተከስቷል።
የአንበጣ መንጋውን ለመከላከል ርብርብ እየተደረገ መሆኑን የክልሉ መንግስት አስታውቋል።
አርሶ አደሩ የደረሱ ሰብሎችን ከማሳ ላይ ፈጥኖ መሰብሰብ እንደሚገባም ተገልጿል። #SRTA
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ፕሬዚዳንት ማክሮን በኮቪድ-19 ተያዙ።
የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት #ኢማኑኤል_ማክሮን በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን የፕሬዚዳንቱ ጽ/ቤት ዛሬ ጠዋት ይፋ አድርጓል፡፡
ማክሮን ምልክቶችን ካሳዩ በኋላ ባደረጉት ምርመራ ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ነው ጽ/ቤቱ የገለጸው፡፡
ከዛሬ ጀምሮ ለ ሰባት ቀናት ራሳቸውን እንደሚያገሉም ስካይ ኒውስን ዋቢ አድርጎ #አልዓይን ዘግቧል፡፡ ይሁንና ፕሬዜዳንቱ ስራቸውን እንደሚቀጥሉ ተገልጿል፡፡
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

#Tigray
በመቐለ ያለውን እንቅስቃሴ ከዕለት ወደ ዕለት መሻሻል እያሳየ መሆኑን በስልክ ያነጋገርናኛቸው ነዋሪዎች ተናግረዋል።
የስልክ ፣ የውሃ ፣ መብራት አገልግሎት መመለስ ብዙ ችግሮችን እንዳቀለለ ገልፀውልናል።
የንግድ እንቅስቃሴ በየዕለቱ መሻሻል እያሳየ ነው። የባንክ አገልግሎት አለመጀመር ግን አሁንም ትልቅ ችግር ሆኖ ቀጥሏል።
የፀጥታ እና የደህንነት ጉዳይም ልዩ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ አሳስበዋል።
በተለይ በከተማው ውስጥ የነበረው ዝርፊያ (ከባለፉት ቀናት እየተሻሸለ ቢመጣም) አሁንም አስተማማኝ ደህንነት እና ሰላም ሊሰፍን እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
የምግብ አቅርቦት ሊሻሻል ይገባል ብለዋል ፤ የምግብ ግብአቶች እጅግ ውድ መሆናቸውን ገልፀዋል።
የፍርድ ቤት ፣ ፖሊስ ሌሎች ተያያዥ የደህንነት ተቋማት ስራ አለመጀመራቸውን ህብረተሰቡን ሙሉ በሙሉ ከስጋት እንዳይላቀቅ አድርጎታል።
በከተማይቱ ከምሽት 12:00 ሰዓት በኃላ ሁሉም ወደቤቱ እንዲገባ ጥዋት ማለዳ 12:00 እንዲወጣ እንዲችል ተደንግጓል።
በሌላ በኩል ፦
ወደአድዋ ፣ ዓዲግራት ፣ ሽረ፣ ውቅሮ መስመር የስልክ ኔትዎርክ ባለመኖሩ አሁንም በአካባቢው ያለውን ሁኔታ ለማውቅ አስቸጋሪ ሆኗል።
በመቐለ ከተማ እና በሌሎች ኔትዎርክ በሚሰራባቸው አካባቢዎች ያሉ አባላቶቻችን የቤተሰቦቻቸውን ደህንነት ለማወቅ መቸገራቸውን ተናግረዋል። ይህም ሁኔታ አሁንም ድረስ ከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ እንደከተታቸው ነው።
www.tikvahethiopia.net
(የነዋሪዎች አስተያየት የተሰበሰበው ከመቐለ ቲክቫህ አባላት እንዲሁም ከጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ ነው)
PHOTO : FILE

IOM በትግራይ ክልል ለተፈናቀሉ ዜጎች ምግብ ነክ ያልሆኑ ድጋፎችን እያደረገ እንደሆነ አሳውቋል።
ድጋፍ ከተደረገባቸው አካባቢዎች መካከል ሽራሮ ፣ ሽረ፣ ሁመራ ፣ ኣዲ ሀገራይ፣ ኣዲ ጎሹ ፣ አክሱም እና መቐለ ይገኙበታል።
አሁንም IOM ሌሎች አመቺ በሆኑ አካባቢዎች ድጋፍ ለሚሹ ዜጎች ድጋፉን ተደራሻ ለማድረግ ዝግጁ እንደሆነ ገልጿል።

መቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን አስመረቀ ! መቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን በዛሬው ዕለት አስመርቋል። ዩኒቨርሲቲው ያስመረቃቸው 3290 ተማሪዎች በመጀመሪያ ዲግሪ ሲሆን ፤ 1 ደግሞ በሶስተኛ ዲግሪ መሆኑ ታውቋል። ከጠቅላላው ተመራቂዎች መካከል 30% እንዲሁም በጤና መስክ ከተመረቁት መካከል ደግሞ 38% ሴቶች መሆናቸው ከኢፕድ የተገኘው መረጃ ያሳያል። @tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#MekelleUniversity
ዛሬ መቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን አስመርቋል።
በምርቃት ስነ ስርዓቱ ላይ ዶ/ር ሙሉ ነጋ እንዲሁም የዩኒቨርሲቲው ፕሬዜዳንት ፕሮፌሰር ፈትየን ኣባይን ጨምሮ የዩኒቨርሲቲው የቦርድ አባላት ተገኝተው ነበር።
የዛሬውን የምርቃት ድባብ የሚያሳዩ ፎቶዎች ከላይ ተያይዘዋል።