TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.4K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#FederalPoliceCommission

የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ሜጀር ጀነራል ገብረመድህን ፈቃዱን (ወዲ ነጮ) በአገር ክህደት ወንጀል ከነ ግብረ አበሮቹ በቁጥጥር ስር እንዲውሉ መደረጉ ገልፀዋል።

ተጠርጣሪዎቹ ጥቅምት 24/2013 የሰሜን ዕዝ ከማዕከል ጋር የሚኖረው የመገናኛ ሥርዓት እንዲቋረጥ በማድረግ "የህዋሃት የጥፋት ቡድን" ጥቃት እንዲፈፅም አመቻችተዋል ተብሏል።

ከዚህ በተጨማሪም ሜ/ጄኔራል ገብረመድህን በውስጣቸው ቦንቦች እና የሚሳየል መሳሪያዎችን የያዙ 11 ሳጥኖች የግንኙነት መሳሪዎች ናቸው በሚል ሽፋን ወደ ትግራይ ክልል ለመላክ ሲዘጋጅ ከተለያዩ የጦር መሳሪያዎች ጋር እጅ ከፍንጅ መያዙ ተገልጿል።

በቁጥጥር ስር የዋሉት ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖችና የበታች ሹማምንቶቻቸው በድምሩ አስራ ሰባት (17) ተጠርጣሪዎች ናቸው።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#EthiopianAirlines

አየር መንገዱ ኮቪድ19 ያመጣውን ቀውስ ተቋቁሞ በማለፉ እና ስኬት በማስመዝገቡ ከ “ግሎባል ፋይናንስ” መጽሔት “የ2020 Outstanding Crisis Leadership” ሽልማት ተበርክቶለታል።

ሽልማቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በወረርሽኙ ወቅት ለአለም ለሰጠው ፈጣን ምላሽ እንዲሁም ለተገበራቸው ስኬታማ የቀውስ ወቅት ስትራቴጂዎች እውቅና የሰጠ ነው ተብሏል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#UPDATE

አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በዛሬው ዕለት ሃገራዊ ሁኔታዎችን በማስመልከት ለውጭ መገናኛ ብዙሃን ማብራሪያ ሰጥተው ነበር።

“ከግጭቱ ዋዜማ የትግራይ ክልል መሪ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ተደዋውለው ነበር” ያሉት ቃል አቀባዩ “ሁኔታውን በቀላሉ እንደሚይዙት እና በንግግር ሊፈቱት እንደሚችሉ ተነጋግረው ነበር” ብለዋል፡፡

ጠ/ሚሩ ይህን ታሳቢ በማድረግ በአዲስ የተቀየረውን ብር ወደ ትግራይ ለመላክ እና ክልሉ የእለት ተዕለት የቢዝነስ እንቅስቃሴ ለመደገፍ ቃል ገብተዋል፡፡

ሆኖም በዚያው ዕለት ምሽት ላይ በክልሉ በሚገኘው የሃገሪቱ ጦር የተለያዩ ጣቢያዎች ላይ ድንገተኛ ጥቃት መከፈቱ ነው የገለጹት፡፡

ጥቃቱም በተመረጡ የሰራዊቱ አካባቢዎች ላይ በተመሳሳይ ሰዓት የተፈጸመ ነው፡፡

ያንብቡ - https://telegra.ph/AlAin-11-10

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#DrAbiyAhmed

ጠ/ሚር ዶክተር አብይ አህመድ ዛሬ ምሽት በትዊተር ገፃቸው ላይ ባሰራጩት መልዕክት የህግ የበላይነት የማረጋገጥ ስራው ሳይጠናቀቅ ድርድር የሚባል ነገር አይኖርም ሲሉ #አረጋግጠዋል

በሌላ በኩል ፦

የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር በትግራይ ክልል ያለው ግጭት በአፋጣኝ እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል።

የፌደራሉ እና የክልሉ መንግሥት ሰላማዊ መፍትሄ ለማምጣት ወደ ንግግር እንዲመለሱ ሊቀመንበሩ ሙሳ ፋኪ ማህማት ጠይቀዋል፡፡

ግጭቱን ለመፍታት የሚደረግን ማንኛውም ጥረት ለማገዝ የአፍሪካ ኅብረት ዝግጁ መሆኑን ገልፀዋል።

ሀገሪቱ ወደ ዕርስ በዕርስ ግጭት ውስጥ እንዳታመራ ኅብረቱ ጣልቃ እንዲገባ የክልሉ ገዢ ፓርቲ ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ባለፈው እሁድ ጥሪ ማድረጋቸው አይዘነጋም፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጠቃሚ የስልክ ቁጥሮች #1

ከላይ ፦

1. የኦሮሚያ ክልል ከተሞች፣ ዞኖች ፖሊስ መምሪያ ስልኮች
2. በሲዳማ ክልል (ሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ)
3. የአማራ ክልል የዞኖች፣ የብሄረሰብ አስተዳደሮች፣ እና ከተሞች ፖሊስ
4. የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን
5. ደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን እንዲሁም የፀጥታ ቢሮዎችን የስልክ ቁጥሮች ማግኘት ትችላላችሁ።

* የሌሎች የከተሞች ፣ የዞኖች የፀጥታ ቢሮ ስልኮች በቀጣይነት ይቀርባሉ።

የምንኖርበትን አካባቢ የፀጥታ አካላት ስልክ ቁጥሮች በእጅ ስልካችን ላይ የመመዝገብ ባህልን እናዳብር።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#FDREDefenseForce

በሀገር መከላከያ ሰራዊት እየተወሰደ ያለዉን የህግ ማስከበር እርምጃ እንጂ የእርስ በርስ ጦርነት አይደለም አለ መከላከያ ሚኒስቴር።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር የሆኑት ዶ/ር ቀነዓ ያደታ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል።

'አጥፊው ቡድን' እየተወሰደ ያለውን የህግ ማስከበር እርምጃ የእርስ በእርስ ጦርነት አስመስሎ የሀሰት መረጃዎችን እየነዛ ነው ብለዋል።

ቡድኑ እያሰራጨ ያለው የሃሰት መረጃ ጭንቀቱን እና ተስፋ መቁረጡን የሚሳይ ነዉ ሲሉ ገልፀዋል።

የትግራይ እና ኢትዮጵያ ህዝብ እነዚህን የሃሰት መረጃዎችን በመለየት ከሀገር መከላከያ ሰራዊቱ ጎን መቆም አለበት ሲሉ አሳስበዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#የመከላከያ_ሰራዊቱ_ማስጠንቀቂያ

መከላከያ ሰራዊት የትግራይ ልዩ ሀይል እና የትግራይ ሚሊሻ አባላት የጥፋት ቡድኑ ከለላ ከመሆን ይልቅ ለሀገር መከላከያ እጃቸውን እንዲሰጡ አሳስቧል።

እጃቸውን ለመከላከያ ሰራዊት የማይሰጡ ከሆነ መከላከያው "ያለምንም ቅድመ ሁኔታ" ለመደምሰስ እንደሚገደድ በዛሬው ዕለት በሰጠው መግለጫ አስጠንቅቋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#AddisAbaba

ዛሬ ጥዋት በአዲስ አበባ ከተማ አድዋ ድልድይ ስር ቦንብ ፈንድቶ በ1 ግለሰብ ላይ የአካል ጉዳት መድረሱ ተገልጿል።

* የታረመ

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#FDREDefenseForce

የመከላከያ ሰራዊቱ በታላቅ ጥንቃቄ እና በሙያዊነት የሀገር ማዳንና ህግን የማስከበር ስራውን እየሰራ መሆኑን መከላከያ ሚኒስቴር አሳውቋል።

ሀገር መከላከያ ሰራዊቱ 'ጥፋተኛውን ቡድን' ብቻ ነጥሎ ነው እያጠቃ የሚገኘው ተብሏል።

መከላከያው ንፁሃንንና መሰረት ልማት ላይ ጥቃት ይፈፅማል እየተባለ በጥፋት ኃይሉ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰት ነው ሲል ሚኒስቴሩ አሳውቋል።

ከዚህ በተጨማሪ የሰራዊቱ የማንንም የውጭ ኃይል ድጋፍ ሳይፈልግ የጥፋት ቡድኑን የመደምሰስ ቁመና አለው ብሏል።

"መከላከያ ሰራዊቱ የትኛውንም ጥቃት ለመመከት ተጨማሪ ድጋፍ አያስፈልገውም ፤ ቡድኑን ለማጥቃት የውጭ ድጋፍ አልጠየቀም አይጠይቅምም" ሲል ገልጿል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#FDREDefenseForce

የመከላከያ ሚኒስትር ዶክተር ቀነዓ ያደታ ፥ "የትግራይ ህዝብ ጦርነት የሰለቸው ነው፣ ሰላምና ልማት ፈላጊ ነው ፣ ሀገሩንም አይወጋም ፣ በጠቅላላው በዚህ ጦርነት ላይ #አልተሳተፈም" ብለዋል።

ይህ ብቻም ሳይሆን የትግራይ ህዝብ ሰራዊቱ በደረሰበት ቦታ ለሰራዊቱ ያለውን ክብር በግልፅ እያሳየ እና እየደገፈ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ጦርነቱ የእርስ በእርስ ጦነርት አይደለም ፤ ጦርነቱ እየተደረገ ያለው ከጥፋተኛው ቡድን ጋር እና ህግን የማስከበር ብቻ ነው ሲሉም አሳውቀዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba ዛሬ ጥዋት በአዲስ አበባ ከተማ አድዋ ድልድይ ስር ቦንብ ፈንድቶ በ1 ግለሰብ ላይ የአካል ጉዳት መድረሱ ተገልጿል። * የታረመ @tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#UPDATE

በአዲስ አበባ ወድቆ የተገኘ ቦንብ ፈንድቶ በ 1 ግለሰብ ላይ 'ቀላል የአካል ጉዳት' ማድረሱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ዛሬ ጥዋት 2፡00 ሰዓት አካባቢ በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታው አድዋ ድልድይ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ ነው ጉዳቱ የደረሰው።

በደረሰበት ጉዳት በምኒልክ ሆስፒታል ህክምና እየተከታተለ የሚገኘው ግለሰብ የታክሲ ረዳት ሲሆን ለመፀዳዳት ወደ ድልድዩ እንደገባ እና በማዳበሪያ የተጠቀለለ እቃ ተመልክቶ በእግሩ ሲረግጠው ከዚያ በኋላ ራሱን እንደሳተ ተናግሯል፡፡

Via Addis Ababa Police Commission
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#FDREDefenseForce

ሰራዊቱ በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች ለሚኖሩ ሰዎች ድጋፍ ማድረግ የሚፈልጉ የእርዳታ ድርጅቶች ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር ተነጋግረው ድጋፍ ማድረግ ይችላሉ ተባለ።

ይህን የገለፁት የሀገር መከላከያ ሰራዊት ኢንዶክትሬሽን ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ሜጄር ጄነራል መሀመድ ተሰማ ናቸው።

በሌላ በኩል ፦

ሜ/ጄ መሀመድ ፥ "የህወሃት ቡድን በአልመዳ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ የኤርትራ መከላከያ ሰራዊትን መለዮ በማዘጋጀት ላደራጃቸው ታጣቂዎች በማልበስ ኤርትራ ወረረችን በማለት ህዝቡን እያደናገረ ነው" ብለዋል።

በተቀናበረ ድራማ ህዝቡ ሳይታለል ለሀገር መከላከያ ሰራዊቱ እያደረገ ያለውን 'ድጋፍ አጠናክሮ' እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#FDREAirForce

የአየር ኃይል ዋና አዛዥ የሆኑት ሜ/ጄ ይልማ መርዳሳ ዛሬ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

የኢፌዴሪ አየር ኃይል የህወሓት ቡድን ሊጠቀምባቸው ያሰባቸውን ኢላማዎች ከጥቅም ውጭ አድርጓቸዋል ብለዋል።

አየር ኃይሉ የነዳጅ ዴፖዎች ፣ የመሳሪያ ማከማቻዎች እና ሌሎች ኢላማዎችን ያለምንም ከልካይ አውድሟል ሲሉ ተናግረዋል።

ሜ/ጄ ይልማ ፥ "ፓይለቶቻችን የተመረጡ ዒላማዎችን ለመደምሰስ መሣሪያ ጭነው እየሄዱ ሲቪል የሚጎዳ ከመሰላቸው ሳይተኩሱ በመመለስ ነጥሎ የመምታት ስትራቴጂ እየተከተሉ ይገኛሉ" ብለዋል።

አሁንም ይህ የጥፋት ኃይል ህግ ፊት እስኪቀርብ ድረስ ያለምንም ከልካይ ተፈላጊ ኢላማዎችን እናጠቃለን ሲሉ አሳውቀዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
'የጋዜጠኞች መታሰር'

የAddis Standard አዘጋጅ መድሃኔ እቁባሚካኤል እንደገና ለእስር መዳረግ፣ የአውሎ ዋና አዘጋጅ በቃሉ አላምረው መታሰር እንዳሳሰባቸው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ ገለፁ።

ኮሚሽነሩ ከሚዲያ ጋር የተገናኘ ጥፋት ጠፍቶም ከሆነ ፍትሃዊ በሆነ መንገድና ስርአትን በተከተለ ሁኔታም እንዲካሄድ ጥሪ አቅርበዋል።

በተጨማሪ የEPA ጋዜጠኞች ሃፍቱ ገ/እግዚአብሔር ፣ ፀጋዬ ሃዱሽ እና አብርሃ ሃጎስ እንዲሁም የOMN ጋዜጠኛ የሆነው ኡዲ ሙሳ ተጨማሪ 4 ጋዜጠኞች መታሰር ስጋት እንደፈጠረባቸው ገልፀዋል።

ቅዳሜ እለት ጥቅምት 28/2013 ዓ.ም በቁጥጥር ስር ውሎ የነበረው መድሃኔ ቢለቀቅም ሰኞ እለት ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ/ም እንደገና እንደታሰረም ተገልጿል።

በሌላ በኩል ፦

ሲፒጄ የአውሎ ሚዲያ ዋና አዘጋጅ በቃሉ አላምረው እንዲፈታ ለኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጥሪ አቅርቧል። (BBC)

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia