TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#UPDATE

የአምቦ ዩኒቨርሲቲ "ተመራቂ ተማሪዎች" ከህዳር 28 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ ትምህርት እንደሚጀምሩ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

ሪፖርት ያላደረጉ ተመራቂ ተማሪዎች ህዳር 24 እና ህዳር 25 ቀን 2013 ዓ/ም ሪፖርት እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።

በቀጣይም የዩኒቨርሲቲዎችን ጥሪ በተመለከተ በ @tikvahethmagazine መከታተል ትችላላችሁ።

በትግራይ ክልል ስለሚገኙ ተማሪዎች ፣ እንዲሁም በትግራይ ክልል ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች ስለሚማሩ ተማሪዎች ጉዳይ ከሚመለከታቸው አካላት ጠይቀን የምናሳውቃችሁ ይሆናል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
አጫጭር መረጃዎች ፦

1. ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ በህግ የሚፈለጉት የህወሓት አባላት ከመቐለ ሸሽተው "ሀገረ ሰላም" (ከመቐለ 52 KM) አካባቢ እየተሰባሰቡ ነው ሲሉ ተናገሩ።

ትላንት ምሽት የነበሩበትን ሁኔታ በቀጥታ ስንከታተል ነበር፤ ጥቃት ግን አልፈፀምንም ለዚህ ምክንያቱ በሽሽት ውስጥ ሚስቶቻቸውን ፣ ልጆቻቸውን ፣ የታፈኑ የኢትዮጵያ ወታደሮችን ይዘው ሄደዋል፤ ሀገር ሰላም እና አብይ ዓዲ አካባቢም መተረማመስ ስለነበር ነው ብለዋል። ይህ ሁኔታ ግን እንደማይቀጥል አሳስበዋል።

2. ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል "ወደ ደቡብ ሱዳን ተሰደዋል" መባሉን "ሐሰት ነው" ሲሉ ለሮይተርስ መናገራቸውን ዶቼ ቨለ ዘግቧል፤ "አሁንም በመቐለ ከተማ አቅራብያ ከመንግስት ኃይሎች ጋር እየተዋጋን ነው" ብለዋል።

የጠ/ሚር ፅ/ቤት ፕሬስ ሰክሬቴሪያት ቢለኔ ስዩም "የፌዴራል መንግሥት በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን በማረጋጋት ስራ ላይ ተጠምዷል ፤ ተበታትኖ ላለ ወንጀለኛ ንግግር መልስ መስጠት ጉዳያችን አይደለም" ሲሉ ዶ/ር ደብረጽዮን "በመቐለ አቅራብያ ከመንግስት ኃይሎች ጋር ውግያ ቀጥለናል" ብለው መናገራቸውን አጣጥለዋል።

3. የወልቃይት እና ሑመራ አካባቢዎች ላይ ተቋርጦ የነበረው 'የስልክ አገልግሎት' ዳግም መጀመሩን የአካባቢውን ነዋሪዎች ማረጋገጣቸውን አል ዓይን ዘግቧል።

4. ሱዳን በኢትዮጵያ ድንበር በምትገኘው ከሰላ ግዛት አከባቢ በርካታ ቁጥር ያለው የጦር መሳሪያ መያዟን አስታውቃለች።

የሀገሪቱ ፀጥታ ኃይሎች የጦር መሳሪያዎችን መያዝ የቻሉት ከኢትዮጵያ በትግራይ ክልል በኩል ወደ ሱዳን በሚያገናኘው ድንበር አከባቢ ሰሞኑን በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ መሆኑን የሱዳኑ ዜና አገልግሎት ሱና ዘግቧል።

ህዳር 21 ቀን 2013 ዓ/ም

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#EHRC

ኢሰመኮ የመልሶ ማቋቋም ተግባራት በሰብአዊ መብቶች የሚመሩ መሆን እንዳለባቸው ዛሬ ህዳር 21 ቀን 2013 ዓ/ም ባወጣው መግለጫ አስገንዝቧል።

* ዛሬ ኢሰመኮ ያወጣው ይፋዊ መግለጫ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#ማስታወሻ

ከነገ ህዳር 22 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ በአሮጌው የብር ኖት መገበያየት አይቻልም።

የአሮጌው ብር ኖት ቅያሬ ታህሳስ 6 ቀን 2013 ይጠናቀቃል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#COVID19Ethiopia

የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 4,817
• በበሽታው የተያዙ - 540
• ህይወታቸው ያለፈ - 6
• ከበሽታው ያገገሙ - 4,493

አጠቃላይ 110,074 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,706 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ 73,808 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።

323 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DonaldTrump

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ ምርጫው እንደተጭበረበረ ዳግም ተናግረዋል።

ከFOX ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ጥቅምት 24 የተደረገው ምርጫ 'ሙሉ በሙሉ የተጭበረበረ ነው' ሲሉ ገልፀዋል።

ይህ የትራምፕ ንግግር የምርጫ 'ውጤቱን እንደማይቀበሉ' አመላካች ነው ሲል ዶቼ ቨለ ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Hawassa

ትላንት ለሊት 8:00 ሰዓት አካባቢ በሀዋሳ በተሽከርካሪ አደጋ የ2 ሰዎች ህይወት አልፏል።

በአደጋው በአካል እና ንብረት ላይም ጉዳት መድረሱን የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ለኢዜአ አስታውቋል።

የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3–12020 ኢ.ት ከባድ ተሽከርካሪ ወደ ሀዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ለጭነት ሲገባ ከአቦስቶ ከተማ እቃ ጭኖ ወደ ነገሌ አርሲ ከተማ ይጓዝ ከነበረው የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 – 77038 አ.አ አይሱዙ ጋር በመጋጨታቸው አደጋው መድረሱ ነው የተገለፀው።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#እራሳችሁን_ጠብቁ !

የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በኢትዮጵያ የኤች አይ ቪ ኤድስ ስርጭት አሁንም የጤና ስጋት ሆኖ ቀጥሏል አሉ።

ዶ/ር ሊያ ይህን ያሉት በኢትዮጵያ ለ33ኛ ጊዜ ዓለም አቀፉ የኤች አይ ቪ ኤድስ ቀን በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ ዛሬ ሲከበር ነው።

አጠቃላይ ህዝቡ፣ ሁሉም ተቋማትና የሚመለከታቸው አካላት ስርጭቱን ለመግታት በትብብር አንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።

አሁን ላይ ኮቪድ-19 ስርጭት የተስፋፋበት ወቅት በመሆኑ ድርብ ስራና ሃላፊነትን ይጠይቃል ብለዋል።     
በአዲስ አበባ ከተማ፣ በጋምቤላ ክልል እና ከተሜነት በተስፋፋባቸው ሌሎች አካባቢዎች የኤች አይቪ ቫይረስ ስርጭት እየጨመረ መምጣቱን ገልፀዋል።

በግንባታ ቦታዎች እና ኢንዱስትሪ ፓርኮች ተመሳሳይ የስርጭት መስፋፋት መኖሩን ጠቁመዋል።

ዶክተር ሊያ ፥ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች የህክምና ክትትል ማድረግ እና መድሃኒት በአግባቡ መውሰድ እንዳለባቸው መክረዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ቫይረሱ በደማቸው የተገኘባቸው ግለሰቦችን እና በቫይረሱ ምክንያት ወላጆቻውን ያጡ ህጻናት እና አረጋዊያንን በመንከባከበ የህብረተሰቡ ትብብር መጠናከር እንዳለበትም አሳስበዋል - ENA

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#Ethiopia

የፌደራል የኤች አይ ቪ መከላከልና መቆጣጠር ጽህፈት ቤት ዳይሬክተር ጽጌረዳ ክፍሌ ፦

• የቫይረሱ ስርጭት በተለይ በልማት ቦታዎች እና ኢንዱስትሪ ፓርኮች በሚሰሩ ወጣቶች ላይ እየተባባሰ ነው።

• ባለፉት ዘጠኝ ዓመታት በኤች አይ ቪ ኤድስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በ75 በመቶ መቀነስ ሲገባው በ52 በመቶ ብቻ ነው የቀነሰው።

• በኢትዮጵያ በየዓመቱ በአማካይ 14 ሺህ 800 ሰዎች በኤች አይ ቪ እየተያዙ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የቫይረሱ ስርጭትም 0 ነጥብ 9 በመቶ ሆኗል።

• በኢትዮጵያ በአሁን ሰዓት ከ666,200 በላይ ሰዎች ቫይረሱ በደማቸው እንደሚገኝ መረጃዎች ያሳያሉ። #ENA

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#UPDATE

በሽረ ከተማ የጊዜያዊ አስተዳደር ከንቲባ የሆነው መምህር ሓጎስ በርሄ ተመርጠዋል።

መምህር ሓጎስ ህዝባዊ ሃላፊነታቸውን በአግባቡ ለመወጣት መዘጋጀታቸውን ለኢዜአ ገልጸዋል።

ኢንጂነር ጀሚል ሙሐመድ የሽረ ከተማ ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሆነው መመረጣቸው ተገልጿል።

በሽረ የአቅም ግንባታ ጽህፈት ቤት ኃላፊ መምህርት ንግሥቲ ፋንታሁን ሆነው ተመርጠዋል።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶ/ር ሙሉ ነጋ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች በመንቀሳቀስ ህዝቡን እያወያዩ እንደሆነ ተገልጿል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#ጥንቃቄ_አይለያችሁ😷

በዓለም አቀፍ ደረጃ የኮቪድ-19 ሟቾች ቁጥር 1,477,487 ደርሷል።

63,761,928 ሰዎች በበሽታው ተይዘዋል ፤ 44,155,441 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#በኢትዮጵያ_ኮቪድ19_እየተባባሰ_ነው😷

የጤና ሚኒስቴር ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር ዶክተር ተገኔ ረጋሳ በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት እየተባባሰ መምጣቱን #ለቪኦኤ ተናገሩ።

ዶ/ር ተገኔ ሰው ‘አስገዳጅ መመሪያ ተነስቷል ፤ ኮሮና ቫይረስ የለም’ በሚሉ የተሳሳቱ አስተሳሰቦች እየተመራ እራሱን ለበሽታው እያጋለጠ መሆኑን ገልፀዋል።

ይሁን እንጂ አስገዳጅ መመሪያውም አለመነሳቱን፣ የቫይረሱ ሥርጭትም እየተባባሰ መሆኑን ዶክተር ተገኔ አሳስበዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም ለመንግስት እጅ ሰጡ !

በህግ ከሚፈለጉት የህወሓት አባላት መካከል ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም ለመንግስት እጅ እንደሰጡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ማጣሪያ አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#COVID19Ethiopia

የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 4,968
• በበሽታው የተያዙ - 480
• ህይወታቸው ያለፈ - 3
• ከበሽታው ያገገሙ - 1,109

አጠቃላይ 110,554 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,709 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ 74,917 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።

330 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NBE በትግራይ ክልል "የባንክ ሂሳብ የከፈቱ" እጅግ በጣም በርካታ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት ላለፉት ቀናት ገንዘብ ለማውጣታ ተቸግረዋል። ለምን ይህ ሊሆን እንደቻለም እጅግ በጣም ግራ ተጋብተው ነበር። በሀገራችን የተለያዩ ከተሞች በትምህርት ላይ የሚገኙ እና ቋሚ ኑሯቸውን ያደረጉ አባላቶቻችን #እየተቸገሩ መሆናቸው እየገለፁ ነው። በዚህ ጉዳይ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ለአዲስ ፎርቹን ጋዜጣ እንደገለፀው…
#NBE

ከነገ ጀምሮ በትግራይ ክልል ባሉ ባንኮች አካውንት የከፈቱና ከትግራይ ክልል ውጭ ያሉ ደንበኞች በያሉበት የሀገሪቱ አካባቢዎች ሂሳባቸውን ማንቀሳቀስ እንዲችሉ መፈቀዱ እና ለባንኮችም ይህ መመሪያ መተላለፉን NBE ዛሬ አሳውቋል።

ይህ በፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ በወንጀል ተጠርጥረው ሂሳባቸው እንዳይንቀሳቀስ የተደረጉ ደንበኞችን የሚመለከት አይደለም።

በሌላ በኩል ፦

የፀጥታ ሁኔታ ለባንኮች አመቺ በሆነባቸው የትግራይ ክልል ከተሞች ባንኮች ተከፍተው ስራ እንዲጀምሩ ብሄራዊ ባንክ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየሰራ መሆኑን አስታውቋል። የፀጥታ ሁኔታ አመቺ ባልሆነባቸው የክልሉ ከተሞች ባንኮች ተዘግተው እንደሚቆዩ NBE ለኢቲቪ ገልጿል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia