TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#FDREDefenseForce

የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄነራል ብርሃኑ ጁላ የWHO ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም የ 'ህወሓትን ቡድን' በመደገፍ ከሰዋል።

የኢትዮጵያ ጎረቤት ሀገራትን ጭምር ጦርነቱን እንዲያወግዙ ሰርተዋል፤ የጦር መሳሪያዎችንም እንዲያገኙ ሰርተዋል ሲሉ ተናገረዋል።

ዶ/ር ቴድሮስ እስካሁን ለቀረበባቸው ክስ ምላሽ አልሰጡም።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ያላባራው የዜጎች ስቃይ በመተከል ፦ (በቲክቫህ መተከል ዞን አባላት) ከ4/3/2013 ጀምሮ እስከ ዛሬ ማባሪያ የሌለው የቤኒሻንጉል ክልል መተከል ዞን ድባጤ እና ቡለን ወረዳ "የንፁሃን ግድያ" አሁንም እንደቀጠለ ነው። ከያምፕ፣ ከአንግቶክ እና ከሌሎችም ቀበሌዎች ተፈናቅለው ድባጤ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተጠለሉት እስከ 3 ሺህ የሚጠጉ ዜጎች በከባድ ረሃብ ላይ ይገኛሉ። በተጨማሪ ከተለያዩ ቀበሌዎች…
#UPDATE

የቲክቫህ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ መተከል ዞን አባላት በአካባቢው እጅግ በተደጋጋሚ እየተፈፀመ ባለው "የንፁሃን ዜጎች" ጥቃት በርካታ ዜጎች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸውን ገልፀዋል።

አባላቶቻችን ባደረጉት ማጣራት እስካሁን ከአልባሳ እና ሙዘን ተፈናቅለው ጋሌሳ ቀበሌ የሰፈሩ 2680፣ ዳላቲ ቀበሌ የሰፈሩ 1500 በላይ ፣ ድባጤ ከተማ የሰፈሩ ደግሞ 4200 እንደሆኑ አሳውቀውናል።

* የሚመለከታቸውን አካላት አስፈላጊውን ሁሉ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
'የተሰደዱ ዜጎቻችን ጉዳይ'

ወደ ሱዳን የተሰደዱ ኢትዮጵያዊያንን ወደ ቀዬአቸው መመለስና ማቋቋም ላይ የሚሰራ ብሔራዊ ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ሥራ መግባቱ ተገልጿል።

ተፈናቃዮች ከልማት አጋሮች እና ዓለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች የሰብአዊ እርዳታ ድጋፍ የሚያገኙበት ሁኔታ ይመቻቻልም ተብሏል።

የኢትዮጵያ መንግስት ዜጎችን ወደቀዬአቸው የመመለስ ሥራውን ከሱዳን መንግስትና ከUNHCR ጋር በመሆን እንደሚከናወን ተገልጿል።

* ዝርዝር መረጃው ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 5,201
• በበሽታው የተያዙ - 499
• ህይወታቸው ያለፈ - 6
• ከበሽታው ያገገሙ - 390

አጠቃላይ 104,427 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,607 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል ፤ 64,983 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።

316 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#FDREDefenseForce የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄነራል ብርሃኑ ጁላ የWHO ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም የ 'ህወሓትን ቡድን' በመደገፍ ከሰዋል። የኢትዮጵያ ጎረቤት ሀገራትን ጭምር ጦርነቱን እንዲያወግዙ ሰርተዋል፤ የጦር መሳሪያዎችንም እንዲያገኙ ሰርተዋል ሲሉ ተናገረዋል። ዶ/ር ቴድሮስ እስካሁን ለቀረበባቸው ክስ ምላሽ አልሰጡም። @tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#DrTedrosAdhanom

ዶ/ር ቴድሮስ ኣድሃኖም ዛሬ በሰጡት መግለጫ በኢትዮጵያ ውስጥ አሁን ባለው ሁኔታ 'ለየትኛውም ወገን አልወገንኩም' ሲሉ አሳውቀዋል።

ከሰሞኑን እሳቸውን በሚመለከት እየወጡ ያሉ ዘገባዎችንም 'እውነት አይደሉም' ብለዋቸዋል።

እኔ የምወግነው ከአንድ ወገን ጋር ብቻ ነው እሱም ከ'ሰላም' ጋር ነው ብለዋል።

ዶክተር ቴድሮስ ኣድሃኖም በመግለጫቸው ፥ ሁሉም ወገኖች "ለሰላም እና ለሲቪሎች ደህንነት መጠበቅ" እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።

* ዶ/ር ቴድሮስ የሰጡት መግለጫ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#ባህርዳር

የባህር ዳር ቲክቫህ አባላት ከለሊት 7:40 አካባቢ ሶስት ጊዜ የፍንዳታ ድምፅ እንደሰሙ ገልፀዋል።

አባላቶቻችን ከዚህ ቀደም የሰሙት አይነት ተመሳሳይ ፍንዳታ እንደሆነም ነው የገለፁት።

ፍንዳታውን ተከትሎ የተኩስ ድምፅ እንደነበርም ገልፀዋል።

ዝርዝር መረጃ በሚመለከታቸው አካላት ሲገለፅ ተከታትለን እናሳውቃለን።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#UPDATE

የአማራ ክልል መንግስት የህወሓት ቡድን 7፡40 አካባቢ ወደ ባህር ዳር የሮኬት ጥቃት መፈፀሙን ለአብመድ አሳውቋል።

በተፈፀመው ጥቃት የደረሰ ጉዳት መኖር አለመኖሩ እየተጣራ መሆኑን የክልሉ መንግስት ገልጿል።

የሮኬት ጥቃቱ የት ቦታ ላይ ኢላማ እንዳደረግ አልተገለፀም።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#UPDATE

ትላንት ለሊት በባህር ዳር ከተማ የተፈፀመው የሮኬት ጥቃት ምንም አይነት ጉዳታ እንዳላደረሰ የክልሉ መንግስት ገልጿል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
'የሮይተርስ የኢትዮጵያ ዘጋቢ ታገደች'

የኢትዮጵያ መንግስት በዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ላይ እርምጃ እየወሰደ መሆኑ ተሰማ።

እርምጃ እየተወሰደባቸው የሚገኙት ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ሁኔታ ዓለም በተሳሳተ መንገድ እንዲያውቀውና በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ጫና እንዲበረታ በማድረጋቸው ነው ተብሏል።

የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 እንደተናገረው መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ወቅታዊውን ሁኔታ በጥንቃቄ እንዲሁም በሞያዊ ስነ ምግባር እንዲዘግቡ ማሳሰቢያ ቢሰጣቸውም በእንቢተኝነት በቀጠሉት ላይ እርምጃ መወሰዱን አሳውቋል።

ዶቼ ቨለ (DW) ፣ BBC ፣ ሮይተርስ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ከተሰጣቻው መካከል ይገኙበታል።

"ሮይተርስ" ከትላንትና ወዲህ በሀገር ውስጥ ያላቸው ዘጋቢ በኢትዮጵያ ጉዳይ ምንም አይነት እንቅስቃሴ እንዳታደርግ ፣ ዘገባዎችን ፣ ዜናዎችን እንዳትሰራ ሙሉ በሙሉ እንደታገደች የብሮድካስት ባለስልጣን ለሬድዮ ጣቢያው ገልጿል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#TiborNagy

አሜሪካ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳዮች ጣልቃ እንደማትገባ በይፋ አሳውቃለች።

በኢትዮጵያ መንግሥት እና በሕወሓት አመራር መካከል ትግራይ ውስጥ ያለው ግጭት የሚያበቃውም በሁለቱ ኃይላት መሆኑን አሜሪካ ገልፃለች።

ትናንት ማምሻውን የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪቃ ጉዳዮች ረዳት ሚንስትር ቲቦር ናዥ እና በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ሚካኤል ራይኖር ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ውስጥ ስላለው ሁኔታ በስልክ ኮንፈረንስ ለጋዜጠኞች ልዩ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ቲቦር ናዥ ፥ «የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ግጭቱ ፍጻሜ እንዲያገኝ፤ ሰላም እንዲሰፍን፤ ሰላማዊ ሰዎች መጠበቃቸውን ለማሳሰብ የተቻለውን ጥረት ያደርጋል» ብለዋል።

«ግጭቱን ማስቆም ያለበት ግን የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት አይደለም» ሲሉ አጽንዖት ሰጥተዋል።

* ዝርዝር መረጃው ከላይ ተያይዟል (በጀርመን ድምፅ ሬድዮ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው ዛሬ በ10,000 ብር ዋስ ፍርድ ቤት ከእስር እንዲለቀቅ ቢወሰንለትም ፣ ፖሊስ ይግባኝ በመጠየቁ ሊለቀቅ እንዳልቻለ "አውሎ ሚዲያ" ገለፀ። "የመዝገብ ክፍል ሰዎች ባለመኖራቸው" ምክንያት ክሊራንስ ጨርሶ ከእስር የሚወጣው ነገ ነው ተብሎ ነበር። ማምሻውን ፖሊስ ይግባኝ ስለጠየቀበት በእስር ይቆያል። @tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ጋዜጠኛ በቃሉ ከእስር ተፈታ !

ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው በ10 ሺ ብር ዋስ ዛሬ ማምሻውን ከእስር ተለቋል።

ባለፈው ማክሰኞ በዋስ እንዲለቀቅ ፍርድ ቤቱ ወስኖ የነበረ ቢሆንም ፤ ፖሊስ ይግባኝ ስለጠየቀበት በእስር እንዲቆይ እንደተደረገ ይታወሳል።

ዛሬ በነበረው የፍርድ ቤት ውሎ በዋስ እንዲለቀቅ ተወስኖ የነበረውን ውሳኔ በማፅደቅ ከእስር መፈታቱን አውሎ ሚዲያ በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የአውሮፓ ኮሚሽን ድጋፍ አደረገ።

በትግራይ ክልል በተከሰተው ጦርነት ምክንያት ወደ ሱዳን እየተሰደዱ ላሉ ዜጎች የአስቸኳይ እርዳታ አራት ሚሊዮን ዩሮ ለግሷል።

የአስቸካይ እርዳታው በጦርነቱ ምክንያት ቤት ንብረታቸውን ጥለው ወደ ሱዳን ለተሰደዱ ኢትዮጵያውያን የሚውል ነው ብሏል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 5,488
• በበሽታው የተያዙ - 452
• ህይወታቸው ያለፈ - 13
• ከበሽታው ያገገሙ - 342

አጠቃላይ 104,879 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,620 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል ፤ 65,325 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።

315 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#FDREDefenseForce ዛሬ ህዳር 11 ቀን 2013 ዓ/ም የሀገር መከላከያ ሠራዊት አክሱምን ፣ አድዋን እና የአዲግራትን ዙሪያ እንደተቆጣጠረ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመረጃ ማጣሪያ ከደቂቃዎች በፊት ባወጣው መግለጫ ገልጿል። * ዝርዝር መግለጫው ከላይ ተያይዟል። @tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
* ማብራሪያ

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ በሰጠው ማብራሪያ ሀገር መከላከያ ሰራዊት አክሱም እና አድዋን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሯል።

በተጨማሪም ሰራዊቱ የአዲግራትን ዙሪያ እንደተቆጣጠረ የተገለፀ ሲሆን ወደ "አዲግራት ከተማ" አየገሰገሰ ይገኛል ብሏል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ATTENTION በደቡብ ክልል የኮንሶ ዞን ፣ የአሌ ልዩ ወረዳ ፣ የቡርጂ እና የደራሼ ልዩ ወረዳ አዋሳኝ አከባቢዎች ከፍተኛ የጸጥታ ስጋት መኖሩን የቲክቫህ ቤተሰቦች ጠቁመዋል። ያንብቡ : https://telegra.ph/TIKVAH-11-19-2 @TIKVAHETHIOPIA @TIKVAHETHIOPIABOT
'94,586 ሰዎች ተፈናቅለዋል'

በደቡብ ክልል ኮንሶ ዞን "በታጣቂዎች የተፈፀመውን ጥቃት" ተከትሎ 94,586 ሰዎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል።

የኮንሶ ዞን ባለስልጣናት ለዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ እንደገለፁት ነዋሪዎች የተፈናቀሉት ኮልሜ ክልስተር፣ ካራትና በሰገን ዙሪያ ወረዳዎች ከሚገኙ መንደሮች ነው።

ከኮልሜ ክላስተር ቦርቆራ ቀበሌ የተፈናቀሉ አንድ አርሶ አደር ፥ ስለሆኔታው ምንም እንደማያውቁ ተናግረዋል። አርሶ አደሩ ፥ "ንብረታቸው ወድሟል፣ ቤታችን ተቃጥሏል፣ ንብረታቸው ተዘርፏል፣ ብዙ ሰውም ሞቷል፣ ቆስሏል በአጠቃላይ በስቃይ ውስጥ ነን ሲሉ" ገልፀዋል።

የኮንሶ ዞን ባለስልጣናት አሁንም የታጠቁ አካላት በአካባቢው እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙ ገልፀዋል።

ትላንትም በሰው እና በተሽከርካሪ ላይ ጥቃት አድርሰዋል።

ለተፈናቀሉ ዜጎች 'የሰብዓዊ እርዳታ' እንዲያገኙ ዞኑ ለደቡብ ክልል የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን የድጋፍ ጥያቄ ማቅረቡን ለዶቼ ቨለ ሬድዮ ገልጿል።

ከዚህ በተጨማሪ ቢቢሲ በዚህ ጉዳይ ያዘጋጀውን ሰፊ ዘገባ ያንብቡ : https://telegra.ph/BBC-11-20

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የኢሰመጉ አስቸኳይ ጋዜጣዊ መግለጫ !

(አስከፊ ደረጃ ላይ ያለው የሰብዓዊ መብቶች ሁኔታ በኢትዮጵያ)

- የኮንሶ ዞን እና አዋሳኝ አካባቢዎች
- የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል
- የምዕራብ ወለጋና የቄለም ወለጋ አካባቢዎች
- የጋዜጠኞች እስር

ህዳር 11 ቀን 2013 ዓ.ም

* ይህ መግለጫ የወጣው ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው ከእስር ከመፈታቱ ቀደም ብሎ ነው።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia