TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.91K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ሰበር_ዜና

ዶናልድ ትራምፕ በምርጫው ተሸነፉ።

ጆ ባይደን 46ኛው የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ሆነ ተመርጠዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#JoeBiden

የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ፥ ጆ ባይደን 46ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው በመመረጣቸው "የእንኳን ደስ አሎት" መልዕክት በትዊተር ገፃቸው አስተላልፈዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#KamalaHarris

ካማላ ሃሪስ የመጀመሪያዋ ሴት ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነዋል።

እንዲሁም ጥቁር እና እሲያ አሜሪካዊ ምክትል ፕሬዝዳንት በመሆን ታሪክ ሰርተዋል።

ካማላ ሃሪስ ከሕንድ ከሆኑት እናታቸው እና ከጀማይካ ከሆኑት አባታቸው በካሊፎርኒያ ነበር የተወለዱት።

የ55 ዓመቷ ካማላ ሃሪስ ከጆ ባይደን ጋር በመሆን አሜሪካንን ለመጪዎቹ 4 ዓመታት ይመራሉ። [BBC]

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#COVID19Ethiopia

የ24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት ፦

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 6,028
• በበሽታው የተያዙ - 455
• ህይወታቸው ያለፈ - 6
• ከበሽታው ያገገሙ - 845

በአጠቃላይ በሀገራችን 99,201 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,518 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 58,948 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

306 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ሰበር_ዜና ዶናልድ ትራምፕ በምርጫው ተሸነፉ። ጆ ባይደን 46ኛው የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ሆነ ተመርጠዋል። @tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ጆ ባይደን ማናቸው?

ጆ ባይደን የቀድሞ የፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ ምክትል ፕሬዝደንት ሆነው አገልግለዋል።

የባይደን ደጋፊዎቻቸው የውጪ ጉዳይ ፖሊስ አዋቂ ናቸው ይሏቸዋል።

ጆ ባይደን የፖለቲካ ሕይወታቸው የጀመረው ከ47 ዓመታት በፊት ነበር።

ባይደን የአሜሪካ ፕሬዝደንት ለመሆን ጥረት ማድረግ የጀመሩት ደግሞ ከ33 ዓመታት በፊት እ.አ.አ. 1987 ጀምሮ ነው።

በጥቁር አሜሪካውያን ዘንድ ትልቅ ተቀባይነት አላቸው።

* የጆ ባይደን ውጭ ፖሊሲ ጉዳይ

ባይደን ዶናልድ ትራምፕ ያበላሹትን የውጭ ግንኙነት አስተካክላለሁ ፤ አሜሪካ ያስቀየመቻቸውን ወዳጆቿን ልብ እጠግናለሁ ብለዋል።

ከኢራን እና ከቻይና ጋር የሚከተሉት ፖሊሲም ትራምፕ ጋር የሚቃረን ነው።

ይህ መረጃ ከBBC የተወሰደ ነው።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#BidenHarris2020

ጠ/ሚር ዶክተር አብይ አሕመድ ለጆ ባይደን እና ካማላ ሃሪስ 'የእንኳን ደስ አላችሁ' መልዕክት በይፋዊ ትዊተር ገፃቸው ላይ አስተላልፈዋል።

"ኢትዮጵያ በቅርበት አብራችሁ ለመስራት በመጠባበቅ ላይ ናት" ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FDREDefenseForce

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ሠራዊት ምክትል ኤታማዦር ሹም እና የኦፕሬሽን ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ መከላከያ ሰራዊቱ ፦
- ዳንሻን
- ባከርን
- ከሽራሮ አስከ ሽሬ ያሉ አካባቢዎች ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሮ ወደ ፊት እየገሠገሠ ነው ብለዋል።

መከላከያ "በከሀዲ ቡድኑ" እጅ ያሉ ከባድ መሳሪያዎች ሙሉ በሙሉ አውድሟልም ብለዋል።

ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ፥ "የመከላከያ ሰራዊት ሕዝብ እንዳይጎዳ ለማድረግ እና ጽንፈኛውን ኃይል ከህዝብ ለይቶ ለመምታት በጥንቃቄ እየተንቀሳቀሰ ነው" ብለዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#FDREDefenseForce

የመከላከያ ሰራዊት ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜ/ጀ መሀመድ ተሰማ፥ ሰራዊቱ ሀገርን ከጥፋት የማዳን ተልዕኮውን በአጭር ጊዜ ያጠናቅቃል አሉ።

የኢትዮጵያን ዕድገት ማይፈልጉ ታሪካዊ የሆኑ ጠላቶች የታላቁ ህዳሴ ግድብ እንዳያደናቅፉ የሀገሪቱ የፀጥታ ሀይሎች በተጠንቀቅ በቆሙበት ባሁኑ ሰዓት ላይ የናት ጡት ነካሾች ሀገሪቱን በመድፈር ውጊያ ከፍተውብናል ብለዋል።

ሜ/ጄ መሀመድ ተሰማ፥ "ይህ ጦርነት ሀገርን ለውጭ አሳልፎ የሚሰጥና ፅንፈኛው ሀይል የስልጣን ጥማቱን ለማርካት የገባበት ነው" ሲሉ ተናገራዋል።

በአሁን ሰዓት ይህን ውጊያ ለመመከት መላው የፀጥታ ኃይሎች እየተዋጉ ወንጀለኞችን ወደ ህግ ለማቅረብ ፍልሚያ ላይ ይገኛሉ ሲሉ አስረድተዋል።

ዳይሬክተሩ ሜ/ጄ መሀመድ ፥ "ሠራዊቱ ፅንፈኛውን ሀይል በአጭር ጊዜ በቁጥጥር ስር በማዋልና ለህግ በማቅረብ የአካባቢው ሕዝብ ከነበረበት ጭቆና ነፃ እንደሚወጣ እናረጋግጣለን" ብለዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#BREAKING

የአማራ ክልል ፕሬዜዳንት አቶ ተመስገን ጥሩነህ የስልጣን መልቀቂያ ጥያቄ አቀረቡ።

አቶ ተመስገን ጥያቄውን ያቀረቡት ምክር ቤትቱ 5ኛ ዙር 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 16ኛ መደበኛ ጉባኤውን በሚያካሂድበት ወቅት ነው።

ሀገሪቱ ካለችበት ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር በተሠጣቸው ተልእኮ ምክንያት ነው ጥያቄውን ያቀረቡት ተብሏል።

የምክር ቤት አባላቱ በጉዳዩ ላይ ሰፊ ምክክር ካካሄዱ በኋላ ጥያቄያቸውን ተቀብሏል።

ለቀጣይ የክልሉ በርእሰ መስተዳድርነት "አቶ አገኘሁ ተሻገር" በእጩነት መቀረባቸውን ኢቲቪ ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#BREAKING

አቶ አገኘው ተሻገር የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር ሆነው ተሾሙ።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#BREAKING

ከጥቅምት 25 ቀን 2013 ዓ.መ ጀምሮ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተሰጡ ሹመቶች ፦

- አቶ ደመቀ መኮንን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

- ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም

- ሌ/ጄኔራል አበባው ታደሰ የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም

- አቶ ተመስገን ጥሩነህ የብሔራዊ መርጃ እና ድህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር

- ኮሚሽነር ደመላሽ ገ/ሚካኤል የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#BREAKING

ጠ/ሚር ዶክተር አብይ አህመድ ከጥቅምት 25 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን የጠቅላይ ሚንስትሩ የብሔራዊ የደህንነት አማካሪ ሚንስትር አድርገው ሾመዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#UPDATE

ረቡዕ ጥቅምት 25 ቀን 2013 ዓ/ም ከጠዋት 2:00 ሰዓት ላይ በፖሊስ ተወስዶ የታሰረው የአውሎ ሚዲያ የዜና እና ወቅታዊ ጉዳዮች ክፍል ዋና አዘጋጅ የሆነውን ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው ፍርድ ቤት ቀርቦ የቀረበበት ክስ ከዚህ በታች የተዘረዘረው ነው ፦

1. ከትግራይ ክልል አመራሮች ትገናኛለህ፣ ቃለ-መጠይቅ ትሰራለህ።
2. መንግስትን ትተቻለህ፣ መንግስትን የሚንቋሽሽ ፅሑፍና ዘገባ ትሰራለህ።
3. መንግስት በዓለም አቀፍ ደረጃ ስሙ እንዲጠልሽ እና ተቀባይነት እንዳያገኝ በማሰብ ከውጭ ኋይሎች ትፃፃፋለህ።
4. ብሄር ከብሄር የሚጋጭ ዜና ትሰራለህ፣ ግጭት የሚቀሰቅስ የፎቶ ቅንብር ትጠቀማለህ።
5. የእርስ-በርስ ጦርነት እንዲደረግ ታነሳሳለህ።

ፖሊስ የተሟላ መረጃና ማስረጃ ለማቅረብ የ14 ቀን ተጨማሪ ጊዜ እንዲሰጠው የጠየቀ ሲሆን ፍርድ ቤት 6 ቀን ፈቅዷል።

Via AWLO MEDIA

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#FDREDefenseForce የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መከላከያ ሠራዊት ምክትል ኤታማዦር ሹም እና የኦፕሬሽን ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ መከላከያ ሰራዊቱ ፦ - ዳንሻን - ባከርን - ከሽራሮ አስከ ሽሬ ያሉ አካባቢዎች ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሮ ወደ ፊት እየገሠገሠ ነው ብለዋል። መከላከያ "በከሀዲ ቡድኑ" እጅ ያሉ ከባድ መሳሪያዎች ሙሉ በሙሉ አውድሟልም ብለዋል። ጄኔራል ብርሃኑ…
#FDREDefenseForce

ሀገር መከላከያ ሰራዊት ማይዳሊ ፣ ልጉዲ ፣ የሁመራ አየር ማረፊያና የሁመራ ሱዳን መንገድን እንደተቆጣጠረ ተገለፀ።

ይህንን የገለፁት መከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል መሐመድ ተሰማ ናቸው።

ሜጀር ጄኔራል መሀመድ ተሰማ፥ "ሰራዊቱ በምዕራብ ግንባር እያደረገ ያለውን የማጥቃት እርምጃ አጠናክሮ ቀጥሏል" ሲሉ ለኢዜአ ተናግረዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት በጦርነቱ የቆሰሉ 98 የመከላከያ ወታደሮች በአማራ ክልል ሰሜናዊ ክፍል የህክምና እርዳታ እንደተደረገላቸው ዘግቧል።

በሳንጃ ከተማ የሚሰሩ አንድ የህክምና ባለሞያ ለሚዲያው እንደተናገሩት በጥይት የቆሰሉ ዘጠና ስምንት ወታደሮች ህክምና ተደርጎላቸዋል።

የጤና ባለሞያው እንዳገለፁት ሁሉም የመከላከያ ሰራዊት አባላት እንደሆኑ ገልፀዋል።

በሆስፒታሉ የሞተ ሰው እንደሌለ የገለፁ ሲሆን ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ወደ ጎንደር እና ሌሎች ቦታዎች መወሰዳቸውን ተናግረዋል።

በትግራይ ክልል የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት በመቋረጡ በይፋዊ መግለጫ ማረጋግጥ አልተቻለም ተብሏል። (AFP)

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#UPDATE

ዛሬ ጥዋት በመቐለ ከተማ የአውሮፕላን ጥቃት መፈፀሙን ዶቼ ቨለ (DW) ዘግቧል።

ጥዋት 1:45 የመጀመሪየው የአውሮፕላን ድምፅ በመቐለ ኩያ አካባቢ ጥቃት መፈፀሙና መቃወሚያ ሊሆን የሚችል የከባድ መሳሪያ ተኮስ እንደነበር ነዋሪዎች አረጋግጠዋል።

ሌላ የተዋጊ አውሮፕላን ድምፅ እና የፀረ አውሮፕላን ድምፅ ረፋድ 5:00 አካባቢ በመቐለ ምስራቃዊ አካባቢ ተሰምቷል።

በጥቃቱ የደረሰ ጉዳት ይኑር አይኑር የትግራይ ክልል ያለው ነገር የለም።

የፌዴራሉ መንግስትም ድብደባውን ስለመፈፀሙ ማብራሪያ አልሰጠም።

* አቶ ጌታቸው ረዳ "ለትግራይ ቴሌቪዥን" በመቐለ አካባቢ ድብደባ ለማካሄድ የተላከ የውግያ ጀት ተመቶ ወድቋል ሲሉ ተናገረዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#COVID19Ethiopia

የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት ፦

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 5,324
• በበሽታው የተያዙ - 474
• ህይወታቸው ያለፈ - 5
• ከበሽታው ያገገሙ - 818

በአጠቃላይ በሀገራችን 99,675 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ፤ የ1,523 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 59,766 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

316 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#FDREDefenseForce

እየተካሄድ ያለው ጦርነት 5 ቀን ሆኖታል።

የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል መሐመድ ተሰማ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል።

ማክሰኞ ምሽት "ህወሓት" ውስጥ ያለው ኃይል የቀጠናውን መብራት በማጥፋትና የስልክ ግንኙነትን በማቋረጥ ሰራዊቱ እርስ በእርስ እንዳይገናኝ በማድረግ ከውስጥ እና ከውጭ ጥቃት መሰንዘሩን አስታውሰዋል።

አሁን እየተካሄደ ባለው ጦርነት የሀገር መከላከያ ሰራዊት ድል እያስመዘገበ እና በርካታ ቦታዎችን በቁጥጥሩ ስር እያደረገ መሆኑን ገልፀዋል።

ሀገር መከላከያ ሰራዊት ሀገርን ከጥፋት የማዳን ተልዕኮውን በአጭር ጊዜ ያጠናቅቃል ብለዋል።

* ሙሉ መግለጫው (14 MB) ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia