TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#DrAbiyAhmed

መንግስት በህግ የሚፈለጉ የህወሓት ቡድን አባላት በ72 ሰዓታት ውስጥ በሰላም 'እጃቸውን እንዲሰጡ' ጥሪ አቀረበ።

ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ ዛሬ ምሽት ባሰራጩት መግለጫ የህወሓት ቡድን አባላት በቀጣዩ 72 ሰዓት ውስጥ በሰላም እጃቸውን በመስጠት የመጨረሻውን ዕድል እንዲጠቀሙ መልዕክት አስተላልፈዋል።

* ዝርዝር መግለጫው ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19Ethiopia

የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 4,495
• በበሽታው የተያዙ - 433
• ህይወታቸው ያለፈ - 11
• ከበሽታው ያገገሙ - 157

አጠቃላይ 105,785 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,647 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል ፤ 65,691 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።

333 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ኃላፊ የነበሩት አቶ ጉልላት ከበደ በኮቪድ-19 ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ ከዚህ አለም በሞት መለየታቸውን የአ/አ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ አሳውቀዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
አምስት የቀድሞ የወላይታ ዞን አመራሮች እና ሌሎች ሁለት ተጠርጣሪዎች ላይ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ ተመሰረተ።

ከአመራሮቹ ጋር በአንድ መዝገብ የጊዜ ቀጠሮ ጉዳያቸው ሲታይ የቆዩ 13 ተጠርጣሪዎች በነጻ እንዲለቀቁ በፍርድ ቤት ተወስኖላቸዋል።

ዛሬ ክስ እንደተመሰረተባቸው ከተገለጸላቸው አመራሮች ውስጥ የቀድሞው የወላይታ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ዳጋቶ ኩምቤ፣ ምክትላቸው ጎበዜ ጎዳና እና የዞኑ ብልጽግና ጽህፈት ቤት ኃላፊ የነበሩት አቶ ጥበቡ ዩሃንስ ይገኙበታል።

ምንጭ፦ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር
@TIKVAHETHIOPIABOT
TIKVAH-ETHIOPIA
#DireDawa በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር "የከባድ ተሽከርካሪዎች" የከተማ ውስጥ እንቅስቃሴ የሰዓት ገደብ ተላልፏል። ከነገ ህዳር 14 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ ከንጋቱ 12 ሰዓት እስከ ምሽት 12 ሰዓት ድረስ ወደ ከተማ ውስጥ መግባት ሆነ በከተማ ውስጥ መንቀሳቀስ አይቻልም። ወደ ከተማ ውስጥ መግባትም ይሁን በከተማ ውስጥ መንቀሳቀስ የፈቀደው ከምሽት 12 ሰዓት በኋላ እስከ ንጋት 12 ሰዓት ድረስ…
* ማሻሻያ

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ከከባድ ተሽከርካሪ ጋር ተያይዞ በተላለፈው የሰአት ገደብ ላይ ማሻሻያ አድርጓል።

ከነዳጅ ጫኝ ከባድ ተሽከርካሪ ውጪ ማንኛውም ከባድ ተሽከርካሪ ጠዋት ከ1 ሰአት እስከ 3 ሰአት እና ቀን ከ5 :30 እስከ 8:30 ወደ ከተማ መግባት ሆነ በከተማ ውስጥ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው።

ከላይ ከተገለፀው ሰአት ውጪ ወደ ከተማ ውስጥ መግባትም ይሁን በከተማ ውስጥ መንቀሳቀስ ይፈቀዳል።

የተጠቀሰውን የሰአት ገደብ ቢሚተላለፉ ላይ የህግ የእርምት እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

ለማሻሻያው ምክንያት ?

አሁን ላይ ካለው ከሀገሪቱ ከወጪ ገቢ ንግድ እና ከሌሎች ተጨማሪ ሁኔታዎች አንፃር ቀደም ብሎ በተላለፈው የእንቅስቃሴ ገደብ ላይ ማሻሻያ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል።

ምንጭ፦ ድሬ ፖሊስ
@tikvahethiopiaBOt @tikvahethiopia
ኮሌራ በዳውሮ 5 ሰዎችን ገደለ !

በደቡብ ክልል ዳዉሮ ዞን በተቀሰቀሰ ኮሌራ የአምስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 66 መታመማቸውን የዞኑ ጤና መምሪያ ለጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ አሳውቋል።

በሽታው የተቀሰቀሰው ካሳለፍነው ሳምንት አጋማሽ ጀምሮ በተርጫ ዙሪያ ወረዳ ፣ ተርጫ ከተማ እና ገና ወረዳ ውስጥ ነው።

በወረዳዎቹ 15 ቀበሌዎች ተቀስቅሷል።

በሽታው መጀመሪያ የተከሰተው በተርጫ ከተማ 02 ቀበሌ ውስጥ ሲሆን በቀናት ውስጥ ወደ ተርጫ ዙሪያ እና ገና ወረዳዎች ተዛምቷል።

በአሁኑ ወቅት በበሽታው ለተያዙ ሰዎች 'በታርጫ ሆስፒታል' በተከፈተ ጊዜያዊ የለይቶ ማከሚያ ማዕከል ውስጥ ህክምና እየተሰጣቸው መሆኑን የዞኑን ጤና መምሪያ ዋቢ አድርጎ ጀርመን ድምፅ ሬድዮ ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#Somali

ዛሬ አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ በጀረር ዞን የተገነባውን 'ጋሻሞ ሆስፒታል' መርቀው ከፍተዋል።

በ80 ሚሊየን ብር የተገነባ ሲሆን ፣ በዙሪያው ለሚገኙ 5 ወረዳዎች አገልግሎት ይሰጣል።

ሆስፒታሉ ለ800 ሺህ ለሚጠጉ የህብረተሰብ ክፍሎች አገልግሎት ይሰጣል ተብሎ ይታሰባል።

አሁን ላይ በሱማሌ ክልል 12 የሚጠጉ ሆስፒታሎች በ1 ቢሊየን ብር በሚጠጋ በጀት የግንባታ፣ የማስፋፊያ እና የማሻሻያ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸው ተገልጿል።

በሌላ በኩል ፦

ዛሬ የሶማሌ ክልል የፋፈን ዞን የአውበሬ ወረዳ የጤና ጣቢያ የአስቸካይ (Emergency) የቀዶ ጥገና የሕክምና ክፍል አስመርቆ አገልግሎት አስጀምራል።

(SRTV)
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
አጫጭር መረጃዎች #1 ፦

- አቶ ሬድዋን ሁሴን ህወሓት ወደ ባህር ዳር የሮኬት ጥቃት መሰንዘሩን ለሮይተርስ ገልፀዋል። ጥቃቱ ጥዋት 12:20 አካባቢ እንደተፈፀመ የተገለፀ ሲሆን የደረሰ ጉዳት ስለመኖሩ አልተገለፀም።

- ህወሓት ጥዋት ወደ ባህር ዳር ከተማ የሮኬት ጥቃት መፈፀሙን አሳውቋል፤ኢላማው ኤርፖርቱ እንደነበረም ገልጿል። በሌላ በኩል በራያ ግንባር ድል እየተቀዳጀው ነው ሲል መግለጫ ሰጥቷል፤ አንድ ሂሊኮፕተር መቶ መጣሉን፣ 3 ታንክ ማቃጠሉን ገልጿል።

- ዶ/ር ደብረፅዮን ለሮተርስ በ3 ግንባር ድል እያደረጉ እንደሆነ ገልፀዋል፤ ተሰጠ የተባለው ጊዜ የፌዴራል ኃይሉን ሽንፈት ለመሸፈን እና ዳግም ለመሰባሰብ ነው ብለዋል።

- ድምፂ ወያነ ቴሌቪዥን ከጥዋት ጀምሮ ዝግጅቶቹ ተቋርጧል፤ ቴሌቪዥን ጣቢያው ከጥዋት እንስቶ እስካሁን እያሳየ የሚገኘው የቻናሉን ሎጎ ብቻ ነው።

- ዛሬ የመከላከያ ሰራዊት መቐለን በ50 ኪሎ ሜትር ርቀት መክበቡን/ቀለበት ውስጥ መክተቱን መንግስት ገልጿል ሲል ሮይተርስ አስነብቧል። የህወሓት ቡድን አባላት በ72 ሰዓት ውስጥ እጃቸውን እንዲሰጡ ጥሪ መቅረቡ ይታወቃል።

- ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ ለኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ለመቐለ ነዋሪዎች የህወሓት አመራሮች ከተደበቁበት አካባቢ እራሳቸውን እንዲያርቁ እና ከመከላከያ ጎን እንዲሰለፉ መልዕክት መተላለፉን ተናግረዋል። ጥሪው በበራሪ ወረቀት መበተኑን ገልፀዋል።

- የጠ/ሚ አብይ ከፍተኛ አማካሪ አቶ ማሞ ምህረቱ ፤ አሁን ላይ አብዛኛው የትግራይ ክፍል በመከላከያ ስር መሆኑ ለቢቢሲ ተናግረዋል። መቐለ ናት በመከላከያ ሠራዊት ቁጥጥር ስር ያልሆነችው፣ ዘመቻው በጥቂት ቀናት ይጠናቀቃል ብለዋል።

ህዳር 13/2013 ዓ/ም
(ቲክቫህ ኢትዮጵያ)

@tikvahethiopiaBOT
#Ethiopia

የጠ/ሚር ዶ/ር አብይ አህመድ ከፍተኛ አማካሪ የሆኑት አቶ ማሞ ምህረቱ ከቢቢሲዋ ጋዜጠኛ ካትሪን ባይሩሃንጋ ጋር ቃለ ምልልስ አድርገው ነበር።

አቶ ማሞ አሁን ላይ 'አብዛኛው' የትግራይ ክፍል በመከላከያ ስር መሆኑ ተናግረዋል።

'ሕግን የማስከበር' ዘመቻው በትግራይ ሕዝብ ላይ ያነጣጠረ አይደለም ሲሉም አሳውቀዋል።

ከዚህም በተጨማሪ ዘመቻው ሁሉንም የ "ህወሓት" አባላትን የሚመለከት ሳይሆን በህወሓት ውስጥ ያሉ ወንጀለኞች ላይ ያነጣጠረ ነው ብለዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፍተኛ አማካሪ አቶ ማሞ በርካታ ጥያቄ ከቢቢሲዋ ጋዜጠኛ ካትሪን ባይሩሃንጋ ተጠይቀው ምላሽ ሰጥተዋል ያንብቡ : https://telegra.ph/BBC-11-23

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#ArbaMinch

በጉማይዴ በተቀሰቀሰው ግጭት ከአንድ ሺህ አምስት መቶ በላይ ተፈናቃዮች በአርባምንጭ ፓሊስ መምሪያ ተጠልለው ይገኛሉ።

እኚህ ተፈናቃዮች በክልሉ መንግስት የምግብ ድጋፍ እያገኙ ሲሆን የአርባ ምንጭ ከተማ ማህረሰብም እያገዘ እያደረገ ይገኛል።

ዛሬ ህዳር 13 ቀን 2013 የአርባ ምንጭ ከተማ የእግር ኳስ ክለብ ደጋፊዎች ከተለያዩ ከንግድ ማህበረሰብ የሰበሰቡትን ፓስታ፣ መኮሮኒ፣ ውሃ ፣ አልባሳት እና የንፅህና መጠበቂያዎች እገዛ አድርገዋል።

የተደረገው እገዛ ከ80 ሺህ ብር በላይ የሚገመት ሲሆን ይህ ተግባር በቀጣነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የአርባ ምንጭ ከተማ የእግር ኳስ ክለብ ደጋፊ (ሙሌ ፉዴ) በፅሁፍ በላከልን መልዕክት አሳውቆናል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#COVID19Ethiopia

የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 4,963
• በበሽታው የተያዙ - 418
• ህይወታቸው ያለፈ - 4
• ከበሽታው ያገገሙ - 148

አጠቃላይ 106,203 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,651 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል ፤ 65,839 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።

326 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia