#SavetheChildren
ባለፉት አራት ሳምንታት ድንበር ተሻግረው ወደ ሱዳን የገቡ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ቁጥር ከ45 ሺህ ማለፉን UNHCR አስታውቋል።
ከነዚህ መካከል 45% ህፃናት እንደሆኑም ገልጿል።
በሱዳን ኡም ራክባ 158 የሚሆኑ ወላጅ እና አሳዳጊ ሳይኖራቸው ብቻቸውን መገኘታቸውን በሱዳን የSave the Children ዳይሬክተር አርሻድ ማሊክ ለቪኦኤ ተናግረዋል።
ዳይሬክተሩ ህፃናቱ በአስር (10) ዓመት የእድሜ ክልል ውስጥ ያሉ መሆናቸውን ገልፀው ካምፕ ውስጥ ባለው መጨናነቅ የተነሳ መሰረታዊ ነገር ለማሟላት ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል።
ከላይ የተጠቀሰው አሃዝ በአንድ የስደተኞች ማዕከል በተደረገ የመረጃ ማሰባሰብ ሂደት የተገኘ መሆኑን ገልፀው እንደ ሃምዳይት ባሉ ከ30 ሺህ በላይ ስደተኞች ባሉበት ትልልቅ ካምፖች ብዙ ህፃናት ሊገኙ ይችላሉ ብሏል።
ሁኔታው ህፃናቱን እና ታዳጊዎቹን ለተለያዩ ጥቃቶች እና ብዝበዛ ሊያጋልጣቸው እንደሚችል ገልፀዋል።
Save the Children ከሱዳን መንግስት እና ከተመድ (UNHCR) ጋር በመተባበር መሰረታዊ የሆነ ድጋፍ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን ለቪኦኤ ራድዮ አሳውቋል።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

#MinistryOfEducation
ትምህርት ሚኒስቴር ትምህርት በሁሉም አካባቢ እንዲጀመር ለማድረግ እየሰራ መሆኑን አሳውቋል።
የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ አቶ ሚሊዮን ማቲዮስ ለኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዛሬ እንደተናገሩት በትግራይ ክልል ትምህርት ለማስጀመር ከ700,000 በላይ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ (ማስክ) ተዘጋጅቷል።
ከዚህ በተጨማሪ የተጎዱ መሰረተ ልማቶችን ለመጠገን 50 ሚሊዮን ብር መያዙን አሳውቀዋል።
በአማራ ክልል አጎራባች አካባቢዎች በህግ ማስከበር ሂደቱ የተጎዱ ትምህርት ቤቶችን ለመጠገን እና ስራ ለማስጀመር እየተሰራ ነው ብለዋል።

#BahirDar
በባሕር ዳር ከተማ ውሃ ተበክሏል እየተባለ የሚናፈሰው ወሬ #ሀሰት መሆኑን የባህር ዳር ከተማ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ለአብመድ ገልጿል፡፡
የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር የውሃ እና ፍሳሽ ባለሙያዎች በየዕለቱ በሁሉም ቦታዎች ማለትም (ታንከር ላይ ፣ መሥመር ላይና ቤት ለቤት በመዞር) የፊዚካል ፣ ባዮሎጂካል እንዲሁም የኬሚካል ናሙና ምርመራ ይደርጋሉ።
ዛሬ እና ትናንት በተደረገው የናሙና ምርመራ ምንም ችግር እንደሌለ መረጋገጡን የከተማው ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት አሳውቋል።
ዛሬ ህዳር 25/2013 ውሃ ተበክሏል በሚል ሥጋት ጥቆማ በተደረገባቸው የከተማዋ አካባቢዎች ናሙና ተወስዶ ምንም አይነት ችግር አለመኖሩ ተረጋግጧል።
የከተማው ውሃ በቀላሉ የሚበከል አለመሆኑ የተገለፀ ሲሆን በተለይም አጠራጣሪ በሆኑ አካባቢዎች የተጠናከረ ጥበቃ እየተደረገ ነው።
ከጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ/ም በኋላም የጥበቃ ሥራው መጠናከሩ ተገልጿል።
ሕዝቡ እውነቱን ተገንዝቦ 'ያለምንም መረበሽ' የእለት ተዕለት ተግባሩን እንዲከውን የከተማው ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት መልዕክት ተላልፏል። (AMMA)

#COVID19Ethiopia
የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :
• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 5,673
• በበሽታው የተያዙ - 512
• ህይወታቸው ያለፈ - 10
• ከበሽታው ያገገሙ - 1,215
አጠቃላይ 112,091 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,734 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ 78,619 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።
317 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

ወቅታዊ መረጃዎች ፦
1. ተመድ (UN) ሰብዓዊ እርዳታ ለማድረግ ትግራይ ዉስጥ በተለያዩ አካባቢዎች የሚታየዉ 'ውጊያ' ነገሩን አክብዶታል ሲል አስታውቋል።
2. ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ዛሬ ለሮይተርስ በላኩት መልዕክት በመቐለ የኤርትራ ወታደሮች እየፈፀሙት ባለው "ዝርፊያ" ምክንያት ከፍተኛ ተቃውሞ ተደርጎ ነበር ብለዋል።
3. ጦርነት ሸሽተው ወደ ሱዳን የተሰደዱ ኢትዮጵያዊያንን ለመመለስ ከሀገሪቱ መንግስት ጋር ስምምነት ላይ መደረሱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።
4. የህወሓት አመራሮችን ወርቅአምባ አካባቢ በ6 በረት ለበስ ዙሪያውን ኮማንዶ እየጠበቃቸው እንደሆነ መከላከያ ሰራዊት አረጋግጧል።
በአሁን ሰዓት በዚህ አካባቢ ዶ/ር ደብረፅዮን ፣ አቶ ጌታቸው ረዳ ፣ አቦይ ስብሃት ፣ አቦይ ፀሃዬ ፣ ሌሎችም ሀገር መከላከያ ሰራዊት የማያውቃቸው አካላት አሉ።
5. መከላከያ ሰራዊት መቐለ ከተማን የማረጋጋት ስራ እየሰራ መሆኑን ገልጿል።
በሌላ በኩል በመቐለ የህወሓት አመራሮች ቤት በተደረገ ብርበራ ለጥፋት አላማ የሚውሉ የጦር መሳሪያዎች መገኘቱ ተገልጿል።
የአቶ ጌታቸው ረዳ፣ የአቶ ስዩም መስፍን፣ የአቶ አባይ ፀሃዬ ፣ መኖሪያ ቤት ህጉ በሚፈቅደው መሰረት ብርበራ ተደርጓል ብሏል ሰራዊቱ።
በዝርዝር ይመልከቱ : https://telegra.ph/Ethiopia-12-04-3
@TIKVAHETHIOPIABOT @TIKVAHETHIOPIA

የአሜሪካ ጦር ከሱማሊያ እንዲወጣ ታዘዘ።
የአሜሪካው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ሁሉም የአሜሪካ የጦር ኃይል አባላት በ2021 መጀመሪያ ወር ላይ ሶማሊያን ለቅቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ ሰጡ።
700 የሚሆኑ የአሜሪካ ሠራዊት አባላት እንዲወጡ የታዘዘው ተመራጭ-ፕሬዚደት ጆ ባይደን ቃለ መሃላ ከመፈጸማቸው አምስት ቀናት ቀደም ብሎ ጃኑዋሪ 15 ነው።
ይህ በሶማሊያ ይሰጥ የነበረውን ስልጠናና ይካሄድ የነበረውን ፀረ-ሽብር ተልዕኮ ፋይዳ አስመልክቶ ባልበረደው ክርክር ላይ ግለትን ጨምሯል።
በሶማሊያ የአሜሪካ ጦር ተልዕኮ ደጋፊዎችና የተወሰኑ ብርቱ የትራምፕ ደጋፊዎች ዘንድ የሠራዊቱ መኖር አል ሻባብ በሪጂኑ ኃይሉን አጠናክሮ እንዳይስፋፋ የገታ መሆኑንና የጦሩ ሶማሊያን ለቅቆ መውጣትም ለሶማሊያ የጸጥታ ኃይላት የሚሰጡትን ስልጠናዎች የሚያቋርጥ መሆኑ ጉዳት እንዳለው በማንሳት ድምጻቸውን አሰምተዋል።
ሆኖም የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር ባለስልጣናት ዓርብ ዕለት እንዳስታወቁት ገሚሱ ጦር ወደ ጎረቤት አገር ኬንያ በመዛወር እዚያ ሆኖ የድሮን አየር ጥቃት ሊፈጽም እንደሚችል ጠቅሰዋል።
የአሜሪካ ጦር ሶማሊያን ለቅቆ የሚወጣው አገሪቱ የፓርላማ ምርጫ ለማድረግ ስድስት ወራት እና ፕሬዚደንታዊ ምርጫም ፌብሪዋሪ 2021 ለማከናወን በዝግጅት ላይ ባለችበትና የኢትዮጵያ ጦርም በአገር ውስጥ ወታደራዊ ግዳጆች ተጠምዶ ባለበት ወቅት መሆኑን ኤስ ቢ ኤስ (SBS) አስነብቧል።

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 6,185
• በበሽታው የተያዙ - 649
• ህይወታቸው ያለፈ - 11
• ከበሽታው ያገገሙ - 960
አጠቃላይ 112,740 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,745 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ 79,579 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።
313 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :
• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 6,185
• በበሽታው የተያዙ - 649
• ህይወታቸው ያለፈ - 11
• ከበሽታው ያገገሙ - 960
አጠቃላይ 112,740 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,745 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ 79,579 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።
313 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Shire #Axum #Mekelle
በሽረ ከተማ ህዝቡ ወደመረጋጋት እና ወደቀደመው ህይወቱ እየተመለሰ መሆኑን ዶ/ር ሙሉ ነጋ (የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ) ለኢቲቪ ተናገሩ።
የወረዳ ፣ የቀበሌ ስራ አስፈፃሚዎች ተመርጠዋል ፤ ወደ ስራም ገብተዋል ብለዋል።
በተመሳሳይ በአክሱም ከተማ የወረዳና የቀበሌ አደረጃጀቶች ተዘርግተዋል ፤ እንቅስቃሴም እንደተጀመረ ገልጸዋል።
መቐለ ከተማ በሚመለከት አሁን ላይ ከተማው ሙሉ በሙሉ በመከላከያ ሰራዊት ቁጥጥር ስር እንደሆነና ሰላማዊ ሁኔታ እንዳለ ዛሬ ከመቐለ ከተማ ሆነው አሳውቀዋል።
ህዝቡ ወደስራው እንዲመለስ ፣ በስጋት ከከተማው ሸሽቶ የወጣም እንዲገባ ጥሪ ቀርቧል።
በሌላ በኩል በመቐለ ከተማ የህዝቡ ስጋት ዝርፊያ እንደሆነና ይህም ዝርፊያ እንዲቆም ጥያቄ እንዳቀረበ አንስተዋል ፤ ዝርፊው በቡድን በመደራጀት የሚፈፀም እንደሆነም ዶክተር ሙሉ ገልፀዋል።
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከሀገር መከላከያ ሰራዊት እና ከፌዴራሉ መንግስት ጋር በመነጋገር በፍጥነት ይህ ሁኔታ መፍትሄ እንዲያገኝ እየሰራ እንደሆነ አሳውቀዋል።

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#UNRefugeeAgency
እንደ UNHCR መረጃ ከሆነ ከኢትዮጵያ ወደሱዳን ከተሰደዱ ዜጎች በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ህፃናት (ከቤተሰቦቻቸው ጋር) ይገኙበታል።
አንዳንዶች ውጊያ ሸሽተው የሄዱ የሀገራችን ዜጎች ሰላም እና ደህንነት ፍለጋ በእግራቸው ለሰዓታት ተጉዘው ነው ሱዳን የገቡት።
እስካሁን ወደ 47,000 ሰዎች ድንበር ተሻግረው ወደ ሱዳን ገብተዋል።
በሁኔታው ህፃናት እና ሴቶች በብዛት ገፈጥ ቀማሽ ሆነዋል።
ቤተሰቦች ሁሉ ነገራቸውን አጥተዋል ፤ መጠለያ ፣ ምግብ ፣ ንፁህ ውሃ ያስፈልጋቸዋል።
UNHCR እና አጋሮቹ የአስቸኳይ ጊዜ የህይወት አድን ድጋፍ እያደረጉ ነው።
donate.unhcr.org/int/ethiopia-emergency/~my-donation

#DrAbiyAhmed
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ በሆስፒታል በህክምና ላይ የሚገኙ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላትን መጎብኘታቸውን በትዊተር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ “ዛሬ ጠዋት ኢትዮጵያን ከራስ በላይ ያስቀመጡ በሆስፒታል የሚገኙ ሴት እና ወንድ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ጀግኖቻችንን ጎብኝቻለሁ! አገልግሎታችሁን እናከብራለን” ብለዋል፡፡
ይሁንና ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት ስላደረጉበት ሆስፒታል የገለጹት ነገር የለም፡፡
Via AlAin News

#Mekelle
መቐለ ዩኒቨርሲቲ አይደር ካምፓስ ሚማሩ ተማሪዎች ምንም አይነት የደህንነት ችግር እንደሌለባቸው ተናግረዋል።
ግቢው በሀገር መከላከያ ሰራዊት ቁጥጥር ስር ነው የሚገኘው።
ለስፔሻላይዜሽን የሄዱ ተማሪ ሃኪሞች ከዚህ ቀደም ከግቢ ውጭ ይኖሩ ነበር አሁን ላይ አብዛኛው ከሌላ አካባቢ የመጡ ወደ ግቢ ገብተው የመኝታ ክፍል (ዶርም) ተሰጥቷቸው እየኖሩ ነው።
ነገር ግን የተሟላ አልባሳት እና ለመኝታ የሚሆን ብርድ ልብስ ይዘው አልገቡም።
በግቢው ውስጥ የውሃ ፣ የመብራት ፣ የምግብ በቂ የአቅርቦት ችግር እንዳለ አሳውቀዋል። ከዚህ ባለፈም ከቤተሰቦቻቸው ጋር ከወር በላይ ባለመገናኘታቸው ተጨንቀዋል።
የመቐለ አይደር ካምፓስ ተማሪዎችም ሆኑ ሃኪሞች ወደ መጡበት አካባቢ እንዲመለሱ መንግስት ጥረት እንዲያደርግ ጠይቀዋል።
ቤተሰቦች እንዳይረበሹ መልዕክት አስተላልፈዋል።
Via ጋዜጠኛ ሃይለሚካኤል ዴቢሳ (ከመቐለ ከተማ)

#UPDATE
ከአላማጣ ወደ መቐለ የሚሄደው ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ሃይል ማስተላለፍያ መስመር #በፍጥነት እየተጠገነ እንደሚገኝ ኢ.ዜ.አ. ከስፍራው በፎቶ ዘገባ ገልጿል።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ከአላማጣ ወደ መቐለ የሚሄደው ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ሃይል ማስተላለፍያ መስመር #በፍጥነት እየተጠገነ እንደሚገኝ ኢ.ዜ.አ. ከስፍራው በፎቶ ዘገባ ገልጿል።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#COVID19Ethiopia
የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :
• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 5,379
• በበሽታው የተያዙ - 555
• ህይወታቸው ያለፈ - 2
• ከበሽታው ያገገሙ - 1,252
አጠቃላይ 113,295 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,747 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ 80,831 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።
316 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :
• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 5,379
• በበሽታው የተያዙ - 555
• ህይወታቸው ያለፈ - 2
• ከበሽታው ያገገሙ - 1,252
አጠቃላይ 113,295 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,747 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ 80,831 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።
316 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት 👆
- በትግራይ ክልል ስለሚኖሩ በ100 ሺዎች የሚቆጠሩ የቲክቫህ አባላት ጋር ከአንድ ወር በላይ አለመገናኘት።
- በማህበራዊ ሚዲያዎች ስለሚሰራጩ የተዛቡ እና ሀሰተኛ መረጃዎች ጉዳይ።
- በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የቲክቫህ አባላት ማድረግ ስላለባቸው ጥንቃቄ።
* ነባር የቲክቫህ አባላት በእንዲህ ያለ ወቅት በቲክቫህ ቤተሰብ መካከል ስለሚደረገው የመረጀ ልውውጥ በቂ ግንዛቤ ቢኖራቸውም አዳዲስ አባላት ስለቤተሰቡ እንዲረዱት የቀረበ ነው።