TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.4K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
'ህወሓት ለጥቃቱ ኃላፊነት ወሰደ' "ህወሓት" ትላንትና ምሽት በኤርትራ አስመራ ከተማ የሮኬት ጥቃት መፈፀሙን አረጋግጧል። ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ፥ የአስመራ ኤርፖርትን ኢላማ ያደረገ ጥቃት መፈፀማቸውን ዛሬ "ለሮይተርስ" ተናግረዋል። በትላንት ምሽቱ ጥቃት ስለደረሰው ጉዳት ዝርዝር እስካሁን አልታወቀም። * የኤርትራ መንግስት እስካሁን ይፋዊ መረጃ አልሰጠም። @tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ግጭቱን ዓለም አቀፍ ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት አሜሪካ አወገዘች !

ትላንት 'ሕወሓት' በኤርትራ ላይ የፈጸመውን ተቀባይነት የሌላቸው ጥቃቶች እና በትግራይ ክልል የተፈጠረውን ግጭት ዓለም አቀፍ ለማድረግ የሚያደርገውን ጥረት አሜሪካ አጥብቃ #እንደምታወግዝ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚነስትር ቲቦር ናጊ አስታወቁ፡፡

ረዳት ሚኒስትር ናጊ ፥ "ሰላማዊ ሰዎችን ለመጠበቅ ፣ ውጥረቶችን ለማርገብ እና ሰላምን ለማስፈን አፋጣኝ እርምጃ እንዲወሰድ ማበረታታችንን እንቀጥላለን" ሲሉ በትዊተር ገፃቸው ላይ ፅፈዋል።

Via AlAin News
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
'የሽምግልና የውይይት ጉዳይ'

በፌዴራል መንግስት ስር የሚገኘው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማጣሪያ በዩጋንዳ የፌዴራሉ ባለስልጣናት "ከህወሓት" ጋር ለሽምግል እና ውይይት ሊቀመጡ እየተባለ የሚሰራጨው መረጃ #ሀሰት ነው ብሏል።

ይህ መረጃ በተለያዩ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ሳይቀር ሲሰራጭ ነበር።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማጣሪያው ፥ "የፌዴራል መንግስት በትግራይ ክልል የህግ የበላይነትን ለማስከበር በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል" ሲል ለህዝብ ባሰራጨው አጭር መግለጫ ገልጿል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
'ከ20 ሺ በላይ ሰዎች ውጊያውን ሸሽተው ሱዳን ገብተዋል'

UNHCR Sudan በትግራይ ክልል እየተካሄደ ያለውን ውጊያ ሸሽተው ወደ ሱዳን የገቡ ሰዎች ከ20,000 ማለፋቸውን ይፋ አድርጓል።

ውጊያውን ሸሽተው ሱዳን የገቡት አብዛኞቹ ሴቶች እና ህፃናት ሲሆኑ ወንዶችም ይገኙበታል።

UNHCR እና አጋሮቹ እገዛ ለማድረግ እየሰሩ የሚገኝ ሲሆን "ሃምዳያት" አካባቢ ያሉ የሱዳን ማህበረሰቦችም ምግብ እና የሚጠጣ እያቀረቡ ነው።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
ዶናልድ ትራምፕ አሁንም በምርጫው መሸነፋቸውን አምነው አልተቀበሉም።

ፕሬዜዳንቱ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት 'ምርጫውን ያሸነፍኩት እኔ ነኝ' የሚል መልዕክት በይፋዊ የትዊተር ገፃቸው ፅፈዋል።

ምንም እንኳን ትራምፕ ደጋግመው ምርጫው ተጨብርብሯል ቢሉም እስካሁን አንድም መጭበርበሩን የሚያሳይ #ማስረጃ አልተገኘም።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የፌዴሬሽን ምክር ቤት ፦

" ... የፌዴራል መንግስቱ ለድርድር ይቀመጥ ማለት ለህወሓት ህጋዊ እና ሞራላዊ የእኩልነት ደረጃ እንደመስጠት ተደርጎ ይቆጠራል።

ሊደራደሩ የሚችሉበት ህጋዊም ሞራላዊም አግባብ የለም። የፌዴራል መንግስቱ ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን ለመታደግ እየሰራ ይገኛል።

ፌዴራል መንግስቱ ህገ መንግስታዊ የሆነ ስልጣኑን ተጠቅሞ ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን ለመታደግ ካልቻለ እና መደራደርን ከመረጠ ወደ ፊት እጅግ አደገኛ ሁኔታ ይገጥመዋል።

ይህም ማለት ሌሎች የፌዴሬሽኑ አካል የሆኑ የክልል መንግስታት የፌዴራሉን መንግስት ያለ ማንም ከልካይነት መገዳደር እንዲችሉ መፍቀድ ማለት ነው።"

* ዛሬ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ያወጣው መግለጫ ሙሉ ሀሳብ ከላይ ተያይዟል (የተዘጋጀው በአልዓይን AlAin ሚዲያ ነው)

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethipia
#Security_Alert

መንበረ ሠላም የሚገኙ የቲክቫህ አባላት በአሁን ሰዓት ከባድ ተኩስ እንዳለ ገልፀዋል።

ታጣቂዎች ወደ #ድባጤ ሰብረው ሊገቡ ነው ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በቂ የሆነ የሰላም አስከባሪ ኃይል እንደሌለ አሳውቀዋል።

* ይህ አካባቢ እስካሁን ድረስ ከስጋት ቀጠና አልተላቀቀም።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
'የUNHCR ሰራተኞች አልታሰሩም'

(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

UNHCR ፥ "በትግራይ ክልል የሚሰሩ ሰራተኞቹ ታስረዋል" በሚል በመገናኛ ብዙሃን የተሰራጨው ዘገባ ሐሰት መሆኑን ገለጸ።

በተጨማሪም 'የድርጅቱ ተሽከርካሪዎች ተወርሰዋል' ተብሎ በመገናኛ ብዙሃን የተሰራጨው መረጃ የተሳሳተ ነው ብሏል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#FireAlert

በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ኤድናሞል አካባቢ 'ከባድ' የእሳት አደጋ ደርሷል።

አደጋው የደረሰው ኤድናሞል አካባቢ ቦሌ መሰናዶ ትምህርት ቤት ፊት ለፊት በሚገኝ አንድ የቻይና ኮንስትራክሽን ድርጅት መጋዘን ላይ መሆኑ ተገልጿል።

እሳቱ አሁን ላይ 'በፍጥነት በመቀጣጠል' ላይ ሲሆን የእሳት አደጋ መቆጣጠር ሰራተኞች ወደ ቦታው እንዳልደረሱ Ethio FM 107.8 አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#Mekelle

ዛሬ ሰኞ ረፋድ ላይ በመቐለ ከተማ የአየር ጥቃት መፈጸሙን የከተማዋ ነዋሪችን ዋቢ አድርጎ ቢቢሲ ከስፍራው ዘግቧል።

የጦር አውሮፕላን ድምጽ በተሰማበት ጊዜ በነዋሪዎች ዘንድ መደናገጥ ተፈጥሮ የነበረ ሲሆን ፤ ጥቃቱ በሰዎች ላይ ጉዳት አለማድረሱን ቢቢሲ አሳውቋል።

"የትግራይ ቴሌቪዥን" ረፋድ 04፡45 ላይ ጥቃቱ መፈጸሙን አረጋግጧል። የጥቃቱ ኢላማ ቀዳማይ "ወያነ ክፍለ ከተማ" ውስጥ በሚገኘው እንዳ ጊዮርጊስ በተባለው አካባቢ መሆኑን ገልጿል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#FDREDefenseForce

የሀገር መከላከያ ሰራዊት 'ህወሓት' ከሰሜን እዝ ወስዷቸው የነበሩትን አብዛኞቹን 'ታንኮቹን' እንዳስመለሰ ዛሬ አሳውቋል።

አንዳንዶቹ ታንኮች ደግሞ እንዲወድሙ መደረጉን ሰራዊቱ ገልጿል።

ፎቶውን ኢቢሲ ከስፍራው እንዳገኛቸው ገልጾ አሰራጭቷል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Security_Alert መንበረ ሠላም የሚገኙ የቲክቫህ አባላት በአሁን ሰዓት ከባድ ተኩስ እንዳለ ገልፀዋል። ታጣቂዎች ወደ #ድባጤ ሰብረው ሊገቡ ነው ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል። በቂ የሆነ የሰላም አስከባሪ ኃይል እንደሌለ አሳውቀዋል። * ይህ አካባቢ እስካሁን ድረስ ከስጋት ቀጠና አልተላቀቀም። @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

በመተከል ዞን ''ድባጤ ወረዳ'' በታጣቂዎች ጥቃት 3 ሰዎች ቆስለዋል።

ይህን የወረዳው የኮሙዩኒኬሽን ቢሮ 'ለኢትዮጵያ ኢንሳይደር' ድረገፅ አረጋግጧል።

በጥቃቱ የቆሰሉት 3 ሰዎች ወደ ድባጤ ከተማ ጤና ጣቢያ ተወስደዋል።

የወረዳው ኮሚኒኬሽን ቢሮ ተኩሱን የከፈቱት “ታጥቀው የገቡ ጸረ-ሰላም ኃይሎች ናቸው” ብሏል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#BREAKING

ሞደርና ያመረተው የኮቪድ-19 ክትባት 94.5 % ውጤታማ መሆኑን በዛሬው ዕለት አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#ሀሰተኛ_ደብዳቤ

ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የወጣ ነው ተብሎ እየተሰራጨ የሚገኘው ይህ ደብዳቤ የተቀነባበረና ሀሰተኛ ደብዳቤ ነው።

* ወላጆችና ተማሪዎች አትረበሹ!

@tikvahethiopiaBOT
#Security_Alert

በደቡብ ክልል 'ጋቶ ቀበሌ' የፀጥታ ችግር መኖሩን የቲክቫህ አባላት አሳውቀዋል።

ዛሬም ከባድ የተኩስ ድምፅ ይሰማ እንደነበር ገልፀዋል።

በተመሳሳይ ሁኔታ 'ጉማይዴ' አካባቢ ከሰሞኑ የፀጥታ ችግር መኖሩን አባላቶቻችን አሳውቀዋል።

* የቲክቫህ አባላት ፣ አርሶ አደሮች በአካባቢው ላይ ዘላቂ እና አስተማማኝ ሰላም እንዲፈጠር ጠይቀዋል። የዜጎች ደህንነት ያሳስበኛል የሚል የመንግስት አካል መፍትሄ እንዲፈልግ ጥሪ አቅርበዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#ማስተካከያ

የአዲስ አበባ ፖሊስ ዛሬ 'ደጎል አደባባይ' ተብሎ በሚጠራው አካባቢ "ፖሊስ ፈንጂ አመከነ" በሚል የተሰራጨው መረጃ 'ስህተት' መሆኑን ማምሻውን አሳውቋል።

ፖሊስ አረጋግጥኩት ባለው መሰረት ቦታው የነበረ በላስቲክ የተሞላ 'ድራፍት ቢራ' እንጂ 'ፈንጂ' አለመሆኑን ህብረተሰቡ እዲገነዘብ ብሏል።

የአ/አ ፖሊስ መግለጫ ከላይ ተያይዟል።

* ከቲክቫህ አባላት ሁኔታውን በሚመለከት የሰጡት መረጃም ተነስቷል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#COVID19

የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ከ30,000 ለሚልቁ የጦር እና የብሄራዊ አገልግሎት አባላቷ የኮቪድ-19 ክትባት መስጠቷን አስታወቀች፡፡

ክትባቱ አባላቱን ከወረርሽኙ ለመጠበቅ ወሳኝ ነው ተብሏል፡፡

ዩኤኢ በቻይናዊው መድኃኒት አምራች "ሲኖፎርማር" የተዘጋጀው የኮቪድ -19 ክትባት የምዕራፍ 3 ሙከራ በሃገሯ ከተካሄደ በኋላ በተወሰነ መልኩ ክትባቱ ግልጋሎት ላይ እንዲውል ፈቅዳለች፡፡

ከዚያ ወዲህ ክትባቱ "ግንባር ቀደም ተጋላጭ" የሆኑ የህክምና፣ የፖሊስ አባላትን እና ከፍተኛ ባለስልጣናትን እንዲሁም የዱባይ ምክትል ፕሬዝዳንት እና ገዥ ሼክ መሀመድ ቢን ራሺድን ጨምሮ ለሃገሪቱ የካቢኔ አባላት ተሰጥቷል እንደ ዘ ናሽናል ዘገባ፡፡

Via AlAin News
@tikvahethiopiaBOT @tikahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
'ህወሓት ለጥቃቱ ኃላፊነት ወሰደ' "ህወሓት" ትላንትና ምሽት በኤርትራ አስመራ ከተማ የሮኬት ጥቃት መፈፀሙን አረጋግጧል። ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ፥ የአስመራ ኤርፖርትን ኢላማ ያደረገ ጥቃት መፈፀማቸውን ዛሬ "ለሮይተርስ" ተናግረዋል። በትላንት ምሽቱ ጥቃት ስለደረሰው ጉዳት ዝርዝር እስካሁን አልታወቀም። * የኤርትራ መንግስት እስካሁን ይፋዊ መረጃ አልሰጠም። @tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#UPDATE

የስፔን መንግስት በኤርትራ (አስመራ ከተማ) ላይ ህወሓት 'ፈጽሞታል' የተባለውን የአየር ጥቃት ማውገዙን ዶቼ ቨለ አስነብቧል።

የኢትዮጵያን የግዛት አንድነት እና ሕገ-መንግሥታዊ ተቋማት የሚያከብር መፍትሔ እንዲፈለግ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ጠይቋል።

የስፔን መንግስት ቀውሱ ከመባባስ እንዲገታ ጠይቋል።

ስፔን የአፍሪካ ህብረት እና የምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) የሚወስዱትን እርምጃ እንደምትደግፍ አስታውቃለች።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia