TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
214 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#FDREDefenseForce

ሀገር መከላከያ ሰራዊት ህወሓት ውስጥ ያለው ቡድን ሰራዊቱ እየወሰደ ያለውን 'የህግ ማስከበር' እርምጃ መቋቋም ተስኖታል ሲል ገልጿል።

በህግ የሚፈለጉት ህወሓት ውስጥ ያሉት ቡድኖች ከዚህ በኃላ ያላቸው አማራጭ "ተዋግቶ መሞት ፤ አልያም እጅ መስጠት ብቻ ነው" ብሏል ሰራዊቱ።

* የመከላከያ ህብረት ዘመቻ ዋና መምሪያ ኃላፊ ብ/ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው የሰጡት በካርታ የተደገፈ ማብራሪያ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#NBE

በትግራይ ክልል "የባንክ ሂሳብ የከፈቱ" እጅግ በጣም በርካታ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት ላለፉት ቀናት ገንዘብ ለማውጣታ ተቸግረዋል።

ለምን ይህ ሊሆን እንደቻለም እጅግ በጣም ግራ ተጋብተው ነበር።

በሀገራችን የተለያዩ ከተሞች በትምህርት ላይ የሚገኙ እና ቋሚ ኑሯቸውን ያደረጉ አባላቶቻችን #እየተቸገሩ መሆናቸው እየገለፁ ነው።

በዚህ ጉዳይ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ለአዲስ ፎርቹን ጋዜጣ እንደገለፀው በትግራይ ክልል የተከፈቱ የባንክ አካውንቶች ሁሉ እንደታገዱ አሳውቋል።

እግዱ "የትኛውንም የባንክ አካውንቶች" የሚመለከት ሲሆን አካውንቶቹ በጊዜያዊነት ለመንቀሳቀስ እንደማይችሉ ነው የተገለፀው፡፡

በክልሉ የተከፈተ አካውንት ያላቸው ግለሰቦች ሆኑ ድርጅቶች ለጊዜው ገንዘብ ማውጣት ሆነ ሂሳብ ማንቀሳቀስ እንዳይችሉ ብሄራዊ ባንኩ መመሪያ ሰጥቷል፡፡

ከሁለት ቀናት በፊት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ በሰጠው መግለጫ በትግራይ ክልል ንብረታቸው እና የባንክ አካውንታቸው የታገደባቸው ኤጀንሲዎች የህወሓት የንግድ እና የወንጀል ማስፈጸሚያ አካል የሆኑት ብቻ ሲል አስታውቆ እንደነበር ይታወሳል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DireDawa

በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር "የከባድ ተሽከርካሪዎች" የከተማ ውስጥ እንቅስቃሴ የሰዓት ገደብ ተላልፏል።

ከነገ ህዳር 14 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ ከንጋቱ 12 ሰዓት እስከ ምሽት 12 ሰዓት ድረስ ወደ ከተማ ውስጥ መግባት ሆነ በከተማ ውስጥ መንቀሳቀስ አይቻልም።

ወደ ከተማ ውስጥ መግባትም ይሁን በከተማ ውስጥ መንቀሳቀስ የፈቀደው ከምሽት 12 ሰዓት በኋላ እስከ ንጋት 12 ሰዓት ድረስ ብቻ ነው።

ምክንያት ?

ይህ የሰዓት ገደብ የተላለፈው በአስተዳደሩ እየተከሰተ ያለው የትራፊክ መጨናነቅና በዚህ ሳቢያ እየተፈጠረ ያለውን የመንገዶች መዘጋት እና መጉላላት ለመቀነስና ለማስቀረት በማሰብ ነው።

ምንጭ፦ ድሬ ፖሊስ
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#FDREDefenseForce

ዛሬ መከላከያ ሠራዊት ከአዲግራት ወደ መቐለ በሚወስደው መንገድ የምትገኘውን 'እዳጋ ሐሙስ' ከተማን መቆጣጠሩን አሳውቋል።

የመከላከያ ሠራዊቱ የዘመቻው የመጨረሻ ግብ የሆነችውን መቐለ ለመያዝ እየገሠገሠ ነው ሲል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ ገልጿል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#REPOST

በግጭቶች ፣ በሌሎች የብጥብጥ ሁኔታዎች / በአደጋዎች ወቅት ሰዎች በቁጥጥር ስር ሊውሉ ወይም ሊጠፉ ይችላሉ።

ይህ ሁኔታ በቤተሰቦቻቸው እና ወዳጆቻቸው ላይ ጭንቀትና አለመረጋጋት ይፈጥራል።

ሰዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ወይም የጠፉ ዘመዶቻቸው ምን እንደገጠማቸው የማወቅ #መብት አላቸው።

የዓለም ቀይ መስቀል ኮሚቴ የዘመዶቻቸውን ዕጣ ፈንታ እና የት እንደሚገኙ ለማወቅ የሚጥሩ ቤተሰቦችን ይደግፋል ፤ ያግዛል።

የICRC አገልግሎትን ለማግኘት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው የICRC ኢትዮጵያ ልዑክ 0943122207 / 011 552 71 10 ላይ በመደወል ማነጋገር ይቻላል።

(ከሰኞ እስከ አርብ ከ2:00 - 11:00 ሰዓት)

* የስልክ መስመሮቹ ሊጨናነቁ ስለሚችሉ ደጋግማችሁ ሞክሩ።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#ICRC

ኣብ ግጭታት እዋን ኣብ ካልኦት ናይ መጥቃዕቲ ኩነታት ወይ ከኣ ሓደጋታት ሰባት ኣብ ትህቲ ቁጽጽር ምስዋኣሉ ክጠፍኡ ወይ ክእሰሩ ይኽእሉ ፤ እዚ ድማ ኣብ ስድራቤቶም ጭንቀትን ዘይምርግጋዕን ይፍጠር።

ሰባት ኣብ ትህቲ ቁጽጽር ምስዋኣሉ ስድራቤቶም ናይ ምፍላጥ መሰል ኣለዎም።

ዓለም ለከ ቀይሕ መስቀል ኮሚቴ ድማ ስድራቤቶም ዝጠፍእዎም ቤተሰብ አበይ ከምዘለዉ ንምፍላጥ ንምድጋፍ ይደሊ።

ኣገልግሎትና ዝደቢ ዝኾነ ሰብ ድማ ናብ ኢትዮጵያ ዓለም ለከ ቀይሕ መስቀል ኮሚቴ ልኡኽ 0943122207 / 011 552 71 10 ብምድዋል ምዝራብን ምርካብን ይኽእሉ ኢዮም።

(ካብ ሶኒ እስካብ አርቢ ካብ 2፡00 ሰዓት እስካብ 11፡00 ሰዓት)

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#DrAbiyAhmed

መንግስት በህግ የሚፈለጉ የህወሓት ቡድን አባላት በ72 ሰዓታት ውስጥ በሰላም 'እጃቸውን እንዲሰጡ' ጥሪ አቀረበ።

ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ ዛሬ ምሽት ባሰራጩት መግለጫ የህወሓት ቡድን አባላት በቀጣዩ 72 ሰዓት ውስጥ በሰላም እጃቸውን በመስጠት የመጨረሻውን ዕድል እንዲጠቀሙ መልዕክት አስተላልፈዋል።

* ዝርዝር መግለጫው ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19Ethiopia

የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 4,495
• በበሽታው የተያዙ - 433
• ህይወታቸው ያለፈ - 11
• ከበሽታው ያገገሙ - 157

አጠቃላይ 105,785 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,647 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል ፤ 65,691 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።

333 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

የቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ኃላፊ የነበሩት አቶ ጉልላት ከበደ በኮቪድ-19 ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዱ ቆይተው ዛሬ ከዚህ አለም በሞት መለየታቸውን የአ/አ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ አሳውቀዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
አምስት የቀድሞ የወላይታ ዞን አመራሮች እና ሌሎች ሁለት ተጠርጣሪዎች ላይ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ ተመሰረተ።

ከአመራሮቹ ጋር በአንድ መዝገብ የጊዜ ቀጠሮ ጉዳያቸው ሲታይ የቆዩ 13 ተጠርጣሪዎች በነጻ እንዲለቀቁ በፍርድ ቤት ተወስኖላቸዋል።

ዛሬ ክስ እንደተመሰረተባቸው ከተገለጸላቸው አመራሮች ውስጥ የቀድሞው የወላይታ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ዳጋቶ ኩምቤ፣ ምክትላቸው ጎበዜ ጎዳና እና የዞኑ ብልጽግና ጽህፈት ቤት ኃላፊ የነበሩት አቶ ጥበቡ ዩሃንስ ይገኙበታል።

ምንጭ፦ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር
@TIKVAHETHIOPIABOT
TIKVAH-ETHIOPIA
#DireDawa በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር "የከባድ ተሽከርካሪዎች" የከተማ ውስጥ እንቅስቃሴ የሰዓት ገደብ ተላልፏል። ከነገ ህዳር 14 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ ከንጋቱ 12 ሰዓት እስከ ምሽት 12 ሰዓት ድረስ ወደ ከተማ ውስጥ መግባት ሆነ በከተማ ውስጥ መንቀሳቀስ አይቻልም። ወደ ከተማ ውስጥ መግባትም ይሁን በከተማ ውስጥ መንቀሳቀስ የፈቀደው ከምሽት 12 ሰዓት በኋላ እስከ ንጋት 12 ሰዓት ድረስ…
* ማሻሻያ

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ከከባድ ተሽከርካሪ ጋር ተያይዞ በተላለፈው የሰአት ገደብ ላይ ማሻሻያ አድርጓል።

ከነዳጅ ጫኝ ከባድ ተሽከርካሪ ውጪ ማንኛውም ከባድ ተሽከርካሪ ጠዋት ከ1 ሰአት እስከ 3 ሰአት እና ቀን ከ5 :30 እስከ 8:30 ወደ ከተማ መግባት ሆነ በከተማ ውስጥ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው።

ከላይ ከተገለፀው ሰአት ውጪ ወደ ከተማ ውስጥ መግባትም ይሁን በከተማ ውስጥ መንቀሳቀስ ይፈቀዳል።

የተጠቀሰውን የሰአት ገደብ ቢሚተላለፉ ላይ የህግ የእርምት እርምጃ የሚወሰድ መሆኑን ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

ለማሻሻያው ምክንያት ?

አሁን ላይ ካለው ከሀገሪቱ ከወጪ ገቢ ንግድ እና ከሌሎች ተጨማሪ ሁኔታዎች አንፃር ቀደም ብሎ በተላለፈው የእንቅስቃሴ ገደብ ላይ ማሻሻያ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል።

ምንጭ፦ ድሬ ፖሊስ
@tikvahethiopiaBOt @tikvahethiopia
ኮሌራ በዳውሮ 5 ሰዎችን ገደለ !

በደቡብ ክልል ዳዉሮ ዞን በተቀሰቀሰ ኮሌራ የአምስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 66 መታመማቸውን የዞኑ ጤና መምሪያ ለጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ አሳውቋል።

በሽታው የተቀሰቀሰው ካሳለፍነው ሳምንት አጋማሽ ጀምሮ በተርጫ ዙሪያ ወረዳ ፣ ተርጫ ከተማ እና ገና ወረዳ ውስጥ ነው።

በወረዳዎቹ 15 ቀበሌዎች ተቀስቅሷል።

በሽታው መጀመሪያ የተከሰተው በተርጫ ከተማ 02 ቀበሌ ውስጥ ሲሆን በቀናት ውስጥ ወደ ተርጫ ዙሪያ እና ገና ወረዳዎች ተዛምቷል።

በአሁኑ ወቅት በበሽታው ለተያዙ ሰዎች 'በታርጫ ሆስፒታል' በተከፈተ ጊዜያዊ የለይቶ ማከሚያ ማዕከል ውስጥ ህክምና እየተሰጣቸው መሆኑን የዞኑን ጤና መምሪያ ዋቢ አድርጎ ጀርመን ድምፅ ሬድዮ ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#Somali

ዛሬ አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ በጀረር ዞን የተገነባውን 'ጋሻሞ ሆስፒታል' መርቀው ከፍተዋል።

በ80 ሚሊየን ብር የተገነባ ሲሆን ፣ በዙሪያው ለሚገኙ 5 ወረዳዎች አገልግሎት ይሰጣል።

ሆስፒታሉ ለ800 ሺህ ለሚጠጉ የህብረተሰብ ክፍሎች አገልግሎት ይሰጣል ተብሎ ይታሰባል።

አሁን ላይ በሱማሌ ክልል 12 የሚጠጉ ሆስፒታሎች በ1 ቢሊየን ብር በሚጠጋ በጀት የግንባታ፣ የማስፋፊያ እና የማሻሻያ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸው ተገልጿል።

በሌላ በኩል ፦

ዛሬ የሶማሌ ክልል የፋፈን ዞን የአውበሬ ወረዳ የጤና ጣቢያ የአስቸካይ (Emergency) የቀዶ ጥገና የሕክምና ክፍል አስመርቆ አገልግሎት አስጀምራል።

(SRTV)
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
አጫጭር መረጃዎች #1 ፦

- አቶ ሬድዋን ሁሴን ህወሓት ወደ ባህር ዳር የሮኬት ጥቃት መሰንዘሩን ለሮይተርስ ገልፀዋል። ጥቃቱ ጥዋት 12:20 አካባቢ እንደተፈፀመ የተገለፀ ሲሆን የደረሰ ጉዳት ስለመኖሩ አልተገለፀም።

- ህወሓት ጥዋት ወደ ባህር ዳር ከተማ የሮኬት ጥቃት መፈፀሙን አሳውቋል፤ኢላማው ኤርፖርቱ እንደነበረም ገልጿል። በሌላ በኩል በራያ ግንባር ድል እየተቀዳጀው ነው ሲል መግለጫ ሰጥቷል፤ አንድ ሂሊኮፕተር መቶ መጣሉን፣ 3 ታንክ ማቃጠሉን ገልጿል።

- ዶ/ር ደብረፅዮን ለሮተርስ በ3 ግንባር ድል እያደረጉ እንደሆነ ገልፀዋል፤ ተሰጠ የተባለው ጊዜ የፌዴራል ኃይሉን ሽንፈት ለመሸፈን እና ዳግም ለመሰባሰብ ነው ብለዋል።

- ድምፂ ወያነ ቴሌቪዥን ከጥዋት ጀምሮ ዝግጅቶቹ ተቋርጧል፤ ቴሌቪዥን ጣቢያው ከጥዋት እንስቶ እስካሁን እያሳየ የሚገኘው የቻናሉን ሎጎ ብቻ ነው።

- ዛሬ የመከላከያ ሰራዊት መቐለን በ50 ኪሎ ሜትር ርቀት መክበቡን/ቀለበት ውስጥ መክተቱን መንግስት ገልጿል ሲል ሮይተርስ አስነብቧል። የህወሓት ቡድን አባላት በ72 ሰዓት ውስጥ እጃቸውን እንዲሰጡ ጥሪ መቅረቡ ይታወቃል።

- ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ ለኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ለመቐለ ነዋሪዎች የህወሓት አመራሮች ከተደበቁበት አካባቢ እራሳቸውን እንዲያርቁ እና ከመከላከያ ጎን እንዲሰለፉ መልዕክት መተላለፉን ተናግረዋል። ጥሪው በበራሪ ወረቀት መበተኑን ገልፀዋል።

- የጠ/ሚ አብይ ከፍተኛ አማካሪ አቶ ማሞ ምህረቱ ፤ አሁን ላይ አብዛኛው የትግራይ ክፍል በመከላከያ ስር መሆኑ ለቢቢሲ ተናግረዋል። መቐለ ናት በመከላከያ ሠራዊት ቁጥጥር ስር ያልሆነችው፣ ዘመቻው በጥቂት ቀናት ይጠናቀቃል ብለዋል።

ህዳር 13/2013 ዓ/ም
(ቲክቫህ ኢትዮጵያ)

@tikvahethiopiaBOT