TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.4K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
'ህወሓት ለጥቃቱ ኃላፊነት ወሰደ'

"ህወሓት" ትላንትና ምሽት በኤርትራ አስመራ ከተማ የሮኬት ጥቃት መፈፀሙን አረጋግጧል።

ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ፥ የአስመራ ኤርፖርትን ኢላማ ያደረገ ጥቃት መፈፀማቸውን ዛሬ "ለሮይተርስ" ተናግረዋል።

በትላንት ምሽቱ ጥቃት ስለደረሰው ጉዳት ዝርዝር እስካሁን አልታወቀም።

* የኤርትራ መንግስት እስካሁን ይፋዊ መረጃ አልሰጠም።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
"መከላከያ የትግራይ ህዝብ ድጋፍ አለው" - አቶ ነብዩ ስሑልሚካኤል

ከEPA ጋር ቃለምልልስ ያደረጉት አቶ ነብዩ ስሑልሚካኤል ህወሓት በፈፀመው መከላከያን የማጥቃት ተግባር በርካታ የትግራይ ነዋሪዎች እያወገዙት ነው አሉ።

አቶ ነብዩ ፥ ምናልባት የሕዝቡን ድምጽ ካለው አፈና አንጻር በጉልህ ባይሰማም በተለያየ መልኩ ድርጊቱን እያወገዘ ነው ብለዋል።

ልዩ ኃይሉ ዓላማ ለሌለው ጦርነት እራሳችንን አንማግድም ማለት ጀምሯል ያሉት አቶ ነብዩ ፤ ሚሊሻውም ይህ ጦርነት የጥቂት 'የህውሓት ካድሬዎች' ጦርነት እንጂ የሕዝብ ጦርነት ባለመሆኑ አንዋጋም እያለ ይገኛል ሲሉ ተናግረዋል።

ይህን ተከትሎ ልዩ ኃይሉም ሆነ ሚኒሻው እጁን ለመከላከያ በመስጠት ላይ እንደሚገኝ አመልክተዋል።

መከላከያ ሰራዊቱ ከትግራይ ሕዝብ ጭምር በሚያገኘው ሕዝባዊ ድጋፍ እየተመራ ጦርነቱን በአጭር ጊዜ ለመቋጨት ወደ አጥፊው ቡድን በመንደርደር ላይ ይገኛል ብለዋል።

አቶ ነብዩ፥ "ቡድኑ የትግራይ ሕዝብ ከጎኔ ነው ቢልም ሕዝቡ ትኩረት ነፍጎታል ፤ ለጦርነት እንዲነሳ ቢጎተጉተውም ግማሹ ዝምታን ሲመርጥ ግማሹ በግላጭ ተቃውሞ እያሰማ ነው ፤ ከቡድኑ ጎን አለመሆኑንም እያሳየ ነው" ብለዋል።

በአጠቃላይ ህወሓት እና ህዝቡ አንድ ናቸው የሚለው ባዶ ትርክት መሆኑን ሕዝቡ በገሃድ እያሳየ ነው ሲሉ ገልፀዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
አቶ ነብዩ ስሑልሚካኤል "በሰሜን ዕዝ" ላይ ስለተፈፀመው ጥቃት ለEPA ከተናገሩት ፦

"በሰሜን ዕዝ ላይ ህወሓት አሳፋሪ የጭካኔ ተግባር ሲፈጽም የትግራይ ሕዝብ መከላከያን ከጨካኙ ደርጊት የመከላከል ታሪካዊ ስራ ሰርቷል።

ህወሓት ድርጊቱን የፈጸመው ጨለማን ተገን አድርጎ እንጂ በብርሃን ቢሆን በመከላከያ ላይ ይህን ያህል ጥቃት ሳይደርስ ሕዝቡ በራሱ ሊያመክነው ይችል ነበር።

ይህ ቡድን ከዚህ በኋላ እንኳን መንግስት ሆኖ ሊቀጥል ቀርቶ ቡድን ሆኖ መቀጠል ከማይችልበት የመጨረሻ ደረጃ ላይ ደርሷል።

በተለይም በሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ በፈጸመው ጥቃት ሕዝብ አንቅሮ ከመትፋቱ ባሻገር ወንጀለኛ ሆኖ እየታደነ ነው፤ በቅርቡ ግብዓተ መሬቱ ይፈጸማል።"

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የትራምፕ ደጋፊዎች ሰልፍ በዋሽንግቶን ዲሲ ፦

ዶናልድ ትራምፕ የምርጫ ውጤት ተጭበርብሯል የሚለውን አስተያየታቸውን ተከትሎ ደጋፊዎቻቸው በዋሽንግቶን ዲሲ በመሰባሰብ በውጤቱ ላይ ያላቸውን ተቃውሞና ለፕሬዝዳንቱ ያላቸውን ድጋፍ ገልጸዋል።

የምርጫው "ሁሉም ግዛቶች" ውጤት የታወቀ ሲሆን ባይደን በሰፊ ልዩነት ትራምፕን አሸንፈዋል ፤ ትራምፕ ግን ምርጫው ተጭበርብሯል በማለት እስካሁን ሽንፈታቸውን አልተቀበሉም።

Via BBC/CNN/Jenn Pellegrino
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ፥ "የሕውሓት ቅጥረኛ ቡድን በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ ባደረሰው ጥቃት የንጹኃን ዜጎች ሕይወት አለፈ" ሲል አስታወቀ። የክልሉ መንግስት ፥ በሕወሓት የሚደገፈው የጥፋት ቡድን ከትናንት በፊት ጀምሮ በውብግሽ ፣ ያምፕ እንዲሁም ቂዶህ ቀበሌዎች ውስጥ ባደረሰው ጥቃት የንጹኃን ዜጎች ሕይወት አልፏል ብላል። በተጨማሪም የጥፋት ኃይሎች ከወምበራ - ቡለን - ድባጤ…
#UPDATE

ኢሰመኮ ትላንት በደባጤ ወረዳ ከወንበራ ወደ ቻግኒ በመጓዝ ላይ በነበረ 'የሕዝብ ማመላሻ አውቶብስ' ላይ በተፈጸመው ዘግናኝ ጥቃት እስካሁን 34 ሰዎች መገደላቸውን ገልጿል።

ቁጥሩ ሊጨምር እንደሚችል ይጠብቃል ብሏል።

በሌላ በኩል ፦

ጥቃቱን ፈፅመው #ንጹሃንን ከገደሉት መካከል 16ቱ ሲደመሰሱ 2 ሰዎች በህይወት መያዛቸውን የክልሉን ፖሊስ ጠቅሶ ኢዜአ ዘግቧል።

* የኢሰመኮ መግለጫ እንዲሁም የኢዜአ ዝርዝር መረጃ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#FDREDefenseForce

ሰራዊቱ አላማጣና አካባቢውን መቆጣጠሩን ገልጿል።

መከላከያ ከአማራ ክልል የልዩ ኃይል ፖሊስ እና ሚሊሻ ጋር በመሆን ዋጃ ፣ ጥሙጋ ፣ አላማጣ እና አካባቢውን በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ይፋ አድርጓል።

መከላከያ አካባቢዎቹን ሲቆጣጠር በህብረተሰቡ ላይ 'ምንም አይነት ጉዳት' እንዳልደረሰም አሳውቋል።

የግራካሶ ተራራና አካባቢውን ለመቆጣጠር እየገሰገሰ እንደሚገኝ ገልጿል።

ሰራዊቱ በምስራቅ አላማጣ ፣ በጨርጨር አካባቢ ድል እያስመዘገበ እንደሚገኝም አሳውቋል።

* መከላከያ ሰራዊት ለህዝብ ያሰራጨው መረጃ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
'እጅግ እየተባባሰ የመጣው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ'

ትላንት ብቻ በመላው ዓለም ላይ 8,802 ሰዎች በኮቪድ-19 ህይወታቸው አልፏል።

በተመሳሳይ በ24 ሰዓት ውስጥ 575,845 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ በአጠቃላይ 54, 480 , 640 በበሽታው መያዛቸው ሲረጋግጥ ፤ 1, 320, 616 ህይወታቸው አልፏል።

#እራሳችሁን_ጠብቁ!

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 5,002
• በበሽታው የተያዙ - 399
• ህይወታቸው ያለፈ - 4
• ከበሽታው ያገገሙ - 191

አጠቃላይ 102,720 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,569 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል ፤ 63,866 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።

319 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
'ህወሓት ለጥቃቱ ኃላፊነት ወሰደ' "ህወሓት" ትላንትና ምሽት በኤርትራ አስመራ ከተማ የሮኬት ጥቃት መፈፀሙን አረጋግጧል። ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ፥ የአስመራ ኤርፖርትን ኢላማ ያደረገ ጥቃት መፈፀማቸውን ዛሬ "ለሮይተርስ" ተናግረዋል። በትላንት ምሽቱ ጥቃት ስለደረሰው ጉዳት ዝርዝር እስካሁን አልታወቀም። * የኤርትራ መንግስት እስካሁን ይፋዊ መረጃ አልሰጠም። @tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ግጭቱን ዓለም አቀፍ ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት አሜሪካ አወገዘች !

ትላንት 'ሕወሓት' በኤርትራ ላይ የፈጸመውን ተቀባይነት የሌላቸው ጥቃቶች እና በትግራይ ክልል የተፈጠረውን ግጭት ዓለም አቀፍ ለማድረግ የሚያደርገውን ጥረት አሜሪካ አጥብቃ #እንደምታወግዝ በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚነስትር ቲቦር ናጊ አስታወቁ፡፡

ረዳት ሚኒስትር ናጊ ፥ "ሰላማዊ ሰዎችን ለመጠበቅ ፣ ውጥረቶችን ለማርገብ እና ሰላምን ለማስፈን አፋጣኝ እርምጃ እንዲወሰድ ማበረታታችንን እንቀጥላለን" ሲሉ በትዊተር ገፃቸው ላይ ፅፈዋል።

Via AlAin News
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
'የሽምግልና የውይይት ጉዳይ'

በፌዴራል መንግስት ስር የሚገኘው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማጣሪያ በዩጋንዳ የፌዴራሉ ባለስልጣናት "ከህወሓት" ጋር ለሽምግል እና ውይይት ሊቀመጡ እየተባለ የሚሰራጨው መረጃ #ሀሰት ነው ብሏል።

ይህ መረጃ በተለያዩ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ሳይቀር ሲሰራጭ ነበር።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማጣሪያው ፥ "የፌዴራል መንግስት በትግራይ ክልል የህግ የበላይነትን ለማስከበር በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል" ሲል ለህዝብ ባሰራጨው አጭር መግለጫ ገልጿል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
'ከ20 ሺ በላይ ሰዎች ውጊያውን ሸሽተው ሱዳን ገብተዋል'

UNHCR Sudan በትግራይ ክልል እየተካሄደ ያለውን ውጊያ ሸሽተው ወደ ሱዳን የገቡ ሰዎች ከ20,000 ማለፋቸውን ይፋ አድርጓል።

ውጊያውን ሸሽተው ሱዳን የገቡት አብዛኞቹ ሴቶች እና ህፃናት ሲሆኑ ወንዶችም ይገኙበታል።

UNHCR እና አጋሮቹ እገዛ ለማድረግ እየሰሩ የሚገኝ ሲሆን "ሃምዳያት" አካባቢ ያሉ የሱዳን ማህበረሰቦችም ምግብ እና የሚጠጣ እያቀረቡ ነው።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
ዶናልድ ትራምፕ አሁንም በምርጫው መሸነፋቸውን አምነው አልተቀበሉም።

ፕሬዜዳንቱ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት 'ምርጫውን ያሸነፍኩት እኔ ነኝ' የሚል መልዕክት በይፋዊ የትዊተር ገፃቸው ፅፈዋል።

ምንም እንኳን ትራምፕ ደጋግመው ምርጫው ተጨብርብሯል ቢሉም እስካሁን አንድም መጭበርበሩን የሚያሳይ #ማስረጃ አልተገኘም።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የፌዴሬሽን ምክር ቤት ፦

" ... የፌዴራል መንግስቱ ለድርድር ይቀመጥ ማለት ለህወሓት ህጋዊ እና ሞራላዊ የእኩልነት ደረጃ እንደመስጠት ተደርጎ ይቆጠራል።

ሊደራደሩ የሚችሉበት ህጋዊም ሞራላዊም አግባብ የለም። የፌዴራል መንግስቱ ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን ለመታደግ እየሰራ ይገኛል።

ፌዴራል መንግስቱ ህገ መንግስታዊ የሆነ ስልጣኑን ተጠቅሞ ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን ለመታደግ ካልቻለ እና መደራደርን ከመረጠ ወደ ፊት እጅግ አደገኛ ሁኔታ ይገጥመዋል።

ይህም ማለት ሌሎች የፌዴሬሽኑ አካል የሆኑ የክልል መንግስታት የፌዴራሉን መንግስት ያለ ማንም ከልካይነት መገዳደር እንዲችሉ መፍቀድ ማለት ነው።"

* ዛሬ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ያወጣው መግለጫ ሙሉ ሀሳብ ከላይ ተያይዟል (የተዘጋጀው በአልዓይን AlAin ሚዲያ ነው)

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethipia
#Security_Alert

መንበረ ሠላም የሚገኙ የቲክቫህ አባላት በአሁን ሰዓት ከባድ ተኩስ እንዳለ ገልፀዋል።

ታጣቂዎች ወደ #ድባጤ ሰብረው ሊገቡ ነው ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በቂ የሆነ የሰላም አስከባሪ ኃይል እንደሌለ አሳውቀዋል።

* ይህ አካባቢ እስካሁን ድረስ ከስጋት ቀጠና አልተላቀቀም።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
'የUNHCR ሰራተኞች አልታሰሩም'

(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

UNHCR ፥ "በትግራይ ክልል የሚሰሩ ሰራተኞቹ ታስረዋል" በሚል በመገናኛ ብዙሃን የተሰራጨው ዘገባ ሐሰት መሆኑን ገለጸ።

በተጨማሪም 'የድርጅቱ ተሽከርካሪዎች ተወርሰዋል' ተብሎ በመገናኛ ብዙሃን የተሰራጨው መረጃ የተሳሳተ ነው ብሏል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#FireAlert

በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ኤድናሞል አካባቢ 'ከባድ' የእሳት አደጋ ደርሷል።

አደጋው የደረሰው ኤድናሞል አካባቢ ቦሌ መሰናዶ ትምህርት ቤት ፊት ለፊት በሚገኝ አንድ የቻይና ኮንስትራክሽን ድርጅት መጋዘን ላይ መሆኑ ተገልጿል።

እሳቱ አሁን ላይ 'በፍጥነት በመቀጣጠል' ላይ ሲሆን የእሳት አደጋ መቆጣጠር ሰራተኞች ወደ ቦታው እንዳልደረሱ Ethio FM 107.8 አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#Mekelle

ዛሬ ሰኞ ረፋድ ላይ በመቐለ ከተማ የአየር ጥቃት መፈጸሙን የከተማዋ ነዋሪችን ዋቢ አድርጎ ቢቢሲ ከስፍራው ዘግቧል።

የጦር አውሮፕላን ድምጽ በተሰማበት ጊዜ በነዋሪዎች ዘንድ መደናገጥ ተፈጥሮ የነበረ ሲሆን ፤ ጥቃቱ በሰዎች ላይ ጉዳት አለማድረሱን ቢቢሲ አሳውቋል።

"የትግራይ ቴሌቪዥን" ረፋድ 04፡45 ላይ ጥቃቱ መፈጸሙን አረጋግጧል። የጥቃቱ ኢላማ ቀዳማይ "ወያነ ክፍለ ከተማ" ውስጥ በሚገኘው እንዳ ጊዮርጊስ በተባለው አካባቢ መሆኑን ገልጿል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia